አጠቃላይ ጉባኤ
ለእግዚአብሄር እና ለስራዎቹ ያደራችሁ ሁኑ
የጥቅምት 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


ለእግዚአብሄር እና ለስራዎቹ ያደራችሁ ሁኑ

ሁላችንም የኢየሱስ ክርስቶስን ምስክርነት መፈለግ፣ ለስሜቶቻችን ልጓም ማበጀት፣ ለሃጢያቶቻችን ንስሃ መግባት እንዲሁም ለእግዚአብሄር እና ለሰራው ማደር አለብን።

ባለፈው ጥቅምት እኔ፣ ፕሬዚዳንት ኤም. ሩሰል ባላርድ እና ሽማግሌ ጄፍሪ አር. ሆላንድ ሦስታችንም ወጣት ሚስዮናውያን ሆነን ያገለገልንበትን ዩናይትድ ኪንግደምን ከእነርሱ ጋር አብሬ እንድንጎበኝ ተመድቤ ነበር። የማስተማር እና የመመስከር እንዲሁም ቅምቅማቴ ሄበር ሲ. ኪምባል እና ጓደኞቹ የመጀመሪያዎቹ ሚስዮናውያን በነበሩበት በብሪቲሽ ደሴቶች የጥንት የቤተክርስቲያኗን ታሪክ የማስታወስ እድል ነበረን።1

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን ስለዚህ የስራ ስምሪት በማሾፍ በወጣትነታቸው ሚስዮናውያን ሆነው ያገለገሉበትን ቦታ እንዲጎበኙ ሦስት ሐዋርያትን ማሰማራት ያልተለመደ መሆኑን ጠቁመዋል። የመጀመሪያ ሚስዮናቸውን ለመጎብኘት ለመመደብ ሁሉም ፍላጎት እንዳላቸው አምነዋል። በፊቱ ላይ በትልቅ ፈገግታ ተሞልቶ ከ60 ከሚበልጡ ዓመታት በፊት በዚሁ ሚስዮን ያገለገሉ ሌላ የሦስት ሐዋርያት ስብስብ ካለ እነሱም እንዲሁ ተመሳሳይ የስራ ስምሪት ሊያገኙ እንደሚችሉ በአጭሩ ገለፀ።

ምስል
ሂበር ሲ ኪምባል

ለዚያ ስምሪት ስዘጋጅ፣ በኋላ በሃዋርያነት እንዲያገለግል በተጠራው በልጅ ልጃቸው በኦርሰን ኤፍ. ዊትኒ የተጻፈውን የሂበርሲ. ኪምባል ሕይወት የተሰኘውን መጽሃፍ በድጋሚ አነበብኩት። ይህ ጥራዝ የተሰጠኝ ወደ ሰባት ዓመት ገደማ ሲሆነኝ ከውድ እናቴ ነበር። ሃምሌ 24 ቀን 1974 (እ.አ.አ) ፕሬዚዳንት ጆርጅ አልበርት ስሚዝ በሚያደርጉት የThis Is the Place Monument ሃውልት የምረቃ ስነስርዓት ላይ ለመገኘት እየተዘጋጀን ነበር።2 በዘር ሐረጌ ውስጥ ስለሆኑት ስለሄበር ሲ.ኪምባል የበለጠ እንዳውቅ ፈለገች።

ይህ መጽሐፍ በፕሬዚዳንት ኪምባል የተሰጠ ለዘመናችን የሚሆን ትልቅ ትርጉም ያለውን ጥልቅ ንግግር ይዟል። ንግግሩን ከማጋራቴ በፊት ታሪካዊ ዳራውን በጥቂቱ ልቅርብ።

ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በሊበርቲ እስር ቤት በታሰረበት ጊዜ ሐዋርያ ብሪገም ያንግ እና ሐዋርያ ሄበር ሲ ኪምባል በአስፈሪ አሉታዊ ሁኔታ ውስጥ ቅዱሳንን ከሚዙሪ የማስወጣቱን ስራ የመቆጣጠር ሃላፊነት ነበረባቸው። ከዚያ በብዛት መውጣት ያስፈለገው በአገረ ገዥው ሊልበርን ደብሊው. ቦግስ በተሰጠው የማጥፋት ትእዛዝ ምክንያት ነበር።3

