መመሪያ መጻህፍቶች እና ጥሪዎች
32. ንስሀ መግባት እና የቤተክርስቲያኗ አባልነት ምክር ቤት


“32. ንስሀ መግባት እና የቤተክርስቲያኗ የአባልነት ምክር ቤት፣” አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ፦ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል [2020 (እ.አ.አ)]።

“32. ንስሀ መግባት እና የቤተክርስቲያኗ የአባልነት ምክር ቤት፣” አጠቃላይ መመሪያ መፅሐፍ።

ምስል
ሰዎች በንግግር ላይ

32.

ንስሀ መግባት እና የቤተክርስቲያኗ የአባልነት ምክር ቤት

32.0

መግቢያ

አብዛኛው ንስሃ መግባት የሚፈጸመው በግለሰብ፣ በእግዚአብሔር እና ኃጢያቱን በፈጸመው ሰው ምክንያት በተጎዱት ሠዎች መካከል ነው። ሆኖም አንዳንዴ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት የቤተክርስቲያኗ አባላት ንስሃ ለመግባት የሚያደርጉትን ጥረት ማገዝ ይኖርበታል።

አባላት ንስሃ እንዲገቡ በሚረዱበት ጊዜ ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች አፍቃሪ እና ተንከባካቢ ናቸው። ግለሰቦች የተሻሉ ሰዎች እንዲሆኑ በመደገፍ ፊታቸውን ከኃጢያት ዘወር እንዲያደርጉ እና ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ የረዳቸውን የአዳኙን ምሳሌ ይከተላሉ (ማቴዎስ 9፥10–13ዮሐንስ 8፥3–11 ተመልከቱ)።

ከዚህ በታች እንደተዘረዘረው፣ ይህ ምዕራፍ የተደራጀው አንድ ሰው ለሰራው ከባድ ኃጢያት ንስሐ እንዲገባ ለመርዳት እና የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ እርዳታ ለመስጠት መሪዎች በሚያደርጓቸው አስፈላጊ ቁልፍ ውሳኔዎች እና እርምጃዎች ላይ ለመምራት ነው።

  • አንድ ግለሠብ ንስሃ እንዲገባ በመርዳት ረገድ ቤተክርስቲያኗ ያላት ሚና ክፍሎች 32.1–32.4 ንስሃ መግባትን እና ይቅርታን የሚመለከተውን የጌታን ትምህርት ያብራራሉ። በተጨማሪም እነዚህ ክፍሎች ሶስቱን ከቤተክርስቲያኗ አባልነት የመገደብ እና የመወገድ ዓላማዎች ያብራራሉ። በተጨማሪም ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዘደንቶች ሰዎች ንስሃ እንዲገቡ በመርዳት ረገድ ያላቸውን ሚና ያብራራሉ።

  • አንድ ግለሠብ ንስሃ እንዲገባ ለመርዳት የሚያስችል ሁኔታን መወሰን። ከፍሎች 32.5–32.7 ከአባልነት ምክር ቤት እና ከግል ምክር የትኛው አንድን ሰው ንስሐ እንዲገባ ለመርዳት ተገቢው ሁኔታ እንደሆነ ለመወሰን መመሪያዎችን ይሰጣሉ።

  • የግል ምክር መስጠት። ክፍል 32.8 ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የግል ምክር የሚሰጡበትን መመሪያዎች ይሰጣል። እንዲሁም መደበኛ ያልሆኑ የቤተክርስቲያኗ የአባልነት ገደቦችን ያብራራል።

  • የቤተክርስቲያን የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ። ክፍሎች 32.9–32.14 የአባልነት ምክር ቤትን ማካሄድ የማን ኃላፊነት እንደሆነ፣ እንዴት እንደሚካሄዱ እና ሊሰጡ ስለሚችሉት ውሳኔዎች ያብራራሉ። የእነዚህ ውሳኔዎች ውጤቶችም ተብራርተዋል።

  • የቤተክርስቲያኗ አባልነት መብቶችን መመለስ። ክፍሎች 32.15–32.17 አንድ ግለሠብ የቤተክርስቲያን አባልነት መብቶችን ንስሃ በመግባት እንዴት መልሶ ሊያገኝ እንደሚችል ያብራራል።

በሌላ መልኩ ካልተገለጸ በስተቀር፣ ስለካስማ ፕሬዚዳንቶች የሚጠቅሰው ሁሉ የሚስዮን ፕሬዚዳንቶችንም ያመለከታል። ስለኤጲስ ቆጶሳት የሚጠቅሰው ሁሉ የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቶችንም ያመለከታል።

ቀዳሚ አመራር የከባድ ኃጢያት ንስሐ አገባብ አቅዋም መመሪያዎችን እና ሂደቶችን ይገልፃሉ። ቀዳሚ አመራርም በChurch’s Confidential Records Office [ቤተክርስቲያኗ ሚስጥራዊ የመዝገቦች ቢሮ] ይታገዛሉ። የካስማ ፕሬዚዳንቱ ወይም ኤጲስ ቆጶሱ የአስተዳደር ወይም የአቋም መመሪያ ጥያቄዎችን በተመለከተ ያን ቢሮ ማነጋገር ይችላሉ። ያም ቢሮ ለቀዳሚ አመራር ፅህፈት ቤት ጥያቄዎችን እንዴት ማስገባት እንደሚቻል መመሪያዎችን ሊሰጥም ይችላል። አድራሻው ከዚህ በታች ተቀምጧል፦

ስልክ፦ 1-801-240-2053 ወይም 1-800-453-3860፣ የውስጥ መስመር 2-2053

ነጻ መስመር (ጂኤስዲ ስልክ)፦ 855-537-4357

ኢሜል፦ ConfidentialRecords@ChurchofJesusChrist.org


አንድ ግለሠብ ንስሃ እንዲገባ በመርዳት ረገድ ቤተክርስቲያኗ ያላት ሚና


32.1

ንስሀ መግባት እና ይቅርታ

ጌታ “ምንም እርኩስ ነገር መንግስተ ሰማያትን ሊወርስ አይችልም” ብሏል (አልማ 11፥37፤ በተጨማሪም 3 ኔፊ 27፥19 ተመልከቱ)። ኃጢያቶቻችን እርኩስ—በሰማያዊ አባታችን ፊት ለመኖር ብቃት የሌለን ያደርጉናል። በዚህ ህይወት ውስጥም ስቃይን ያመጣሉ።

የእግዚአብሔር የፍትህ ህግ ኃጢያት በምንሰራበት ጊዜ የሚከተል መዘዝ መኖር እንዳለበት ያስገድዳል (አልማ 42፥14፣ 17–18 ተመልከቱ)። ሆኖም የእርሱ የሆነው ታላቁ የምህረት እቅድ “የፍትህን ፍላጎት ሊያሟላ ይችላል፣ እናም በጠባቂ ክንዶቹ [ይከበናል]” (አልማ 34፥16፤ በተጨማሪም ሞዛያ 15፥9 ተመልከቱ)።

የምህረት እቅዱ ይከናወን ዘንድ፣ የሰማይ አባት አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ለኃጢያታችን ክፍያ እንዲፈጽም ላከው (አልማ 42፥15 ተመልከቱ)። ኢየሱስም የፍትህ ህግ ለኃጢያታችን እንዲከፈል የሚፈልገውን ቅጣት ተቀብሏል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 19፥15–19 ተመልከቱ፤ በተጨማሪም አልማ 42፥24–25 ተመልከቱ)። በዚህ መስዋዕት አማካኝነት አብ እና ልጁ ለእኛ ያላቸውን ማለቂያ የሌለው ፍቅራቸውን አሳይተዋል (ዮሐንስ 3፥16 ተመልከቱ)።

“በንስሃ እምነት[ን]” ስንለማመድ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት ምህረትን በመስጠት የሰማይ አባት ይቅር ይለናል (አልማ 34፥15፤ በተጨማሪም አልማ 42፥13 ተመልከቱ)። ስንነጻ እና ይቅር ስንባል፣ በመጨረሻ የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ እንችላለን (ኢሳይያስ 1፥18ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥42 ተመልከቱ)።

ንስሃ መግባት ባሕርይን ከመቀየር በላይ ነው። ኃጢያትን መተው እንዲሁም ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መመለስ ነው። ልብን እና አዕምሮን ወደመለወጥ ይመራል (ሞዛያ 5፥2አልማ 5፥12–14ሔለማን 15፥7 ተመልከቱ)። በንስሃ አማካኝነት፣ ከእግዚአብሔር ጋር የታረቅን አዲስ ሰዎች እንሆናለን (2 ቆሮንቶስ 5፥17–18ሞዛያ 27፥25–26 ተመልከቱ)።

ንስሐ የመግባት እድል የሰማይ አባት በልጁ ስጦታ አማካኝነት ከሰጠን የላቁ በረከቶች መካከል አንዱ ነው።

32.2

የቤተክርስቲያኗ የአባልነት ገደብ ወይም ከአባልነት የማስወገድ አላማዎች

አንድ ግለሠብ ሲጠመቅ፣ እርሱ ወይም እርሷ “የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች” አካል ይሆናሉ (ኤፌሶን 2፥19)። የጥምቀት ቃል ኪዳኑ በክርስቶስ ትምህርቶች እና ትእዛዛት መሰረት ለመኖር የመጣር ቃል ኪዳንን ያካትታል። አንድ ግለሠብ ሲወድቅ፣ እሱ ወይም እሷ በሚያጠናክረው እና ይቅር በሚለው ምህረቱ በመታመን በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ያደርጋሉ እንዲሁም ንስሃ ይገባሉ።

አንድ ግለሠብ ከባድ ኃጢያት ከሰራ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ እርሱ ወይም እርሷ ንስሃ እንዲገባ/እንድትገባ ይረዳል። እንደሂደቱ አካል፣ ለተወሰነ ጊዜ አንዳንድ የቤተክርስቲያኗ አባልነት መብቶችን መገደብ ሊያስፈልገው ይችላል። በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ፣ ለተወሰነ ጊዜ አንድን ግለሠብ ከአባልነት ማስወገድ ሊያስፈልገው ይችላል።

አንድን ግለሠብ ከአባልነት ማገድ ወይም ማስወገድ ቅጣትን ያለመ አይደለም። ከዚያ ይልቅ፣ አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ተግባራት አንድ ግለሠብ ንስሃ እንዲገባ እና የልብ ለውጥ እንዲያደርግ ለመርዳት አስፈላጊ ናቸው። እንዲሁም አንድ ግለሠብ የእርሱን ወይም የእርሷን ቃል ኪዳን ለማደስ እና ለመጠበቅ በመንፈሳዊ የሚዘጋጅበት/የምትዘጋጅበትን ጊዜ ይሰጣሉ።

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ በ32.5–32.14 ውስጥ በተዘረዘረው መሰረት የአባልነት ገደብን ወይም ከአባልነት የማስወገድን ሥልጣን ይቆጣጠራል። እነዚህ ተግባራት በንስሐ ሁኔታዎች ይታጀባሉ። አንድ ግለሠብ በቅንነት ንስሃ ሲገባ፣ የእርሱ ወይም የእርሷ የቤተክርስቲያኗ አባልነት መብቶች ሊመለሱለት/ላት ይችላል።

የአባልነት ገደቦች ወይም መወገድ አስፈላጊ ሲሆኑ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የመንፈስ ቅዱስን ምሪት እና በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ይከተላል። በፍቅር መንፈስም ይሰራል (32.3 ተመልከቱ)።

የቤተክርስቲያኗ የአባልነት ገደቦች የቤተክርስቲያን እንጂ የፍትሐ ብሄር ወይም የወንጀል ጉዳዮች አይደሉም። ግለሠቡ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ያለውን አቋም ብቻ ነው የሚነኩት። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 134፥10 ተመልከቱ።)

የአባልነት ገደቦች ወይም ከአባልነት የማስወገድ ሶስቱ አላማዎች የሚከተሉት ናቸው።

32.2.1

የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ ይረዳል

የመጀመሪያው አላማ የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ መርዳት ነው። አንዳንድ ጊዜ አንድ ግለሠብ አካላዊ ወይም መንፈሳዊ ስጋት ሊሆን ይችላል። ሌላን ለመጉዳት ሆን ብሎ የሚደረግ ወንጀለኛ ባሕርይ፣ አካላዊ ጉዳት፣ ወሲባዊ ጥቃት፣ የዕፅ ሱሰኝነት፣ ማጭበርበር እና ክህደት ይህ ሊከሰት ከሚችልባቸው መንገዶች ጥቂቶቹ ናቸው። አንድ ግለሠብ በእነዚህ እና በሌሎች ከባድ መንገዶች ስጋት ሲፈጥር፣ በሚያገኘው መነሳሳት፣ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ እርምጃ ይወስዳል (አልማ 5፥59–60 ተመልከቱ)።

32.2.2

አንድ ግለሠብ በንስሃ አማካኝነት የኢየሱስ ክርስቶስን የማዳን ሃይል አንዲያገኝ እርዳታ መስጠት

ሁለተኛው ዓላማ ሰው በንስሃ አማካኝነት የኢየሱስ ክርስቶስን የማዳን ሃይል አንዲያገኝ መርዳት ነው። በዚህ ሂደት፣ እርሱ ወይም እርሷ እንደገና ንጹህ ለመሆን እና ሁሉንም የእግዚአብሔር በረከቶች ለመቀበል ብቁ ሊሆን/ልትሆን ይችላል/ትችላለች።

አዳኙ “የተሰበረ ልብ እና የተዋረደ መንፈስ” ለኃጢያት ይቅርታ የሚፈልጋቸው መስዋዕቶች እንደሆኑ አስተምሯል (3 ኔፊ 9፥20)። ይህም ለኃጢያት ልባዊ ጸጸት መሰማትን እና የእነዚህን ውጤቶች ያካትታል (2 ቆሮንቶስ 7፥9–10 ተመልከቱ)።

አንድ ግለሠብ ከባድ ኃጢያት ሲሠራ፣ ኃጢያትን በእውነት ለመተው እና የኃጢያትን መዘዞች ለመገንዘብ፣ የአባልነት ገደቦች ወይም ከአባልነት ማስወገድ የተሰበረ ልብን እና የተዋረደ መንፈስን ለማዳበር ሊረዳ ይችላል። ይህ ግንዛቤ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን ቃል ኪዳኖች ይበልጥ በጥልቅ እንዲያከብሩ እና ወደፊት እነዚያን ቃል ኪዳኖች ለመጠበቅ እንዲፈልጉ ሊረዳቸው ይችላል።

32.2.3

የቤተክርስቲያኗን ሀቀኝነት ይጠብቃል

ሶስተኛው ዓላማ የቤተክርስቲያኗን ሀቀኝነት ለመጠበቅ ነው። ምግባሩ ወይም ምግባሯ ቤተክርስቲያንን በእጅጉ የሚጎዳ ከሆነ፣ በግለሠቡ/ቧ የቤተክርስቲያኗ አባልነት ላይ ገደብ መጣል ወይም አባልነት ማስወገድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል (አልማ 39፥11 ተመልከቱ)። እነዚህን በማስተካከል እንጂ፣ ከባድ ኃጢያቶችን መደበቅ ወይም ማሳነስ የቤተክርስቲያኗን ሀቀኝነትን አይጠበቅም።

32.3

የእስራኤል ዳኛዎች ሚና

ምስል
ኤጲስ ቆጶስ ከአንድ ሰው ጋር ሲነጋገር

ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች የእስራኤል ዳኛዎች እንዲሆኑ ይጠራሉ እንዲሁም ይለያሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥72–74 ተመልከቱ)። የቤተክርስቲያኗ አባላት ንስሐ እንዲገቡ በመርዳት ረገድ ጌታን ለመወከል የክህነት ቁልፎች አሏቸው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13፥1107፥16–18 ተመልከቱ)።

አብዛኛውን ጊዜ ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች በግል ምክር አማካኝነት ንስሃ መግባትን ያግዛሉ። ይህ እገዛ ለተወሰነ ጊዜ መደበኛ ባልሆነ ሁኔታ አንዳንድ የቤተክርስቲያን የአባልነት መብቶችን መገደብን ሊያካትት ይችላል። (32.8 ተመልከቱ)።

መሪዎች ለአንዳንድ ከባድ ኃጢያቶች የአባልነት ምክር ቤት በማካሄድ ንስሃ መግባትን ይደግፋሉ (32.6 እና 32.9–32.14 ተመልከቱ)። ይህ እገዛ መደበኛ በሆነ ሁኔታ ለተወሰነ ጊዜ የግለሠቡን አንዳንድ የቤተክርስቲያን አባልነት መብቶችን መገደብን ወይም ከቤተክርስቲያኗ አባልነት ማስወገድን ሊያካትት ይችላል (32.11.3 እና 32.11.4 ተመልከቱ)።

ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች፣ የቤተክርስቲያኗ አባላት እግዚአብሔር ልጆቹን እንደሚወድ እንዲገነዘቡ ይረዳሉ። ደስተኛ እንዲሆኑ እና በረከቶችን እንዲቀበሉ ስለሚፈልግ ስለታዛዥነታቸው እና ንስሐ ስለመግባታቸውም በጣም ያስባል።

ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች፣ አባላት ንስሃ እንዲገቡ በሚረዱበት ጊዜ አፍቃሪ እና ተንከባካቢ ይሆናሉ። አዳኙ ስታመነዝር ከተያዘችው ሴት ጋር ያደረገው ግንኙነት መመሪያ ይሆናል (ዮሐንስ 8፥3–11 ተመልከቱ)። ኃጢያትዋ እንደተሠረየላት ባይናገርም፣ አልኮነናትም። ከዚያ ይልቅ “ከአሁን ጀምሮ ደግማ ኃጢያት እንዳትሰራ”—ንስሃ አንድትገባ እና ህይወቷን እንድትቀይር—ነገራት።

እነዚህ መሪዎች “ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢያተኛ በሰማይ ደስታ [እንደሚሆን]” ያስተምራሉ (ሉቃስ 15፥7)። ታጋሽ፣ ደጋፊ እና አዎንታዊ ናቸው። ተስፋን ያነሳሳሉ። በአዳኙ የኃጢያት ክፍያ መስዋዕትነት ምክንያት ሁሉም ንስሃ መግባት እና ንጹህ መሆን እንደሚችሉ ያስተምራሉ እንዲሁም ይመሰክራሉ።

ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች፣ እያንዳንዱ ግለሠብ ንስሃ እንዲገባ እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ለማወቅ ከመንፈስ መመሪያን ይሻሉ። ቤተክርስቲያኗ በጣም ከባድ ለሆኑት ኃጢያቶች ብቻ ነው መሪዎቿ ምን ዓይነት እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለባቸው የተቀመጠ መስፈርትያላት (32.6 እና 32.11 ተመልከቱ)። ሁለት ሁኔታዎች ተመሳሳይ አይደሉም። መሪዎች የሚሰጡት ምክር እና የሚያመቻቹት ንስሃ የመግባት ሂደት በመንፈስ የተነሳሳ መሆን አለበት እንዲሁም ለእያንዳንዱ ግለሠብ የተለየ ሊሆን ይችላል።

ጌታ የእያንዳንዱን ግለሠብ ሁኔታዎች፣ አቅም እና መንፈሳዊ እድገት ያውቃል። መሪዎች፣ አባላት እንዲፈወሱ እና ኃጢያቱን ለመድገም የሚመጣውን ፈተና ለመቋቋም ይችሉ ዘንድ አስፈላጊውን ለውጥ እንዲያደርጉ እንዴት መርዳት እንደሚችሉ እንዲገነዘቡ መንፈስ ቅዱስ ይረዳቸዋል።

አንድን ግለሠብ ንስሀ እንዲገባ፣ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለስ እና በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት እንዲፈወስ መርዳት አንድ ግለሠብ ሊያገኛቸው ከሚችላቸው እጅግ አስደሳች ተሞክሮዎች አንዱ ነው። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፥10–13 እንዲህ ያብራራል፦

“የነፍስ ዋጋ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ እንደሆነ አስታውሱ፤

“ስለሆነም፣ እነሆ ጌታ አዳኛችሁ የስጋ ሞትን ሞተ፤ ስለዚህ ሰዎች ንስሀ ገብተው ወደ እርሱ ይመጡ ዘንድ የሰዎችን ሁሉ ህመም ተሰቃየ።

“እናም በንስሀ ብቻ ሰዎችን ሁሉ ወደእርሱ ያመጣ ዘንድ፣ ከሞት ዳግም ተነሳ።

እናም ንስሀ በሚገባ ነፍስ ደስታው እንዴት ታላቅ ነው!“

32.4

መናዘዝ፣ ሚስጥራዊነት እና ለመንግስት ባለስልጣናት ማሳወቅ

32.4.1

መናዘዝ

ንስሃ መግባት ለሰማይ አባት ኃጢያት መናዘዝን ይጠይቃል። ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሏል “በዚህም ሰው ለኃጢያቶቹ ንስሀ እንደገባ ታውቃላችሁ—እነሆ፣ ይናዘዛቸዋል እናም ይተዋቸዋልም“ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 58፥43፤ በተጨማሪም ሞዛያ 26፥29 ተመልከቱ)።

የቤተክርስቲያኗ አባላት ከባድ ኃጢያት በሚሰሩበት ጊዜ፣ ንስሃቸው ለኤጲስ ቆጶሳት እና ለካስማ ፕሬዚዳንቶች መናዘዝን ያካትታል። ከዚያም እነርሱን በመወከል የንስሐ ወንጌልን ቁልፎች መጠቀም ይችላል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 13፥184፥26–27107፥18፣ 20 ተመልከቱ)። ይህም በአዳኙ የኃጢያት ክፍያ ኃይል እንዲፈውሱ እና ወደ ወንጌል መንገድ እንዲመለሱ ይረዳቸዋል።

የመናዘዝ አላማ፣ አባላት ለመለወጥ እና ለመፈወስ ሙሉ በሙሉ የጌታን እርዳታ ይፈልጉ ዘንድ ሸክማቸውን ከላያቸው እንዲያወርዱ ማበረታታት ነው። “የተሰበረ ልብ እና የተዋረደ መንፈስ“ ማዳበር በመናዘዝ ይታገዛል (2 ኔፊ 2፥7)። በፈቃደኝነት መናዘዝ አንድ ግለሠብ ንስሃ መግባት እንደሚፈልግ ያሳያል።

አንድ አባል በሚናዘዝበት ጊዜ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ በ32.8 ውስጥ የተቀመጠውን ምክር የመስጠት መመሪያ ይከተላል። አባሉን ንስሐ ለመግባት ስለሚረዳው ተስማሚ ጊዜና ቦታ መመሪያ ለማግኘት በጸሎት መንፈስ ይጠይቃል (32.5 ተመልከቱ)። የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ ሊረዳ ይችል እንደሆነም ግምት ውስጥ ያስገባል። የቤተክርስቲያኗ ፖሊሲ የአባልነት ምክር ቤትን ማካሄድ እንደሚያስፈልግ የሚያመለክት ከሆነ፣ ይህንን ያብራራል (32.6 እና 32.10 ተመልከቱ)።

አንዳንድ ጊዜ አባል የትዳር ጓደኛን ወይም ሌላ አዋቂን ጎድቶ ሊሆን ይችላል። እንደ ንስሐው አካል፣ እርሱ ወይም እርሷ አብዛኛውን ጊዜ ለዚያ ግለሠብ መናዘዝ እና ይቅርታ መጠየቅ አለበት/አለባት። ከባድ ኃጢያት የሰራ/ች ወጣት ከአርሱ ወይም ከእርሷ ወላጆች ጋር እንዲማከር/እንድትማከር ይበረታታል/ትበረታታለች።

32.4.2

ኑዛዜ ያልተደረገባቸው ወይም የተካዱ ከባድ ኃጢያቶች

አንድ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት በተለይ ስለከባድ ኃጢያት የሚያውቀው በኑዛዜ አማካኝነት ወይም ከሌላ ግለሠብ በመስማት ነው። ሊኖር ስለሚችል ከባድ ኃጢያት በመንፈስ ቅዱስ በኩል መነሳሳትን ሊቀበልም ይችላል። አንድ ግለሠብ ከኃጢያት ጋር እየታገለ እንደሆነ በመንፈስ መነሳሳት ከተሰማው፣ ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ከዚህ ግለሠብ ጋር ቀጠሮ መያዝ ይችላል። በቃለ መጠይቁ ወቅት፣ ያሳሰበውን ነገር በደግነት እና በአክብሮት መንገድ ያጋራል። ማንኛውንም የክስ ቃና ያለው ንግግር ያስወግዳል።

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ደጋፊ መረጃ ያለው ከባድ ኃጢያት መስራቱን አንድ አባል ከካደ፣ አሁንም የአባልነት ምክር ቤት ሊካሄድ ይችላል። ሆኖም፣ መንፈሳዊ ግንዛቤ ብቻውን የአባልነት ምክር ቤትን ለማካሄድ በቂ አይደለም (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 10፥37 ተመልከቱ)። አስፈላጊ ከሆነ መሪው ተጨማሪ መረጃ ሊያሰባስብ ይችላል። በ32.4.3 እና 32.10.2 ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ይከተላል።

32.4.3

መረጃን መሰብሰብ

የአባልነት ምክር ቤት ከመካሄዱ በፊት፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የሚያስፈልገውን ያህል መረጃ ይሰበስባል። አብዛኛውን ጊዜ ከአባል ኑዛዜ የሚገኝ መረጃ በቂ ነው። መረጃ ከቤተሰብ አባል፣ ከሌላ የቤተክርስቲያን መሪ፣ ከተጠቂ ወይም ከኃጢያቱ ተሳታፊ ሊመጣም ይችላል።

መረጃ በሚሰበስብበት ጊዜ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ለክህነት መሪ ተገቢ የሆኑ ዘዴዎችን ብቻ መጠቀም ይኖርበታል። የአንድን ግለሠብ ቤት በስለላ መመልከት ወይም ያለፍቃድ በድምጽ ወይም በቪድዮ መቅዳት የለበትም። ከህግ ያፈነገጠ አሰራር መጠቀምም የለበትም።

