አጠቃላይ ጉባኤ
ከእግዚአብሄር ጋር የሚገቡ ቃል ኪዳኖች፣ ያጠነክራሉ፣ ይጠብቃሉ እንዲሁም ለዘላለማዊ ክብር ያዘጋጁናል።
የሚያዝያ 2022 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


ከእግዚአብሄር ጋር የሚገቡ ቃልኪዳኖች፣ ያጠነክራሉ፣ ይጠብቃሉ እናም ለዘላለማዊ ክብር ያዘጋጁናል።

ቃልኪዳኖችን ለመግባት እና ለመጠበቅ ስንመርጥ በዚህ ህይወት ውስጥ የበለጠ ደስታ እንዲሁም በሚመጣው አለም በከበረ የዘላለም ህይወት እንባረካለን።

እህቶች፣ በአለም አቀፋዊ እህትማማችነት መሰባሰባችን እንዴት ያለ ደስታ ነው! ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን የምንገባ እና የምንጠብቅ ሴቶች እንደመሆናችን መጠን የዘመናችንን ተግዳሮቶች እንድንቋቋም እና ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት እንድንዘጋጅ የሚያግዙን መንፈሳዊ ትስስርን እንጋራለን። እንዲሁም እነዚያን ቃል ኪዳኖች መጠበቅ ሌሎችን ወደ አዳኙ መሳብ የምንችል ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች እንድንሆን ያስችለናል።

በዛች መቼም በማትረሳ ቀን በተመለሰችው የእሱ ቤተክርስቲያን አባል በመሆን የተጠመቁት የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በላያቸው ላይ ለመውሰድ፣ እርሱን ሁሌም ለማስታወስ፣ ትዛዛቱን ለመጠበቅ ፣ አና እስከመጨረሽው ለማገልገል ቃል ኪዳን ገብተዋለ። እነዚህን ነገሮች ስናደርግ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የማረጋገጫ ሥርዓት በኩል እግዚአብሔር ሐጢያታችንን ይቅር ለማለትና የመንፈስ ቅዱስን አብሮነት ሊሰጠን ቃል ገብቷል። እነዚህ በረከቶች ወደፊት መግፋታችንን ከቀጠልን እና እስከ መጨረሻው ከጸናን፣ ከእርሱ እና ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በሰለስቲያል መንግሥት እንድንኖር በሚያስችለን መንገድ ላይ ያስጀምሩናል። በዚያ ልዩ ቀን የገባውን/ችውን ቃልኪዳን ከጠበቀ/ች፣ሁሉም የተጠመቀ ሰው የእነዚህ አድሎች ተስፋ አለው።

በግላዊ ታማኝነት መሰረት፣ ተጨማሪ ቃልኪዳኖችን በቤተመቅደስ ውስጥ የሚያደርጉ ኃይለኛ ተስፋዎችን ይቀበላሉ። የእግዚአብሔርን ትዛዛት ለመታዘዝ፣ የኢየሱስ ክርቶስን ወንጌል ለመኖር፣ እና ጊዜያችንን እንዲሁም ችሎታችንን ለጌታ አገልግሎት ለመስጠት በክብር ቃል እንገባለን። በምላሹ፣ እግዚአብሔር በዚህ ሂወት ውስጥ ድንቅ በረከቶችን እና ወደ እሱ በመመለስ በድጋሚ ከሱ ጋር ለዘላለም የመኖርን እድል ተስፋ ይሰጠናል።1 በዚያ ሂደት ውስጥ፣ ከየአቅጣጫው በሚወረወሩብን ግራ የሚያጋቡ እና አሉታዊ ድምፆች ብዛት፣ በእውነት እና በስህተት፣ ትክክል በሆነው እና ትክክል ባልሆነው መካከል የመለየት ሀይል ተሰጥቶናል ወይም ተባርከናል። ምን የመሰለ ሐያል ስጦታ!