ከ30 ዓመታት ገደማ በኋላ፣ በወቅቱ የቀዳሚ አመራር አባል የነበሩት ሄበር ሲ. ኪምባል ይህንን ታሪክ አሰላስለው ለአዲሱ ትውልድ እንዲህ አስተምረዋል፦“አብዛኞቻችሁ ልትጋፈጡት የምትችሉትን ችግር፣ ፈተና እና ስደት የሚገጥማችሁን ጊዜ እንዲሁም ለእግዚአብሄር እና ለስራው ያደራችሁመሆናችሁን ለማሳየት ብዙ እድሎችን እንደምታዩ ልንገራችሁ።”4

ሄበር ይቀጥላሉ፦“እየመጡ ያሉትን ችግሮች ለመቋቋም የዚህን ስራ እውነትነት በግላችሁ ማወቃችሁ አስፈላጊ ይሆናል። ችግሮቹ እንደዚህ አይነት ባህርይ ይኖራቸዋል፤ ይኸውም የግል እውቀት ወይም ምስክርነት የሌለው ወንድ ወይም ሴት ይሰናከላል። ምስክርነቱ ከሌላችሁ በትክክል ኑሩ፣ ጌታን ጥሩ እንዲሁም እስክታገኙት ድረስ አታቁሙ። ይህን ከላደረጋችሁ አትጸኑም። ማንም ወንድ ሆነ ሴት በብድር ብርሃን መፅናት የማይችሉበት ጊዜ ይመጣል። እያንዳንዱ በውስጡ ባለው ብርሃን ሊመራ ይገባል። እርሱ ከሌላችሁ አትጸኑም፤ ስለዚህ ስለኢየሱስ ምስክርነትን ፈልጉ እንዲሁም የፈተና ጊዜ ሲመጣ እንዳትሰናከሉ እና እንዳትወድቁ ከእርሱ ጋር ተጣበቁ።5

እያንዳንዳችን ስለእግዚአብሔር ሥራ6 እንዲሁም ስለኢየሱስ ክርስቶስ የተጽዕኖ ፈጣሪነት ሚና የግል ምስክርነት ያስፈልገናል። ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 76ኛ ክፍል ሶስቱን የክብር ደረጃዎች ይጠቅሳል እንዲሁም የሲለስቲያል መንግስትን ከጸሃይ ጋር ያነጻጽራል። ከዚያም የቲሬስትሪያል መንግሥትን ከጨረቃ ጋር ያወዳድራል።7

ፀሐይ የራሷ ብርሃን ሲኖራት ጨረቃ ያላት ግን የተንጸባረቀ ወይም “የብድር ብርሃን” መሆኑ የሚስብ ነው። ቁጥር 79 ስለቲሬስትሪያል መንግሥት ሲናገር “እነዚህም በኢየሱስ ምስክርነት ደፋር ያልሆኑት ናቸው“ ሲል ይገልጻል። በብድር ብርሃን የሲለስቲያል መንግሥትን በማግኘት ከእግዚአብሔር አብ ጋር መኖር አንችልም፤ ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለወንጌሉ የግል ምስክርነት ያስፈልገናል።

የምንኖረው ኃጢአት በበዛበት8 እና በሰዎች ደንብ ምክንያት ልቦች ከእግዚአብሔር በራቁበት ዓለም ውስጥ ነው።9 ሂበርሲ. ኪምባልን ያሳሰባቸው የእግዚአብሔርን ስራ እና የኢየሱስ ክርስቶስን ምስክርነት ስለመፈለግ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ካሉት በጣም አሳማኝ ከሆኑት ምሳሌዎች ውስጥ አንዱ አልማ ለሶስቱ ልጆቹ—ለሄለማን፣ ለሺብሎን እና ለቆሪአንተን በሰጠው ምክር ላይ ተቀምጧል።10 ሁለቱ ልጆቹ ለእግዚአብሔር እና ለስራው ያደሩነበሩ። ሆኖም አንደኛው ልጅ መጥፎ ውሳኔዎችን አድርጎ ነበር። ለእኔ የአልማ ምክር ትልቁ አስፈላጊነት እንደአባት ለገዛ ልጆቹ ጥቅም የሰጠው መሆኑ ነው።