የሃሰት ውንጀላዎች እምብዛም ቢሆኑም ሊከሰቱ ይችላሉ። ከሰው ቃል በቀር ውስን የሆነ መረጃ በሚኖርበት ጊዜ የክህነት መሪዎች ጠንቃቃ መሆን አለባቸው። ለምሳሌ በዝሙት የተወነጀለ አባል ክሱን ላይቀበል ይችላል። ቅዱሳት መጻህፍት እንደሚያብራሩት፣ “በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ የቤተክርስቲያን ምስክሮች ፊት እያንዳንዱ በእርሱ ወይም በእርሷ ላይ የሚሰጠው ቃል ይጸናል” (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥80)። “ሁለት ምስክሮች” ማለት ሁለት የተለያዩ የመረጃ ምንጮች ማለት ነው። ይህም የአንድን ተሳታፊ እውቀት እና የአንድን ሌላ አስተማማኝ ምንጭ ሊያካትት ይችላል። አንዳንድ ጊዜ፣ የክህነት መሪ ተጨማሪ መረጃ እስኪገኝ ድረስ እርምጃ ሳይወስድ መጠበቅ ሊኖርበት ይችላል።

የቤተክርስቲያን መሪ ለአባልነት ምክር ቤት መረጃ በሚያሰባስብበት ጊዜ፣ የህግ አስከባሪ አካላት አባሉን በትኩረት እየመረመሩት እንደሆነ ካወቀ ወዲያውኑ ማቆም አለበት። ይህ የሚደረገው መሪው ፍትህ ላይ እንቅፋት ሊሆን ይችላል የሚሉ ሰበቦችን ለማስወገድ ነው። ስለእነዚህ ሁኔታዎች በዩናይትድ ስቴትስ እና በካናዳ ውስጥ የህግ ምክር ለማግኘት፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ የቤተክርስቲያኗን አጠቃላይ አማካሪ ቢሮን [Office of General Counsel] ያነጋግራል፦

1-800-453-3860 የውስጥ መስመር 2-6301

1-801-240-6301

ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከካናዳ ውጪ ከሆነ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ በአካባቢው ቢሮ የሚገኘውን የአካባቢውን የህግ አማካሪ ያነጋግራል።

ፍርድ ቤቱ የመጨረሻውን ብያኔ እስኪሰጥ ድረስ፣ በፍትሐ ብሄር ወይም በወንጀል ችሎት ላይ የሚመረመርን ምግባር በተለምዶ የአባልነት ምክር ቤቱ አይመለከተውም። በአንዳንድ ሁኔታዎች የህግ የይግባኝ ጊዜ ገደብ እስኪያልቅ ወይም ይግባኙ ውድቅ እስኪደረግ ድረስ የአባልነት ምክር ቤትን ማካሄድን ማዘግየት ተገቢ ሊሆን ይችላል።

32.4.4

ሚስጥራዊነት

ኤጲስ ቆጶሳት፣ የካስማ ፕሬዚዳንቶች፣ እና አማካሪዎቻቸው የተሰጧቸውን ሚስጥራዊ መረጃዎች ሁሉ የመጠበቅ የተቀደሰ ሃላፊነት አለባቸው። ይህ መረጃ በቃለ መጠይቅ፣ በማማከር እና በመናዘዝ ወቅት ሊገኝ ይችላል። በአባልነት ምክር ቤት ውስጥ የሚሳተፉ ሁሉ ተመሳሳይ ምስጢር የመጠበቅ ግዴታው አለባቸው። ሚስጥራዊነት አስፈላጊ ነው ምክንያቱም አባላት የሚያጋሩት ነገር በሚስጥር የማይያዝ ከሆነ ኃጢያቶችን ላይናዘዙ ወይም መመሪያ ላይፈልጉ ይችላሉ። መተማመንን ማፍረስ የአባላትን እምነት ይሸረሽራል እንዲሁም በመሪዎቻቸው ላይ እምነት እንዲያጡ ያደርጋቸዋል።

ኤጲስ ቆጶሳት፣ የካስማ ፕሬዚዳንቶች ወይም አማካሪዎቻቸው እነዚህን መረጃዎች ሚስጥራዊ ኃላፊነታቸውን በጠበቀ መልኩ፣ እንደሚከተለው ብቻ ሊያጋሩ ይችላሉ፦

  • የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድን ወይም ተዛማጅ ጉዳዮችን በተመለከተ ከአባሉ የካስማ ፕሬዚዳንት፣ የሚስዮን ፕሬዚዳንት ወይም ከኤጲስ ቆጶሱ ጋር መነጋገር ያስፈልጋቸዋል። የካስማ ፕሬዚዳንቱ ከተመደበለት የአካባቢ ሰባ ጋርም ሊነጋገር ይችላል። አስስፈላጊ ከሆነ፣ የአካባቢ ሰባው የካስማ ፕሬዚዳንቱን ወደ አካባቢው አመራር ይመራዋል። የአባልነት ምክር ቤት መካሄድ እንዳለበት ወይንም ውጤቱን የሚወስነው የካስማ ፕሬዚዳንቱ ብቻ ነው።

  • የአባልነት ውሳኔዎችን ወይም ሌሎች አሳሳቢ ጉዳዮችን በመጠባበቅ ላይ እያሉ ግለሠቡ ወደ አዲስ አጥቢያ ከተዛወረ (ወይም የክህነት መሪው ከጥሪው ከለቀቀ)። በእነዚህ ሁኔታዎች፣ መሪው ስለአሳሳቢ ጉዳዮቹ ወይም ሊወሰድ ስለሚችለው እርምጃ ለአዲሱ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት ያሳውቃል (32.14.7 ተመልከቱ)። አባሉ በሌሎች ላይ ስጋት የሚፈጥር ከሆነም ለመሪው ያሳውቃል።

  • አንድ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት ከአጥቢያው ወይም ከካስማው ውጭ የሚኖር የቤተክርስቲያኗ አባል በከባድ ኃጢያት ውስጥ ተሳታፊ ሊሆን እንደሚችል ያወቀ ከሆነ። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ፣ የዚያን አባል ኤጲስ ቆጶስ በሚስጥር ያነጋግራል።

  • የአባልነት ምክር ቤት በሚካሄድበት ወቅት መረጃን መግለጽ አስፈላጊ ነው። በአባልነት ምክር ቤት ደረጃ የተሰበሰቡ እና የተገለጹ መረጃዎች ሁሉ ሚስጥራዊ ናቸው።

  • አባሉ፣ መረጃን ለተወሰኑ ሰዎች እንዲያካፍል ለመሪው ፍቃድ ለመስጠት ሊመርጥ ይችላል። እነዚህም ወላጆችን፣ የቤተክርስቲያን መሪዎችን ወይም ሌሎች ድጋፍ ሊሰጡ የሚችሉ ሰዎችን ሊያካትት ይችላል። መሪው፣ አባሉ ፍቃድ ከሰጠው መረጃ ውጪ አያካፍልም።

  • የአባልነት ምክር ቤት ውሳኔን አስመልክቶ የተወሰነ መረጃን ማካፈል አስፈላጊ ሊሆን ይችላል (32.12.2 ተመልከቱ)።

በሌሎች ሁኔታዎች ሁሉ፣ መሪው 32.4.5 ሊመለከት ይገባል። እነዚህም በልጆች ላይ ጥቃት እንደመፈፀም ያሉ፣ ሕጉ ለመንግስት ባለስልጣናት ሪፖርት እንዲደረጉ አስገዳጅ ሊያደርጋቸው የሚችላቸውን ጉዳዮች ይጨምራሉ።

የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና ህጉን ለማክበር መሪዎችን መርዳት እንዲቻል ቤተክርስቲያኗ በሰለጠኑ ባለሙያዎች እርዳታ ትሰጣለች። ይህንን መመሪያ ለማግኘት፣ መሪዎች አገልግሎቱ ባለበት ቦታ የቤተክርስቲያኗን የጥቃት እርዳታ መስጫ የስልክ መስመር ወዲያውኑ ይደውላሉ (32.4.5 እና 38.6.2.1 ተመልከቱ)። አገልግሎቱ የማይገኝ ከሆነ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ በአካባቢ ቢሮ የሚገኘውን የአካባቢውን የህግ አማካሪ ያነጋግራል።

አንድ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት መጀመሪያ እንደዚህ አይነት መመሪያ ሳያስፈልገው ሚስጥራዊ መረጃን መግለጽ የሚኖርበት በአንድ ሁኔታ ውስጥ ብቻ ነው ። ይህም ለህይወት አስጊ የሆኑ ጥቃቶችን ወይም ከባድ ጉዳቶችን ለመከላከል ሲባል መረጃን መግለጽ አስፈላጊ ሲሆን እና መመሪያ ለመጠየቅ ጊዜ ከሌለው ነው። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ፣ ሌሎችን የመጠበቅ ግዴታ ሚስጥራዊ ከመሆን ግዴታ የበለጠ አስፈላጊ ነው። መሪዎች የመንግሥት ባለስልጣናትን በአስቸኳይ ማነጋገር አለባቸው።

መሪዎች ማስታወሻ የሚይዙ ከሆነ ወይም እርስ በእርሳቸው የሚገናኙት በኤሌክትሮኒክ መንገድ ከሆነ፣ ይህን መረጃ ሌሎች እንዳያገኙት ይከላከላሉ። እንዲሁም መረጃውን ከእንግዲህ ወዲህ የማይፈልጉት ከሆነ ይሰርዙዝታል ወይም ያጠፋታል። አስፈላጊ ሳይሆን የግል መረጃን አያካፍሉም።

የመንግሥት ባለስልጣናት ከክህነት መሪ የሚጠበቀውን ሚስጥራዊነት ሊጋፉ ይችላሉ። ይህ በዩናይትድ ስቴትስ እና በካናዳ ውስጥ ከተከሰተ የካስማ ፕሬዚዳንቱ ከቤተክርስቲያኗ አጠቃላይ አማካሪ ቢሮ [Office of General Counsel] የህግ ምክር ይጠይቃል።

1-800-453-3860 የውስጥ መስመር 2-6301

1-801-240-6301

ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከካናዳ ውጪ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ በአካባቢ ቢሮ የሚገኘውን የአካባቢ የህግ አማካሪ ያነጋግራል።

32.4.5

ለመንግስት ባለስልጣናት ማሳወቅ

ንስሃ የሚገቡ አንዳንድ ሰዎች የፍትሐ ብሄር ወይም የወንጀል ህጎችን የጣሱ ናቸው። በአንዳንድ ሁኔታዎች የመንግስት ባለስልጣናት ይህንን አያውቁም። ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዳንቶች አባላት ህጉን እንዲከተሉ እና አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜም እንደዚህ ያሉ ጉዳዮችን እንዲያሳውቁ ያበረታታሉ። በተጨማሪም አባላት ሪፖርት በሚያደርጉበት ጊዜ ብቃት ያለው የህግ ምክር እንዲያገኙ መሪዎች ይመክራሉ። የቤተክርስቲያኗ ፖሊሲ ህግን ማክበር ነው።

በብዙ ቦታዎች፣ የክህነት መሪዎች የሚያውቋቸውን አንዳንድ ህገወጥ ባሕርያት ሪፖርት እንዲያደርጉ ህግ ያስገድዳቸዋል። ለምሳሌ አንዳንድ ግዛቶች እና ሀገራት በልጆች ላይ የሚደርስ ጥቃትለህግ አስፈጻሚ አካላት ሪፖርት እንዲደረግ ያስገድዳሉ።

በአንዳንድ አገሮች፣ ቤተክርስቲያኗ ኤጲስ ቆጶሳትን እና የካስማ ፕሬዚዳንቶችን ለመርዳት ሚስጥራዊ የጥቃት እርዳታ መጠየቂያ ስልክ ቁጥር አዘጋጅታለች። እነዚህ መሪዎች ጥቃት ደርሶበት ሊሆን ስለሚችል ወይም የመጠቃት ሥጋት ውስጥ ስላለ ግለሠብ ስለእያንዳንዱ ሁኔታ በፍጥነት ወደ እርዳታ መጠየቂያ ስልክ ቁጥር መደወል አለባቸው (38.6.2.1 ተመልከቱ)። ይህም በቀን 24 ሰዓታት፣ በሳምንት 7 ቀናት አገልግሎት ይሠጣል።

የጥቃት እርዳታ መጠየቂያ ስልክ ቁጥር በሌለባቸው አገሮች ውስጥ፣ ጥቃት እየተፈጸመ እንደሆነ የሚያውቅ ኤጲስ ቆጶስ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱን ማነጋገር ይኖርበታል፤ እርሱም በአካባቢ ቢሮ ከሚገኘው የአካባቢው የህግ አማካሪ መመሪያ ማግኘት አለበት።

የጥቃት ሪፖርት ስለማቅረብ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት 38.6.2.1 እና 38.6.2.7 ተመልከቱ።


አንድ ግለሠብ ንስሃ እንዲገባ ለመርዳት የሚያስችል ሁኔታን መወሰን


32.5

አንድ ግለሠብ ንስሃ እንዲገባ ለመርዳት የሚያስችሉ ሁኔታዎች

አንድ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት፣ አንድ ግለሠብ ከባድ ኃጢያት እንደሰራ ካወቀ፣ የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ እርምጃ ይወስዳል። እንዲሁም ግለሠቡ ንስሃ እንዲገባ እና ወደ አዳኙ እንዲቀርብ ለመርዳት የሚያስችል ሁኔታን ለመወሰን የመንፈስ ቅዱስን መመሪያ ይጠይቃል።

32.5.1

የሁኔታዎቹ አጠቃላይ እይታ

የሚከተለው ሰንጠረዥ ሰው ንስሃ እንዲገባ ለመርዳት የሚያስችሉ ሶስት ሁኔታዎችን ይዘረዝራል። እንዲሁም መሪዎች የትኛውን ሁኔታ መጠቀም እንዳለባቸው ሲወስኑ ግምት ውስጥ የሚያስገቧቸውን አንዳንድ ነገሮች አጠቃልሎ ይዟል።

አንድ ግለሠብ ንስሃ እንዲገባ ለመርዳት የሚያስችሉ ሁኔታዎች

ሁኔታዎች

ግምት ውስጥ የሚገቡ አንዳንድ ነገሮች (በተጨማሪም 32.7 ተመልከቱ)።

ሁኔታዎች

የካስማ የአባልነት ምክር ቤት

ግምት ውስጥ የሚገቡ አንዳንድ ነገሮች (በተጨማሪም 32.7 ተመልከቱ)።

  • የቤተመቅደስ ቡራኬን ለተቀበሉ አባላት።

  • ይህ አስፈላጊ የሚሆነው በ32.6.132.6.2፣ ወይም 32.6.3 ውስጥ የተገለጹትን ከባድ ኃጢያቶች ወይም ድርጊቶች የፈጸመ/ች የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበለ/ች ወንድ ወይም ሴት ከቤተክርስቲያኗ አባልነት የሚወገድ/የምትወገድ ከሆነ ነው።

ሁኔታዎች

የአጥቢያ የአባልነት ምክር ቤት

ግምት ውስጥ የሚገቡ አንዳንድ ነገሮች (በተጨማሪም 32.7 ተመልከቱ)።

  • ለማንኛውም አባል።

  • 32.6.1 ውስጥ ለተገለጹት ከባድ ኃጢያቶች አስፈላጊ ነው።

  • 32.6.2 እና 32.6.3 ውስጥ ለተገለጹት ከባድ ኃጢያቶች ሊያስፈልግ ይችላል።

  • 32.6.132.6.2፣ ወይም 32.6.3 ውስጥ የተገለጹትን ከባድ ኃጢያቶች ወይም ድርጊቶች የፈጸመ/ች የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበለ/ች ወንድ ወይም ሴት ከቤተክርስቲያኗ አባልነት የሚወገድ/የምትወገድ ከሆነ በቂ አይደለም።

ሁኔታዎች

የግል ምክር (32.8 ተመልከቱ)።

ግምት ውስጥ የሚገቡ አንዳንድ ነገሮች (በተጨማሪም 32.7 ተመልከቱ)።

  • ለማንኛውም አባል።

  • መደበኛ ያልሆኑ የቤተክርስቲያኗ የአባልነት ገደቦችን ሊያካትት ይችላል።

  • በንስሃ ሂደቱ የአባልነት ምክር ቤት ለሚያስፈልጋቸው ከባድ ኃጢያቶች ወይም ድርጊቶች በቂ ላይሆን ይችላል (32.6.2 እና 32.6.3 ተመልከቱ)።

  • የአባልነት ምክር ቤት ለሚያስፈልጋቸው ከባድ ኃጢያቶች በቂ አይደለም (32.6.1 ተመልከቱ)።

  • 32.6.132.6.2፣ ወይም 32.6.3 ውስጥ የተገለጹትን ከባድ ኃጢያቶች ወይም ድርጊቶች የፈጸመ/ች የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበለ/ች ወንድ ወይም ሴት ከቤተክርስቲያኗ አባልነት የሚወገድ/የምትወገድ ከሆነ በቂ አይደለም።

በኤጲስ ቆጶሱ ወይም በካስማ ፕሬዚዳንቱ የሚደረግ የግል ምክር እና መደበኛ ያልሆነ እገዳ ሰው ለከባድ ኃጢያቶች ንስሃ እንዲገባ ለመርዳት አንዳንድ ጊዜ በቂ አይደለም። በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ የእስራኤል ዳኛን ለመርዳት ጌታ የአባልነት ምክር ቤት አዘጋጅቷል። (ዘጸዓት 18፥12–27ሞዛያ 26፥29–36ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42፥80–83፤ 102 ተመልከቱ።) ለአንዳንድ ከባድ ኃጢያቶች በቤተክርስቲያን አቅዋም መመሪያ መሰረት የአባልነት ምክር ቤት በግድ ያስፈልጋል (32.6.1 ተመልከቱ)። የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን ማፍረስ የአባልነት ምክር ቤትን አስፈላጊ የመሆን እድል ይጨምራል (32.7.4 ተመልከቱ)።

በአጥቢያ ውስጥ የኤጲስ ቆጶስ አማካሪዎች በአባልነት ምክር ቤት ያግዛሉ። በካስማ ውስጥ የካስማ ፕሬዚዳንቱ አማካሪዎች ያግዛሉ። በአንዳንድ የካስማ የአባልነት ምክር ቤት የካስማው ከፍተኛ ምክር ቤት አባላት ይሳተፋሉ (32.9.2 ተመልከቱ)። በአባልነት ምክር ቤት ውስጥ የኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ አመራሩ ከግለሠቡ ጋር በፍቅር መንፈስ ይገናኛሉ።

32.5.2

ሁኔታዎቹን እና ጊዜውን መወሰን

ከእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ የትኞቹ አንድን ግለሠብ በተሻለ ሁኔታ ንስሃ እንዲገባ ሊረዱት እንደሚችሉ ሲወስኑ፣ መሪዎች የመንፈስ ቅዱስን መመሪያ ይፈልጋሉ። የሚቀጥሉትን ነገሮችንም ግምት ውስጥ ያሰገባሉ፦

  • የኃጢያቱ ክብደት እና የአባልነት ምክር ቤት የግድ ስለማስፈለጉ የተቀመጠ የቤተክርስቲያኗን ፖሊሲ (32.6 ተመልከቱ)።

  • የግለሠቡ ሁኔታዎች (32.7 ተመልከቱ)።

ኤጲስ ቆጶሱ የተወሰኑ ሁኔታዎችን በተመለከተ ከካስማ ፕሬዚዳንቱ ጋር ይማከራል። የአባልነት ምክር ቤት ከማካሄዱ በፊት ከካስማ ፕሬዚዳንቱ ፈቃድ መቀበል አለበት።

የካስማ ፕሬዚዳንቱ በአስቸጋሪ ጉዳዮች ላይ ከተመደበለት የአካባቢ ሰባ ምክር ሊጠይቅ ይችላል። የካስማ ፕሬዚዳንቱ በ32.6.3 ውስጥ በተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይ ከአካባቢው አመራር ጋር መማከር ይኖርበታል። ሆኖም ምግባሩን ለመመልከት የአባልነት ምክር ቤት መካሄድ እንዳለበት የሚወስነው የካስማ ፕሬዚዳንቱ ብቻ ነው። የአባልነት ምክር ቤት ከተካሄደ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ ወይም ኤጲስ ቆጶሱ ውጤቱን ይወስናል።

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የግል ምክር እንደሚበቃ ከወሰነ፣ በ32.8 ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ይከተላል። የአባልነት ምክር ቤት እንደሚያስፈልግ ከወሰነ ወይም የቤተክርስቲያኗ ፖሊሲ ምክር ቤት ማካሄድን አስፈላጊ ካደረገው፣ ይህን የሚያካሂደው ግለሠብ በ32.9–32.14 ውስጥ ያሉትን የአሰራር ቅደም ተከተሎች ይከተላል።

ምክር ቤት ከመካሄዱ በፊት ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ መደበኛ ያልሆነ የአባልነት ገደብ መጣል ለጊዜውተመራጭ እንደሆነ ሊወስን ይችላል። አባሉ ልባዊ ንስሐ እንዲገባ የሚያበረታታ ሲሆን ምክር ቤቱን ያካሂዳል። ሆኖም የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊ ከሆነ፣ ምክር ቤቱን ማካሄድን ማዘግየት የለበትም።

32.6

የኃጢያቱ ክብደት እና የቤተክርስቲያኗ ፖሊሲ

የኃጢያት ክብደት (1) የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና (2) አንድ ግለሠብ ንስሐ እንዲገባ የሚረዳውን ሁኔታ ለመወሰን ጠቃሚ የሆነ ግምት ውስጥ መግባት ያለበት ነገር ነው። ጌታ “ኃጢያትን በዝቅተኛ ደረጃ መመልከት አይቻለኝም” ብሏል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥31፤ በተጨማሪም ሞዛያ 26፥29) ተመልከቱ)። አገልጋዮቹ የከባድ ኃጢያት ማስረጃዎችን ችላ ማለት አይገባቸውም።

ከባድ ኃጢያቶች ሆን ተብሎ በእግዚአብሔር ህግጋት ላይ የሚፈጸሙ ትልቅ ወንጀሎች ናቸው። የከባድ ኃጢያት ምድቦች ከታች ተዘርዝረዋል።

  • የጠበኝነት ድርጊቶች እና ጥቃት (32.6.1.1 እና 32.6.2.1 ተመልከቱ)።

  • ወሲባዊ የስነምግባር ጉድለት (32.6.1.2 እና 32.6.2.2 ተመልከቱ)።

  • የማጭበርበር ድርጊቶች (32.6.1.3 እና 32.6.2.3 ተመልከቱ)።

  • እምነት ማጉደል (32.6.1.4 እና 32.6.2.4 ተመልከቱ)።

  • አንዳንድ ሌሎች ድርጊቶች (32.6.1.5 እና 32.6.2.5 ተመልከቱ)።

የሚከተሉት ክፍሎች የአባልነት ምክር ቤት የግድ አስፈላጊ የሚሆንበትን ጊዜ፣ አስፈላጊ ሊሆን የሚችልበትን ጊዜ እና አስፈላጊ የማይሆንበትን ጊዜ ይገልፃሉ።

32.6.1

የአባልነት ምክር ቤት የግድ አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜ

አንድ አባል በዚህ ክፍል የተገለጹትን ማንኛቸውንም ኃጢያቶች ሰርቶ ሊሆን እንደሚችል መረጃ በሚያመለክትበት ጊዜ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ አለበት። የአባላት መንፈሳዊ ብስለት ደረጃ እና የወንጌል ግንዛቤ ምንም ይሁን ምን ለእነዚህ ኃጢያቶች የግድ የአባልነት ምክር ቤትን ማካሄድ ያስፈልጋል።

በዚህ ክፍል ለተዘረዘሩት ኃጢያቶች የሚካሄዱ የአባልነት ምክር ቤቶች ሊያመጡ ስለሚችሏቸው ውጤቶች በ32.11 ውስጥ ተመልከቱ። መደበኛ ያልሆኑ የአባልነት ገደቦች ለእነዚህ ምክር ቤቶች አማራጭ አይሆኑም።

32.6.1.1

የጠበኝነት ድርጊቶች እና ጥቃት

ነፍስ ግድያ። አንድ አባል አንድን ግለሠብ ከገደለ የግድ የአባልነት ምክር ቤትን ማካሄድ ያስፈልጋል። እዚህ ላይ ባለው አጠቃቀም፣ ነፍስ ግድያ ማለት ሆን ብሎ፣ ያለምክንያት የሰውን ህይወት ማጥፋት ነው። ግለሰቡን ከቤተክርስቲያኗ አባልነት የግድ ማስወጣትያስፈልጋል።

ነፍስ ግድያ ፖሊስ ወይም ወታደር በስራ ላይ እያለ የሚፈጽማቸውን ድርጊቶች አያካትትም። በዚህ አውድ ውስጥ ፅንስ ማስወረድ ነፍስ ግድያ ተብሎ አይገለጽም። በአደጋ ወይም የራስን ወይም የሌሎችን ደህንነት በመጠበቅ ሂደት ሞት የተከሰተ ከሆነ፣ የሰውን ህይወት ማጥፋቱ ነፍስ ግድያ ተብሎ ላይተረጎም ይችላል። ይህ በሌሎች ሁኔታዎች ላይም እውነት ሊሆን ይችላል፣ ለምሳሌ ሰው የአእምሮ አቅም ውስንነት በሚኖረው ጊዜ።

አስገድዶ መድፈር። አስገድዶ መድፈር በሚፈጸምበት ጊዜ የግድ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ ያስፈልጋል። እዚህ ላይ ባለው አጠቃቀም፣ አስገድዶ መድፈር ማለትየግዳጅ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ወይም አእምሯዊ ወይም አካላዊ አቅም በመቀነሱ ምክንያት በህጋዊ መንገድ ፍቃድ መስጠት ከማይችል ሰው ጋር የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈፀም ማለት ነው። እዚህ ላይ ባለው አጠቃቀም፣ አስገድዶ መድፈር በእድሜ በሚቀራረቡ ለአካለ መጠን ባልደረሱ ሁለት ልጆች መካከል በስምምነት የሚደረግን የግብረ ሥጋ ግንኙነትን አያካትትም።