ለመጀመሪያ ጊዜ ወደቤተመቅደስ ለመሄድ ስዘጋጅ፣ እናቴ እና ልምድ ያካበቱ የሴቶች መረዳጃ ማህበር እህቶች፣ የሚያምሩ የሥርዓት ልብሶችን ጨምሮ የምፈልጋቸውን ዕቃዎች እንድመርጥ ረዱኝ። ግን የበለጠው ዝግጅት የጀመረው ምን መልበስ አንዳለብኝ ከማወቅ በፊት ነው። ብቁ እንደነበርኩኝ ለማወቅ ቃለ መጠይቅ ካደረጉልኝ በኋላ፣ ኤጲስ ቆጶሴ ስለምገባቸው ቃል ኪዳኖች አብራሩ። የእሱ ጥንቃቄ የተሞላበት ማብራሪያ ለማሰብ እና እነዚያን ቃል ኪዳኖች የመግባትን ሃላፊነት ለመቀበል እንድዘጋጅ እድል ሰጠኝ።

ቀኑ ሲደርስ፣ በምስጋና አና በሰላም ስሜት በእነዛ ቅዱስ ስርዓቶች ተካፈልኩኝ። በዚያ ቀን የገባኋቸውን ቃል ኪዳኖች ሙሉ አስፈላጊነት ባልረዳም አንኳ፣ በነዛ ቃልኪዳኖች በኩል ከእግዚሐብሔር ጋር የተሳሰርኩኝ አንደነበርኩ እና ቃል ኪዳኖቹን ከጠበኩኝ ልረዳቸው የማልችል በረከቶችን ቃል እንደተገባልኝ አውቅ ነበር ። በጌታ ቤት ከነበረኝ ከዚያ የመጀመሪያ ልምዴ ጀምሮ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የገባነውን ቃልኪዳን መጠበቅ ፣ በማይቀሩት መከራዎች ወቅት የሚያጠነክረንን፣ ከጠላት ተጽዕኖ የሚጠብቀንን፣ እንዲሁም ለወደፊት የዘላለማዊ ክብር ለሚያዘጋጀው ወደ አዳኙ ሀይል አንድንቀርብ አንደሚረዳን፣ በተደጋጋሚ ማረጋገጫን አግኝቻለሁ።

የህይወት ተሞክሮዎች ከሚያስቁ በጥልቅ እስከሚያሳዝኑ፣ ከዝቅታ እስከ ክብር ሊደርሱ ይችላሉ። እያንዳንዱ ልምድ ስለ አባታችን የማያልቅ ፍቅር እና በአዳኙ የጸጛ ስጦታ በኩል ለመለወጥ ስላለን አቅም እንድናውቅ ይረዳናል። በተሞክሮዎች አማካኝነት ስንማር፣ አነስተኛ የተሳሳተ ውሳኔ ብናደርግም ሆነ ትልቅ ውድቀት ቢገጥመን ቃልኪዳኖቻችንን መጠበቅ የአዳኙ ሀይል ንጹህ እንዲያደርገን ያስችላል። ወደ እሱ ከተመለስን በምንወድቅበት ጊዜ አዳኙ ሊያነሳን ቅርብ ነው።