እንደ ሄበር ሲ.ኪምባል አልማን በመጀመሪያ ያሳሰበው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ያላቸው ስለመሆኑ እና ለእግዚአብሔር እና ለስራው ያደሩ የመሆናቸውጉዳይ ነበር።

አልማ ለልጁ ሔለማን ባስተማረው አስደናቂ ትምህርት “እምነታቸውን በእግዚአብሔር ላይ ያደረጉ ሁሉ፣ በፈተናቸው፣ እናም በችግራቸው፣ እናም በስቃያቸው እንደሚደገፉ፣ እናም በመጨረሻው ቀን ከፍ እንደሚደረጉ” ታላቅ ተስፋ ሰጥቷል።11

አልማ መልአክ ያየበትን መገለጥ ተቀብሎ ነበር፤ ይህም ብዙ ጊዜ የሚከሰት አልነበረም። ከመንፈስ ቅዱስ የሚገኙ ግንዛቤዎች ይበልጥ የተለመዱ ናቸው። እነዚህ ግንዛቤዎች እንደመላዕክት መገለጥ በእኩል ደረጃ ሊጠቅሙ ይችላሉ። ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ፊልዲንግ ስሚዝ እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል፦“ከመንፈስ ቅዱስ ለነፍስ የሚመጡ ግንዛቤዎች ከራእይ የበለጠ ጉልህ ናቸው። መንፈስ ለመንፈስ በሚናገርበት ጊዜ በነፍስ ላይ የሚተወውን አሻራ ማጥፋት በጣም ከባድ ነው።12

ይህ አልማ ለሁለተኛው ልጁ ለሺብሎን ወደሰጠው ምክር ይመራናል። ሺብሎን እንደወንድሙ ሄለማን ጻድቅ ነበር። ላተኩርበት የፈለኩት ጥቅስ አልማ 38፥12ሲሆን በከፊል እንዲህ ይነበባል፣ “እናም ደግሞ በፍቅር ትሞላ ዘንድ ስሜትህን በሙሉ ተቆጣጠር።“

መቆጣጠር የሚስብ ቃል ነው። ፈረስ በምንጋልብበት ጊዜ ልጓሙን ለመምራት እንጠቀምበታለን። መምራት፣ መቆጣጠር ወይም መገደብ ጥሩ ተመሳሳይ ቃላት ሊሆኑ ይችላሉ። ሥጋዊ አካል እንደሚኖረን በተማርን ጊዜ በደስታ እንደጮህን ብሉይ ኪዳን ይነግረናል።13 አካል ክፉ አይደለም—ቆንጆ እና አስፈላጊ ነው—ሆኖም አንዳንድ ስሜቶች በአግባቡ ጥቅም ላይ ካልዋሉ እና በተገቢ ሁኔታ ቁጥጥር ካልተደረገባቸው ከእግዚአብሄር እና ከስራው ሊለዩን እንዲሁም በምስክርነታችን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።

ስለሁለት ስሜቶች እንነጋገር፤ በተለይ—በመጀመሪያ ስለቁጣ ከዚያም ሁለተኛ ስለምኞት።14 የሚገርመው ነገር ሁለቱም ልጓም ካልተደረገባቸው ወይም ቁጥጥር ካልተደረገባቸው ታላቅ የልብ ስብራት ሊያስከትሉ፣ የመንፈስን ተፅእኖ ሊቀንሱ እንዲሁም ከእግዚአብሔር እና ከስራው ሊለዩን ይችላሉ። ጠላት ህይወታችንን በአመጽ እና ሥነ-ምግባር በጎደላቸው ነገሮች ምስሎች ለመሙላት ሁሉንም አጋጣሚዎች ይጠቀማል።