የወሲባዊ አካላዊ ጥቃት ጥፋተኝነት አንድ አባል የወሲባዊ አካላዊ ጥቃት ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ፣ የግድ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ ያስፈልጋል።

በልጆች ወይም በወጣቶች ላይ የሚደርሥ ጥቃት።38.6.2.3 ውስጥ በተገለጸው መሰረት አንድ ግለሠብ በልጆች ወይም በወጣቶች ላይ ጥቃት ከፈፀመ የግድ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ ያስፈልጋል።

በትዳር አጋር ወይንም በሌላ አዋቂ ላይ ጥቃት መፈፀም። የጥቃት ባሕርይ ክብደት በደረጃ የተለያየ ነው። በትዳር አጋር ወይንም በሌላ አዋቂ ላይ ለሚፈፀም ጥቃት መቼ የአባልነት ምክር ቤት የግድ ማካሄድ እንደሚያስፈልግ 38.6.2.4ን ተመልከቱ።

ሌላን ለመጉዳት ሆን ብሎ በጉልበት የሚደረግ ወንጀለኛ ባሕርይ። አንድ አዋቂ ሰው ሌላን ለመጉዳት ሆን ብሎ በሚያደርገው ወንጀለኛ ባሕርይ በተደጋጋሚ በሰዎች ላይ አካላዊ ጉዳት የሚያደርስ ከሆነ እና ለሌሎች ሥጋት ከሆነ የግድ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ ያስፈልጋል።

32.6.1.2

ወሲባዊ የስነምግባር ጉድለት

በቅርብ የቤተሰብ አባላት መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት።38.6.10 ውስጥ በተገለጸው መሰረት በቅርብ ቤተሰብ አባላት መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚፈጸምበት ጊዜ የግድ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ ያስፈልጋል። ሁል ጊዜ ግለሠቡን ከቤተክርስቲያኗ አባልነት የግድ ማስወገድ ያስፈልጋል።

የልጆች የብልግና ምስሎች።38.6.6 ውስጥ በተገለጸው መሠረት አንድ ግለሠብ በልጆች የብልግና ምስሎች ላይ ከተሳተፈ የግድ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ ያስፈልጋል።

ከአንድ በላይ ጋብቻ ። አንድ ግለሠብ እያወቀ ከአንድ በላይ ጋብቻ ከፈፀመ፣ የግድ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ ያስፈልጋል። አንድ የትዳር ጓደኛ፣ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የትዳር ጓደኞች እንዳሉት/እንዳላት ሳያውቅ/ሳታውቅ. አንዳንድ ከአንድ በላይ ጋብቻዎች በሚስጥር ሊፈፀሙ ይችላሉ። አንድ ግለሠብ እያወቀ ከአንድ በላይ ጋብቻ ከፈፀመ ከቤተክርስቲያኗ አባልነት መወገድ አለበት።

ፆታዊ በደል የማድረስ ባሕርይ። አንድ አዋቂ ሰው በተደጋጋሚ በሌሎች ላይ ፆታዊ በደል የሚያደርስ ከሆነ እና ለሌሎች ሥጋት ከሆነ የግድ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ ያስፈልጋል።

32.6.1.3

የማጭበርበር ድርጊቶች

ሌላን ሠው ለመጉዳት ሆን ተብሎ የሚደረግ የገንዘብ አጭበርባሪነት ባሕርይ። አንድ አዋቂ ሰው ሆን ብሎ እንዲሁም በተደጋጋሚ በሰዎች ላይ ገንዘብ ነክ ጥቃት የማድረስ ታሪክ ካለው እና ለሌሎች አስጊ ከሆነ የግድ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ ያስፈልጋል (38.6.2.4 ተመልከቱ)። ይህም የኢንቨስትመንት ማጭበርበርን እና ተመሳሳይ ተግባራትን ያጠቃልላል። በኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ምክንያት የሚከሰት ያልታሰበ የገንዘብ ኪሳራ እንደ ማጭበርበር አይቆጠርም። የህግ ክርክር እየተደረገ ከሆነ፣ የክህነት መሪዎች የመጨረሻ ውጤቱ እስኪታወቅ ድረስ ለመጠበቅ ሊወስኑ ይችላሉ። አንድ አባል የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ ወይም ንብረት በመመዝበር ላይ ተሳትፎ የነበረ ከሆነ 32.6.3.3 ተመልከቱ።

32.6.1.4

እምነት ማጉደል

በታወቀ የቤተክርስቲያን የሃላፊነት ቦታ ላይ በመሆን ከባድ ኃጢያት መስራት። አንድ አባል በታወቀ የቤተክርስቲያን የሃላፊነት ቦታ ላይ በመሆን ከባድ ኃጢያት ከሰራ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ በግድ ያስፈልጋል። እነዚህ አጠቃላይ ባለስልጣናትን፣ አጠቃላይ መሪዎችን፣ የአካባቢ ሰባን፣ የቤተመቅደስ ፕሬዚዳንትን ወይም ባለቤቱን (matron [ሜትሮን])፣ የሚስዮን ፕሬዚዳንትን ወይም ባለቤቱን፣ የካስማ ፕሬዚዳንትን፣ ፓትርያርክን ወይም ኤጲስ ቆጶስን ያካትታሉ። ይህ የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንቶችን አይመለከትም። ሆኖም እንደ ሌሎች አባላት፣ በቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት የቤተክርስቲያን አባልነት መብቶች ላይም ገደብ ሊጣል ወይም ከአባልነት ሊወገድ ይችላል።

32.6.1.5

አንዳንድ ሌሎች ተግባራት

እጅግ ከባድ የሆነ ወንጀል ጥፋተኝነት። አንድ ግለሠብ እጅግ ከባድ በሆነ ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች የግድ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ ያስፈልጋል።

32.6.2

የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜ

በሚከተሉት ሁኔታዎች የአባልነት ምክር ቤት ምናልባት ሊያስፈልግ ይችላል።

32.6.2.1

የጠበኝነት ድርጊቶች እና ጥቃት

ጌታ ”አትግደል፣ ወይም እንደዚህ ዓይነት ነገሮችን አታድርግ” ሲል አዟል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥6 ትኩረት ተጨምሮበታል)። የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ሊሆን የሚችልባቸው የጠበኝነት ድርጊቶች እና ጥቃት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያካትታሉ (ሆኖም በእነዚህ ብቻ የተገደቡ አይደሉም)።

የነፍስ ግድያ ሙከራ። ሆነ ብሎ አንድን ሰው ለመግደል መሞከር።

ወሲባዊ ጥቃት፣ አካላዊ ጥቃትን እና ትንኮሳን ጨምሮ። ወሲባዊ ጥቃት ብዛት ያላቸው ድርጊቶችን ይሸፍናል (38.6.18 ተመልከቱ)። አንድ ግለሠብ ወሲባዊ ትንኮሳ ወይም ጥቃት ከፈጸመ የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። እርሱ ወይም እርሷ የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን ከጣሰ/ች ወይም ኃጢያቱ/ቷ ተደጋጋሚ ከሆነ አባሉ/ሏ ንስሃ እንዲገባ/ድትገባ ለመርዳት የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ የበለጠ አስፈላጊ ይሆናል። የአባልነት ምክር ቤት መቼ የግድ እንደሚያስፈልግ 38.6.18.3 ተመልከቱ።

በትዳር አጋር ላይ ወይንም በሌላ አዋቂ ላይ የሚደርሥ ጥቃት። የጥቃት ባሕርይ የክብደት ደረጃ ይለያያል (38.6.2.4 ተመልከቱ)። በትዳር ጓደኛ ላይ ወይም በሌላ አዋቂ ሰው ላይ ጥቃት ለፈፀመ ግለሠብ የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። እርሱ ወይም እርሷ የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን ከጣሰ/ች ወይም ኃጢያቱ/ቷ ተደጋጋሚ ከሆነ አባሉ/ሏ ንስሃ እንዲገባ/ድትገባ ለመርዳት የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ የበለጠ አስፈላጊ ይሆናል። የአባልነት ምክር ቤት መቼ የግድ እንደሚያስፈልግ 38.6.2.4 ተመልከቱ።

32.6.2.2

ወሲባዊ የስነምግባር ጉድለት

የጌታ የንጽህና ህግ ከህጋዊ ጋብቻ ውጭ በወንድና በሴት መካከል ከሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት መራቅን ያዛል (ዘጸዓት 20፥14ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 63፥16 ተመልከቱ)። በ38.6.5 ውስጥ በተገለጸው መሰረት ወሲባዊ የስነምግባር ጉድለት በሚፈጸምበት ጊዜ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። እርሱ ወይም እርሷ የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን ከጣሰ/ች ወይም ኃጢያቱ/ቷ ተደጋጋሚ ከሆነ አባሉ/ሏ ንስሃ እንዲገባ/ድትገባ ለመርዳት በእነዚህ ሁኔታዎች የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ የበለጠ አስፈላጊ ይሆናል። የአባልነት ምክር ቤት መቼ የግድ እንደሚያስፈልግ 32.6.1.2 ተመልከቱ።

32.6.2.3

የማጭበርበር ድርጊቶች

አሥርቱ ትዕዛዛት “አትስረቅ” ወይም ”በሃሰት አትመስክር” በማለት ያስተምራል (ዘጸዓት 20፥15–16)። በተለይ ስርቆት ለመፈጸም የሰው ቤት ውስጥ መግባት፣ ስርቆት፣ ምዝበራ፣ የሀሰት ምስክርነት እና ማጭበርበር ላሉ ድርጊቶች የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። ታዋቂ ሰዎችን በመጠቀም ስለማጭበርበር 38.8.2 ተመልከቱ። እርሱ ወይም እርሷ የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን ከጣሰ/ች ወይም ኃጢያቱ/ቷ ተደጋጋሚ ከሆነ አባሉ/ሏ ንስሃ እንዲገባ/ድትገባ ለመርዳት በእነዚህ ሁኔታዎች የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ የበለጠ አስፈላጊ ይሆናል።

ታዋቂ ሰዎችን በመጠቀም ስለማጭበርበር 38.8.2 ተመልከቱ። ለማጭበርበር ድርጊቶች የአባልነት ምክር ቤት መቼ የግድ እንደሚያስፈልግ 32.6.1.3 ተመልከቱ። አንድ አባል የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ ወይም ንብረት በመመዝበር ላይ ተሳትፎ የነበረ ከሆነ 32.6.3.3 ተመልከቱ።

32.6.2.4

እምነትን ማጉደል

አንድ አባል የሚከተሉትን ካደረገ የአባልነት ምክር ቤት ምናልባት ሊያስፈልግ ይችላል።

  • በታወቀ የቤተክርስቲያን ወይም የህብረተሰብ የሃላፊነት ቦታ ወይም ባለአደራ ሆኖ/ሆና እያለ/እያለች ከባድ ኃጢያት ከሰራ/ች።

  • በሰፊው የታወቀ ከባድ ኃጢያት ከሰራ/ች።

እርሱ ወይም እርሷ የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን ከጣሰ/ች ወይም ኃጢያቱ/ቷ ተደጋጋሚ ከሆነ አባሉ/ሏ ንስሃ እንዲገባ/ድትገባ ለመርዳት በእነዚህ ሁኔታዎች የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ የበለጠ አስፈላጊ ይሆናል።

የአባልነት ምክር ቤት መቼ በግድ እንደሚያስፈልግ 32.6.1.4 ተመልከቱ። አባል የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ ወይም ንብረት በመመዝበር ላይ ተሳትፎ የነበረ ከሆነ 32.6.3.3 ተመልከቱ።

32.6.2.5

አንዳንድ ሌሎች ተግባራት

ንጉስ ቢንያም “ኃጢያት ልትፈፅሙ የምትችሉባቸውን ነገሮች ሁሉ ልነግራችሁ አልችልም፤ ምክንያቱን መቁጠር የማልችለው ብዙ መንገዶችና ዘዴዎች ስለሚኖሩ ነው” ብሎ አስተምሯል (ሞዛያ 4፥29)። አንድ አባል የሚከተሉትን ካደረገ/ካደረጋች የአባልነት ምክር ቤት ምናልባት ሊያስፈልግ ይችላል፦

  • ከባድ ኃጢያት የመሥራት ልማድን የሚያሳይ ከሆነ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 82፥7 ተመልከቱ)።

  • የልጅ ማሳደጊያ ድጋፍ መስጠትን እና ለትዳር አጋር እንዲሰጥ በፍርድ ቤት የተወሰነን ቀለብ አለመክፈልን ጨምሮ ሆን ብሎ የቤተሰብ ኃላፊነቶችን የተወ ከሆነ።

  • በአካልም ሆነ በይነመረብ የመገናኛ ዘዴዎች አካላዊ ጥቃት እንደሚያደርስ የሚያስፈራራ ከሆነ (32.2.1 ተመልከቱ)።

  • ህገወጥ መድሃኒቶችን የሚሸጥ ከሆነ።

  • ሌሎች ከባድ የሆኑ የወንጀል ድርጊቶችን የሚፈጽም ከሆነ።

እርሱ ወይም እርሷ የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን ከጣሰ/ች ወይም ኃጢያቱ/ቷ ተደጋጋሚ ከሆነ አባሉ/ሏ ንስሃ እንዲገባ/ድትገባ ለመርዳት በእነዚህ ሁኔታዎች የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ የበለጠ አስፈላጊ ይሆናል።

አንድ አባል ፅንስ ማስወረድን ከፈቀደ/ች፣ ካከናወነ/ች፣ ካመቻቸ/ች፣ ክፍያ ከፈጸመ/ች ወይም ካበረታታ/ች የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። መመሪያዎችን ለማግኘት 38.6.1 ተመልከቱ።

የአባልነት ምክር ቤት የግድ ወይም ምናልባት አስፈላጊ ሊሆን የሚችልበት ጊዜ

የኃጢያት አይነት

የአባልነት ምክር ቤት የግድ ያስፈልጋል (32.6.1ን ተመልከቱ)።

የአባልነት ምክር ቤት ምናልባት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል(32.6.2 ተመልከቱ)።

የኃጢያት አይነት

የጠበኝነት ድርጊቶች እና ጥቃት

የአባልነት ምክር ቤት የግድ ያስፈልጋል (32.6.1ን ተመልከቱ)።

  • ነፍስ ግድያ

  • አስገድዶ መድፈር

  • የወሲብ ጥቃት ጥፋተኝነት

  • በልጆች ወይም በወጣቶች ላይ ጥቃት መፈፀም

  • ሌላን ለመጉዳት ሆን ብሎ በጉልበት የሚደረግ ወንጀለኛ ባሕርይ

የአባልነት ምክር ቤት ምናልባት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል(32.6.2 ተመልከቱ)።

  • የነፍስ ግድያ ሙከራ

  • ፆታዊ ጥቃት፣ አካላዊ ጥቃትን እና ትንኮሳን ጨምሮ (የአባልነት ምክር ቤት መቼ የግድ እንደሚያስፈልግ 38.6.18 ተመልከቱ)።

  • በትዳር አጋር ወይንም በሌላ አዋቂ ላይ ጥቃት መፈፀም (የአባልነት ምክር ቤት መቼ የግድ እንደሚያስፈልግ 38.6.2.4 ተመልከቱ)።

የኃጢያት አይነት

ወሲባዊ የስነምግባር ጉድለት

የአባልነት ምክር ቤት የግድ ያስፈልጋል (32.6.1ን ተመልከቱ)።

  • በቅርብ ቤተሰብ አባላት መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት

  • የልጆች የብልግና ምስሎች

  • ከአንድ በላይ ጋብቻ

  • ፆታዊ በደል የማድረስ ባሕርይ።

የአባልነት ምክር ቤት ምናልባት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል(32.6.2 ተመልከቱ)።

  • ምንዝር፣ ዝሙት፣ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነቶች እና በይነመረብ አማካኝነት ወይም በስልክ የሚደረጉ ወሲባዊ ግንኙነቶችን ጨምሮ ከህጋዊ ጋብቻ ውጪ በወንድና በሴት መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነቶች

  • ሳይጋቡ አብሮ መኖር፣ በማንኛውም ጊዜ በስምምነት ሊፈርስ የሚችል ህግ እውቅና ያልሰጠው ጥምረት፣ እና የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ

  • በአባሉ ትዳር ወይም ቤተሰብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ የብልግና ምስሎችን በከፍተኛ ደረጃ ወይም በአስገዳጅ መጠቀም

የኃጢያት አይነት

የማጭበርበር ድርጊቶች

የአባልነት ምክር ቤት የግድ ያስፈልጋል (32.6.1ን ተመልከቱ)።

  • ማጭበርበር እና ተመሳሳይ ተግባራት አይነት ሌላን ለመጉዳት ሆን ብሎ የሚደረግ የገንዘብ አጭበርባሪነት ባሕርያት (አባል የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ ወይም ንብረት በመመዝበር ላይ ተሳትፎ የነበረ ከሆነ 32.6.3.3 ተመልከቱ)።

የአባልነት ምክር ቤት ምናልባት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል(32.6.2 ተመልከቱ)።

  • ዝርፊያ፣ በተለይ ስርቆት ለመፈጸም የሰው ቤት መግባት፣ ወይም ምዝበራ (አባል የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ ወይም ንብረት በመመዝበር ላይ ተሳትፎ የነበረ ከሆነ 32.6.3.3 ተመልከቱ)።

  • የሀሰት ምስክርነት

የኃጢያት አይነት

እምነትን ማጉደል

የአባልነት ምክር ቤት የግድ ያስፈልጋል (32.6.1ን ተመልከቱ)።

  • በታወቀ የቤተክርስቲያን የሃላፊነት ቦታ ላይ በመሆን ከባድ ኃጢያት መስራት

የአባልነት ምክር ቤት ምናልባት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል(32.6.2 ተመልከቱ)።

  • በታወቀ የቤተክርስቲያን ወይም የህብረተሰብ የሃላፊነት ቦታ ወይም ባለአደራ በመሆን ከባድ ኃጢያት ከሰራ (አባል የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ ወይም ንብረት በመመዝበር ላይ ተሳትፎ የነበረ ከሆነ 32.6.3.3 ተመልከቱ)።

  • በሰፊው የታወቀ ከባድ ኃጢያት

የኃጢያት አይነት

አንዳንድ ሌሎች ተግባራት

የአባልነት ምክር ቤት የግድ ያስፈልጋል (32.6.1ን ተመልከቱ)።

  • አብዛኛዎቹ እጅግ ከባድ የሆኑ ወንጀል ጥፋተኝነቶች

የአባልነት ምክር ቤት ምናልባት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል(32.6.2 ተመልከቱ)።

  • ፅንስ ማስወረድ (በ38.6.1 ውስጥ የተቀመጠው የተለየ ሁኔታ ከሌለ በስተቀር)

  • ከባድ ኃጢያቶችን የመሥራት ልማድ

  • የልጅ ማሳደጊያ ድጋፍ መስጠትን እና ለትዳር አጋር እንዲሰጥ በፍርድ ቤት የተወሰነን ቀለብ አለመክፈልን ጨምሮ ሆን ብሎ የቤተሰብ ኃላፊነቶችን የተወ ከሆነ

  • ህገወጥ መድሃኒቶችን መሸጥ

  • ሌሎች ከባድ የሆኑ የወንጀል ድርጊቶችን መፈጸም

32.6.3

የካስማ ፕሬዚዳንቱ የአባልነት ምክር ቤት ወይም ሌላ እርምጃ የሚያስፈልግ ስለመሆኑ ከአካባቢ አመራር ጋር የሚማከሩበት ጊዜ

አንዳንድ ጉዳዮች ተጨማሪ ጥንቃቄ እና መመሪያ ያስፈልጋቸዋል። እንዴት በተሻለ ሁኔታ መርዳት እንደሚቻል ለማወቅ የካስማ ፕሬዚዳንቱ በዚህ ክፍል ውስጥ ስላሉት ሁኔታዎች ከአካባቢ አመራር ጋር መማከር ይኖርበታል። ሆኖም ምግባሩን ለመመልከት የአባልነት ምክር ቤት መካሄድ እንዳለበት የሚወስነው የካስማ ፕሬዚዳንቱ ብቻ ነው። ምክር ቤቱ ከተካሄደ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ ወይም ኤጲስ ቆጶሱ ውጤቱን ይወስናል።

በዚህ ክፍል ውስጥ ከተዘረዘሩት ጉዳዮች ለአንዱ የአባልነት ምክር ቤት ከተካሄደ፣ የምክር ቤቱ ውሳኔ “በጥሩ አቋም ላይ የሚገኝ፣” “መደበኛ የአባልነት ገደቦች፣” ወይም “ከአባልነት ማስገድ” መሆን ይኖርበታል። መደበኛ ገደቦችን ለማንሳት ወይም ሰውን እንደገና ወደ ቤተክርስቲያን ለመቀበል የቀዳሚ አመራር ፈቃድ ያስፈልጋል (32.16.1፣ ቁጥር 9 ተመልከቱ)።

32.6.3.1

ሌሎች ተግባራት

የአባልነት ምክር ቤት ካልተካሄደ፣ የሚወሰዱ ሌሎች ተግባራት የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • መደበኛ ያልሆነ የአባልነት ገደቦች (32.8.3 ተመልከቱ)።

  • የአባልነት መዝገብ ላይ ማስታወሻ መጻፍ (32.14.5 ተመልከቱ)።

  • አንድ ግለሠብ ክህነትን እንዳይቀበል ወይም ጥቅም ላይ እንዳያውል ወይም የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ እንዳይቀበል ወይም እንዳይጠቀም የሚገድቡ የሥርዓት ገደቦች።

ከእነዚህ እርምጃዎች አንዱ ከመወሰዱ በፊት የካስማ ፕሬዚዳንት ከአካባቢ አመራር ጋር ይማከራል።

32.6.3.2

ክህደት

የክህደት ጉዳዮች ብዙውን ጊዜ ከአጥቢያው ወይም ከካስማው ወሰን ውጪ ተፅእኖ አላቸው። የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል በአፋጣኝ መፍትሄ ማግኘት አለባቸው።

የአንድ አባል ድርጊት ክህደትን ሊያመለክት እንደሚችል ከተሰማው ኤጲስ ቆጶሱ ከካስማ ፕሬዚዳንቱ ጋር ይማከራል። ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ በአባሉ ላይ መደበኛ ያልሆነ የአባልነት ገደቦች ሊጥል ይችላል (32.8.3 ተመልከቱ)። የካስማ ፕሬዚዳንቱ በአፋጣኝ ከአካባቢ አመራር ጋር ይማከራል። ሆኖም የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ ወይም ሌላ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት የሚወስነው የካስማ ፕሬዚዳንቱ ብቻ ነው።

እዚህ ላይ ባለው አጠቃቀም፣ ክህደት ከሚከተሉት ውስጥ በአንዱ ውስጥ የሚሳተፍ አባልን ያመለክታል፦

  • በተደጋጋሚ ቤተክርስቲያኗን፣ ትምህርቶቿን፣ ፖሊሲዎቿን ወይም መሪዎቿን በግልፅ እንዲሁም ሆን ብሎ በገሃድ መቃወም

  • በኤጲስ ቆጶሱ ወይም በካስማ ፕሬዚዳንቱ እርማት ከተሰጠው በኋላ የቤተክርስቲያኗ ትምህርት ያልሆነውን እንደ ቤተክርስቲያኗ ትምህርት በማስተማር መቀጠል

  • ሆን ብሎ የቤተክርስቲያኗን አባላት እምነት እና እንቅስቃሴ የማዳከም ስራ ልምድን ማሳየት

  • በኤጲስ ቆጶሱ ወይም በካስማ ፕሬዚዳንቱ እርምት ከተሰጠው በኋላ የክህደት ኑፋቄ ትምህርቶችን መከተልን መቀጠል

  • በመደበኛነት የሌላ ቤተክርስቲያን አባል መሆን እና አስተምህሮቶቹን መደገፍ (በቤተክርስቲያኗ ሙሉ ለሙሉ ተሳትፎ አለማድረግ ወይም ወደ ሌላ ቤተክርስቲያን መሄድ በራሱ ክህደትን አያመለክትም። ሆኖም፣ አንድ አባል በመደበኛነት የሌላ ቤተክርስቲያን አባል ከሆነ/ነች እና አስተምህሮቶቹን የሚደግፍ/የምትደግፍ ከሆነ/ከሆነች፣ ከአባልነቱ/ቷ ማስወገድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።)

አዳኙ፣ ኔፋውያን ኃጢያት የሠራን ሰው ማገልገላቸውን እንዲቀጥሉ አስተምሯቸዋል። “ነገር ግን ንሰሃ ካልገባ፣ ህዝቦቼን እንዳያጠፋ፣ ከህዝቦቼ መካከል አይቆጠርም” (3 ኔፊ 18፥31)።

32.6.3.3

የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ መመዝበር

አንድ አባል የቤተክርስቲያኗን ገንዘብ ከመዘበረ ወይም የቤተክርስቲያኗን ውድ ንብረት ከሰረቀ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ የአባልነት ምክር ቤት እንዲካሄድ ወይም ሌላ እርምጃ የሚያስፈልግ ስለመሆኑ ከአካባቢ አመራር ጋር ይማከራል። መሪዎች የሚከተሉትን ግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፦