ምስል
ከተራራ ቀልቁል በገመድ እየተንሸራተቱ መውረድ

ከፍ ባለ ገደል ላይ ጣቶቻቹህን በጠርዙ ላይ አድርጋችሁ፣ ጀርባችሁን ከታች ላለው ገደል ሰጥታችሁ ቆማችሁ ታውቃላችሁ? ተራራን በመውጣት ዘዴ፣ ምንም እንኳን በደህና ወደ ገደል ታችኛው ክፍል ሊያደርሷችሁ ከሚችሉ ጠንካራ ገመዶች እና መሳሪያዎች ስርዓት ጋር ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ የተያያዛችሁ እንደሆነ ብታውቁም፣ እዚያ ጠርዝ ላይ መቆም አሁንም የሚያስፈራ ነው። ከተራራው ወደኋላ መውረድ እና ከአንዱ ቦታ ወደሌላው ቦታ በአየር ላይ መሸጋገር ከማይንቀሳቀስ ነገር ጋር በታሰረው መንጠቆ ላይ መተማመንን ይጠይቃል። መውረድ በምትቀጥሉበት ወቅት ገመዱን ወጥሮ በሚይዘው ሰው ላይ መተማመንን ይጠይቃል። ምንም እንኳን መሳሪያዎቹ የአወራረዳችሁን የፍጥነት መጠን ለመቆጣጠር የተወሰነ ችሎታ ቢሰጣሁም፣ ጓደኛችሁ እንድትወድቁ የማይፈቅድ መሆኑን መተማመን አለባችሁ።

ምስል
ከተራራ ወደታች የመንሸራተቻ ገመድ መንጠቆ
ምስል
ወጣት ሴት በገመድ እየተንሸራተተች ከተራራ ወደታች ስትወርድ

ከጥቂት አመታት በፊት ከወጣት ሴቶች ጋር ተራራ ስወርድ በግልፅ አስታውሳለሁ። ለመውረድ ከምድቡ የመጀመሪያው ነበርኩኝ። ከተራራው ወደኋላ ስወርድ ሳላስበው ከቁጥጥር ውጪ ሆኜ ወደ ኋላ መውደቅ ጀመርኩኝ። ምስጋና ይግባውና፣ ገመዱ ተናወጠ እናም የፍጥነት አወራረዴ ቆመ። በረዥሙ ገደል ላይ ካለው ቋጠሮ ቋጥኝ ፊት በግማሽ መንገድ ስንጠለጠል፣ እታች ያለው ድንጋይ ላይ እንዳልወድቅ ይዞኝ የነበረው ነገር ወይም ሰው እንዳይለቀኝ እጸልይ ነበር።

በኋላ ላይ፣ መንጠቆው ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዳልተዘጋጀ ተረዳሁ እና ልክ ጠርዙን እንደወጣሁ እኔን የሚይዘኝ ሰው ጀርባው ላይ ተመቶ እና በፍጥነት ወደ ገደል ዳር ተወስዶ ነበር። እንደምንም ፈጥኖ እግሩን በአንዳንድ ቋጥኞች ላይ አጣመረ። በዚያ ቦታ ተረጋግቶ፣ እጅ በእጅ በገመዱ በትጋት ሊያወርደኝ ቻለ። ልመለከተው ባልችልም አንኳን ይበልጥ ወደ አደጋ እንዳልገባ በሙሉ አቅሙ እየሰራ እንደነበር አውቄ ነበር። ገመዱ ሊይዘኝ ካልቻለ ከተራራውረ ግርጌ ላይ ሆኖ እኔን ለመያዝ ዝግጁ የነበረ ሌላ ጓደኛ ነበር። አየቀረብኩኝ ስመጣ፣ መታጠቂያዬን ያዘና የቀረውን መንገድ ወደ መሬት አወረደኝ።

እንደ መልህቅ እና ፍፁም አጋራችን ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር፣ በፈተና ጊዜ ፍቅራዊ ጥንካሬው እንዲሁም በመጨረሻ በእርሱ በኩል መዳን እንደሚገኝ እርግጠኞች ነን። ፕሬዘደንት ኤም. ራስል ባላርድ፣ እንዳስተማሩት፡ “በእግዚአብሔር እና በልጁ ላይ ያለ እምነት፣ ጌታ ኢየሱስ በህይወታችን በማህበራዊ ችግር እና በክፋት ጊዜ.አጥብቆ እንዲይዘን ሊኖረን የሚገባን መልህቅ ነው። እምነታችን… በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በህይወቱ እና በኃጢያት ክፍያው፣ እና በመጨረሻው ቀን… የተመለሰውን ወንጌሉን ያማከለ መሆን አለበት።2

