2014 (እ.አ.አ)
የኢየሱስ ክርሰቶስ መለኮታዊ ተልዕኮ፥ አዳኝ እና ቤዛ
ኤፕረል 2014


የሴቶች የቤት ለቤት ማስተማሪያ መልእክት፣ ሚያዝያ 2014 (እ.አ.አ)

የኢየሱስ ክርሰቶስ መለኮታዊ ተልዕኮ፥ አዳኝ እና ቤዛ

በጸሎት መንፈስ ይህንን መረጃ አንብቡት እና ምን እንደምታካፍሉ ለማወቅ ጣሩ። የአዳኝንን ህይወት እና ተልእኮ መረዳት በእርሱ ያላችሁን እምነት የሚያሳድገው እና በሴቶች የቤት ለቤት ትምህርት ምክንያት የምትንከባከቧቸውን የሚባርከው እንዴት ነው? ለተጨማሪ መረጃ፣ ወደ www.reliefsociety.lds.org ሂዱ

እምነት • ቤተሰብ • እርዳታ

ሽማግሌ ዲ ታድ ክርስቶፈርሰን የአስራሁለቱ ሐዋርያት ቡድን አባል የሆኑት፣ “በጣም ትርጉም ካዘለው የኢየሱስ ክርስቶስ ገላጭ መአረጎች መሃከል አዳኝ የሚለው ነው፣” አሉ። “ማዳን ማለት ግዴታን ወይም እዳን ከፍሎ መጨረስ ማለት ነው። ማዳን መታደግ ወይም ማስለቀቂያ በመክፈል ነፃ ማውጣት ማለትም ሊሆን ይችላል። … እያንዳንዶቹ እነዚህ ትርጉሞች የሚያመለክቱት በመዝገበ ቃላቶች ውስጥ የሚያካትተውን ‘ለሃጥያተኛው መስዋዕትነትን በማድረግ በኩል፣ ከሃጢያት እና ከቅጣቶቹ አርነት ማውጣት’ የሚለውን በኢየሱስ ክርሰቶስ የሃጢያት ክፍያ የተከናወነው የታላቁ ቤዛነት የተለያዩ አካሎች ነው።”1

ሊንዳ ኬ በርተን፣ የሴቶች መረዳጃ ማህበር አጠቃላይ ፕሬዘደንት፣ እንዲህ ብለዋል፥ “የሰማይ አባት… አንድያ እና ፍፁም ወንድ ልጁን ለሃጢያቶቻችን፣ ለልብ ህመሞቻች እና ለሁሉም ተገቢ ያልሆኑ ለሚመስሉ በራሳችን የግል ሕወቶቻችን ውስጥ ላሉ ነገሮች እንዲሰቃይልን ላከው።

“… ለአመታት በመከራ እና በሀዘን ውስጥ ያሳለፈች አንድ ሴት እያነባች እንዲህ አለች፣ ‘እኔ እንደ አሮጌ የባለ 20 ዶላር ገንዘብ—የተጨማደድኩ፣ የተቀደድኩ፣ የቆሸሽኩ፣ የተንገላታው እና ጠባሳ ያለብኝ እንደሆንኩ እየተገነዘብኩ መጣው። ነገር ግን… አሁንም ቢሆን የሙሉ 20 ዶላሮች ጥቅም አለኝ።’ ይቺ ሴት [እግዚአብሔር] ልጁን ለእርሷ በተናጠል ቤዛ እንዲሆንላት መላክ እንዲችል ለእርሱ ዋጋ እንዳላት ታውቃለች። እያንዳንዷ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለች እህት ይቺ ሴት የምታውቀውን ማወቅ አለባት።”2

ከቅዱሳት መጽሐህፍት

2 ኔፊ 2፥6ሔለማን 5፥11–12ሙሴ 1፥39

ከታሪካችን

አዲስ ኪዳን እምነታቸውን በኢየሱስ ክርስቶስ የተለማመዱ፣ ትምህርቶቹን የተማሩና የኖሩ፣ እና አገልግሎቱን፣ ታምራቶቹን እና ግርማውን የመሰከሩ ሴቶችን መዝገብ ያካትታል።

ኢየሱስ በጉድጓዱ አጠገብ ላለችው ሴት እንዲህ አለ፥

“እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል።

“ሴቲቷ ጌታ ሆይ እዳልጠማ ይህንን ውኃ ስጠኝ አለችው። …

“[መሲሁ] እንደሚመጣ አውቃለው፣…፥ ሲመጣ፣ ሁሉንም ነገሮች ይነገግረናል።

“ኢየሱስም እኔ የማዋራሽ እሱ ነኝ አላት።”

እሷ “ከዛም የውኃ ማሰሮዋን ተወች” እና ስለ እርሱ በከተማው ውስጥ ምስክርነቷን ሰጠች። ዮሀንስ 4፥6–30 ተመልከቱ።

ማስታወሻዎች

  1. ዲ. ታድ ክሪስቶፈርሰን፣ “Redemption፣” Ensign ወይም Liahona፣ ግንቦት 2013፣ 109።

  2. ሊንዳ ኬ. በርተን፣ “Is Faith in the Atonement of Jesus Christ Written in Our Hearts?” Ensign ወይም Liahona፣ ህዳር 2012፣ 114።

ምን ማድረግ እችላለሁ?

  1. ለአዳኙ እና ለቤዛው ኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋናን እንዴት ማሳየት እንችላለን?

  2. የአዳኛችንን የሃጢያት ክፍያ በረከቶች በህይወታችን ውስጥ እንዴት አድርገን መካፈል እንችላለን?