  • የተመዘበረውን ወይም የተሰረቀውን ገንዘብ ብዛት።

  • ምዝበራው የተካሄደው ለአንድ ጊዜ ብቻ ነው ወይንስ በተደጋጋሚ።

  • መልሶ የተከፈለ ስለመሆኑ።

  • የግለሠቡ የጸጸት ደረጃ።

  • አባሉ የያዘው የሃላፊነት ቦታ (የታወቀ የቤተክርስቲያን የሃላፊነት ቦታ የያዙ አባላትን በሚመለከት 32.6.1.4 ተመልከቱ)።

የካስማ ፕሬዚዳንቱ ከሚከተሉት አንዱን በLeader and Clerk Resources ውስጥ ሀተታ ያደርጋል፦

  • የአባልነት ምክር ቤት ውጤቶች

  • ከአካባቢ አመራር ጋር እንደመከረ እና የአባልነትምክር ቤት ወይም ሌላ እርምጃ የሚያስፈልግ ስለመሆኑ እንደወሰነ

የቤተክርስቲያኗ የገንዘብ ተቆጣጣሪ ክፍል፣ አንድ መሪ ወይም የቤተክርስቲያኗ ሰራተኛ የቤተክርስቲያንን ገንዘብ ወይም ንብረት መመዝበሩን ካረጋገጠ፣ ቀዳሚ አመራሩ በአባልነት መዝገብ ላይ ማስታወሻ እንዲጻፍ አጠቃላይ መመሪያ ይሰጣል። “መሪ“ ማለት በቤተክርስቲያኗ የታወቀ ሀላፊነት የያዘ ሰው፣ እንዲሁም አማካሪዎች፣ ጸሃፊዎች እና የቅርንጫፍ አመራር ማለት ነው። ንስሃው ሲጠናቀቅ፣ የካስማ ፕሬዚዳንት የተመዘገበውን ማስታወሻ እንዲወገድ ሊጠይቅ ይችላል (32.14.5 እና 34.7.5 ተመልከቱ)። ማስታወሻ ማለት የአባልነት ምክር ቤት ተካሂዷል ወይም ሌላ እርምጃ ተወስዷል ማለት አይደለም።

32.6.3.4

በውልደት ጊዜ ካገኙት ጾታ በተቃራኒ የሚገለጹ ግለሰቦች

ራሳቸውን በውልደት ጊዜ ካገኙት ጾታ በተቃራኒ ከሚገልጹ ግለሰቦች ጋር የሚሰሩ ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች በ38.6.23 ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች መከተል አለባቸው።

32.6.4

የአባልነት ምክር ቤት በተለምዶ አስፈላጊ የማይሆንበት ጊዜ

በሚከተሉት ሁኔታዎች የአባልነት ምክር ቤት በተለምዶ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል።

32.6.4.1

አንዳንድ የቤተክርስቲያን መስፈርቶችን ማሟላት አለመቻል

ከዚህ ቀጥሎ ለተዘረዘሩት ተግባራት የአባልነት ምክር ቤት አይካሄድም። ይሁን እንጂ፣ የመጨረሻው ንጥል ላይ ያለውን ልዩነት አስተውሉ።

  • በቤተክርስቲያን ውስጥ ንቁ ተሳታፊ አለመሆን

  • የቤተክርስቲያን ሃላፊነቶችን አለማሟላት

  • አስራትን አለመክፈል

  • ማድረግ የሚገባን ነገር ባለማድረግ የሚደረግ ኃጢያት

  • የግል ወሲባዊ ስሜትን ማርካት

  • የጥበብ ቃልን አለማክበር

  • የብልግና ምስሎችን መጠቀም፣ የልጆች የብልግና ምስሎችን ሳይጨምር (በ38.6.6 ውስጥ እንደተዘረዘረው) ወይም በአባሉ ትዳር ወይም ቤተሰብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ የብልግና ምስሎችን በከፍተኛ ደረጃ ወይም በአስገዳጅነት መጠቀም (በ38.6.13 ውስጥ እንደተዘረዘረው)።

32.6.4.2

የንግድ ኪሳራ ውስጥ መውደቅ ወይም እዳን አለመክፈል

መሪዎች የንግድ ክርክሮችን ለመፍታት የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ የለባቸውም። የንግድ ኪሳራ ውስጥ መውደቅ ወይም እዳን አለመክፈል የአባልነት ሸንጎን ለማካሄድ ምክንያት አይደለም። ሆኖም፣ ለከባድ የማጭበርበር ድርጊቶች ወይም ለሌሎች ከባድ የገንዘብ ማታለል ተግባራት የአባልነት ምክር ቤት መካሄድ አለበት (32.6.1.3 ተመልከቱ)።

32.6.4.3

የፍትሐ ብሄር ክርክሮች

የፍትሐ ብሄር ክርክሮችን ለመፍታት የአባልነት ምክር ቤት አይካሄድም (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 134፥11 ተመልከቱ)።

32.7

የግለሰብ ሁኔታዎች

ጌታ “የምህረት ክንዴ ወደ እናንተ ተዘርግታለች፣ እናም ማንም ቢመጣ እቀበለዋለሁ፣ እናም ወደ እኔ የሚመጡ የተባረኩ ናቸው” ብሏል (3 ኔፊ 9፥14)። የሚከተሉትን ለመወሰን የግለሠቡን ሁኔታዎች ግምት ውስጥ መግባት አስፈላጊ ነው፦

  • እሱ ወይም እሷ ከከባድ ኃጢያቶች ንስሐ እንዲገባ/እንድትገባ የሚረዳ ትክክለኛው ሁኔታ (32.5 እና 32.6 ተመልከቱ)።

  • በግል ምክር ወይም በአባልነት ምክር ቤት ላይ የተሰጠ ውሳኔ (32.8 እና 32.11 ተመልከቱ)።

ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች ለእያንዳንዱ ሁኔታ የጌታን ሀሳብ እና ፈቃድ ይሻሉ። የትኛውን ሁኔታ መጠቀም እንዳለባቸው እና ውጤቱ ምን መሆን እንደሚገባው ለመወሰን የሚከተሉትን ነጥቦች ግምት ውስጥ ያስገባሉ። እነዚህ ነጥቦች ወደተወሰነ ውሳኔ አይመሩም። ከዚያ ይልቅ፣ መሪዎች በጸሎት እና በመንፈስ ተመርተው ሊወስኑ ለሚገባቸው ውሳኔ አጋዥ ናቸው።

32.7.1

የኃጢያቱ መጠን

የኃጢያት ከባድነት በኃጢያቱ መጠን ይለካል። ይህ ምናልባት የተፈጸሙ የኃጢያቶችን ብዛት እና ድግግሞሽ፣ ያደረሱትን ጉዳት ክብደት እንዲሁም በእነሱ ምክንያት የተጎዱትን ሰዎች ቁጥር ሊያካትት ይችላል።

32.7.2

የተጠቂው ፍላጎቶች

መሪዎች የተጠቂዎችን እና የሌሎችን ፍላጎቶች ግምት ውስጥ ያስገባሉ። ይህ የሰውየውን/የሴትዮዋን የትዳር ጓደኛ እና ሌሎች የቤተሰብ አባላት ሊያካትት ይችላል። መሪዎች የጉዳቱን ክብደት ግምት ውስጥ ያሰገባሉ።

32.7.3

ንስሃ የመግባት ማስረጃዎች

ሰው ከልቡ ንስሐ እንደገባ ለማወቅ መንፈሳዊ ምሪት ያስፈልጋል። እንዲህ ያለው ንስሐ በአንድ ቃለ መጠይቅ ወቅት ከሚገለጽ ጥልቅ ሀዘን ይልቅ በጊዜ ሂደት በሚደረጉ የጽድቅ ተግባራት የበለጠ አስተማማኝ በሆነ ሁኔታ ይታያል። ግምት ውስጥ ሊገቡ የሚገባቸው ነጥቦች የሚከተሉትን ያካትታል፦

  • በኢየሱስ ክርስቶስ ያለ የእምነትጥንካሬ።

  • የኑዛዜ አይነት።

  • ስለኃጢያቱ የሚሰማ የሃዘን ጥልቀት።

  • ለተጎዱ ሰዎች ካሳ መስጠት።

  • የህግ መስፈርቶችን ማሟላት።

  • ኃጢያቱን በመተው ረገድ የተገኘ ስኬት።

  • ከኃጢያቱ በኋላ ትእዛዛትን ለመጠበቅ ያሳየው ታማኝነት።

  • ለቤተክርስቲያን መሪዎች እና ለሌሎች የሚያሳየው ታማኝነት።

  • የቤተክርስቲያን መሪዎችን ምክር ለመከተል የሚያሳየው ፈቃደኝነት።

ምስል
ሴት እየጸለየች

32.7.4

የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን መጣስ

ጌታ “ብዙ ለተሰጠው ከእርሱ ብዙ ይጠበቅበታል“ በማለት አውጇል (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 82፥3)። የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበለ ሰው ከፍ ባለ መስፈርት ለመኖር ቃል ኪዳኖችን ገብቷል። እነዚህን ቃል ኪዳኖች ማፍረስ የኃጢያቱን ክብደት ያጎላዋል። የአባልነት ምክር ቤትን አስፈላጊ የመሆን እድል ይጨምራል።

32.7.5

የባለአደራነት ወይም የሥልጣን ደረጃ

አንድ ግለሠብ እንደ ወላጅ፣ መሪ፣ ወይም አስተማሪ በመሰለ በታወቀ የቤተክርስቲያን ወይም የህብረተሰብ የሃላፊነት ቦታ ወይም ባለአደራ ሆኖ እያለ ኃጢያት ከፈጸመ፣ የፈጸመውን የኃጢያቱን ክብደት ያጎላዋል።

32.7.6

ድግግሞሽ

ያንኑ ከባድ ኃጢያት የመድገም ልምድ ወደ እውነተኛ ንስሐ መግባትን የሚገታ ሥር የሰደደ ባሕርይ ወይም ሱስ መኖሩን ሊያሳይ ይችላል። አስፈላጊ ሊሆኑ ከሚችሉት የአባልነት ገደቦች በተጨማሪ፣ ከሱስ ማገገሚያ ፕሮግራሞች እና ምክር ከሚሰጡ ባለሙያዎች ጋር መነጋገር ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ (32.8.2 ተመልከቱ)።

32.7.7

እድሜ፣ ብስለት እና ልምድ

መሪዎች ለአባል ምክር ሲሰጡ ወይም የአባልነት ምክር ቤት ውጤትን ሲወስኑ እድሜን፣ ብስለትን እና ልምድን ግምት ውስጥ ያስገባሉ። ብዙውን ጊዜ፣ በወንጌል ላልበሰሉ ሰዎች ይቅርባይነት ተገቢ ነው። ለምሳሌ፣ ኃጢያትን በመተው እውነተኛ ንስሐ ከገቡ፣ የሥነ ምግባር ብልግና የፈጸሙ ወጣት አባላትን ይቅር ማለት ተገቢ ሊሆን ይችላል። ሆኖም በባህሪው ከቀጠሉ የበለጠ ከባድ እርምጃ ሊያስፈልግ ይችላል።

32.7.8

የአዕምሮ ችሎታ

የአእምሮ ህመም፣ ሱስ ወይም የአዕምሮ ችሎታ ከባድ ኃጢያት ለሠራ ሰው ሰበብ አይሆኑም። ሆኖም እነዚህ ከግምት ውስጥ የሚገቡ ነገሮች ናቸው። አንድን ሰው ንስሃ እንዲገባ በሚረዱበት ጊዜ፣ መሪዎች ግለሰቡ ስለወንጌል መርሆዎች ያለውን ግንዛቤ እና የተጠያቂነት ደረጃ በተመለከተ የጌታን መመሪያ ይሻሉ።

32.7.9

በራስ ተነሳሽነት መናዘዝ

አንድ ግለሰብ ላደረገው ድርጊት በራስ ተነሳሽነት መናዘዙ እና አምላካዊ ሀዘን መሰማቱ የንስሃ ፍላጎትን ያሳያል።

32.7.10

በኃጢያት እና በመናዘዝ መካከል ያለው ጊዜ

መናዘዝ የንስሐ አካል ስለሆነ መዘግየት የለበትም። አንዳንድ ጊዜ ከኃጢያት በኋላ ረጅም የመካስ ጊዜ እና በታማኝነት መኖር ይከተላል። አንድ አባል ሀጢያትን ከተናዘዘና ካልደገመ፣ እሱ ወይም እሷ እንደተውት ያሳያል። በዚያ ሁኔታ፣ መናዘዝ የንስሐ ሂደቱን ከመጀመር ይልቅ ሊያጠናቅቅ ይችላል።

32.7.11

በተለያዩ አጥቢያዎች ወይም ካስማዎች የሚኖሩ አባላትን የሚያካትቱ ኃጢያቶች

አንዳንድ ጊዜ በተለያዩ አጥቢያዎች ወይም ካስማዎች የሚኖሩ አባላት ከባድ ኃጢያትን በህብረት ይሰሩ ይሆናል። በዚህ ሁኔታ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቶቹ የአባልነት ገደቦችን ስለማስቀመጥ ወይም ስለአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊነት በጋራ ይማከራሉ። እንዲሁም ገደቦች ወይም የምክር ቤት ውሳኔዎች ተገቢነት ካላቸው ወይም የተለዩ ውጤቶችን እንደሚፈልጉ የሚጠቁሙ ሌሎች ጉዳዮች ካሉም ይወያያሉ።


የግል ምክር መስጠት


32.8

የግል ምክር እና መደበኛ ያልሆኑ የአባልነት ገደቦች

አብዛኛውን ጊዜ የግል ምክር የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ ለመርዳት በቂ ነው፣ እንዲሁም አንድ ግለሠብ በንስሃ አማካኝነት የኢየሱስ ክርስቶስን የማዳን ሃይል አንዲያገኝ ይረዳል። እንዲህ ያለው ምክር አባላትን ከባሰ ከባድ ኃጢያት ለመጠበቅ ሊረዳም ይችላል። በግል ምክር ጊዜ፣ አንድ አባል ለአንዳንድ ከባድ ኃጢያቶች ንስሃ እንዲገባ ለመርዳት መሪዎች መደበኛ ያልሆነ የአባልነት ገደቦችን ሊጥሉም ይችላሉ (32.8.3 ተመልከቱ)።

ከባድ ኃጢያቶች በቀላሉ መታየት የለባቸውም (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥31 ተመልከቱ)። የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን ማፍረስ የአባልነት ምክር ቤትን አስፈላጊ የመሆን እድል ይጨምራል (32.7.4 ተመልከቱ)።

መሪዎች ምክር እና መደበኛ ያልሆኑ ገደቦች መቼ በቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ ያውቁ ዘንድ የሚረዱ መመሪያዎች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል (በተጨማሪም 32.7 ተመልከቱ)።

  • አንድ ግለሠብ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ የሚፈልግን ኃጢያት ያልሠራ ከሆነ (32.6.1 ተመልከቱ)።

  • አንድ ግለሠብ በፈቃዱ ሲናዘዝ እና እውነተኛ ንስሐ ሲገባ።

  • አንድ ግለሠብ ከዚህ በፊት ሰርቶት ለማያውቀው ከባድ ኃጢያት ንስሐ ሲገባ።

  • የግለሠቡ ኃጢያት የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን ካላፈረሰ።

  • አንድ ግለሠብ ጉልህ የሆነ ክብደቱን ዝቅ የማድረጊያ ሁኔታዎች ካሉት።

32.8.1

የግል ምክር

አንድ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት አንድ አባል ንስሐ እንዲገባ/ድትገባ ሲመከሩ የሚከተሉትን መመሪያዎች ተግባራዊ ያደርጋሉ።

  • (1) አባሉ ስለኃጢያተኛ ባሕርዩ ያለውን አመለካከት እና (2) የባህሪውን ተፈጥሮ፣ ድግግሞሽ እና የባሕርዩ ቆይታ ብዛት ለማወቅ የሚረዳ በቂ መረጃ ብቻ ጠይቁ። ሁኔታውን ለመረዳት ከሚያስፈልገው በላይ ዝርዝር ነገሮችን አትጠይቁ። ከግል የማወቅ ጉጉት የመነጩ የማያስፈልጉ ጥያቄዎችን አትጠይቁ።

  • ባህርዩ በሌሎች ሰዎች ላይ እንዴት ጉዳት እንዳደረሰ ጠይቁ።

  • የአባላቱን ወደ ጌታ መለወጥ እና ቁርጠኝነት ጥልቅ በሚያደርጉ አዎንታዊ ሁኔታዎች ላይ አተኩሩ። አባሉ ንስሃ መግባት ይችል ዘንድ የባሕርይ እና የልብ ለውጥ ለማምጣት የተወሰኑ እርምጃዎችን እንዲወስድ አበረታቱት። እርሱ ወይም እርሷ ወደ አዳኙ እንዲቀርብ/እንድትቀርብ፣ ጥንካሬውን እንዲሻ/ድትሻ፣ እና የማዳን ፍቅሩ እንዲሰማው/ት ጋብዙት/ዟት።

  • እንደመጸለይ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን እንደማጥናት እና በቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ላይ እንደመገኘት የመሳሰሉ የሚያንጹ እንቅስቃሴዎችን አበረታቱ። የቤተሰብ ታሪክ እና የቤተመቅደስ ስራ የጠላትን ተፅእኖ ሊቀንሱ እንደሚችሉ አስተምሩ። ሌሎችን ማገልገልን እና ወንጌልን ማካፈልን አበረታቱ።

  • በኃጢያት ለተጎዱ ሰዎች ካሳ መስጠትን እና ይቅርታ መጠየቅን ማበረታታት

  • ከመጥፎ ተጽዕኖዎች መራቅን ማበረታታት። አባላት የተወሰኑ ፈተናዎችን ለመቋቋም የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ መርዳት።

  • የቤተክርስቲያን መሪ እንጂ በሙያው የሰለጠናችሁ አማካሪ እንዳልሆናችሁ መገንዘብ። ከምትሰጡት ምክር በተጨማሪ፣ አንዳንድ አባላት ከሥነ ባሕርይ የማማከር አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን ይችላሉ። አንዳንዶች በአዕምሮ ህመም ይሰቃያሉ። እንደአስፈላጊነቱ፣ አባላት ብቃት ካላቸው የውስጥ ደዌ እና የአእምሮ ጤና ባለሙያዎች እርዳታ እንዲያገኙ ምክር ስጡ (31.3.6ን ተመልከቱ)።

  • መደበኛ ያልሆኑ የአባልነት ገደቦችን ከመጣላችሁ በፊት በጸሎት መንፈስ ሆናችሁ ከመንፈስ መመሪያ ፈልጉ። አንዳንድ አባላት የቤተክርስቲያኗ አባልነት መብቶቻቸው ከሚገደቡ ይልቅ የበለጠ በብቃት ቢለማመዷቸው ሊጠቀሙ ይችላሉ።

  • ማበረታቻ ለመስጠት፣ መንፈሳዊ ጥንካሬን ለማጎልበት እና እድገትን ለመቆጣጠር ክትትል አድርጉ።

አባል ለኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት ከተናዘዘ/ች በኋላ የክትትል ምክር በተለያዩ መንገዶች ሊሰጥ ይችላል። መሪው ራሱ ይህን ሊሰጥ ይችላል። ወይም በአባሉ ፈቃድ ከአማካሪዎቹ አንዱ ይህን እንዲሰጥ ሊመድብ ይችላል።

ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት በአባሉ ስምምነት የሽማግሌዎች ቡድን አባላትን ወይም የሴቶች መረዳጃ ማህበር አባላትን በልዩ መንገዶች እንዲረዱ ሊመድብ ይችላል። ወጣቶችን ይረዱ ዘንድ፣ የወጣት ሴቶች ፕሬዚዳንትን ወይም የአሮናዊ ክህነት ቡድን አማካሪዎችን ሊመድብ ይችላል። እንዲረዱ የተመደቡት ያንን የስራ ምድብ ለማከናወን ይችሉ ዘንድ መነሳሳትን የማግኘት መብት አላቸው (4.2.6 ተመልከቱ)።

አንድ ግለሠብ በክትትል ምክር እንዲረዳ ሲመደብ፣ መሪው አባሉን ለመርዳት አስፈላጊ የሆነውን በቂ መረጃ ብቻ ይሰጣል። የተመደበው ሰው ሚስጥራዊነትን መጠበቀ አለበት። እሱ ወይም እሷ የአባሉን እድገት እና ፍላጎቶች ለኤጲስ ቆጶሱ ያሳውቃል/ታሳውቃለች።

ምስል
አንዲት ሴት እየጸለየች

32.8.2

በሱስ የተጠመዱ ሰዎችን መርዳት

አንዳንድ ጊዜ ፣የግል ምክር አባላት ከሱሶች ጋር ለተያያዙ ወይም በሱሶች ምክንያት ለሚከሰቱ ኃጢያቶች ንስሃ እንዲገቡ መርዳትን ያካትታል። እነዚህ ሱሶች፣ ንጥረ ነገሮችን ወይም ብዛት ያላቸውን ባሕርያት ሊያካትቱ ይችላሉ። ሱሶች ግለሰቦችን፣ ትዳርን እና ቤተሰብን ይጎዳሉ። ኤጲስ ቆጶሳት፣ አባላት ከቤተክርስቲያኗ የሱስ ማገገሚያ ፕሮግራም እና ብቃት ካላቸው የውስጥ ደዌ እና የአዕምሮ ህክምና ባለሙያዎች እርዳታን እንዲያገኙ ምክር ሊሰጡ ይችላሉ።

የብልግና ምስሎችን መመልከት ተባብሶ የተለመደ ሆኗል። ከፍተኛ አጠቃቀም፣ አስገዳጅ ወይም በጣም አልፎ አልፎ ሱስ ሊሆን ይችላል። የብልግና ምስሎችን በከፍተኛ ደረጃም ሆነ አልፎ አልፎ መጠቀም ጎጂ ነው። መንፈስን ያሸሻል። ቃል ኪዳኖችን በመጠበቅ የሚገኘውን ኃይል የመቀበል ችሎታን ያዳክማል። ውድ የሆኑ ግንኙነቶችንም ይጎዳል።

የግል ምክር እና መደበኛ ያልሆኑ የአባልነት ገደቦች የብልግና ምስሎችን የሚመለከትን ግለሠብ ንስሃ እንዲገባ ለመርዳት በተለምዶ በቂ ነው። በተለምዶ የአባልነት ምክር ቤት አይካሄድም። ለተለዩ ሁኔታዎች 38.6.6 እና 38.6.13 ተመልከቱ። ሙያዊ ምክር ሊረዳ ይችላል።

የካስማ ፕሬዚዳንቶች እና ኤጲስ ቆጶሳት እንዳስፈላጊነቱ የቤተሰብ አባላትን ይረዳሉ። ወጣቶች የብልግና ምስሎችን ስለመመልከት ምክር በሚሰጣቸው ጊዜ ወላጆችም ሊካተቱ ይችላሉ። ላገባ ሰው ምክር በሚሰጥበት ጊዜ የትዳር ጓደኛን ማካተት ይቻላል።

የብልግና ምስሎችን ለሚመለከቱ አባላት ምክር ስለመስጠት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት 38.6.13 ተመልከቱ።

32.8.3

መደበኛ ያልሆኑ የአባልነት ገደቦች

ምክር በሚሰጥበት ጊዜ አዎንታዊ ድርጊቶችን ከማበረታታት በተጨማሪ አንድ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት መደበኛ ባልሆነ መንገድ ለተወሰነ ጊዜ በቤተክርስቲያን አባልነት አንዳንድ መብቶች ላይ ገደብ ሊጥል ይችላል። በጥበብ ከተጠቀሙባቸው፣ እነዚህ ገደቦች ንስሐ ለመግባት እና መንፈሳዊ እድገት ለማድረግ ሊረዱ ይችላሉ። መደበኛ ያልሆኑ የሚባሉበት ምክንያት በአባልነትመዝገብ ላይ ማስታወሻ ስለማይጻፍ ነው።

መደበኛ ያልሆኑ ገደቦች ለጥቂት ሳምንታት፣ ለብዙ ወራት ወይም ግለሠቡ ሙሉ በሙሉ ንስሃ ይገባ ዘንድ አስፈላጊ ከሆነ ከዚያ በላይ ሊቆዩ ይችላሉ። ባልተለመዱ ሁኔታዎችም፣ ጊዜው ከአንድ አመት በላይ ሊሆን ይችላል።

መሪዎች፣ ሰው ንስሃ እንዲገባ የበለጠ የሚረዱት የትኞቹ ገደቦች እንደሆኑ ለማወቅ የመንፈስን መመሪያ ይሻሉ። እነዚህ በቤተክርስቲያን ጥሪ ውስጥ ማገልገልን፣ የክህነት ስልጣንን መለማመድን፣ ወይም ቤተመቅደስ የመግባት እድልን (ነገር ግን በዚህ ብቻ አይገደብም) ሊያካትቱ ይችላሉ። በተጨማሪም መሪው፣ አባሉ በቤተክርስቲያን ውስጥ ንግግር እንዳያቀርብ፣ ትምህርት እንዳይሰጥ ወይም እንዳይጸልይ ገደብ ሊጥልም ይችላል። መሪው ቤተመቅደስ የመግባት መብቱን ካገደው፣ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃዱን በLeader and Clerk Resources (LCR) ውስጥ ይሰርዘዋል።

ቅዱስ ቁርባንን መካፈል አስፈላጊ የንስሃ ክፍል ነው። የተሰበረ ልብ እና የተዋረደ መንፈስ ላለው ግለሠብ የመጀመሪያው ገደብ መሆን የለበትም። ሆኖም፣ አንድ ግለሠብ ከባድ ኃጢያት ሰርቶ ከሆነ፣ መሪው ይህንን መብት ለተወሰነ ጊዜ ሊያግደው ይችላል።

ማሳወቅ አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር፣ በተለምዶ መሪዎች መደበኛ ስላልሆኑ ገደቦች ለማንም አይነግሩም (32.12.2ን ተመልከቱ)።

ግለሰቡ በእውነተኛ ንስሃ የተወሰነ እድገት በሚያደርግበት ጊዜ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ መንፈስ በሚመራው መሰረት መደበኛ ያልሆኑ ገደቦችን ሊያነሳ ይችላል። አባሉ በኃጢያት ልምዱ ከቀጠለ የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ ጠቃሚ ወይም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።


