2014 (እ.አ.አ)
ስራውን ማፍጠን
ጁን 2014


የቀዳሚ አመራር መልእክት፣ ሰኔ 2014 (እ.ዓ.ዓ)

ስራውን ማፍጠን

ምስል
ፕሬዘደንት ቶማስ ኤስ. ሞንሰን

በዳግም የተመለሰችው ቤተክርስቲያን 100 ካስማዎች ከመኖሯት በፊት 98 አመቷ እንደነበር ታውቃላችሁ? ነገር ግን ከ30 አመት በኋላ፣ ቤተክርስቲያኗ ሁለተኛውን 100 ካስማዎች አደራጀች። እናም ከዚያ ከስምንት አመት በኋላ ቤተክርስቲያኗ ከ300 በላይ ካስማዎች ነበሯት። ዛሬ ከ3 ሺህ በላይ የሆኑ ካስማዎች አሉን።

ይህ እድገት ለምን በፍጥነት እየሄደ ነው? እኛ በደንብ እየታወቅን ስለሆነ ነውን? አስደሳች የማምለኪያ ህንፃዎች ስላለን ነውን?

እነዚህ ነገሮች አስፈላጊ ናቸው፣ ነገር ግን ቤተክርስቲያኗ ዛሬ የምታድግበት ምክንያት ጌታ እንደሚሆን ስላመለከተ ነው። በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ውስጥ፣ እንዲህ አለ፣“እ ነሆ፣ ስራዬን በራሱ ጊዜ እንዲፈጥን አደርጋለሁ”1

እኛ፣ እንደ ሰማይ አባታችን መንፈስ ልጆች፣ በዚህ ጊዜ ወደ ምድር የተላክነው ይህን ታላቅ ስራ ለማፍጠን እንድንሳተፍ ነው።

ባለኝ እውቀት ውስጥ፣ ጌታ ስራው በስጋዊ ህይወት ብቻ እንደሚወሰን አመልክቶም አያውቅም። ግን፣ ስራው ዘለአለምን የሚያቅፍ ነው። ስራውን በመንፈስ አለም እያፈጠነ እንደሆነ እምነት አለኝ። ጌታ በዚያ በሚገኙ አገልጋዮቹ በኩል መንፈሶች ወንጌል እንዲቀበሉ እያዘጋጀ እንደሆነም አምናለሁ። ስራችንም ሙታኖቻችንን እንድንፈልግ እናም ወደ ቤተመቅደስ እንድንሄድና ከመጋረጃው አልፈው የሄዱትን እኛ ያለንን አይነት እድል የሚያመጣላቸውን ቅዱስ ስርዓቶች እንድናከናውን ነው።

ፕሬዘደንት ብሪገም ያንግ (1801–1877) እንዳሉት፣ በመንፈስ አለም ያሉ መልካም የኋለኛው ቀን ቅዱሳንም በስራ ተጠምደዋል። “በዚያ ምን እያደረጉ ነው? እነርሱም እየሰበኩ፣ በሁሉም ሰዓት እየሰበኩ፣ እናም እዚህ እና በሌሎች ቦታዎችም ቤተመቅደስ የምንገነባበትን ስራዎቻችን የምናፈጥንበትን መንገዶችን እያዘጋጁ ናቸው።”2

አሁን፣ የቤተሰብ ታሪክ ስራ ቀላል አይደለም። ለእናንተ ከስካንዴኔቪያ ለመጣችሁት፣ ብስጭታችሁን እጋራለው። ለምሳሌ፣ ከስዊድን ከመጡት ዘሮቼ፣ የአያቴ ስም ኔልስ ሞንሰን ነበር፤ የእርሱ አባት ስም ሞንሰን ሳይሆን ሞንስ ኦክሰን ነበር። የሞንስ አባት ስም ኦክ ፔደርሰን ነበር፣ እናም የእርሱ አባት ስምም ፒተር ሞንሰን ነበር—እንደገናው ወደ ሞንሰን ይመለሳል።

ጌታ እኔ እና እናንተ የቤተሰብ ታሪካችንን በደንብ እንድናከናውን ይጠብቃል። ስራችንን በደንብ ለማከናወን መጀመሪያ ማድረግ የሚያስፈልገን የሰማይ አባታችን መንፈስ ከእኛ ጋር እንዲሆን ማድረግ እንደሆነ ይሰማኛል። በጽድቅ ለመኖር እንደምናውቀው ስንኖር፣ በቅንነት እና በትጋት የምንፈልጋቸውን በረከቶች ለማሟላት መንገዶች ይከፍትልናል።