በአንዳንድ ቤተሰቦች ዘንድ የተናደደ ባል ወይም የተናደደች ሚስት የትዳር አጋርን ወይም ልጅን መምታት እንግዳ ነገር አይደለም። በሃምሌ ወር ለንደን ውስጥ በተካሄደ የዩናይትድ ኪንግደም የሁሉም ፓርቲዎች የፓርላማ ፎረም ላይ ተሳትፌ ነበር።15 በሴቶች እና ወጣቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እንደትልቅ ዓለም ዓቀፍ ችግር ጎልቶ ታይቶ ነበር። ከአካላዊ ጥቃት በተጨማሪ ሌሎች በቃላት ስድብ ተሳትፈዋል። የቤተሰብ አዋጁ “በትዳር አጋር ወይም በልጆች ላይ የቃላት ስድብ የሚያደርሱ በእግዚአብሄር ፊት ተጠያቂዎች እንደሚሆኑ” ይነግረናል።16

ፕሬዘደንት ኔልሰን በትናልትና ጠዋት ይህን በጥብቅ ትኩረት ሰጥተውታል።17 ወላጆቻችሁ ጥቃት አድርሰውባችሁ የነበረ ቢሆንም ባይሆንም እባካችሁ በትዳር ጓደኛችሁ ወይም በልጆቻችሁ ላይ አካላዊ ወይም የቃላት ወይም ስሜታዊ ጥቃት ላለማድረስ ወስኑ።

በዘመናችን እጅግ በጣም አስቸጋሪ ከሆኑት ነገሮች አንዱ ከማህበራዊ ጉዳዮች ጋር የተያያዘ ክርክር እና የቃላት ስድብ ነው። በብዙ ሁኔታዎች ቁጣ እና የስድብ ቃላት ምክንያታዊነትን፣ ውይይትን እና ጨዋነትን ተክተዋል። ብዙዎች ራስን እንደ መግዛት፣ እንደ ትዕግሥት፣ እንደ ፈሪሃ እግዚአብሔር፣ እንደ የወንድማማች ደግነት እንዲሁም እንደ ልግስና ያሉትን የክርስቶስ መሰል ባሕርያት እንዲፈልጉ ከአዳኙ ከፍተኛ ሐዋርያ ከጴጥሮስ የተሰጠውን ማሳሰቢያ ትተዋል።18 በተጨማሪም የክርስቶስ መሰል የትህትና ባህርይንም ትተዋል።

ንዴትን ከመቆጣጠር እና ለሌሎች ስሜቶች ልጓም ከማበጀት በተጨማሪ አስተሳሰባችንን፣ አንደበታችንን እና ድርጊቶቻችንን በመቆጣጠር በስነምግባር የታነጸ ንጹህ ህይወት መምራት ያስፈልገናል። የብልግና ምስሎችን ማስወገድ፣ በቤታችን ውስጥ የምናሰራጨውን ነገር ተገቢነት መገምገም እንዲሁም ከማንኛውም ዓይነት የኃጢአት ድርጊቶች መራቅ ያስፈልገናል።

ይህ አልማ ለልጁ ለቆሪአንተን ወደሰጠው ምክር ያመጣናል። ከወንድሞቹ ከሄለማን እና ከሺብሎን በተለየ መልኩ ቆሪያንተን ሥነ ምግባራዊ መተላለፍ ፈጽሟል።

ቆሪያንቶን በሥነ ምግባር ብልግና ስለተሳተፈ አልማ ስለንስሐ ሊያስተምረው ያስፈልግ ነበር። ስለኃጢአት ከባድነት እንዲሁም እንዴት ንስሐ እንደሚገባ እሱን ማስተማር ነበረበት።19