የቤተክርስቲያን አባልነት ምክር ቤትን ማካሄድ


የቤተክርስቲያን የአባልነት ምክር ቤቶች፣ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ ሲወስኑ ወይም የቤተክርስቲያኗ ፖሊሲ አስፈላጊ ሲያደርጋቸው ይካሄዳሉ (32.6 ተመልከቱ)። በአጥቢያ፣ በካስማ፣ በቅርንጫፍ፣ በአውራጃ ወይም በሚስዮን ደረጃ ይካሄዳሉ። ይህ ክፍል እንዴት እንደሚካሄዱ መረጃ ይሰጣል።

32.9

ተሳትፎ እና ሀላፊነት

የሚከተለው ሰንጠረዥ በአባልነት ምክር ቤት በተለምዶ ማን እንደሚሳተፍ ያሳያል።

የአባልነት ምክር ቤት ተሳታፊዎች

የአጥቢያ የአባልነት ምክር ቤት

የአባልነት ምክር ቤት ተሳታፊዎች

  • የአባልነት ምክር ቤት የሚካሄድለት ግለሠብ

  • ኤጲስ ቆጶሱ እና አማካሪዎቹ

  • የአጥቢያ ጸሃፊ

  • የሽማግሌዎች ቡድን ወይም የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንት (አማራጭ፤ 32.10.1 ተመልከቱ)

የካስማ የአባልነት ምክር ቤት

የአባልነት ምክር ቤት ተሳታፊዎች

  • የአባልነት ምክር ቤት የሚካሄድለት ግለሠብ

  • የካስማ ፕሬዚዳንት እና አማካሪዎቹ

  • የካስማ ጸሃፊ

  • ከፍተኛ አማካሪዎች ( በ32.9.2 ውስጥ እንደተብራራው)

  • የአባልነት ምክር ቤት የሚካሄድለት ግለሠብ ኤጲስ ቆጶስ (አማራጭ፤ 32.9.3 ተመልከቱ)

  • የሽማግሌዎች ቡድን ወይም የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንት (አማራጭ፤ 32.10.1 ተመልከቱ)

32.9.1

የካስማ ፕሬዚዳንት

የካስማ ፕሬዚዳንቱ፦

  • በካስማው ውስጥ ለሚደረጉ የአባልነት ምክር ቤት ስልጣን አለው፤ ሆኖም፣ አብዛኞቹ የአባልነት ምክር ቤቶች በኤጲስ ቆጶሳቱ ይካሄዳሉ።

  • አንድ ኤጲስ ቆጶስ የአባልነት ምክር ቤት ከማካሄዱ በፊት ፈቃድ መስጠት አለበት።

  • የቤተመቅደስ ቡራኬን የተቀበለ/ች ወንድ ወይም ሴት ከቤተክርስቲያን አባልነት የሚወገድ/የምትወገድ ከሆነ/ከሆነች የካስማ አባልነት ምክር ቤት ያካሂዳል።

  • አንድ አባል በአጥቢያ የአባልነት ምክር ቤት ውሳኔ ላይ ቅሬታ ካቀረበ ምክር ቤት ሊያካሂድ ይችላል።

  • የአጥቢያ የአባልነት ምክር ቤት የቤተመቅደስ ቡራኬ ያልተቀበለን ሰው ከአባልነት ለማስወገድ የሚያቀርበው ሃሳብ የመጨረሻ ከመሆኑ በፊት ፈቃድ መስጠት አለበት።

32.9.2

ከፍተኛ ምክር ቤት

የከፍተኛ ምክር ቤቱ አባላት በተለምዶ በካስማ የአባልነት ምክር ቤት አይሳተፉም። ሆኖም፣ የከፍተኛ ምክር ቤቱ አባላት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲገጥሙ ሊሳተፉ ይችላሉ (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 102፥2 ተመልከቱ)። ለምሳሌ፣ በሚከተሉት ሁኔታዎች የካስማ አመራሩ የከፍተኛ ምክር ቤቱን አባላት እንዲሳተፉ ሊጋብዝ ይችላል፦

  • የሚያከራከሩ እውነታዎች ሲኖሩ።

  • እሴትን እና ሚዛናዊነትን የሚጨምሩ ሲሆን።

  • አባሉ የእነርሱን ተሳትፎ ሲጠይቅ።

  • የካስማ አመራር አባል ወይም ቤተሰቡ የተሳተፈበት ሲሆን (32.9.7 ተመልከቱ)።

32.9.3

ኤጲስ ቆጶስ (ወይም በካስማ ውስጥ ያለ የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት)

ኤጵስ ቆጶሱ፦

  • በአጥቢያ የአባልነት ከፍተኛ ምክር ቤቶች ላይ ስልጣን አለው።

  • የአባልነት ምክር ቤት ከማካሄዱ በፊት ከካስማ ፕሬዚዳንቱ ጋር በመነጋገር ፈቃዱን ያገኛል።

  • የቤተመቅደስ ቡራኬን የተቀበለ/ች ወንድ ወይም ሴት ከቤተክርስቲያን አባልነት የሚወገድ/የምትወገድ ከሆነ ምክር ቤት ላያካሂድ ይችላል። በእነዚያ ሁኔታዎች ውስጥ የካስማ የአባልነት ምክር ቤት መደረግ ይኖርበታል።

  • አባልነቱ እየተገመገመ ባለ የአጥቢያ አባል በካስማ የአባልነት ምክር ቤት ላይ እንዲሳተፍ ሊጋበዝ ይችላል። ለመሳተፍ ከካስማ ፕሬዚዳንቱ እና ከግለሰቡ ፈቃድ ማግኘት አለበት።

የአጥቢያ ወይም የቅርንጫፍ የአባልነት ምክር ቤት፣ አንድ ግለሰብ የቤተመቅደስ ቡራኬ ያልተቀበለ/ች ከሆነ/ከሆነች ከቤተክርስቲያን አባልነት እንዲወገድ/እንድትወገድ ሃሳብ ሊያቀርብ ይችላል። ሆኖም ውሳኔው የመጨረሻ ከመሆኑ በፊት የካስማ ፕሬዚዳንቱ ፈቃድ ያስፈልጋል።

አንዳንድ ጊዜ የቤተመቅደስ ቡራኬን ለተቀበለ አባል የአጥቢያ የአባልነት ምክር ቤት ሊደረግ እና ሂደቶቹም አባሉ/ሏ ከቤተክርስቲያኗ አባልነት እንደሚወገድ/እንደምትወገድ ሊያሳይ ይችላል። በእነዚህ ሁኔታዎች ኤጲስ ቆጶሱ ጉዳዩን ወደካስማ ፕሬዚዳንቱ ይልከዋል።

32.9.4

የሚስዮን ፕሬዚዳንት

የሚስዮን ፕሬዚዳንቱ፦

  • በሚስዮን ቅርንጫፎች እና አውራጃዎች በሚደረጉ የአባልነት ምክር ቤት ላይ ስልጣን አለው።

  • አንድ የአውራጃ ወይም የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት የአባልነት ምክር ቤት ከማካሄዱ በፊት ፈቃድ መስጠት አለበት።

  • የቤተመቅደስ ቡራኬን የተቀበለ/ች ወንድ ወይም ሴት ከቤተክርስቲያን አባልነቱ/ቷ የሚወገድ/ምትወገድ ከሆነ የአባልነት ምክር ቤት ያካሄዳል። ጊዜ እና ርቀት ይህንን የማይፈቅድ ከሆነ ከአማካሪዎቹ አንዱ በበላይነት እንዲቆጣጠር ሊመድብ ይችላል። ሁለት ሌሎች የመልከ ጼዴቅ ክህነት ስልጣን ተሸካሚዎች እንዲሳተፉ ሊመድብ ይችላል።

  • ከተቻለ፣ የቤተመቅደስ ቡራኬን ላልተቀበሉ የአባልነት ምክር ቤትን ያካሂዳል። ጊዜ እና ርቀት ይህንን የማይፈቅድ ከሆነ ሶስት የመልከ ጼዴቅ ክህነት ስልጣን ተሸካሚዎች እንዲያካሂዱ ፈቃድ ሊሰጥ ይችላል። በዚህ ሁኔታ፣ በተለምዶ የአባሉ የአውራጃ ፕሬዚዳንት ወይም የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት ምክር ቤቱን ይመራል።

  • አንድ አባል በአውራጃ ወይም በቅርንጫፍ የአባልነት ምክር ቤት ውሳኔ ላይ ቅሬታ ካቀረበ ምክር ቤት ሊያካሂድ ይችላል።

  • ከሚስዮን ክፍል አጠቃላይ ባለስልጣን ፈቃድ ሲያገኝ፣ አንድ ሚስዮናዊ በሚያገለግልበት ሚስዮን እያለ ከባድ ኃጢያት ከሰራ የአባልነት ምክር ቤት ያካሂዳል (32.9.8 ተመልከቱ)። ጉዳዩን ከአንድ የአካባቢ አመራር ጋርም ይገመግማል እንዲሁም ሚስዮናዊው ከመጣበት አገር የካስማ ፕሬዚዳንት ጋር ይማከራል።

  • የአውራጃ ወይም የቅርንጫፍ የአባልነት ምክር ቤት የቤተመቅደስ ቡራኬ ያልተቀበለን ሰው ከአባልነት ለማስወገድ የሚያቀርበው ሃሳብ የመጨረሻ ከመሆኑ በፊት ፈቃድ መስጠት አለበት።

ሚስዮናዊ በሚስዮን ከማገልገሉ በፊት የሰራውን ከባድ ኃጢያት ከተናዘዘ፣ የሚስዮን ፕሬዚዳንቱ መመሪያ ለመቀበል በሚስዮናዊ ክፍል ውስጥ ያለውን የእርሱን ወኪል ያነጋግራል።

አንድ የሚስዮን ፕሬዚዳንት የአባልነት ሸንጎ ሲያካሂድ ሁለት የመልከ ጼዲቅ ክህነት ተሸካሚዎች እንዲረዱት ይመድባል። ወጣት ሚስዮናውያን እንዲረዱት መመደብ የሚችለው ባልተለመዱ ሁኔታዎች ውስጥ ብቻ ነው። የካስማ የአባልነት ምክር ቤት የሚከተለውን ተመሳሳይ የስራ ሂደት ይከተላል (32.10 ተመልከቱ)። ሆኖም ከፍተኛ አማካሪ ወይም የአውራጃ አማካሪ አይሳተፍም።

32.9.5

በሚስዮን ውስጥ ያለ የአውራጃ ወይም የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት

በሚስዮን ውስጥ ያለ የአውራጃ ወይም የቅርንጫፍ ፕሬዚዳንት በሚስዮን ፕሬዘደንቱ ሲፈቀድለት የአባልነት ምክር ቤት ሊያካሂድ ይችላል። የአውራጃ አማካሪው አይሳተፍም።

የአውራጃ ወይም የቅርንጫፍ የአባልነት ምክር ቤት፣ አንድ ግለሠብ የቤተመቅደስ ቡራኬ ያልተቀበለ/ች ከሆነ/ች ከቤተክርስቲያን አባልነት እንዲወገድ/ድትወገድ ሃሳብ ሊያቀርብ ይችላል። ሆኖም ውሳኔው የመጨረሻ ከመሆኑ በፊት የሚስዮን ፕሬዚዳንቱ ፈቃድ ያስፈልጋል።

32.9.6

የካስማ ወይም የአጥቢያ ጸሃፊ

የካስማ ወይም የአጥቢያ ጸሃፊው፦

  • የቤተክርስቲያን የአባልነት ምክር ቤት ሪፖርትን ለማቅረብ አስፈላጊ እስከሚሆንበት ጊዜ ድረስ ብቻ የምክር ቤትን የጽሁፍ ማስታወሻ ያስቀምጣል።

  • ምክር ቤቱን ባካሄደው መሪ ከተጠየቀ ቅጹን ያዘጋጃል።

  • በምክር ቤት ውይይት ወይም ውሳኔ አሰጣጥ አይሳተፍም።

32.9.7

ባልተለመዱ ሁኔታዎች ውስጥ መሳተፍ

በካስማ አመራር ውስጥ ያለ አማካሪ በአባልነት ምክር ቤት መሳተፍ የማይችል ከሆነ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ አንድ ከፍተኛ አማካሪ ወይም ሌላ ሊቀ ካህን ቦታውን እንዲይዝ ይጠይቃል። የካስማ ፕሬዚዳንቱ መሳተፍ የማይችል ከሆነ ቀዳሚ አመራር በእርሱ ቦታ ከአማካሪዎቹ አንዱ በበላይነት እንዲቆጣጠር ፈቃድ ሊሰጥ ይችላል።

በኤጲስ ቆጶስ አመራር ውስጥ ያለ አማካሪ በአባልነት ምክር ቤት መሳተፍ የማይችል ከሆነ፣ ኤጲስ ቆጶሱ በአጥቢያው ያለ አንድ ሊቀ ካህን ቦታውን እንዲይዝ ሊጠይቅ ይችላል። ኤጲስ ቆጶሱ መሳተፍ የማይችል ከሆነ ጉዳዩን ወደካስማ ፕሬዚዳንቱ ይወስደዋል፣ እርሱም የካስማ የአባልነት ምክር ቤትን ይሰበስባል። ኤጲስ ቆጶሱ የአባልነት ሸንጎ እንዲሰበስብ አንድን አማካሪ ላይመድብ ይችላል።

የኤጲስ ቆጶሱ ወይም ከአማካሪዎቹ የአንዱ የቤተሰብ አባል ለሆነ የአባልነት ምክር ቤት የሚካሄድ ከሆነ፣ ይህ የሚካሄደው በካስማ ደረጃ ነው። ከካስማ ፕሬዚዳንቱ አማካሪዎች የአንዱ የቤተሰብ አባል ለሆነ የሚካሄድ ከሆነ፣ የካስማ ፕሬዘደንቱ የአማካሪውን ቦታ የሚይዝ ሌላ ሊቀ ካህን ይመድባል። ምክር ቤቱ የሚካሄደው ለካስማ ፕሬዚዳንቱ የቤተሰብ አባል ከሆነ፣ ከቀዳሚ አመራር ቢሮ ጋር ይማከራል።

አንድ አባል የኤጲስ ቆጶሱን ወይም የአማካሪዎቹን ተሳትፎ የሚቃወም ከሆነ፣ የአባልነት ምክር ቤት የሚካሄደው በካስማ ደረጃ ነው። አንድ አባል ከካስማ ፕሬዚዳንቱ አማካሪዎች የአንዱን ተሳትፎ የሚቃወም ከሆነ፣ የካስማ ፕሬዘደንቱ የአማካሪውን ቦታ የሚይዝ ሌላ ሊቀ ካህን ይመድባል። አባሉ የካስማ ፕሬዚዳንቱን ተሳትፎ የሚቃወም ከሆነ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ከወገኝተኝነት ነጻ እንደማይሆን ከተሰማው፣ ከቀዳሚ አመራር ቢሮ ጋር ይማከራል።

32.9.8

በልዩ ሁኔታዎች ውስጥ የትኛው መሪ ምክር ቤቱን እንደሚመራ መወሰን

የአባልነት ምክር ቤቶች ሁል ጊዜ የግለሰቡ የአባልነት መዝገብ ባለበት የቤተክርስቲያን ክፍል ውስጥ ይካሄዳሉ።

አንዳንድ ጊዜ ከቦታ ቦታ ለሚዘዋወር ሰው የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ይሆናል። ዝውውሩ በተመሳሳይ ካስማ ውስጥ ከሆነ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ ከሁለቱም አጥቢያዎች ኤጲስ ቆጶሳት ጋር ተሰብስቦ የት መካሄድ እንዳለበት ይወስናል።

አባሉ ከካስማ ውጭ የሚዛወር ከሆነ፣ የሁለቱም ካስማዎች የካስማ ፕሬዚዳንቶች በመማከር ምክር ቤቱ የት መካሄድ እንዳለበት ይወስናሉ። በቀድሞው አጥቢያ ወይም ካስማ መካሄድ እንዳለበት ከወሰኑ፣ ምክር ቤቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የአባልነት መዝገቡ በዚያ አጥቢያ ይቆያል። አለበለዚያ መዝገቡ ወደ አዲሱ አጥቢያ ይዛወራል። ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ምክር ቤት ለምን እንዳስፈለገ ለአባሉ የወቅቱ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ለካስማ ፕሬዚዳንቱ በሚስጥር ያሳውቃል።

አንዳንድ ጊዜ በጊዜያዊነት ከአገሩ ርቆ ለሚኖር አባል የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ይሆናል። ለምሳሌ፣ ለአንድ ተማሪ ወይም ወታደር ምክር ቤት ሊያስፈልግ ይችላል። አባሉ በጊዜያዊነት በሚኖርበት ቦታ ያለው ኤጲስ ቆጶስ ምክር እና ድጋፍ ሊሰጥ ይችላል። ሆኖም የአባልነት መዝገቡ በእርሱ ክፍል ውስጥ ካልሆነ እና ከሚኖርበት አጥቢያ ኤጲስ ቆጶስ ጋር ካልተማከረ በስተቀር የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ አይገባውም።

አንዳንድ ጊዜ አንድ ሚስዮናዊ በሚስዮን እያለ/እያለች እስኪሰናበት/እስክትሰናበት ድረስ የማይገለጽ ከባድ ኃጢያት ሊፈጽም/ልትፈጽም ይችላል/ትችላለች። ኤጲስ ቆጶሱ እና የካስማ ፕሬዚዳንቱ ማንኛቸው የአባልነት ምክር ቤትን ማካሄድ እንዳለባቸው ለመወሰን ይወያያሉ። ምክር ቤቱን ከማካሄዳቸው በፊት አንዳቸው ከቀድሞው የሚስዮን ፕሬዚዳንት ጋር ይወያያሉ።

32.10

የአባልነት ምክር ቤት የአሰራር ቅደም ተከተል

32.10.1

ለምክር ቤቱ ማስታወቂያ መሥጠት እና መዘጋጀት

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ እሱን ወይም እሷን አስመልክቶ ስለሚካሄደው የአባልነት ምክር ቤት ለአባሉ/ሏ የጽሁፍ ማስታወቂያ ይሰጣል። ደብዳቤው ላይ ይፈርማል። ይህም የሚከተሉትን መረጃ ያካተታል፦

“[ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዘደንት] አንተ/ለአንቺ የአባልነት ምክር ቤት ያካሂዳል። ሸንጎው በ[ቀን እና ሰዓት] በ[ቦታ] ይካሄዳል።

“ይህ ምክር ቤት [የስነምግባር ጉድለቱን በአጠቃላይ ቃላት በጥቅል አስቀምጡ ሆኖም ዝርዝሩን እና ማስረጃውን አትግለጹ] ይመለከታል።

“መልስህን/ሽን ለመስጠት በምክር ቤቱ እንድትገኝ/ኚ ተጋብዘሃል/ሻል። ከጉዳዩ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው መረጃዎችን ሊሰጡ ከሚችሉ ሰዎች የጽሁፍ መግለጫዎችን ማቅረብ ትችላለህ/ያለሽ። በካስማ ፕሬዚዳንት ወይም በኤጲስ ቆጶስ በቅድሚያ ከተፈቀደላቸው እነዚህ ሰዎች አንተን/ችን ወክለው በምክር ቤቱ እንዲናገሩ መጋበዝ ትችላለህ/ያለሽ። እንዲሁም [የአጥቢያ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ወይም የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንትን] እንዲገኙ እና ድጋፍ እንዲሰጡ ልትጋብዝ/ዢ ትችላለህ/ያለሽ።

“የሚሳተፍ ማንኛውም ግለሠብ፣ የምክር ቤቱን የአሰራር ሂደት እና ሚስጥራዊነት ጨምሮ፣ የምክር ቤቱን የአክብሮት ባህሪ ለማክበር ፈቃደኛ መሆን አለበት። ከላይ ከተጠቀሱት ውጪ የህግ አማካሪዎች እና ደጋፊዎች ለመገኘት አይችሉም።”

የመጨረሻው አንቀጽ የፍቅርን፣ የተስፋን እና የመተሳሰብን ሃሳብ ሊያካትት ይችላል።

32.10.3፣ ቁጥር 4 ውስጥ ግለሰቡ ከምክር ቤቱ ጋር እንዲነጋገርለት ሊጋብዝ ስለሚችለው ሰው መመሪያ ቀርቧል።

ደብዳቤውን በግንባር ለመስጠት የማይቻል ከሆነ፣ መልዕክቱ ስለመድረሱ ማረገገጫ የሚሰጥ አገልግሎት ተጠይቆ በተመዘገበ ወይም እውቅና ባለው የፖስታ አገልግሎት ሊላክ ይችላል።

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የአባልነት ምክር ቤትን መርሐግብር ለግለሰቡ በሚመች ጊዜ ያደርጋል። በተጨማሪም የስነምግባር ጉድለቱ ተጠቂዎች ቃላቸውን ለመስጠት ከፈለጉ ለመቀበል ጊዜ እንዳለ ያረጋግጣል (32.10.2 ተመልከቱ)።

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የምክር ቤቱን ዓላማ እና የአሰራሩን ቅደም ተከተል በማብራራት አባሉን ያዘጋጃል። እንዲሁም ምክር ቤቱ የሚደርስባቸውን ውሰኔዎች እና ውጤታቸውን ያብራራል። አንድ አባል የተናዘዘ ከሆነ፣ የተናዘዛቸው ነገሮች በአባልነት ምክር ቤት ውስጥ ጥቅም ላይ መዋል እንዳለባቸው መሪው ያብራራል።

32.10.2

ከተጠቂዎች ቃል መቀበል

የቤተክርስቲያኗ አባል ተጠቂ በሚሆንበት ጊዜ (በቅርብ ቤተሰብ አባላት መካከል የሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኘነት፣ በልጆች ላይ የሚፈፀም ጥቃት፣ በትዳር ጓደኛ ላይ የሚፈፀም ጥቃት ወይም ማጭበርበር) ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዘደንቱ የግለሰቡን የወቅቱን ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት ያነጋግራል። እነዚህ መሪዎች ተጠቂው ስለስነምግባር ጉድለቱ እና ስላስከተላቸው ጉዳቶች የጽሁፍ ቃላቸውን እንዲሰጡ እድል መስጠት ጠቃሚ ስለመሆን ወይም አለመሆኑ ይወስናሉ። የተሰጡት ቃሎች በአባልነት ምክር ቤቱ ላይ ይነበባሉ (32.10.3፣ ቁጥር 3 ተመልከቱ)። የቤተክርስቲያኗ መሪዎች የቤተክርስቲያኗ አባላት ካልሆኑ ተጠቂዎች ጋር ግንኙነት የመጀመር ስልጣን የላቸውም።

ከተጠቂው ጋር ለዚሁ ዓላማ የሚደረግ ማንኛውም ግንኙነት የሚደረገው በእርሱ ወይም በእርሷ የወቅቱ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት ነው። ተጠቂው ቃል ከሰጠ፣ መሪው የአባልነት ምክር ቤትን ለሚያካሂደው ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት ይሰጠዋል። መሪዎች ተጨማሪ ጉዳት ከማድረስ ለመራቅ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። ለሌሎች ጥንቃቄዎች 32.4.3 ተመልከቱ።

ይህን ማድረግ ተጠቂውን አደጋ ላይ ሊጥለው የሚችል ካልሆነ በስተቀር፣ ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች ለሆነ ተጠቂ ማንኛውም ጥያቄ የሚቀርበው በወላጆች ወይም በህጋዊ አሳዳጊዎች በኩል ነው።

ጥቃት በሚደርሥበት ጊዜ ኤጲስ ቆጶሳት እና የካስማ ፕሬዚዳንቶች እንዴት መመሪያ እንደሚያገኙ መረጃ ለማግኘት በ32.4.5 እና 38.6.2.1. ተመልከቱ።

32.10.3

ምክር ቤቱን ማካሄድ

ምክር ቤቱ ከመጀመሩ ጥቂት ቀደም ብሎ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ምክር ቤቱ ለማን እንደሚካሄድ እንዲሁም መረጃ የተሰጠበት የስነምግባር ጉድለት ምን እንደሆነ ለተሳታፊዎች ይነግራቸዋል። አስፈላጊ ከሆነ የምክር ቤቱን የአሰራር ቅደም ተከተሎች ያብራራል።

ግለሰቡ/ቧ የተገኘ/ች ከሆነ/ች፣ ወደ ክፍሉ እንዲገባ/እንድትገባ መልካም አቀባበል ይደረግለታል። ኤጲስ ቆጶሱ የካስማ የአባልነት ምክር ቤት ላይ እንዲሳተፍ ከተጋበዘ፣ እርሱም በዚህ ሰዓት ወደ ክፍሉ እንዲገባ ይጋበዛል። ግለሰቡ የአጥቢያ የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንትን ወይም የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዘደንትን እንዲገኙ እና ድጋፍ እንዲሰጡ ከጋበዘ/ች፣ እርሱ ወይም እርሷ ወደ ክፍሉ እንዲገባ/እንድትገባ ይጋበዛሉ።

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ከታች በተዘረዘረው መሰረት ምክር ቤትን በፍቅር መንፈስ ይመራል።

  1. አንድ ሰው የመክፈቻ ጸሎት እንዲያቀርብ ይጋብዛል።

  2. ሪፖርት የተደረገን የስነምግባር ጉድለት ይገልጻል። ግለሰቡ (በዚያ የሚገኝ/የምትገኝ ከሆነ/ች) ይህንን ቃል እንዲያረጋግጥ/እንድታረጋግጥ፣ እንዲክድ/እንድትክድ ወይም እንዲያብራራ/እንድታብራራ እድል ይሰጠል።