በጠላት ድንጋዮች ላይ ከመውደቅ የሚጠብቁን መንፈሳዊ መሳሪያዎቻችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለን ምስክርነቶቻችን እና እንደ የጌታ ቤተክርስቲያን አባላት የምንገባቸው ቃል ኪዳኖች ናቸው። እኛን ለመምራት እና ወደ ደህንነት ለመውሰድ በእነዚህ ድጋፎች ላይ መተማመን እንችላለን። እንደ ፈቃደኛ አጋራችን፣ አዳኙ ከአቅማችን በላይ እንድንወድቅ አይፈቅድም። በስቃይ እና በሀዘን ጊዚያችን እንኳ እኛን ለማንሳት እና ለማበረታታት እዛ ይገኛል። በተጨማሪም የእሱ ኃይል ብዙ ጊዜ አሳዛኝ ተጽዕኖ ከሚያሰከትሉ ከሌሎች ሰዎች ምርጫዎች እንድናገግም ይረዳናል። ሆኖም እያንዳንዳችን ማሰሪያውን መልበስ እና ቋጠሮዎቹ በአስተማማኝ ሁኔታ መያዛቸውን ማረጋገጥ አለብን። በቃል ኪዳናችን ከእርሱ ጋር ለመተሳሰር ከአዳኙ ጋር ለመጣበቅ መምረጥ አለብን።3

ያንን መልህቅ እንዴት ማጠናከር እንችላለን? ፍላጎት ባለው እና በትሁት ልብ እንጸልያለን፣ ቅዱሳት መጻህፍትን እናጠናለን እንዲሁም እናሰላስላለን፣ እናም በየሳምንቱ በንስሃ እና በአክብሮት ቅዱስ ቁርባንን እንወስዳለን፣ ትእዛዛቱን ለመጠበቅ እንጥራለን እንዲሁም የነቢዩን ምክር እንከተላለን። እናም የበኩላችንን እንድናደርግ እንደተጠየቅነው የእለት ተእለት ተግባራችንን “ከፍ ባለ እና የተቀደሰ”4 መንገድ ስንፈጽም ከአዳኝ ጋር በይበልጥ የተገናኘን እንሆናለን፤ በተመሳሳይ ጊዜም ሌሎች ወደ እሱ እንዲመጡ እንረዳለን።

ያ “ከፍ ያለ እና የተቀደሰ መንገድ” ምን ይመስላል? ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት ሁሉ ወንጌልን ለመኖር እንሞክራለን። ቀለል ባሉ አገልግሎቶች በኩል በእውነት በማገልገል፣ ፍቅርን በመግለጽ፣ እርዳታ የሚያሻቸውን እንንከባከባለን። በሕይወታቸው ሰላም እና ብርታት ለሚፈልጉ እና “ወዴት እንደሚያገኙት ለማያውቁ” ወንጌልን እናካፍላለን።5 በመጋረጃው በሁለቱም በኩል ያሉትን፣ በጌታ የተመረጡትን ለመሰብሰብ እንሰራለን። ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳብራሩት፣ በጌታ ቤት ውስጥ ቃል ኪዳን ለገቡት፣ “እያንዳንዱ አዋቂ የቤተመቅደስ ተሳታፊ የክህነት ስልጣንን የተቀደሰ ልብስ ይለብሳል፣ ይህም… እያንዳንዳችን በቃል ኪዳኑ መንገድ ቀን በቀን፣ በተቀደሰ መንገድ” እንድንሄድ ያስታውሰናል” ።6 እነዚሕ ድርጊቶች አልፎ አልፎ የምናደርጋቸው ነገሮች አይደሉም ነገር ግን ለእለት ተእለት ደስታችን እና ለዘላለም ሐሴታችን ወሳኝ ናቸው።

