2023 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አደረጃጀት
ጥቅምት 2023 (እ.አ.አ)


“የኢየሱስ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን አደረጃጀት፣” ሊያሆና፣ ጥቅምት 2023 (እ.አ.አ)

ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ ጥቅምት 2023 (እ.አ.አ)

የኢየሱስ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ድርጅት

ምስል
የኢየሱስ ክርስቶስ ምስል

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በዴል ፓርሰን

ኢየሱስ ክርስቶስ የኋላኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ዋና መሪ ነው። በአዲስ ኪዳን ዘመን እንዳደረገው፣ ዛሬም ቤተክርስቲያኗን እንዲመሩ ነቢያትንና ሐዋርያትን ያነሳሳል። በሌሎች የቤተክርስቲያኗ መሪዎችም ይረዳሉ።

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የአዳኙ ቤተክርስቲያን ናት። እርሷም “በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻ[ለች]፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” (ኤፌሶን 2፥20)። ይህ ማለት እርሱ የመሠረቱ በጣም አስፈላጊ አካል ነው ማለት ነው። መሪ እንዲሆኑ በመረጣቸው ነቢያትና ሐዋርያት አማካኝነት ቤተክርስቲያኗን ይመራል።

ምስል
ቀዳሚ አመራር

የቀዳሚ አመራር

የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንት ዛሬ በምድር ላይ ያለው የእግዚአብሔር ነቢይ ነው። እርሱ ታላቅ ሐዋርያ እና መላ ቤተክርስቲያኗን ለመምራት ራዕይን የሚቀበል በምድር ላይ ያለ ብቸኛው ሰው ነው። ጌታ የእርሱ አማካሪዎች በመሆን የሚያገለግሉትን የትኞቹን ሁለት ሐዋርያት እንደሚጠራ እንዲያውቅ ያነሳሳዋል። እነርሱም ቀዳሚ አመራርን ይመሰርታሉ። ሦስቱም ነቢያት፣ ባለራዕያት፣ እና ገላጮች ናቸው።

የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን

የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ቡድን አባላትም ነቢያት፣ ባለ ራዕያት እና ገላጮች ናቸው። የኢየሱስ ክርስቶስ ልዩ ምስክሮች እንዲሆኑ ተጠርተዋል። ስለ እርሱ ለማስተማር እና ለመመስከር በዓለም ዙሪያ ይጓዛሉ። ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥23፣ 33ን ይመልከቱ።)

የሰባዎቹ ቡድን

የሰባዎች አባላትም የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክሮች እንዲሆኑ ተጠርተዋል ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 107፥25ን ይመልከቱ)። እነርሱም የአስራ ሁለቱን ቡድን አባላት ወንጌልን በማስተማር እና ቤተክርስቲያኗን በአለም ዙሪያ በመገንባት ይረዷቸዋል።

ምስል
መሪዎች በጋራ ሲማከሩ

ፎቶግራፍ በማቺኮ ሆሪ

የቅርብ አካባቢ መሪዎች

የእናንተ የካስማ ወይም የአውራጃ አመራር፣ የኤጲስ ቆጶስ ወይም የቅርንጫፍ አመራር፣ እና የሽማግሌዎች ቡድን እና የሴቶች መረዳጃ ማህበር አመራሮችም በእግዚአብሔር የተጠሩ ናቸው። ወንጌሉን መማር እና መኖር እንድትችሉ ሊረዷችሁ ይችላሉ። ስለእነዚህ ጥሪዎች “በቤተክርስቲያን ጥሪዎች ውስጥ ማገልገል” በሚለው በመጋቢት 2022 (እ.አ.አ) የወንጌል መሰረታዊ ነገሮች ፅሁፍ ውስጥ መማር ትችላላችሁ።