ስለዚህ የአልማ የቅድመ ጥንቃቄ ምክር ስሜትን መቆጣጠር ሲሆን መተላለፍን ለፈጸሙት ግን የእርሱ ምክር ንስሃ መግባት ነበር። ፕሬዚዳንት ኔልሰን በ2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ስለንስሃ ለአባላት ጥልቅ ምክር ሰጥተዋል። የእለት ተእለት ንስሃ ለተሟላ ህይወታችን አስፈላጊ መሆኑን ግልፅ አድርገዋል። “ንስሃ አንድ ጊዜ የሚደረግ ክስተት ሳይሆን ሂደት ነው። ለደስታ እና ለአእምሮ ሰላም ዋናው ቁልፍ ነው” ሲሉ አስተምረዋል። “በየቀኑ የሚደረግ ንስሃ የንጽህና መንገድ ነው ንጽህናም ሃይልን ያስገኛል፡፡”20 ቆርያንተን ፕሬዚዳንት ኔልሰን የሰጡትን ምክር ተግባራዊ አድርጎ ቢሆን ኖሮ ንፅህና የጎደላቸው ሀሳቦችን በአዕምሮው ማመላለስ እንደጀመረ ንስሃ ይገባ ነበር። ዋና ዋና መተላለፎች አይከሰቱም ነበር።

አልማ ለወንድ ልጆቹ የሰጠው የማጠቃለያ ምክር በሁሉም ቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ካሉት በጣም አስፈላጊ ትምህርቶች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው። በኢየሱስ ክርስቶስ ከተደረገው የኃጢያት ክፍያ ጋር ይዛመዳል።

ክርስቶስ ሃጢያትን እንደሚያስወግድ አልማ መስክሯል። 21 ያለአዳኙ የሃጢያት ክፍያ የፍትህ ዘላለማዊ መርህ ቅጣትን የግድ ይላል።22 በአዳኙ የሃጢያት ክፍያ ምክንያት ንስሐ ለገቡ ሰዎች ምሕረት ሊደረግላቸው ይችላል፤ እንዲሁም ወደ እግዚአብሄር ፊት ለመመለስ ሊፈቅድላቸዋል ይችላል። በዚህ አስደናቂ ትምህርት ላይ ብናሰላስል መልካም ይሆናል፡፡

ማንም ሰው በራሱ ወይም በራሷ መልካም ሥራዎች ብቻ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ አይችልም ወይም አትችልም፤ ሁላችንም የአዳኙን መስዋዕት መጠቀም ይኖርብናል። ሁሉም ሀጢያት ሰርተዋል እናም ይቅርታን ማግኘት እንዲሁም ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር የምንችለው በኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ አማካኘነት ብቻ ነው።23

በተጨማሪም አልማ ኃጢአቶቹ ትንሽም ሆኑ በቆሪያንተን የተፈፀመውን ያህል ከባድ ቢሆኑ በንስሐ ሂደት ውስጥ ላለፍን ወይም ለምናልፍ ሁሉ የሚሆን አስደናቂ ምክር ለቆሪያንተን ሰጥቷል። አልማ 42 ቁጥር 29 እንዲህ ይነበባል፤ “እናም አሁን ልጄ፣ እነዚህ ነገሮች ከእንግዲህ እንዳያስቸግሩህ እፈልጋለሁ፤ እናም ኃጢያትህ ብቻ በዚያ ወደ ንስሃ በሚያመጣህ ጭንቀት ያስጨንቅህ።“

ቆሪያንተን የአልማን ምክር ሰማ እናም ሁለቱም ንስሐ ገቡ በክብርም አገለገሉ። በአዳኙ የሃጢያት ክፍያ ምክንያት ሁሉም ፈውስ ያገኛል።

በአልማ ዘመን፣ በሄበር ዘመን፣ እና በእርግጠኝነት በእኛ ዘመን ሁላችንም የኢየሱስ ክርስቶስን ምስክርነት መፈለግ፣ ለስሜቶቻችን ልጓም ማበጀት፣ ለሃጢያቶቻችን ንስሃ መግባት እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ አማካኝነት ሰላም ማግኘት እንዲሁም ለእግዚአብሄር እና ለሰራው ማደር አለብን።

ፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን በቅርቡ ባደረጉት ንግግር እና በድጋሜ ዛሬ ጠዋት በዚህ መንገድ አስቀምጠውታል፦ “የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነታችሁን ኃላፊነት እንድትወስዱበት እማጸናችኋለሁ። እሱን ለማግኘት ስሩ። የራሳችሁ አድርጉት። ተንከባከቡት። ያድግ ዘንድ መግቡት። ከዚያም በህይወታችሁ ውስጥ ተአምራት እንዲፈጸሙ ጠብቁ።24

አሁን ፕሬዚዳንት ኔልሰን ሲናገሩ ስለምንሰማ አመስጋኝ ነኝ። ፕሬዘደንት ኔልስን የዘመናችን የጌታ ነቢይ መሆናቸውን እመሰክራለሁ። በእርሱ በኩል የምንቀበለውን አስደናቂ ማነሳሻ እና መመሪያ እወደዋለሁ እንዲሁም ውድ አድርጌ እይዘዋለሁ።

እንደጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያነቴ፣ የአዳኙን አምላክነት እና የኃጢያት ክፍያውን እውነታ ትክክለኛ ምስክርነቴን እሰጣለሁ፤በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ሮናልድኬ. ኤስፕሊን፣ “A Great Work Done in That Land፣” ኢንሳይን, ሐምሌ 1987፣ 20 “ሰኔ 13 ሽማግሌ ኪምባል፣ ኦርሰን ሃይድ፣ ጆሴፍ ፊልዲንግ እና የሄበር ጓደኛ የነበረው ዊላርድ ሪቻርድስ ከከርትላንድ ወደ እንግሊዝ ሄዱ። ሰኔ 22፣ ካናዳውያን የሆኑት አይዛክ ራሰል፣ ጆን ጉድሰን እና ጆን ስናይደር ኒውዮርክ ላይ ተቀላቀሏቸው። ከዚያም ሰባቱ ሚስዮናውያን በጋሪክወደሊቨርፑል አቀኑ።” (See Heber C. Kimball papers, 1837–1866; Willard Richards journals and papers, 1821–1854, Church History Library, Salt Lake City.)

  2. በምስራቃዊ ሶልት ሌክ ሲቲ ዩታ ኢሚግሬሽን ካንየን ጫፍ የሚገኘው የ This Is the Place Monument የመታሰቢያ ሃውልት ቅዱሳን ሃምሌ 24 ቀን 1847(እ.አ.አ)ወደ ሶልት ሌክ ሸለቆ የመጡበትን 100ኛ አመት ያስታውሳል። የመታሰቢያ ሐውልቱ የብሪገም ያንግን፣ የሄበር ሲ ኪምቦልን እና የዊልፎርድ ውድሩፍን ምስሎች ያሳያል።

  3. ከ8,000 እስከ 10,000 የሚሆኑ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን በ1839 (እ.አ.አ) መጀመሪያ ላይ ሥልጣን ከሌላቸው ህግ አሰከባሪዎች/ከቪጂላንቴዎች/ እና ከመንጋ ፍርድ ለማምለጥ ከሚዙሪ ሸሹ። በብሪገም ያንግ እና በሄበር ሲ. ኪምባል አመራር ስር አቅርቦቶችን ለመሰብሰብ፣ ፍላጎቶችን ለመገምገም እና ለአድካሚው የ200 ማይል (320 ኪሎ ሜትር) የክረምት የኢሊኖይ ስደት መንገዶችን ለማዘጋጀት ኮሚቴ ተቋቋመ። የኩዊንሲ ከተማ አዛኝ ነዋሪዎች መጠለያ እና ምግብ በማቅረብ እየተሰቃዩ ለነበሩት ቅዱሳን ጊዜያዊ መሸሸጊያ አቅርበዋል። ቅዱሳን፤ የኋለኛው ቀን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ታሪክ፣ ቅጽ 1፣ የእውነት መስፈርት 1815–1846 [2018 (እ.አ.አ)]፣ 375–77፤ ዊሊያም ጂ. ሃርትሊ፣ “The Saints’ Forced Exodus from Missouri፣ in Richard Neitzel Holzapfel and Kent P. Jackson, eds.” በ Joseph Smith, the Prophet and Seer (2010), 347–90.ውስጥ ይመልከቱ።