  3. ግለሰቡ የሥነ ምግባር ጉድለቱ መፈፀወሙን ካረጋገጠ/ች፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ከታች ወደሚገኘው ወደ ቁጥር 5 ይቀጥላል። አባሉ ይህን ከካደ/ደች፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ያለውን ማስረጃ ያቀርባል። ይህ አስተማማኝ ሰነዶችን ማቅረብን እና ማንኛውንም የተጠቂዎችን የጽሁፍ ቃል በድምጽ ማንበብን ሊያካትት ይችላል (32.10.2 ተመልከቱ)። እንዲህ ያለውን የጽሁፍ ቃል ካነበበ፣ የተጠቂዎችን ማንነት ይደብቃል።

  4. አባሉ የሥነ ምግባር ጉድለትን ከካደ/ች፣ እርሱ ወይም እርሷ ያለውን/ያላትን ማስረጃ ማቅረብ ይችላል/ትችላለች። የፅሁፍ ሊሆንም ይችላል። ወይንም አባሉ ከጉዳዩ ጋር ዝምድና ያለውን መረጃ መስጠት የሚችሉ ሰዎች ለምክር ቤቱ እንዲናገሩ ለመጠየቅ ይችላል/ትችላለች። ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ አባል ያልሆነ ሊሳተፍ እንደሚችል አስቀድሞ የወሰነ ካልሆነ በስተቀር እነዚህ ሰዎች የቤተክርስቲያኗ አባላት መሆን አለባቸው። እንዲናገሩ እስኪፈቀድላቸው ድረስ በተለየ ክፍል ውስጥ ይቆያሉ። እያንዳንዱ ግለሠብ ሲጨርስ/ስትጨርስ ምክር ቤቱ ከሚካሄድበት ክፍል ይወጣሉ። የምክር ቤት የአሰራር ሂደትን እና ሚስጥራዊነት ጨምሮ የዚህን ምክር ቤት የአክብሮት ባህሪን ለመጠበቅ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው። አባላት የህግ አማካሪ ከእነርሱ ጋር እንዲገኝ አይፈቀድላቸውም። እንዲሁም በዚህ ክፍል በሁለተኛው አንቀጽ ውስጥ ከተጠቀሱት ውጪ ደጋፊዎች ሊኖሯቸው አይችሉም።

  5. ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ አባሉን በትህትና እና ክብር በተሞላበት መንገድ ጥያቄዎችን ሊጠይቀው ይችላል። አባሉ መረጃ እንዲሰጡ የጠየቃቸውን ሌሎች ሰዎች ጥያቄዎችን ሊጠይቅም ይችላል። የኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማው አመራር አማካሪዎችም ጥያቄዎችን ሊጠይቁ ይችላሉ። ማናቸውም ጥያቄዎች አጭር እና በአስፈላጊ እውነታዎች ላይ የተወሰኑ መሆን አለባቸው።

  6. ከጉዳዩ ጋር የሚያያዙ ሁሉም መረጃዎች ከቀረቡ በኋላ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ አባሉን ከክፍሉ እንዲወጣ ይጠይቁታል። ከፍተኛ አማካሪው በካስማ የአባልነት ምክር ቤት ካልተሳተፈ በስተቀር ጸሃፊውም እንዲወጣ ይጠየቃል። የአባሉ ኤጲስ ቆጶስ በካስማ የአባልነት ምክር ቤት ላይ ከተገኘ፣ እርሱም እንዲወጣ ይጠየቃል። የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንት ወይም የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንት ድጋፍ ለመስጠት ከተገኙ እርሱ ወይም እርሷም እንዲወጣ/እንድትወጣ ይጠየቃል/ትጠየቃለች።

  7. ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የአማካሪዎቹን አስተያየት ወይንም ግንዛቤያቸውን ይጠይቃቸዋል። ከፍተኛ አማካሪው በካስማ የአባልነት ምክር ቤት ከተሳተፈ አስተያየታቸውን እና ግንዛቤያቸውን ይጠይቃቸዋል።

  8. ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ከአማካሪዎቹ ጋር በመሆን ስለጉዳዩ የጌታን ፈቃድ በጸሎት መንፈስ ይጠይቃል። በዚህ ጊዜ ኤጲስ ቆጶሱ እና አማካሪዎቹ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ እና አማካሪዎቹ ብቻ በክፍሉ ውስጥ ይገኛሉ። የካስማ የአባልነት ምክር ቤቱ ከፍተኛ አማካሪን የሚያካትት ከሆነ፣ በተለምዶ የካስማ አመራሩ ወደ ካስማው ፕሬዚዳንት ቢሮ ይሄዳል።

  9. ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ውሳኔውን ለአማካሪዎቹ ይነግራቸዋል እንዲሁም እንዲደግፉት ይጠይቃቸዋል። የካስማ የአባልነት ምክር ቤት ከፍተኛ አማካሪን የሚያካትት ከሆነ፣ የካስማ አመራር ወደ ክፍሉ ይመለሳል እንዲሁም ከፍተኛ አማካሪውን እንዲደግፈው ይጠይቀዋል። አንድ አማካሪ ወይም ከፍተኛ አማካሪ የተለየ ሃሳብ ካለው፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ያዳምጣል ከዚያም ለልዩነቶቹ መፍትሄን ለማግኘት ይሻል። ውሳኔውን የማድረግ ሃላፊነት ይህን በበላይነት በሚቆጣጠረው ሃላፊ ላይ ነው።

  10. ግለሰቡ ተመልሶ ወደክፍሉ እንዲገባ ይጋብዘዋል። ጸሃፊውም እንዲወጣ ተደርጎ ከነበረ፣ እርሱም ወደ ክፍሉ እንዲገባ ይጋበዛል። የአባሉ ኤጲስ ቆጶስ በካስማ የአባልነት ሸንጎ ላይ ከተገኘ፣ እርሱም ወደ ክፍሉ እንዲገባ ይጋበዛል። የሴቶች መረዳጃ ማህበር ፕሬዚዳንት ወይም የሽማግሌዎች ቡድን ፕሬዚዳንት ድጋፍ ለመስጠት ከተገኙ፣ እርሷ ወይም እርሱ ወደ ክፍሉ እንዲገቡ ይጋበዛሉ።

  11. ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የምክር ቤቱን ውሳኔ በፍቅር መንፈስ ያጋራል። ውሳኔው የግለሰቡን የቤተክርስቲያን አባልነት መብቶችን መገደብ ወይም ከአባልነት ማስወገድ ከሆነ፣ ሁኔታዎቹን ያብራራል (32.11.3 እና 32.11.4 ተመልከቱ)። በተጨማሪም ገደቦችን ለማሠረዝ ምን ማድረግ እንደሚቻል ያብራራል እንዲሁም ሌሎች መመሪያዎችን እና ምክሮችን ይሰጣል። ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት ውሳኔ ከማድረጉ በፊት ተጨማሪ መመሪያ ወይም መረጃ ለማግኘት ምክር ቤቱን ለተወሰነ ጊዜ ሊያዘገይ ይችላል። እንደዚያ ከሆነም፣ ይህንኑ ያብራራል።

  12. የግለሰቡን ይግባኝ የመጠየቅ መብት ያብራራል (32.13 ተመልከቱ)።

  13. አንድ ሰው የመዝጊያ ጸሎት እንዲያቀርብ ይጋብዛል።

ግለሰቡ በዚያ የተገኘ ቢሆንም ባይሆንም፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ውሳኔውን በ32.12.1 ውስጥ በተብራራው መሠረት ለእርሱ ወይም ለእርሷ ያሳውቃል።

ማንኛውም የአባልነት ምክር ቤት ተሳታፊ የድምፅ፣ የቪዲዮ ወይም የጽሁፍ ቀረጻ እንዲያደርግ አይፈቀድለትም። ጸሐፊው የቤተክርስቲያን አባልነት ምክር ቤት ሪፖርትን ለማዘጋጀት ማስታወሻ ሊወስድ ይችላል። ሆኖም እንዲህ አይነት ማስታወሻዎች የቃል በቃል ቅጂ ወይም ግልባጭ መሆን የለባቸውም። ሪፖርቱ ከተዘጋጀ በኋላ ማንኛውንም ማስታወሻ ወዲያውኑ ያጠፋል።

32.11

በአባልነት ምክር ቤቶች የተሠጡ ውሳኔዎች

በአባልነት ምክር ቤቶች የሚሠጡ ውሳኔዎች በመንፈስ የተመሩ መሆን አለባቸው። አዳኙ ንስሃ ለሚገቡ የሚሰጠውን ፍቅር እና ተስፋ ማንጸባረቅ አለባቸው። ሊሠጡ የሚችሉ ውሳኔዎች ከዚህ በታች ተብራርተዋል። መሪዎች እነዚህን ውሳኔዎች ሲወስኑ በ32.7 ውስጥ የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ግምት ውስጥ ያስገባሉ።

ማንኛውም የአባልነት ምክር ቤት ከተደረገ በኋላ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የቤተክርስቲያን የአባልነት ምክር ቤት ቅጽ ሪፖርትን በLCR ውስጥ በፍጥነት ያስገባል (32.14.1 ተመልከቱ)።

በአባልነት ምክር ቤቶች ሊሠጡ የሚችሉ ውሳኔዎች በሚከተሉት ክፍሎች ተዘርዝረዋል።

32.11.1

በጥሩ አቋም ላይ የሚገኝ

በአንዳንድ ሁኔታዎች አንድ ግለሰብ ንጹህ እና በጥሩ አቋም ላይ የሚገኝ ሊሆን ይችላል። በአንዳንድ ሁኔታዎች ግለሰቡ ኃጢያትን የፈፀመ፣ ከልቡ ንስሃ የገባ፣ እና በጥሩ አቋም ላይ የሚገኝ ሊሆን ይችላል። ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ወደፊት ስለሚወሰዱት እርምጃዎች ምክር እና ማስጠንቀቂያ ሊሠጥ ይችላል። ምክር ቤቱ ከተካሄደ በኋላ፣ እንዳስፈላጊነቱ ድጋፍ መስጠቱን ይቀጥላል።

ምስል
ጥንዶች አብረው ተቀምጠው

32.11.2

ከኤጲስ ቆጶስ ወይም ከካስማ ፕሬዚዳንት ጋር የሚደረግ የግል ምክር

በአንዳንድ የአባልነት ምክር ቤቶች ላይ፣ መሪዎች አባሉ በጥሩ አቋም ላይ እንደማይገኝ —ነገር ግን መደበኛ የአባልነት ገደቦች አስፈላጊ እንዳልሆኑ ሊወስኑ ይችላሉ። በእነዚህ ሁኔታዎች፣ ግለሰቡ ከኤጲስ ቆጶሱ ወይም ከካስማ ፕሬዚዳንቱ የግል ምክር እና ማስተካከያ እንዲቀበል ምክር ቤቱ ሊወስን ይችላል። ይህ ምክር በ32.8.3 ውስጥ በተዘረዘረው መሰረት መደበኛ ያልሆነ የአባልነት ገደቦችን ሊያካትት ይችላል።

32.6.1 ውስጥ ለተዘረዘሩት ኃጢያቶች ምክር ቤት ሲካሄድ፣ የግል ምክር እና መደበኛ ያልሆኑ የአባልነት ገደቦች አማራጮች አይሆኑም።

32.11.3

መደበኛ የአባልነት ገደቦች

በአንዳንድ የአባልነት ምክር ቤቶች፣ መሪዎች በአንድ ግለሠብ የቤተክርስቲያን የአባልነት መብቶች ላይ ለተወሰነ ጊዜ መደበኛ ገደብ መጣል የተሻለ እንደሆነ ሊወስኑ ይችላሉ። የአባልነት መወገድን ከሚያስከትሉ በጣም ከባድ ኃጢያቶች ወይም ሁኔታዎች በስተቀር መደበኛ ገደቦች ለሌሎች ለሁሉም በቂ ሊሆኑ ይችላሉ (32.11.4 ተመልከቱ)።

መደበኛ የአባልነት ገደቦች የተጣሉባቸው ግለሠቦች አሁንም የቤተክርስቲያኗ አባላት ናቸው። ሆኖም የቤተክርስቲያን አባልነት መብቶቻቸው እንደሚከተለው ገደብ ተጥሎባቸዋል፦

  • ወደ ቤተመቅደስ መግባት አይችሉም። ሆኖም፣ የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበሉ ከሆኑ የቤተመቅደስ ልብሶች መልበሳቸውን ሊቀጥሉ ይችላሉ። አባሉ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ካለው፣ መሪው በLCR ውስጥ ይህን ይሰርዘዋል።

  • የክህት ስልጣንን መጠቀም አይችሉም።

  • ቅዱስ ቁርባንን አይካፈሉም ወይም በቤተክርስቲያኗ የመሪዎች ድጋፍ አሰጣጥ ላይ አይሳተፉም።

  • ንግግር አያቀርቡም፣ ትምህርት አይሰጡም ወይም በቤተክርስቲያን ውስጥ አይጸልዩም። በቤተክርስቲያን ጥሪም አያገለግሉም።

ሥርዓት ያለው ሥነ ምግባር ካላቸው በቤተክርስቲያኗ ስብሰባዎች እና በተለያዩ ድርጊቶች ላይ እንዲገኙ ይበረታታሉ። አስራትን እና የጾም በኩራትን እንዲከፍሉም ይበረታታሉ።

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ከብልግና ምስሎች እና ከሌሎች ክፉ ተጽዕኖዎች መራቅን የመሰሉ ሌሎች ገደቦችንም ሊጨምር ይችላል። ብዙውን ጊዜ አዎንታዊ ሁኔታዎችን ይጨምራል። እነዚህም በመደበኛነት በቤተክርስቲያን መሣተፍን ፣ የዘወትር ጸሎት ማድረግን፣ እና ቅዱሳት መጻህፍትን እና ሌሎች የቤተክርስቲያኗን ጽሁፎችን ማንበብን ሊያካትቱ ይችላሉ።

በግለሠቡ የቤተክርስቲያን የአባልነት መብቶች ላይ መደበኛ ገደብ ከተጣለ፣ በአባልነት መዝገቡ ላይ ማስታወሻ ይጻፋል።

የመደበኛ ገደብ የጊዜ ርዝመት በአብዛኛው ቢያንስ አንድ አመት ነው እናም ከዚያ ረዘም ያለ ሊሆንም ይችላል። አባሉ እውነተኛ ንስሐ በመግባት የተወሰነ እድገት ሲያደርግ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ገደቦቹን ለማስወገድ ሌላ ምክር ቤት ያካሂዳል (32.16.1 ተመልከቱ)። አባሉ በኃጢያት ልምዱ ከቀጠለ፣ መሪው ሌሎች እርምጃዎችን ግምት ውስጥ ለማስገባት ሌላ ምክር ቤት ሊያካሂድ ይችላል።

32.11.4

ከአባልነት ማስወገድ

በአንዳንድ የአባልነት ምክር ቤቶች፣ መሪዎች ከቤተክርስቲያን አባልነት ማስወገድ የተሻለ እንደሆነ ሊወስኑ ይችላሉ (ሞዛያ 26፥36አልማ 6፥3ሞሮኒ 6፥7ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥83 ተመልከቱ)።

ነፍስ ግድያ (በ32.6.1.1 ውስጥ በተገለጸውመሰረት) እና ከአንድ በላይ ጋብቻ (32.6.1.2 ውስጥ በተገለጸው መሰረት) የፈጸመ ግለሰብ ከቤተክርስቲያን አባልነት መወገድ አለበት። በ32.6.1.2 እና 38.6.10 ውስጥ በተገለጸውው መሰረት፣ በቤተሰብ አባላት መካከል ለሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ይህ ሁልጊዜ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል።

መንፈስ እንደሚመራ አንድን ግለሰብ ከቤተክርስቲያን አባልነት ማስወገድ ለሚከተሉት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፦

  • ምግባራቸው በሌሎች ላይ ከባድ ስጋት የሚፈጥር ግለሰቦች።

  • የተለየ እጅግ በጣም ከባድ ኃጢያት ለሠሩ ግለሰቦች።

  • ለከባድ ኃጢያቶች ንስሐ እንደገቡ በተግባር ለማያሳዩ ግለሰቦች (ግምት ውስጥ የሚገቡ ነገሮችን በ32.7 ውስጥ ተመልከቱ)።

  • ቤተክርስቲያኗን የሚጎዳ ከባድ ኃጢያት ለሰሩ ግለሰቦች።

የአጥቢያ፣ የቅርንጫፍ ወይም የአውራጃ የአባልነት ምክር ቤት የቤተመቅደስ ቡራኬ ያልተቀበለ ግለሰብን ከቤተክርስቲያን አባልነት እንዲወገድ ሃሳብ ሊያቀርብ ይችላል። ሆኖም ውሳኔው የመጨረሻ ከመሆኑ በፊት የካስማ ወይም የሚስዮን ፕሬዚዳንቱ ፈቃድ ያስፈልጋል።

ከቤተክርስቲያን አባልነት የተወገዱ ምንም የአባልነት መብት አይኖራቸውም።

  • ወደ ቤተመቅደስ መግባት ወይም የቤተመቅደስ ልብሶችን መልበስ አይችሉም ። አባሉ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ካለው፣ መሪው በLCR ውስጥ ይሰርዘዋል።

  • የክህት ስልጣንን መጠቀም አይችሉም።

  • ቅዱስ ቁርባንን አይካፈሉም ወይም በቤተክርስቲያኗ የመሪዎች ድጋፍ አሰጣጥ ላይ አይሳተፉም።

  • ንግግር አያቀርቡም፣ ትምህርት አይሰጡም ወይም በቤተክርስቲያን ውስጥ አይጸልዩም ወይም በቤተክርስቲያን ምንም አይነት ድርጊቶችን አይመሩም። በቤተክርስቲያን ጥሪም አያገለግሉም።

  • አስራትን እና የጾም በኩራትን አይከፍሉም።

ሥርዓት ያለው ሥነ ምግባር ካላቸው በቤተክርስቲያኗ ስብሰባዎች እና በተለያዩ ድርጊቶች ላይ እንዲገኙ ይበረታታሉ።

ከቤተክርስቲያን አባልነት የተወገዱ በመጠመቅ እና ማረጋገጫ በመቀበል እንደገና ወደ ቤተክርስቲያኗ ለመቀላቀል ግምት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ። አብዛኛውን ጊዜ፣ በመጀመሪያ ቢያንስ ለአንድ ዓመት እውነተኛ ንስሐ እንደገቡ ማሳየት አለባቸው። ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማው ፕሬዚዳንት እንደገና ቤተክርስቲያኗን መቀላቀልን ከግምት ለማስገባት ሌላ የሸንጎ ሊያካሂድ ይችላል (32.16.1 ተመልከቱ)።

የአባልነት ሸንጎ ውሳኔዎች እና ውጤቶች

ውሳኔዎች

ውጤቶች

ውሳኔዎች

በጥሩ አቋም ላይ ይገኛል (32.11.1 ተመልከቱ)

ውጤቶች

  • ምንም

ውሳኔዎች

ከኤጲስ ቆጶስ ወይም ከካስማ ፕሬዚዳንት ጋር የሚደረግ የግል ምክር (32.11.2 ተመልከቱ)።

ውጤቶች

  • የተወሰኑ የቤተክርስቲያን አባልነት መብቶቻቸው መደበኛ ባልሆነ መንገድ ሊገደቡ ይችላሉ።

  • በተለምዶ ገደቦች የሚጣሉት ከአንድ ዓመት ላነሰ ጊዜ ሲሆን ባልተለመዱ ሁኔታዎች ከዚያ ሊረዝምም ይችላል።

  • ከእውነተኛ ንስሃ በኋላ መደበኛ ያልሆኑ ገደቦች ሊነሱ ይችላሉ።

  • እርምጃው በአባልነት መዝገብ ላይ አይመዘገብም።

ውሳኔዎች

መደበኛ የአባልነት ገደቦች (32.11.3 ተመልከቱ)።

ውጤቶች

  • የአባልነት መብቶች በመደበኛ ሁኔታ ገደብ ይጣልባቸዋል።

  • የመደበኛ ገደብ የጊዜ ርዝመት በአብዛኛው ቢያንስ አንድ አመት ነው እናም ከዚያ ረዘም ያለ ሊሆንም ይችላል።

  • እርምጃው በአባልነት መዝገብ ላይ ይመዘገባል።

  • መደበኛ ገደቦች የሚነሱት ከእውነተኛ ንስሃ፣ የአባልነት ሸንጎ ከተካሄደ እና፣ አስፈላጊ ከሆነ፣ ከቀዳሚ አመራር ፈቃድ በኋላ ነው።

  • ከአባልነት ሸንጎ በኋላ ገደቦች ከተነሱ፣ የአባልነት መዝገብ አመልካቹ (ከሚያስፈልጉ ማስታወሻዎች በስተቀር፤ 32.14.5 ተመልከቱ) ይሰረዛል።

ውሳኔዎች

ከአባልነት መወገድ (32.11.4 ተመልከቱ)

ውጤቶች

  • ሁሉም ስርዓቶች ይሻራሉ።

  • በተለምዶ ቢያንስ ለአንድ ዓመት ጊዜ የአባልነት መብቶች ይወገዳሉ።

  • አንድ ግለሰብ በመጠመቅ እና ማረጋገጫ በመቀበል እንደገና ወደ ቤተክርስቲያኗ ለመቀላቀል ብቁ የሚሆነው እውነተኛ ንስሃ ከገባ፣ የአባልነት ምክር ቤትን ከተካሄደ እና አስፈላጊ ከሆነም፣ ከቀዳሚ አመራር ፈቃድ ካገኘ በኋላ ነው (32.16 ተመልከቱ)።

  • ከዚህ ቀደም የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበለ ሰው የበረከቶች መመለስን ለመቀበል ብቁ የሚሆነው በመጀመሪያ አመራር ፈቃድ ብቻ እና እንደገና ወደ ቤተክርስቲያኗ ከተቀላቀለ ቢያንስ አንድ አመት በኋላ ነው (32.17.2 ተመልከቱ)።

  • ከዚህ ቀደም የቤተመቅደስ ቡራኬ ለተቀበለ ግለሠብ “የበረከቶች መመለስ ያስፈልጋል” የሚለው አመልካች ከአባልነት መዝገብ የሚወጣው ስርዓቱ ከተከነናወነ በኋላ ብቻ ነው (አስፈላጊ ማስታወሻዎች ይቆያሉ፤ 32.14.5 ተመልከቱ)።

32.11.5

ከባድ ጉዳዮችን ስለመወሰን የሚነሱ ጥያቄዎች

ኤጲስ ቆጶሳት የአባልነት ምክር ቤትን የተመለከቱ የመመሪያ መፅሐፍ መመሪያዎች ጥያቄዎችን ወደካስማ ፕሬዚዳንቱ ይልካሉ።

በአስቸጋሪ ጉዳዮች ላይ የካስማ ፕሬዚዳንቱ ከተመደበለት የአካባቢ ሰባ ምክር ሊጠይቅ ይችላል። የካስማ ፕሬዚዳንቱ በ32.6.3 ውስጥ በተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይ ከአካባቢው አመራር ጋር መማከር ይኖርበታል። ሆኖም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የአካባቢ ሰባን ወይም አጠቃላይ ባለሥልጣን በአስቸጋሪ ጉዳዮች ላይ እንዴት እንደሚወሰን መጠየቅ የለበትም፡፡ የካስማ ፕሬዚዳንቱ ምግባሩን ለመመልከት የአባልነት ምክር ቤት ማካሄድ ስለማስፈለጉ ይወስናል። ምክር ቤቱ ከተካሄደ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ ወይም ኤጲስ ቆጶሱ ውጤቱን ይወስናል።

32.11.6

የቀዳሚ አመራር ሥልጣን

የቀዳሚ አመራር በሁሉም የቤተክርስቲያን የአባልነት ገደቦች እና ከአባልነት ማስወገድ ላይ የመጨረሻው ሥልጣን አለው።

32.12

ማሳወቂያዎች እና ማስታወቂያዎች

የአባልነት ምክር ቤት ውሣኔ ለግለሰቡ—እና አስፈላጊ ከሆነም ለሌሎች—ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት ይነገራል።

32.12.1

ውሳኔውን ለግለሰብ ማሳወቅ

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ፣ ምክር ቤቱ ተካሂዶ ሲፈጸም የዚህን የመጨረሻ ውጤት ለግለሰቡ ይነግራሉ። ሆኖም፣ ውሳኔ ከማድረጉ በፊት ተጨማሪ መመሪያ ወይም መረጃ ለማግኘት ምክር ቤቱን ለተወሰነ ጊዜ ሊያዘገይ ይችላል።

የአጥቢያ፣ የቅርንጫፍ ወይም የአውራጃ የአባልነት ምክር ቤት የቤተመቅደስ ቡራኬ ያልተቀበለ ግለሰብን ከቤተክርስቲያን አባልነት እንዲወገድ ሃሳብ ሊያቀርብ ይችላል። ሆኖም ውሳኔው የመጨረሻ ከመሆኑ በፊት የካስማ ወይም የሚስዮን ፕሬዚዳንቱ ፈቃድ ያስፈልጋል።

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የውሳኔውን ውጤቶች በ32.11 ውስጥ በተዘረዘረው መሠረት ያብራራል። በተለምዶ ገደቦች እንዲነሱ ወይም ግለሰቡ እንደገና ወደ ቤተክርስቲያኗ እንዲቀላቀል የሚያስችሉ የንስሐ ሁኔታዎችን በምክር ይሰጣል።

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ፣ ውሳኔውን እና ውጤቶቹን የሚመለከት የጽሁፍ ማሳሰቢያ በአፋጣኝ ለግለሠቡ ይሰጣል። ይህ ማሳሰቢያ፣ እርምጃው የተወሰደው የቤተክርስቲያኗን ህግና ስርዓት የሚጻረር ድርጊት በመፈጸሙ መሆኑን የሚጠቁም ጥቅል ሃሳብን ያካትታል። የአባልነት ገደቦችን ስለማንሳት ወይም ግለሰቡን ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደገና የመቀላቀል ምክርን ሊያካትትም ይችላል። እርሱ ወይም እርሷ ይግባኝ መጠየቅ እንደሚችል/ምትችል ማሳወቅም አለበት (32.13 ተመልከቱ)።