ስህተቶች እንሰራለን፣ ነገር ግን ማንኛችንም በመጀመሪያ ጀማሪ ሳንሆን በቤተሰብ ታሪክ ስራ ባለሙያ ለመሆን አንችልም። ስለዚህ፣ ወደዚህ ስራ በመዝለል መጀመር አለብን፣ እናም ከባድ ነገሮችን ለማከናወንም መዘጋጀት ይገባናል። ይህም ቀላል ስራ አይደለም፣ ነገር ግን ጌታ ይህን በእናንተ ላይ አሳርፏል፣ እናም በእኔም ላይ ይህን አሳርፏል።

የቤተሰብ ታሪክ ስራን ስታከናውኑ፣ የሚያሰናክል ያጋጥማችኋል፣ እናም ለእራሳችሁም “ሌላ ማድረግ የምችለው ነገር የለም” ትላላችሁ። እዛ ቦታ ላይ ስትደርሱም፣ ተንበርከኩ እናም ጌታ መንገድን እንዲከፍትላችሁ ጠይቁ፣ እናም መንገድን ይከፍትላችኋል። ይህም እውነት እንደሆነ እመሰክራለሁ።

የሰማይ አባት ልክ እኔንና እናንተን እንደሚወደን ያህል በመንፈስ አለም ያሉትን ልጆቹን ይወዳል። የሞቱብንን የማዳን ስራ በተመለከተ፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዳሉት፣ “እናም አሁን የእግዚአብሔር ታላቅ አላማዎች ወደ ሚከናወኑበት ደረጃ ሲፈጥኑ፣ እና ነቢያት የተናገሩት ሲሟሉ፣ የእግዚአብሔር መንግስት በምድር ላይ ስትመሰረት፣ እና የጥንት ነገሮች ስርዓት በዳግም ሲመለሱ፣ ጌታ ይህን መጋቢነት እና እድል ለእኛ ገልጿል።”3

ስለወንጌሉ ሳያውቁ ስለሞቱት ቅድመ አያቶቻችን በሚመለከትም፣ ፕሬዘደንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ (1838–1918) እንዳወጁት፣ “ለእነርሱ በምናደርገው ጥረት በኩል የታሰሩበት ሰንሰለቶች ይወድቃሉ፣ እናም ብርሀን እንዲበራባቸው እና በመንፈስ አለም በልጆቻቸው ለእነርሱ የተከናወነውን ስራ እንዲሰሙ፣ የከበባቸው ጭለማም ይበተናል፣ እናም ከእናንተ ጋር ሀላፊነቶቻችሁን ባከናወናችሁት ይደሰታሉ።”4

ከመሞታቸው እና ወደ መንፈስ አለም ከመሄዳቸው በፊት የክርስቶን ስም ሰምተው የማያውቁ በብዙ ሚልዮን ቁጥር የሆኑ የሰማይ አባት የመንፈስ ልጆች አሉ። ነገር ግን ወንጌሉን ተምረዋል እናም ወደ ጌታ ቤት ለመሄድ እና እነርሱ ለማከናወን የማይችሉትን ስራ ለእነርሱ ለማከናወን እንድንችል የሚያደርግ መንገድን ለማጽዳት የሚያስፈልገውን ጥናት እናንተ እና እኔ የምናደርግበትን ቀን እየጠበቁ ናቸው።

ወንድሞቼና እህቶቼ፣ ስራውን ስንቀበል እና መልስ ስንሰጥ ጌታ እንደሚባርከን እመሰክራለሁ።

ከዚህ መልእክት ማስተማር

ከቤተሰባችሁ ታሪክ ውስጥ የምትወዱትን ታሪክ አስቡ እና ይህን ታሪክ ከምትጎበኟቸው ጋር አካፍሉ። የምትጎበኟቸው ን ሰዎች ታሪኮቻቸውን እንዲካፈሉ ለማበረታታት በቀዳሚ አመራር መልእክት በልጆች ክፍል (ገጽ 6) ውስጥ ያሉትን ጥያቈዎች ለመጠቀም ትፈልጉ ይሆናል። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 128፥15ን ለማንበብ እና የቤተመቅደስ ስርዓቶችን በቅድመ አያቶቻችን ስም የማከናወን አስፈላጊነት ላይ ለመወያየት አስቡበት።

ማስታወሻዎች

  • ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥73

  • Teachings of Presidents of the Church: Brigham Young, [1997 (እ.አ.አ)]፣ 208።

  • Teachings of Presidents of the Church: Joseph Smith, [2007 (እ.አ.አ)]፣ 409።

  • የቤተክርስትያኗ ፕሬዘደንቶች ትምህርቶች፧ ጆሴፍ ኤፍ ስሚዝ, 1998 (እ.አ.አ)፣247።