2022 (እ.አ.አ)
አትዘግዩ! እንደ እረኞቹ ሁኑ
ታህሳስ 2022 (እ.አ.አ)


አትዘግዩ! “እንደእረኞቹ ሁኑ፣” ለወጣቶች ጥንካሬ፣ ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)

ወርሀዊ የ ለወጣቶች ጥንካሬ መልዕክት፣ ታህሳስ 2022 (እ.አ.አ)

ሉቃስ 2፥8–20

አትዘግዩ! እንደ እረኞቹ ሁኑ

እረኞች

ከረጅም ጊዜ በፊት አንድ ፀጥ ባለ ምሽት እረኞች መንጎቻቸውን በትጋት ይጠብቁ ነበር።

በግ

እረኞቹ አንድ ጠቃሚ ስራ ነበራቸው። በጎቹ ምግብ ውሃ እና ከአደጋ ጥበቃ ያስፈልጋቸው ነበር።

መልአክ

በድንገትም አንድ መልአክም ተገለጠ።

“እነሆ፥ ታላቅ ደስታ የምስራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፥ … ዛሬ …መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”

መልአክ

መልአኩ፣ ህፃኑ በጨርቅ ተጠቅልሎ በቤተልሔም በግርግም ተኝቶ እንደሚያገኙት ለእረኞቹ ነገራቸው።

የመላዕክት ዝማሬ

የመላዕክት ዝማሬ ሰማዩን በመሙላት ከመልአኩ ጋር እግዚአብሔርን አመሰገኑ።

“ክብር ለእግዚአብሄር በዓርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ።”

እረኞች

“እንግዲህ እስከ ቤተልሔም ድረስ እንሂድ እግዚአብሔር የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ።“

እረኞች ኮከብ እየተከተሉ።

እረኞቹ አልዘገዩም። ይህ በጣም አስፈላጊ ነበር። ወደቤተልሄም “ፈጥነው መጡ።“

እረኞች በግርግም።

ልክ መልአኩ እንዳለው እረኞቹ ኢየሱስ በጨርቅ ተጠቅልሎ በግርግም ተኝቶ አገኙት።

ህጻኑ ኢየሱስ

አዳኝ እና የአለም ቤዛ ለመሆን የመጣው እንዲሁም እውነተኛ ደስታን ሊያመጣልን ተስፋ የተጣለበት መሲህ ይህ ነበር!

እረኞች

እረኞቹ በጣም ተደስተው ነበር! ሰምተው እና አይተው የነበሩትን አጋሩ።

“የአለም አዳኝ ተወለደ!“

“በመጨረሻ መሲሑ መጣ!“

ወጣት ሰው ቅዱሳት መጻህፍትን ሲያነብ

እረኞቹ ወደ ኢየሱስ “ፈጥነው መጡ።“ እናንተም ትችላላችሁ!

ከእርሱ መማር ትችላላችሁ።

ወጣት ወንድ ሳር እያጨደ

ሌሎችን በማገልገል እርሱን ማገልገል ትችላላችሁ።

ወጣት ሴት መፅሐፈ ሞርሞንን ለወጣት ወንድ እያካፈለች።

ስለእርሱ መመስከር ትችላላችሁ።