ግለሰቡ በምክር ቤት ካልተሳተፈ/ፈች፣ ውሳኔውን ለእሱ ወይም ለእሷ ለማሳወቅ የጽሁፍ ማስታወቂያ በቂ ሊሆን ይችላል። ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ግለሰቡን በግል ሊያገኘውም ይችላል።

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ፣ የቤተክርስቲያን አባልነት ምክር ቤት ሪፖርት ቅጂን ለግለሰቡ አይሰጥም።

32.12.2

ውሳኔን ለሌሎች ማሳወቅ

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ በግል ምክር ወቅት መደበኛ ባልሆነ ሁኔታ በግለሰቡ የአባልነት መብቶች ላይ ገድብ ከጣለ፣ በተለምዶ ለሌላ ለማንም አያሳውቅም (32.8.3 ተመልከቱ)። ሆኖም፣ እነዚህ መሪዎች አባላትን በሚረዱበት ጊዜ መደበኛ ስላልሆኑ ገደቦች ይነጋገራሉ።

የአንድ ግለሰብ የአባልነት መብቶች በአባልነት ምክር ቤት በመደበኛነት ገደብ ከተጣለባቸው ወይም ከአባልነት ከተወገደ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ውሳኔውን የሚያሳውቁት ማወቅ ለሚያስፈልጋቸው ብቻ ነው። የሚከተሉት መመሪያዎች ተግባራዊ ይሆናሉ።

  • የተጠቂዎችን እና ተጠቂ ሊሆኑ የሚችሉትን እና የግለሰቡን ቤተሠብ ስሜት ግምት ውስጥ ያስገባል።

  • ግለሰቡ ይግባኝ ካለ ውሳኔውን ለማንም አያሳውቅም። ሆኖም፣ ተጠቂ ሊሆኑ የሚችሉትን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ፣ ይግባኝ መጠየቁን ሊገልጽ ይችላል። እንዲሁም የተጠቂዎችን (የተጠቂዎችን ስም ባይጠቅስም) የፈውስ ሂደት ለመደገፍ ወይም የቤተክርስቲያኗን ሃቀኝነት ለመጠበቅ ሲባል ይህን ሊያሳውቅ ይችላል።

  • እንዳስፈላጊነቱ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ውሳኔውን ለአጥቢያ የምክር ቤት አባላት በሚስጥር ያሳውቃል። ይህ የሚሆነው ግለሰቡ ጥሪ ለመቀበል፣ ትምህርት ለማስተማር፣ ጸሎት ለማቅረብ ወይም ንግግር ለመስጠት ዝግጁ እንደሆነ አድርገው ሊያስቡ የሚችሉ መሪዎችን ለማሳወቅ ነው። ይህም መሪዎች ለአባሉ እና ለቤተሰቡ እንክብካቤ እና ድጋፍ እንዲሰጡ ለማበረታታት ነው።

  • ሁኔታው ከታች የተዘረዘሩትን የሚያካትት ከሆነ፣ በካስማ ፕሬዚዳንቱ ፈቃድ፣ ኤጲስ ቆጶሱ በአጥቢያ የሽማግሌዎች ቡድን እና በሴቶች መረዳጃ ማህበር ስብሰባዎች ላይ ውሳኔውን ሊያሳውቅ ይችላል።

    • ሌሎችን ለአደጋ የሚያጋልጡ ሌላን ለመጉዳት ሆን ተብሎ የሚደረጉ ባሕርያት።

    • የሃሰት ትምህርት ወይም ሌላ የክህደት መልክ ያለው ነገር ማስተማር።

    • ከአንድ በላይ ጋብቻን እንደመፈጸም ወይም ተከተታይ ለማፍራት የአምልኮ ስርዓቶች ያሉባቸው ትምህርቶችን እንደመጠቀም ያሉ ችላ ሊባሉ የማይቻሉ መጥፎ ኃጢያቶች።

    • የአጠቃላይ ወይንም የአካባቢ የቤተክርስቲያን መሪዎችን ተግባራት ወይም ትምህርቶች በግልጽ መቃወም።

  • እንደዚህ ባሉ ሁኔታዎች፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ በካስማው ውስጥ ላሉ ለሌሎች የአጥቢያ አባላት ማሳወቅን መፍቀድ ሊያስፈልገው ይችላል።

  • በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ፣ የአባልነት ምክር ቤት ለግለሰቡ መካሄዱን ለተወሰኑ ወይም ለሁሉም ተጠቂዎች እና ቤተሰቦቻቸው ማሳወቅ የሚጠቅም እንደሆነ ሊሰማው ይችላል። ይህንን የሚያደርገው በኤጲስ ቆጶሳቸው ወይም በካስማ ፕሬዚዳንታቸው በኩል ነው።

  • የግለሰቡ ሌላን ለመጉዳት ሆን ብሎ የሚደረጉ ዝንባሌዎች ሌሎችን አደጋ ላይ የሚጥል ከሆነ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይንም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የሌሎችን ደህንነት ለመጠበቅ ለመርዳት ማስጠንቀቂያ ሊሰጥ ይችላል። ሚስጥራዊ መረጃን አይገልጽም እንዲሁም አስቀድሞ ምን እንደነበር አይገምትም።

  • በሌሎች በሁሉም ሁኔታዎች ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ማንኛውንም የሚናገረውን ነገር ጥቅል ሃሳብ የያዘ እንዲሆን ያደርጋል። የግለሰቡ የቤተክርስቲያን የአባልነት መብቶች ገደብ የተጣለባቸው ወይም ከአባልነት የተወገደው የቤተክርስቲያኗን ህግና ሥርዓት የሚጻረር ድርጊት በመፈጸሙ መሆኑን የሚጠቁም ጥቅል ሃሳብን ይገልጻል። በቦታው የተገኙትን እንዳይወያዩበት ይጠይቃቸዋል። እርምጃውን እንደሚደግፉት ወይም እንደሚቃወሙት አይጠይቃቸውም።

  • ከአባልነት ሸንጎ በኋላ አባሉ በጥሩ አቋም ላይ የሚገኝ ከሆነ (32.11.1 ተመልከቱ) ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ወሬውን ለማስተባበል ያንን ሊያሳውቅ ይችላል።

32.12.3

ከአባልነት በፈቃደኝነት መልቀቅን ማሳወቅ

በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ ኤጲስ ቆጶሱ፣ አንድ ግለሰብ የቤተክርስቲያን አባልነቱን/ቷን መልቀቁን/ቋን ማሳወቅ ሊያስፈልገው ይችላል (32.14.9 ተመልከቱ)። ኤጲስ ቆጶሱ ምንም ሌላ ዝርዝር አይሰጥም።

32.13

በተሰጠ ውሳኔ ላይ ይግባኝ መጠየቅ

አንድ አባል የአጥቢያ የአባልነት ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔን በ30 ቀናት ውስጥ ለካስማ ፕሬዚዳንቱ ይግባኝ ማቅረብ ይችላል። የካስማ ፕሬዚዳንቱ ይግባኙን ለመመልከት የካስማ የአባልነት ሸንጎ ሊያካሂድ ይችላል። ኤጲስ ቆጶስ ሸንጎን እንደገና እንዲሠበስብ እና በተለይ አዲስ መረጃ ካለ ውሳኔውን እንዲያጤነው ሊጠይቀውም ይችላል።

አባል የካስማ የአባልነት ሸንጎ ያሳለፈውን ውሳኔ በ30 ቀናት ውስጥ ደብዳቤ በመጻፍ ለቀዳሚ አመራር ይግባኝ ማቅረብ ይችላል። አባሉ ደብዳቤውን ለቀዳሚ አመራር እንዲያቀርብለት ለካስማ ፕሬዚዳንቱ ይሰጣል።

በሚስዮን ውስጥ፣ አባል የቅርንጫፍ ወይም የአውራጃ የአባልነት ሸንጎ ያሳለፈውን ውሳኔ በ30 ቀናት ውስጥ ለሚስዮን ፕሬዚዳንቱ ይግባኝ ማቅረብ ይችላል። የሚስዮን ፕሬዚዳንቱ ይግባኙን ለመመልከት የአባልነት ሸንጎ ያካሂዳል። ጊዜ ወይም ርቀት ይህንን ከማድረግ የሚገድበው ከሆነ በ32.9.4 ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ይከተላል።

ሸንጎን ያካሄደው የሚስዮን ፕሬዚዳንት ከሆነ፣ አባሉ የተላለፈውን ውሳኔ በ30 ቀናት ውስጥ ደብዳቤ በመጻፍ ለቀዳሚ አመራር ይግባኝ ማቅረብ ይችላል። አባሉ ደብዳቤውን ለቀዳሚ አመራር እንዲያቀርብለት ለሚስዮን ፕሬዘደንቱ ይሰጣል።

በውሳኔው ላይ ይግባኝ የሚጠይቀው ግለሠብ በሂደቱ ወይም በውሳኔው ውስጥ የተፈጠሩትን ስህተቶች ወይም ኢፍትሃዊነት በጽሁፍ በግልጽ ይለያል።

ይግባኙን ለመመልከት የአባልነት ሸንጎ ከተካሄደ፣ ከሁለት ውሳኔዎች አንዱ ነው ሊወሰንበት ይቻላል፦

  • የመጀመሪያው ውሳኔ እንዲጸና ማድረግ።

  • በመጀመሪያው ውሳኔ ላይ ማስተካከያ ማድረግ።

የቀዳሚ አመራር ውሳኔዎች የመጨረሻ ናቸው እናም ይግባኝ የላቸውም።

32.14

ሪፖርቶች እና የአባልነት መዝገቦች

32.14.1

የቤተክርስቲያን አባልነት ምክር ቤት ሪፖርት

ከማንኛውም የአባልነት ምክር ቤት በኋላ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የቤተክርስቲያን አባልነት ምክር ቤት ቅጽ ሪፖርትን በLCR ውስጥ በፍጥነት ያልካል። ጸሃፊው ሪፖርቱን እንዲያዘጋጅ ሊጠይቀው ይችላል። ምንም የቅጹ የታተመ ቅጂ ወይም የኤሌክትሮኒክ ቅጂ እርሱ ጋር እንዳልቀረ ያረጋግጣል። ሪፖርቱን ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ የዋሉ ማናቸውም ማስታወሻዎች ወዲያውኑ መጥፋታቸውንም ያረጋግጣል።

32.14.2

መደበኛ የቤተክርስቲያን የአባልነት ገደቦች

መደበኛ የቤተክርስቲያን የአባልነት ገደቦች በግለሰቡ የአባልነት መዝገብ ላይ ይጻፋሉ። የቤተክርስቲያኗ ዋና መስሪያ ቤት፣ የቤተክርስቲያን የአባልነት ምክር ቤት ሪፖርትን ከተቀበለ በኋላ ይህንን ማስታወሻ ይጽፋል። አባሉ ንስሐ ሲገባ፣ መሪው እነዚህን ገደቦች ለማንሳት ሌላ ምክር ቤት ያካሂዳል (32.16.1 ተመልከቱ)።

32.14.3

አንድ ግለሠብ ከቤተክርስቲያን አባልነት ከተወገደ በኋላ የሚኖር መዝገብ

አንድ ግለሠብ ከቤተክርስቲያን አባልነት ከተወገደ፣ የቤተክርስቲያኗ ዋና መስሪያ ቤት የቤተክርስቲያን የአባልነት ምክር ቤት ሪፖርትን ከተቀበለ በኋላ የአባልነት መዝገቡን ያስወግዳል። ግለሰቡ/ቧ ከፈለገ/ች፣ መሪዎች፣ እርሱ ወይም እርሷ በመጠመቅ እና ማረጋገጫ በመቀበል እንደገና ወደ ቤተክርስቲያኗ እንዲቀላቀል/እንድትቀላቀል እንዲዘጋጅ/እንድትዘጋጅ ይረዱታል/ይረዷታል (32.16.1 ተመልከቱ)።

32.14.4

ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደገና ከመቀላቀል በኋላ የሚኖር መዝገብ

ግለሠቡ ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደገና ከተቀላቀለ በኋላ ኤጲስ ቆጶሱ የቤተክርስቲያን የአባልነት ምክር ቤት ቅጽ ሪፖርትን ይልካል። የጥምቀት እና የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አይፈጠርም። ከዚያ ይልቅ፣ ጥምቀቱ እና ማረጋገጫው በቤተክርስቲያን የአባልነት ምክር ቤት ቅጽ ላይ ይመዘገባል።

አባሉ የቤተመቅደስ ቡራኬን ያልተቀበለ ከሆነ፣ የቤተክርስቲያኗ ዋና መስሪያ ቤት የቀድሞውን የጥምቀት እና የሥርዓቶች ቀን የሚያሳይ የአባልነት መዝገብ ይሰጠዋል። መዝገቡ ከቤተክርስቲያን አባልነት ስለመወገድ አይጠቅስም።

አባሉ የቤተመቅደስ ቡራኬን የተቀበለ ከሆነ፣ የቤተክርስቲያኗ ዋና መስሪያ ቤት አዲሱን የጥምቀት እና ማረጋገጫ የተቀበለበትን ቀን እንዲያሳይ የአባልነት መዝገቡን ያድሳል። ይህ መዝገብ “የበረከቶች መመለስ ያስፈልጋል” የሚል መልዕክትንም ያካትታል። የአባሉ በረከቶች ከተመለሱ በኋላ (32.17.2 ተመልከቱ) የአባልነት መዝገቡ የቀድሞውን የጥምቀት እና የሌሎች ሥርዓቶች ቀን እንዲያሳይ እንዲታደስ ይደረጋል። መዝገቡ ከቤተክርስቲያኗ አባልነት ስለመወገድ አይጠቅስም።

32.14.5

ማስታወሻዎች የተጻፉባቸው የአባልነት መዝገቦች

በቀዳሚ አመራር በሚፈቀደው መሰረት፣ የቤተክርስቲያኗ ዋና መሥሪያ ቤት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት በማናቸውም ሁኔታዎች ውስጥ በግለሠብ የአባልነት መዝገብ ላይ ማብራሪያ ያስቀምጣል።

  1. ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የግለሰቡ አባልነት በሚከተሉት በማናቸውም የሥነ ምግባር ጉድለቶች መደበኛ ገደብ የተጣለበት ወይም ከአባልነት የተወገደ መሆኑን የሚያመለክት የቤተክርስቲያን የአባልነት ምክር ቤት ቅጽ ሪፖርት ያቀርባል።

    1. በቅርብ ቤተሰብ አባላት መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት

    2. በልጆች ወይም በወጣቶች ላይ የሚፈፀም ፆታዊ ጥቃት ወይም ፣ የልጆች ወይም የወጣቶች የወሲብ ብዝበዛ ወይም የልጆች ወይም የወጣቶች ከባድ አካላዊ ወይም ስሜታዊ ጥቃት

    3. የልጆች የብልግና ምስሎችን መመልከት (በ38.6.6 ውስጥ እንደተዘረዘረው)

    4. ከአንድ በላይ ጋብቻ መፈፀም

    5. የአዋቂ ሰው ፆታዊ በደል የማድረስ ባሕርይ

    6. በውልደት ጊዜ ካገኙት ጾታ በተቃራኒ የሚገለጹ ግለሰቦች—በውልደት ጊዜ የተገኘን ጾታ ወደ ተቃራኒ ለመቀየር የሚደረግ ድርጊት (38.6.23 ተመልከቱ)

    7. የቤተክርስቲያንን ገንዘብ መመዝበር ወይም ንብረት መስረቅ (32.6.3.3 ተመልከቱ)

    8. የቤተክርስቲያንን የበጎ አድራጎት ገንዘብ አላግባብ ጥቅም ላይ ማዋል

    9. የማስፈራራት ባሕርይ (በወሲብ፣ በጉልበት ወይም በገንዘብ) ወይም ቤተክርስቲያኗን የሚጎዳ ሥነምግባር

  2. ኤጲስ ቆጶሱ እና የካስማ ፕሬዚዳንቱ፣ ግለሰቡ ያደረጋቸውን የሚከተሉትን በጽሁፍ ማሳወቂያ ይልካሉ፦

    1. ከላይ ከተዘረዘሩት ድርጊቶች ውስጥ በአንዱ ጥፋተኛነቱ እንደተረጋገጠ ወይም እንደተፈረደበት

    2. ከላይ ከተዘረዘሩት ድርጊቶች ውስጥ በአንዱ ህግን በመጣስ፣ በማጭበርበር ወይም በሌላ ጥፋተኛነቱ በፍትሐ ብሄር ፍርድ እንደተረጋገጠ።

ኤጲስ ቆጶሱ ማብራሪያ የተጻፈበት የአባልነት መዝገብ ሲቀበል፣ በማብራሪያዎቹ ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ይከተላል።

ማብራሪያን ከአባልነት መዝገብ ውስጥ እንዲወገድ ሊፈቅድ የሚችለው ቀዳሚ አመራር ብቻ ነው። የካስማ ፕሬዚዳንቱ ማብራሪያን ለማስወገድ ሃሳብ የሚያቀርብ ከሆነ LCR ይጠቀማል (6.2.3) ተመልከቱ)። የቀዳሚ አመራር ቢሮ ያቀረበው ሃሳብ መፈቀድ ወይም አለመፈቀዱን ያሳውቀዋል።

32.14.6

የቤተክርስቲያንን ገንዘብ ስርቆት በሚመለከት ሪፖርት ማቅረብ

የአንድ ግለሰብ አባልነት የቤተክርስቲያንን ገንዘብ በመመዝበሩ ምክንያት ገደብ ከተጣለበት ወይም ከአባልነትከተወገደ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ በ34.7.5 ውስጥ በተዘረዘረው መሰረት ሪፖርት ያደርጋል።

32.14.7

የአባልነት መዝገቦች ወደሌላ ቦታ እንዳይዛወሩ መገደብ

አንዳንድ ጊዜ አንድ የቤተክርስቲያኗ አባል የአባልነት ውሳኔዎችን ወይም ሌሎች አሳሳቢ ጉዳዮች በመጠባበቅ ላይ እያለ ግለሰቡ ወደ ሌላ ቦታ ይዛወራል። አንዳንድ ጊዜ ኤጲስ ቆጶሱ የአባልነት መዝገቡን ወደ አዲሱ ክፍል ከማስተላለፉ በፊት ለአዲሱ ኤጲስ ቆጶስ መረጃ ማካፈል ያስፈልገዋል። እንደዚህ ባሉ ሁኔታዎች፣ ኤጲስ ቆጶሱ (ወይም ፀሐፊው የተፈቀደለት ከሆነ) በአባልነት መዝገቡ ላይ የማዛወር ገደብ ሊያስቀምጥ ይችላል። ኤጲስ ቆጶሱ (ወይም ፀሐፊው የተፈቀደለት ከሆነ) ገደቡን እስከሚያስወግድ ድረስ መዝገቡ በዚያች የቤተክርስቲያኗ ክፍል ይቆያል። ይህም ኤጲስ ቆጶሱ ያሉትን ስጋቶች እና መረጃዎች እንዲያስተላልፍ እድል ይሠጠዋል።

32.14.8

በማረሚያ ቤት ያሉ ግለሠቦች መዝገቦች

አንዳንድ አባላት በወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው በማረሚያ ቤት ይገኛሉ። ወንጀሉ በተፈጸመበት ጊዜ አባሉ ይኖርበት የነበረው የቤተክርስቲያኗ ክፍል ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት መደበኛ የአባልነት ገደቦችን ለመጣል ወይም ከአባልነት ለማስወገድ ማንኛውንም አስፈላጊ እርምጃ ይወስዳል። የአባልነት መብቶች የተገደቡ ከሆኑ፣ መሪው (ወይም ፀሐፊው የተፈቀደለት ከሆነ) የአባልነት መዝገቡን ግለሠቡ በታሰረበት ቦታ ኃላፊነት ላለበት የቤተክርስቲያኗ ክፍል ያስተላልፈዋል። አባልነቱ የተወገደ ከሆነ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የዚያን የቤተክርስቲያን ክፍል መሪ ያነጋግራል። (32.15 ተመልከቱ።)

32.14.9

በገዛ ፈቃድ ከአባልነት ለመልቀቅ የሚቀርብ ጥያቄ

አንድ አባል የቤተክርስቲያን አባልነቱን በገዛ ፈቃዱ ለመልቀቅ ከጠየቀ፣ ኤጲስ ቆጶሱ በችግሮቹ ላይ ለመወያየት እና መፍትሄ ለማግኘት ሙከራ ለማድረግ እርሱ ወይም እርሷ ፈቃደኛ እንደሆነ/ች ለማየት ይሞክራል። ኤጲስ ቆጶሱ እና አባሉ ከካስማ ፕሬዚዳንቱ ጋር ሊማከሩም ይችላሉ። አባሉ ከቤተክርስቲያን አባልነት በገዛ ፈቃድ መልቀቅ የሚከተሉትን ውጤቶች እንደሚያስከትል መረዳቱን መሪው ያረጋግጣል።

  • ሁሉንም ሥርዓቶች ይሰርዛል።

  • ሁሉንም የአባልነት መብቶች ይሰርዛል።

  • በመጠመቅ እና ማረጋገጫ በመቀበል እንደገና ወደ ቤተክርስቲያኗ ለመቀላቀል የሚቻለው ከጥልቅ ቃለ መጠይቅ በኋላ ሲሆን በብዙ ሁኔታዎችም የአባልነት ምክር ቤት መካሄድ አለበት (32.16.2 ተመልከቱ)።

  • ከዚህ ቀደም የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበለ ሰው የበረከቶች መመለስን እና የቤተመቅደስ በረከቶችን ለመቀበል ብቁ የሚሆነው በቀዳሚ አመራር ፈቃድ ብቻ እና እንደገና ወደ ቤተክርስቲያኗ ከተቀላቀለ ቢያንስ አንድ አመት በኋላ ነው (32.17.2 ተመልከቱ)።

አባሉ/ሏ አሁንም የቤተክርስቲያን አባልነቱን/ቷን በገዛ ፈቃዱ/ዷ ለመልቀቅ ከፈለገ/ች፣ እርሱ ወይም እርሷ ለኤጲስ ቆጶሱ የተፈረመ የጽሁፍ ጥያቄ ያቀርባል/ታቀርባለች። ኤጲስ ቆጶሱ ጥያቄውን በLCR በኩል ለካስማ ፕሬዚዳንቱ ይልካል። ከዚያም፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ ጥያቄውን ገምግሞ በዚሁ ስርዓት በኩል ጥያቄውን ይልካል። መሪዎች ለጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ መስጠት አለባቸው።

ግለሰቡ የተፈረመና የተረጋገጠ ጥያቄ ወደ ቤተክርስቲያኗ ዋና መስሪያ ቤት በመላክ አባልነቱን በገዛ ፈቃዱ መልቀቅም ይችላል።

እድሜው ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ የቤተክርስቲን አባልነቱን በገዛ ፈቃዱ ለመልቀቅ ቢፈልግ ከአንድ ልዩ ነገር በስተቀር እንደ አዋቂ ሰው ተመሳሳይ የአሰራር ሂደትን ይከተላል፦ ጥያቄው እድሜው ለአካለመጠን ባልደረሰው ልጅ (ከ8 አመት በላይ ከሆነ) እና እድሜው ለአካለመጠን ባልደረሰው ልጅ ወላጅ(ጆች) ወይም ህጋዊ የማሳደግ መብት ባላቸው አሳዳጊ(ዎች) መፈረም አለበት።

የቤተክርስቲያን አባልነቱን በገዛ ፈቃዱ የሚለቅ አባል ቤተክርስቲያኗን ወይም መሪዎቿን እንደሚከስ የሚያስፈራራ ከሆነ፣ የካስማ ፕሬዚዳንቱ በ38.8.23 ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ይከተላል።

የክህነት መሪዎች የከባድ ኃጢያት መረጃ ቢኖራቸውም በገዛ ፈቃድ ከአባልነት የመልቀቅ ጥያቄውን መተግበር አለበት። ጥያቄው LCR በኩል በሚላክበት ጊዜ መፍትሄ ስላልተገኘላቸው ኃጢያቶች ያሉት ማናቸውም መረጃዎች ይጻፋሉ። ይህም ግለሰቡ ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደገና ለመቀላቀል ካመለከተ የክህነት መሪዎች ወደፊት እንደዚህ ያሉትን ጉዳዮች ለመፍታት ያስችላቸዋል (32.16.2 ተመልከቱ)።

የክህነት መሪ የአባልነት ምክር ቤትን ላለማካሄድ ሲል ከቤተክርስቲያን አባልነት በገዛ ፈቃድ የመልቀቅን ምክር መስጠት የለበትም።

ከእነርሱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳይደረግ ካልጠየቁ በስተቀር መሪዎች አባልነታቸውን በገዛ ፈቃድ የለቀቁትን ማገልገላቸውን ይቀጥላሉ።


የቤተክርስቲያን አባልነት መብቶችን መመለስ


የአንድ ግለሰብ የቤተክርስቲያን አባልነት መብቶች ገደብ የተጣለባቸው ወይም ከአባልነት የተወገደ ከሆነ፣ መሪዎች ከእርሱ/ሷ ጋር ወዳጃዊ ግንኙነት ይኖራቸዋል፣ ይመክሩታል/ይመክሯታል እንዲሁም ግለሰቡ እንደፈቀደው/እንደፈቀደችው ድጋፍ ይሰጣሉ። ይህ ክፍል እነዚያ መብቶች እንዴት ሊመለሱ እንደሚችሉ ይገልጻል።