ለዘላለማዊ እድገታችን ከእግዚአብሄር ጋር ያለንን ቃልኪዳኖች ከመጠበቅ የበለጠ አስፈላጊ የሆነ ነገር የለም። የተቀደሱ የቤተመቅደስ ቃልኪዳኖቻችን በተግባር ላይ ሲውሉ፣ ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር በሌላኛው የመጋረጃ በኩል የደስታ ስብስብ አንደሚኖረን ማመን እንችላለን። ይህንን ጊዜያዊ ህይወት ትቶ የሄደ ልጅ ወይም ወላጅ ወይም የትዳር አጋር በሙሉ ልቡ ወይም ልቧ አንድ ላይ ለዘላለም ለሚያጠምራችሁ ቃልኪዳን ታማኝ እንደምትሆኑ ተስፋ ያደርጋሉ። ከእግአብሄር ጋር የገባነውን ቃል ኪዳን ቦታ የማንሰጠው ወይም ቀለል አድርገን የምንመለከተው ከሆነ ዘላለማዊ ትስስሩን እደጋ ውስጥ እየጣልን ነው። አሁን ንሰሃ የመግባት፣ የተበሸውን የመጠገን አና እንዳዲስ የመጀመር ጊዜ ነው!

ለጊዜያዊ ምቾት ስንል የዘላለም ደስታ በረከቶችን የምንለውጥ ከሆነ ደስታ ጥቅም አልባ ነው። እድሜያችን ምንም ያህል ይሁን፣ ይህ ፍጹም እውነት ነው። ለዘላለም ደስታ ቁልፉ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንገል መኖርና የገባናቸውን ቃልኪዳኖች መጠበቅ ነው። ነቢያችን፣ ፕሬዘደንት ኔልሰን፣ “የእኛ የመጨረሻ ደህንነታችን እና ብቸኛው ዘላቂ ደስታችን የተመለሰውን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል፣ ቃል ኪዳኖቹን እና ስርዓቶቹን የያዘውን የብረት ዘንግ መያዝ ነው። 7ይህንን ስናደርግ የእግዚያብሄርን ሃይል ማግኘት ስለምንችል አስቸጋሪ በሆነ ባህር ውስጥ በጥንቃቄ ማለፍ እንችላለን።

አብዛኞቻችን አስቸጋሪ ባህር እያጋጠመን ነው። በመከራ ማዕበል ስንመታ እና አንዳንድ ጊዜ በእነዚያ ችግሮች ሳቢያ በሚመጡት የእንባ ጎርፎች እይታችን ሲጋረድ የህይወት ታንኳችንን በየትኛው አቅጣጫ እንደምንቀዝፍ ላናውቅ እንችላለን። ወደባህሩ ዳርቻ ለመድረስ የሚያስችል ጥንካሬ አለን ብለን ላናስብም እንችላለን። ማን አንደሆናችሁ ማስታወስ፣ የእግአብሄር ተወዳጅ ልጅ ናችሁ። በምድር ላይለምን እንዳላችሁ፣ እና ከእግዚአብሄር ጋር እና ከምትወዷቸው ጋር በሴሌስቲያል አለም ውስጥ ለመኖር ያላችሁ ግብ ራዕያችሁን ያጠራል እንዲሁም በትክክለኝው መንገድ ይመራችኋል። በማእበል መካከል አንኳን መንገዱን የሚያሳየን ደማቅ የሆነ ብርሃን አለ። “እኔ በጨለማ የማበራ ብርሀን ነኝ”8 ሲል ተናግሯል ኢየሱስ ክርስቶስ።. ወደ እሱ ብርሃን ስንመለከት እና የቃልኪዳኖቻችንን ታማኝነት ስንጠብቅ ደህንነትን አንደምናገኝ ማረጋገጫ አለን።