  4. ኦርሰን ኤፍ. ዊትኒ Life of Heber C. Kimball: An Apostle, the Father and Founder of the British Mission (1945)(እ.አ.አ)፣ 449 አትኩሮት ተጨምሮበታል።

  5. Life of Heber C. Kimball፣ በኦርሰን ኤፍ ዊትኒ፣ 450

  6. ሙሴ1:39 በተጨማሪም “The Work of Salvation and Exaltation፣” ክፍል 1.2አጠቃላይ መመሪያ መጽሃፍ-በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ማገልገል፣ ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ። የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በመኖር፣ የተቸገሩትን በመንከባከብ፣ ሁሉም ወንጌልን እንዲቀበሉ በመጋበዝ እና ቤተሰቦችን ለዘለአለም አንድ በማድረግ ወደ ክርስቶስ እንመጣለን እንዲሁም በእግዚአብሔር ስራ እንረዳለን። በተጨማሪም ለደህንነት ሥራ የተሰጡትን ቁልፎች የሚገልጸውን ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110ይመልከቱ።

  7. በተጨማሪም 1 ቆሮንቶስ 15:40–41ይመልከቱ።

  8. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥27ይመልከቱ።

  9. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥29ይመልከቱ።

  10. አልማ የነቢዩ አልማ ልጅ ነበር። የሕዝቡ ዋና ዳኛ፣ ሊቀ ካህን እና ነቢይ ነበር። በወጣትነቱ ተአምራዊ ለውጥ አድርጓል።

  11. አልማ 36፥3

  12. ጆሴፍ ፊልዲንግ ስሚዝ፣ “The First Presidency and the Council of the Twelve,” Improvement Era፣ ህዳር 1966(እ.አ.አ) 979።

  13. ኢዮብ 38፥7ይመልከቱ።

  14. አልማ 39፥9ይመልከቱ። አልማ “በዓይንህ ምኞት እንዳትጓዝ፡” ሲል ቆሪአንተንን አስተምሮታል።

  15. የሁሉም ፓርቲ ፓርላማ ቡድን፣ የፓርላማ ስብሰባ፣ ማክሰኞ ሃምሌ 5 ቀን፣ 2022(እ.አ.አ)፣ “Preventing Violence and Promoting Freedom of Belief።”

  16. ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ አዋጅ” ChurchofJesusChrist.org፤ በተጨማሪም ፓትሪክ ኪረን፣ “He Is Risen with Healing in His Wings: We Can Be More Than Conquerors,” ሊያሆና፣ግንቦት 2022 (እ.አ.አ)፣ 37–39 ይመልከቱ።

  17. ራስል ኤ. ኔልሰን፣ “እውነት ምንድን ነው፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2022 (እ.አ.አ)፣ 29።

  18. 2 ጴጥሮስ 1፥5–10 ይመልከቱ።

  19. አልማ 39፥9 ይመልከቱ።

  20. ራስል ኤም ኔልሰን “We Can Do Better and Be Better፣” ኢንሳይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 67፣68።

  21. አልማ 39፥15 ይመልከቱ።

  22. አልማ 42፥16 ይመልከቱ።

  23. 2 ኔፊ 25፥23 ይመልከቱ።

  24. ረስልኤም. ኔልሰን፣ ፌስቡክ፣ ነሐሴ 1፣ 2022 (እ.አ.አ)፣ facebook.com/russell.m.nelson፤ ትዊተር፣ ነሐሴ 1፣ 2022, twitter.com/nelsonrussellm; Instagram, ነሐሴ 1፣ 2022 (እ.አ.አ)፣ instagram.com/russellmnelson፤ “Choices for Eternity” (worldwide devotional for young adults፣ ግንቦት 15፣ 2022 እ.አ.አ)፣ broadcasts.ChurchofJesusChrist.org ይመልከቱ።