32.15

ማገልገልን መቀጠል

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ እንደ ዋና ዳኛ ያለው ሀላፊነት አንድ አባል የአባልነት ገደብ ሲጣልበት ወይም እርሱ ወይም እርሷ ከቤተክርስቲያን አባልነት ሲወገድ/ ስትወገድ አያበቃም። እርሱ ወይም እርሷ እንደገና በቤተክርስቲያን አባልነት በረከቶች መደሰት ይችል/ትችል ዘንድ፣ ግለሰቡ እንደፈቀደው/ችው መሪው ማገልገሉን ይቀጥላል። ኤጲስ ቆጶሱ በየጊዜው ከግለሰቡ እንዲሁም ጠቃሚ እና አስፈላጊ ሲሆን ከትዳር ጓደኛው ጋር ይገናኛል። አዳኙ ኔፋውያንን እንዲህ አስተማረ፦

“… ከማምለኪያ ስፍራዎቻችሁ አታስወጡ፣ ምክንያቱም ለእነዚህ አይነት ለማገልገል መቀጠል አለባችሁ፤ ምክንያቱም አንድ ቀን እንደሚለወጡና ንሰሃ እንደሚገቡ እናም በልባቸው ሙሉ አላማ ወደ እኔ እንደሚመጡ አታውቁምና፣ እናም እፈውሳቸዋለሁ፤ እናንተም ደህንነትን ወደ እነርሱ ለማምጣት መሳሪያ ትሆናላችሁ” (3 ኔፊ 18፥32)።

ሰው የአባልነት ገደብ ከተጣለበት ወይም ከአባልነት ከተወገደ በኋላ ያለው ጊዜ ለእርሱ ወይም ለእርሷ ቤተሰብ ከባድ እና ወሳኝ ነው። መሪዎች ለእነዚህ ፍላጎቶች ፈጣን ምላሽ የሚሰጡ መሆን አለባቸው እንዲሁም የቤተሰብ አባላትን ማበረታታት እና መርዳት አለባቸው።

ኤጲስ ቆጶሱ፣ የቤተክርስቲያን አባልነት ገደብ የተጣለበትን ወይም የተወገደን ግለሰብ (ግለሰቡ እንደፈቀደው) ለማገልገል አሳቢ አባላት መመደባቸውን ያረጋግጣል። ደግሞም ሌሎች የቤተሰብ አባላትንም ያገለግላሉ። የአባልነት ገደብ የተጣለባቸው ግለሰቦች በቤተሰብ ታሪክ ማቀናበር ስራ ውስጥ በመሳተፍ ሊጠቀሙ ይችላሉ (25.4.3 ተመልከቱ)።

ግለሰቡ ከአጥቢያው ውጪ ከተዛወረ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ለአዲሱ ኤጲስ ቆጶስ ጉዳዩን ያሳውቃል እንዲሁም የቤተክርስቲያን አባልነት ገደቦች ከመነሳታቸው በፊት ምን መሆን እንዳለበት ያብራራል። ግለሰቡ ከቤተክርስቲያን አባልነት ከተወገደ ወይም ከአባልነት በገዛ ፈቃዱ ከለቀቀ፣ ከቤተክርስቲያኗ መሪዎች እርዳታ ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆነ ኤጲስ ቆጶሱ ይህንኑ ግንኙነት ያደርጋል።

32.16

መደበኛ ገደቦችን ማንሳት ወይም ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደገና መቀላቀል

32.16.1

መደበኛ ገደቦችን ለማንሳት ወይም አንድን ግለሠብ እንደገና ለመቀበል የሚካሄዱ የአባልነት ምክር ቤቶች

የአባልነት መብቶች በአባልነት ምክር ቤት በመደበኛነት ገደብ ከተጣለባቸው ወይም ከተወገዱ፣ ገደቦቹን ለማንሳት ወይም ግለሰቡን ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደገና መቀላቀልን ግምት ውስጥ ለማስገባት ሌላ ምክር ቤት መካሄድ አለበት። ይህ ምክር ቤት እንደመጀመሪያው ምክር ቤት ተመሳሳይ ስልጣን (ወይም ከዚይ የላቀ) ሊኖረው ይገባል። ለምሳሌ የመጀመሪያውን ምክር ቤት በበላይነት የመራው የካስማ ወይም የሚስዮን ፕሬዚዳንት ከሆነ፣ ገደቦቹን ለማንሳት ወይም ግለሰቡን ወደ ቤተክርስቲያኗ በድጋሚ ለመቀላቀል ምክር ቤትን የሚመሩት የካስማ ወይም የሚስዮን ፕሬዚዳንት ይሆናል።

የወቅቱ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት ምክር ቤቱን ያካሂዳሉ። በመጀመሪያ ግለሰቡ ንስሃ ገብቶ እንደሆነ እንዲሁም በቤተክርስቲያን አባልነት በረከቶች ለመደሰት ዝግጁ እና ብቁ መሆኑን ያረጋግጣል።

የቤተክርስቲያን አባልነታቸው መደበኛ ገደብ የተጣለባቸው፣ ገደቡን ማንሳትን ግምት ውስጥ ለማስገባት በተለምዶ ቢያንስ ለአንድ ዓመት እውነተኛ ንስሐ እንደገቡ ማሳየት አለባቸው። ከቤተክርስቲያን አባልነታቸው የተወገዱ፣ እንደገና ወደ ቤተክርስቲያኗ ለመቀላቀል በተለምዶ ቢያንስ ለአንድ ዓመት እውነተኛ ንስሐ እንደገቡ ማሳየት አለባቸው። ከባድ ኃጢያት በተሠራ ጊዜ በታወቀ የቤተክርስቲያን የሃላፊነት ቦታ ላይ ለነበረ አባል፣ ይህ ጊዜ ይረዝማል (32.6.1.4 ተመልከቱ)።

ገደቦችን ማንሳትን ወይም ግለሠቡን ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደገና መቀላቀልን ግምት ውስጥ የሚያስገባ ምክር ቤት ልክ እንደ ሌሎች የአባልነት ምክር ቤት ተመሳሳይ መመሪያን ይከተላል። አንድ ኤጲስ ቆጶስ የአባልነት ምክር ቤትን ለማካሄድ ከካስማ ፕሬዚዳንቱ ፈቃድ ማግኘት አለበት። በሚስዮን ውስጥ፣ የቅርንጫፍ ወይም የአውራጃ ፕሬዚዳንት ከሚስዮን ፕሬዚዳንቱ ፈቃድ ማግኘት አለበት።

የቤተክርስቲያን የአባልነት ገደቦችን ለማንሳት ወይም ግለሰቡን ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደገና መቀላቀልን ግምት ውስጥ ለማስገባት የአባልነት ምክር ቤት ሲካሄድ የሚከተሉት መመሪያዎች ተግባራዊ ይሆናሉ። ሁሉም እነዚህ መመሪያዎች በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ተግባራዊ ላይሆኑ ይችላሉ።

  1. የመጀመሪያውን የአባልነት ምክር ቤት ይገመግማል። ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ፣ የቤተክርስቲያን አባልነት ምክር ቤት ቅጽ ሪፖርትን ይገመግማል። በLCR በኩል ቅጂውን ይጠይቃል። ቅጹን ከገመገመ በኋላ፣ ማብራሪያ ለማግኘት የመጀመሪያው ምክር ቤት የተካሄደበትን ቦታ ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት ሊያነጋግር ይችላል።

  2. ግለሰቡን ቃለ መጠይቅ ያደርጋል። ግለሰቡ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለውን/ላትን የእምነት ጥንካሬ እንዲሁም የንስሃውን/ዋን መጠን ለማወቅ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ በደንብ ቃለ መጠይቅ ያደርገዋል/ጋታል። ግለሰቡ በመጀመርያው ድርጊት ውስጥ የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ማሟላት ወይም አለማሟላቱን ይወስናል።

  3. የወንጀል ወይም የፍትሐ ብሔር ችሎት ድርጊት ሁኔታን መወሰን። አንዳንድ ጊዜ አንድ ግለሠብ ወንጀል መፈጸሙን ሊያምን ወይም በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ሊገኝ ይችላል። አንዳንድ ጊዜ አንድ ግለሠብ በማጭበርበር ወይም በሌሎች ሕገ ወጥ የፍትሐ ብሔር ድርጊቶች ተጠያቂ ሆኖ ሊገኝ ይችላል። በእነዚህ ሁኔታዎች፣ በአጠቃላይ ግለሰቡ በህግ አካላት የተሰጠውን ማንኛውንም ፍርድ፣ ትእዛዝ ወይም የመጨረሻ ውሳኔ ሁሉ እስኪፈጽም ድረስ መሪው ምክር ቤትን አያካሂድም። እነዚህ ሁኔታዎች እስራትን፣ የሙከራ ጊዜን፣ ይቅርታን እና መቀጫን ወይም ካሳ መክፈልን ሊያካትቱ ይችላሉ። የአባልነት ምክር ቤትን ከማካሄድ በፊት ልዩ ሁኔታዎች የቀዳሚ አመራር ፈቃድ ያስፈልጋቸዋል። እነዚህ ልዩ ሁኔታዎች ከህግ የሚጠበቅበትን ግዴታዎች ያጠናቀቀ እና እውነተኛ ንስሃ መግባቱን ያሳየ ነገር ግን የዕድሜ ልክ የሙከራ ጊዜ ላይ ያለ ወይም ከፍተኛ ቅጣት የተጣለበትን ሰው ሊያካትቱ ይችላሉ።

  4. የተጠቂዎችን የክህነት መሪዎች ማነጋገር። ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የማንኛውንም ተጠቂ የወቅቱን ኤጲስ ቆጶስ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንት ያነጋግራል (32.10.2 ተመልከቱ)።

  5. ስለሚካሄደው ምክር ቤት ማስታወቂያ ይሰጣል። ምክር ቤት የሚካሄድበትን ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ለግለሰቡ ያሳውቃል።

  6. ምክር ቤትን ያካሄዳል። ምክር ቤትን በ32.10.3 ውስጥ ባሉት መመሪያዎች መሠረት ያካሂዳል። ንስሃ ለመግባት የሚያስፈልገው ምን ድርጊት እንደፈጸመ/ች እርሱን ወይም እርሷን ይጠይቃል። ለኢየሱስ ክርስቶስ እና ለቤተክርስቲያኗ ስላለው/ላት ቁርጠኝነትም ይጠይቃል። ከጉዳዩ ጋር የሚያያዙ ሁሉም ጉዳዮች ከቀረቡ በኋላ አባሉ እንዲወጣ ይጠይቀዋል። ምን እርምጃ እንደሚወስድ ለማወቅ ከአማካሪዎቹ ጋር ይጸልያል። ሊሆኑ የሚችሉ ሶስቱ ውሳኔዎችም፦

    1. በአባልነት ላይ የተጣለ ገደብን ወይም ከአባልነት መወገድን መቀጠል።

    2. ገደቦችን ማንሳት ወይም ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደገና መቀላቀልን መፍቀድ።

    3. ገደቦች እንዲነሱ ወይም ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደገና መቀላቀል እንዲፈቀድ ለቀዳሚ አመራር ሃሳብ ማቅረብ (አስፈላጊ ከሆነ ይህ የሚደረገው ከታች ባለው “ከቀዳሚ አመራር ፈቃድ ለማግኘት ማመልከት” በሚለው መሰረት ነው)።

  7. ውሳኔውን ማጋራት። ምክር ቤት ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ የበላይ ተቆጣጣሪ ሃላፊው ለግለሰቡ ውሳኔን ያሳውቀዋል። ከቀዳሚ አመራር ፈቃድ ማግኘት አስፈላጊ ከሆነ፣ ውሳኔው ለቀዳሚ አመራር የቀረበ ምክረ ሃሳብ እንደሆነ ይገልጻል።

  8. ሪፖርት ማቅረብ። ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ፣ የቤተክርስቲያን አባልነት ምክር ቤት ቅጽ ሪፖርትን በLCR በኩል ይልካል። ጸሃፊው ሪፖርቱን እንዲያዘጋጅ ሊጠይቀው ይችላል። ምንም የቅጹ ታተመ ቅጂ ወይም የኤሌክትሮኒክ ቅጂ እርሱ ጋር እንዳልቀረ ያረጋግጣል። ሪፖርትን ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ የዋሉ ማናቸውም ማስታወሻዎች ወዲያውኑ መጥፋታቸውንም ያረጋግጣል።

  9. ከቀዳሚ አመራር ፈቃድ ለማግኘት ማመልከት (አስፈላጊ ከሆነ)። በሚከተሉት ሁኔታዎች፣ መደበኛ የአባልነት ገደቦችን ለማንሳት ወይም ግለሰቡን ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደገና ለመቀላቀል የቀዳሚ አመራር ፈቃድ አስፈላጊ ነው። የሥነ ምግባር ጉድለቱ የተከሰተው የቤተክርስቲያን አባልነት ገደብ ከተጣለ ወይም ከአባልነት ከተወገደ በኋላ ቢሆንም ይህ ፈቃድ ያስፈልጋል።

    የካስማ ፕሬዚዳንቱ ለቀዳሚ አመራር ማመልከቻ የሚያቀርበው እንዲፈቀድ ምክረ ሃሳብ የሚያቀርብ ከሆነ ብቻ ነው(6.2.3 ተመልከቱ)።

    1. ነፍስ ግድያ

    2. በቅርብ የቤተሰብ አባላት መካከል የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት

    3. በልጆች ወይም በወጣቶች ላይ የሚደረግ ፆታዊ ጥቃት፣ የልጆች ወይም የወጣቶች የወሲብ ብዝበዛ ወይም በአዋቂ ሰው ወይም በእድሜ በብዙ አመታት በሚበልጥ ወጣት በልጆች ወይም በወጣቶች ላይ የሚደረግ ከባድ አካላዊ ወይም ስሜታዊ ጥቃት

    4. በህግ ጥፋተኛ ሆኖ እያለ የልጆች የብልግና ምስሎችነን መመልከት

    5. ክህደት

    6. ከአንድ በላይ ጋብቻ

    7. በታወቀ የቤተክርስቲያን የሃላፊነት ቦታ ላይ ሆኖ ከባድ ኃጢያት መስራት

    8. በውልደት ጊዜ ካገኙት ጾታ በተቃራኒ የሚገለጹ ግለሰቦች—በውልደት ጊዜ የተገኘን ጾታ ወደ ተቃራኒ ለመቀየር የሚደረግ ድርጊት (38.6.23 ተመልከቱ)

    9. የቤተክርስቲያንን ገንዘብ ወይንም ንብረት መመዝበር

  10. የውሳኔውን የጽሁፍ ማስታወቂያ መስጠት። ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ውሳኔውን እና ውጤቶቹን የሚመለከት የጽሁፍ ማሳሰቢያ በአፋጣኝ ለግለሰቡ መሰጠቱን ያረጋግጣል።

  11. ማጥመቅ እና ማረጋገጥ። አንድ ግለሰብ በመጀመሪያ በተደረገ ምክር ቤት ከቤተክርስቲያን አባልነት የተወገደ ከሆነ፣ እርሱ ወይም እርሷ እንደገና መጠመቅ እና ማረጋገጫ መቀበል አለበት/አለባት። የቀዳሚ አመራር ፈቃድ የሚያስፈልግ ከሆነ፣ እነዚህ ስርዓቶች ይህ ፈቃድ ከተገኘ በኋላ ብቻ ሊከናወኑ ይችላሉ። የጥምቀት እና የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አይፈጠርም (32.14.4 ተመልከቱ)።

32.16.2

ከቤተክርስቲያን አባልነት በገዛ ፈቃድ ከመልቀቅ በኋላ ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደገና መቀላቀል

አንድ ግለሰብ በመደበኛነት የቤተክርስቲያን አባልነትን በገዛ ፈቃድ ከለቀቀ/ች፣ እርሱ ወይም እርሷ ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደገና ለመቀላቀል መጠመቅ እና ማረጋገጫ መቀበል አለበት/ባት። አዋቂዎች፣ አባልነትን በገዛ ፈቃዳቸው ከለቀቁ በኋላ አብዛኛውን ጊዜ ቢያንስ እስከ አንድ አመት ድረስ ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደገና መቀላቀል ግምት ውስጥ አይገባም።

አንድ ግለሰብ ወደቤተክርስቲያኗ እንደገና ለመቀላቀል ሲጠይቅ፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ቤተክርስቲያንን በገዛ ፈቃድ ለመልቀቅ ከቀረበው መጠየቂያ ጋር አብሮ ያለው የአስተዳደራዊ እርምጃ ቅጽ ሪፖርት ቅጂን ያገኛል። ይህንን በLCR በኩል ማግኘት ይችላል።

ከዚያም ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ግለሰቡን በደንብ ቃለ መጠይቅ ያደርገዋል። ስለመጀመሪያው ጥያቄ እና ወደ ቤተክርስቲያኗ በድጋሚ ለመቀላቀል ያነሳሳውን ምክንያቶች ይጠይቃል። በፍቅር መንፈስ፣ አባልነቱን በገዛ ፈቃድ ከለቀቀ በኋላ ግለሰቡ ፈጽሟቸው ሊሆን የሚችሉ ከባድ ኃጢያቶች እንዳሉ ይጠይቃል። መሪው፣ ግለሰቡ ንስሃ ገብቶ እንደሆነ እንዲሁም እንደገና በቤተክርስቲያኗ አባልነት በረከቶች ለመደሰት ዝግጁ እና ብቁ መሆኑን ሳያረጋግጥ ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደገና የመቀላቀልን ሂደትን አይቀጥልም።

የቤተክርስቲያን አባልነትን በገዛ ፈቃድ ከለቀቁ በኋላ ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደገና ለመቀላቀል የሚረዱ መመሪያዎች፦

  • ግለሰቡ የቤተክርስቲያን አባልነቱን በገዛ ፈቃዱ በለቀቀ ጊዜ መደበኛ የአባልነት ገደብ ተጥሎበት የነበረ ከሆነ የአባልነት ምክር ቤት ይካሄዳል።

  • ግለሰቡ የቤተክርስቲያን አባልነቱን በገዛ ፈቃዱ ከመልቀቁ በፊት ክህደትን ጨምሮ ከባድ ኃጢያት ሰርቶ የነበረ ከሆነ የአባልነት ምክር ቤት ይካሄዳል።

በሌሎች ሁኔታዎች፣ ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ እንደሚያስፈልግ ካልወሰነ በስተቀር የአባልነት ምክር ቤት አይካሄድም።

የቤተመቅደስ ቡራኬ ለተቀበለ ግለሰብ የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ሲሆን የካስማ ፕሬዚዳንቱ ያካሂደዋል። የቤተመቅደስ ቡራኬ ላልተቀበለ ግለሰብ የአባልነት ምክር ቤት አስፈላጊ ሲሆን ኤጲስ ቆጶሱ ከካስማ ፕሬዚዳንቱ በሚያገኘው ፈቃድ ያካሂደዋል።

ግለሰቡ የቤተክርስቲያን አባልነቱን በገዛ ፈቃዱ በለቀቀ ጊዜ ወይም ከለቀቀ በኋላ በ32.16.1፣ ቁጥር 9 ውስጥ ከሰፈሩት የሥነ ምግባር ጉድለቶች በአንዳቸው ተሳትፎ የነበረ ከሆነ፣ እንደገና ወደ ቤተክርስቲያኗ ለመቀላቀል የቀዳሚ አመራር ፈቃድ ያስፈልጋል። ግለሰቡ የቤተክርስቲያን አባልነቱን በገዛ ፈቃዱ በለቀቀ ጊዜ ወይም ከለቀቀ በኋላ በ32.14.5፣ ቁጥር 1ውስጥ ከሰፈሩት የስነምግባር ጉድለቶች በአንዳቸው ተሳትፎ የነበረ ከሆነ በአባልነት መዝገቡ ላይ ማብራሪያ ይፃፍበታል።

ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደገና ለመቀላቀል የሚጠይቅ ግለሰብ እንደሌሎቹ እንደተጠመቁት ተመሳሳይ መስፈርቶችን ማሟላት አለበት። ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ ግለሰቡ ብቁ እንደሆነ እና እንደገና ወደ ቤተክርስቲያኗ ለመቀላቀል ልባዊ ፍላጎት እንዳለው ካረጋገጠ፣ ግለሰቡ ሊጠመቅ እና ማረጋገጫ ሊቀበል ይችላል። የጥምቀት እና የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አይፈጠርም (32.14.4 ተመልከቱ)።

ምስል
አንድ ሠው ቅዱስ ቁርባን እየወሰደ

32.17

ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደገና ከመቀላቀል በኋላ የሚደረግ የቤተክርስቲያን ተሳትፎ፣ ሹመት እና የበረከቶች መመለስ

32.17.1

የቤተክርስቲያን ተሳትፎ እና ሹመት

የሚከተለው ሰረንጠዥ በጥምቀት እና ማረጋገጫ በመቀበል እንደገና ወደ ቤተክርስቲያኗ የተቀላቀለ ግለሰብ የሚኖረውን ተገቢ የቤተክርስቲያን ተሳትፎ ደረጃ ያመለክታል።

ከዚህ በፊት የቤተመቅደስ ቡራኬ ያልተቀበለ

የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበለ

የቀድሞ የክህነት ተሸካሚዎች

ከዚህ በፊት የቤተመቅደስ ቡራኬ ያልተቀበለ

  • ከተጠመቁ እና ማረጋገጫ ከተቀበሉ በኋላ ወዲያውኑ ክህነት እንዲሰጣቸው እና ከቤተክርስቲያን አባልነታቸው ሲወገዱ ወይም የቤተክርስቲያን አባልነታቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ሲለቁ ይዘውት ወደ ነበረው ክህነት ሊሾሙ ይችላሉ። ድጋፍ ለመቀበል አይቀርቡም።

  • ለሞቱ ዘመዶቻቸው እንዲጠመቁ እና ማረጋገጫ እንዲቀበሉ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ሊሰጣቸው ይችላል።

የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበለ

  • በማንኛውም የክህነት ሃላፊነት አይሾሙም። ክህነታቸው እና የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃዳቸው ሲመለስ የቀድሞ የክህነት ሃላፊነታቸው በ32.17.2 ውስጥ በተዘረዘረው መሰረት ይመለሳል። እስከዚያ ጊዜ ድረስ ሥርዓቶችን ማካሄድ አይችሉም።

  • የቤተመቅደስ ቡራኬ ላልተቀበለ ክህነት ለሌለው አባል እንዲሳተፍ በሚፈቀድ በማንኛውም የቤተክርስቲያን እንቅስቃሴ መሳተፍ ይችላል።

  • በረከቶቻቸው እስከሚመለሱ ድረስ የቤተመቅደስ ልብሶችን አይለብሱም ወይም ምንም ዓይነት የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ አይቀበሉም።

ሌሎች አባላት

ከዚህ በፊት የቤተመቅደስ ቡራኬ ያልተቀበለ

  • እንደ አዲስ ተጠማቂዎች በቤተክርስቲያን እንቅስቃሴዎች ሊሳተፉ ይችላሉ።

  • ለሞቱ ዘመዶቻቸው እንዲጠመቁ እና ማረጋገጫ እንዲቀበሉ የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ ሊሰጣቸው ይቻላል።

የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበለ

  • የቤተመቅደስ ቡራኬ ላልተቀበለ ክህነት ለሌለው አባል እንዲሳተፍ በሚፈቀድ በማንኛውም የቤተክርስቲያን እንቅስቃሴ መሳተፍ ይችላሉ።

  • በረከቶቻቸው እስከሚመለሱ ድረስ የቤተመቅደስ ልብሶች አይለብሱም ወይም ምንም ዓይነት የቤተመቅደስ መግቢያ ፈቃድ አይቀበሉም (32.17.2 ተመልከቱ)።

32.17.2

የበረከቶች መመለስ

በመጠመቅ እና ማረጋገጫ በመቀበል ከዚህ ቀደም የቤተመቅደስ ቡራኬ የተቀበሉ እና እንደገና ወደ ቤተክርስቲያኗ የተቀላቀሉ ክህነታቸውን እና የቤተመቅደስ በረከቶቻቸውን የሚቀበሉት በበረከቶች መመለስ ሥርዓት አማካኝነት ብቻ ነው (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 109፥21 ተመልከቱ)። በክህነት ሃላፊነቶች አይሾሙም ወይም እንደገና የቤተመቅደስ ቡራኬ አይቀበሉም። እነዚህ በረከቶች የሚመለሱት በሥርዓት አማካኝነት ነው። ከሰባ፣ ከኤጲስ ቆጶስ ወይም ከፓትርያርክ ሃላፊነቶች በስተቀር ወንድሞች ወደ ቀድሞው የክህነት ሹመታቸው ይመለሳሉ።

የበረከቶች መመለስ ሥርዓት እንዲከናወን ፈቃድ መስጠት የሚችለው ቀዳሚ አመራር ብቻ ነው። ግለሰቡ በጥምቀት እና ማረጋገጫ በመቀበል እንደገና ወደ ቤተክርስቲያኗ ከተቀላቀለ በኋላ አንድ አመት ከማለፉ በፊት ይህን ሥርዓት ለማከናወን የሚቀርብ ማመልከቻ ግምት ውስጥ አይገባም።

ኤጲስ ቆጶሱ ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱ የእርሱን ወይም የእርሷን ብቁነት እና ዝግጁነት ለመወሰን ግለሠቡን ቃለ መጠይቅ ያደርጋል። የካስማ ፕሬዚዳንቱ፣ ግለሰቡ ዝግጁ እንደሆነ ሲሰማው፣ በLCR በኩል የበረከቶች መመለስ ማመልከቻ ያቀርባል። የካስማ ፕሬዚዳንቱ ለቀዳሚ አመራር ማመልከቻ ሲያስገባ ስላለበት ሃላፊነት 6.2.3 ተመልከቱ።

ቀዳሚ አመራር የበረከቶች መመለስን ከፈቀዱ፣ ግለሠቡን ቃለ መጠይቅ እንዲያደርገው አንድ አጠቃላይ ባለስልጣንን ወይም የካስማ ፕሬዚዳንቱን ይመድባሉ። ግለሰቡ ብቁ ከሆነ፣ ይህ መሪ የግለሰቡን የበረከቶች መመለስ ሥርአት ያከናውናል።

ስለአባልነት መዝገብ እና በረከቶችን ስለመመለስ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት 32.14.4 ተመልከቱ።