በአለም ዙሪያ ካሉ፣ ሰፋ ባሉ የተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ እየኖሩ ቃልኪዳናቸውን የሚጠብቁ ከሁሉም የእድሜ ክልል የተውጣጡ ሴቶችን መተዋወቅ ክብር ነበር። ከታዋቂው ሚዲያ ይልቅ በእያንዳንዱ ቀን ወደ ጌታ እና ወደ ነብዩ ለምሪት ይመለከታሉ። ከግላዊ ፈተናዎቻቸው እና ቃልኪዳናቸውን ከመጠበቅ ሊያስቀሯቸው ከሚችሉ ጉዳት የሚያመጡ የአለም አመለካከቶች ባሽገር እንኳ፣ ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር ወደ ዘላለማዊ ሂወት የሚመራቸው መንገድ ላይ ለመቆየት ቁርጠኛ ናቸው። “አብ ያለውን ሁሉ” 9ተብሎ በተሰጠው ተስፋ ይታመናሉ። እድሜያችሁ የቱንም ያህል ይሁን ከእግዚሐብሄር ጋር ቃልኪዳን የገባችሁ ሴቶች የጌታን ብርሃን ከፍ አድርጎ የመያዝ እና በምሳሌያቹ ሌሎችን ወደ እሱ የመምራት አቅም አላችሁ።10 ቃል ኪዳኖቻችሁን ስትጠብቁ በክህነት ስልጣን ሀይሉ ይባርካችኋል እናም ከሰዎች ጋር ሁሉ ግንኙነት ስታደርጉ መሰረታዊ የሆነ ተፅዕእኖ አንዲኖራችሁ ያደርጋል። ፕሬዝደንት ኔልሰን እንዳወጁት፣ አስቀድሞ የተገሩትን ትንቢቶች የምታሟሉ ሴቶች ናችሁ!11

ውድ እህቶች፣ ከሁሉም በላይ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚወስደው የቃል ኪዳን መንገድ ላይ ቆዩ። ቤተመቅደሶች አለምን በሞሉበት ዘመን ወደ ምድር በመምታጣችን ተባርከናል። የቤተመቅደስ ቃል ኪዳኖችን ማድረግ እና መጠበቅ ለእያንዳንዱ ብቁ የቤተክርስቲያን አባል ክፍት ነው። ወጣት አዋቂዎች፣ እነዚህን የተቀደሱ ቃልኪዳኖች ለመፈጸም እስክታገቡ ወይም ለሚስዮናዊ አገልግሎት እስክትሄዱ መጠበቅ አያስፈልጋችሁም። ከ18 አመት በኋላ ዝግጁ ስትሆኑ አና አነዛን የቤተመቅደስ ቃልኪዳኖች የመቀበል እና የማክበር ፍላጎት ሲኖራችሁ፣ እንደ ወጣት ሴቶች የቤተመቅደስ ቃልኪዳኖች የሚሰጡትን ጥበቃዎች እና ጥንካሬ ለመቀበል መዘጋጀት ትችላላችሁ።12 የቤተመቅደስ በረከትን ለተቀበላችሁ፣ አጥፊዎች ወይም ሃሳብ ሰራቂዎች ከዚህ ዘላለማዊ እውነታ ጎትተው እንዲወስዷችሁ አትፍቀዱ። ስለገባችሁት የተቀደሰ ቃልኪዳን ልዩነት እና በረከቶች ይበልጥ ለመረዳት ታማኝ የሆኑ ምንጮችን አጥኑ። የተቻላችሁን ያህል ጊዜ ወደ ቤተመቅደስ ሂዱ እና መንፈስ ቅዱስን አዳምጡ። በጌታ መንገድ ላይ እንደሆናችሁ ጣፋጭ ማረጋገጫ ይሰጣችኋል። የመቀጠልን ድፍረት ታገኛላችሁ እንዲሁም ሌሎችን ከእናንተ ጋር ታመጣላችሁ።

ከሰማይ አባታችን ጋር ቃልኪዳኖችን ለመግባት ስንመርጥ እና የአዳኙን ሀይል ስንጠቀም በዚህ ህይወት ውስጥ ልናስበው ከምንችለው በላይ ይበልጥ ደስታ እና በሚመጣው አለም የከበረ የዘላለም ህይወት እንደምትባረኩ እመሰክራለው።13 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።