ምዕራፍ ፲፭
ጌታ ኔፋውያንን የሚገስጻቸው ስለሚወዳቸው ነው—የተለወጡ ላማናውያን በእምነታቸው ፅኑ እንዲሁም የማይነቃነቁ ናቸው—ጌታ በኋለኛው ቀናት ለላማናውያን መሃሪ ይሆናል። በ፮ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም እንግዲህ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ እነሆ፣ ንስሃ ካልገባችሁ ቤታችሁ ሀእንደሚወድምባችሁ እናገራለሁ።
፪ አዎን፣ ንስሃ ካልገባችሁ፣ ሴቶቻችሁ በሚያጠቡበት ቀን የሚያዝኑበት ታላቅ ምክንያት ይኖራቸዋል፤ ምክንያቱም ለመሸሽም ትሞክራላችሁ እናም የምትሰደዱበት ስፍራ አይኖራችሁም፤ አዎን፣ ሀለእርጉዞች ወዮላቸው፣ እነርሱም ከባድ ይሆናሉ እናም መሸሽም አይችሉምና፤ ስለዚህም ይረገጣሉ እናም እንዲጠፉም ወደኋላ ይቀራሉ።
፫ አዎን፣ የኔፊ ህዝብ ተብለው ለሚጠሩት እነዚህን ሁሉ ምልክቶች እናም አስደናቂ ነገሮች በሚመለከቱበት ጊዜ ንስሃ ካልገቡ ወዮላቸው፤ እነሆም፣ በጌታ የተመረጡ ህዝቦች የነበሩ ናቸውና፤ አዎን፣ የኔፊን ህዝብ ወዷቸዋል እናም ደግሞ ሀገስጿቸዋል፤ አዎን፣ ስለሚወዳቸው በክፋታቸው ዘመን ቀጥቷቸዋል።
፬ ነገር ግን እነሆ ወንድሞቼ ላማናውያን ስራቸው ያለማቋረጥ ክፉ ስለነበር ጠልቷቸው ነበር፣ እናም ይህም የሆነበት በአባቶቻቸው ሀወግ ክፋት የተነሳ ነበር። ነገር ግን እነሆ፣ ደህንነት ግን በኔፋውያን ስብከት የተነሳ መጥቶላቸዋል፤ እናም ለዚህም አላማ ጌታ ቀናቸውን ለአርዝሞላቸዋል።
፭ እናም ሀአብዛኞቹ ክፍሎች በተወሰነላቸው ጎዳና እንደሚንቀሳቀሱ ልብ እንድትሉ እፈልጋለሁ፣ በእግዚአብሔርም ፊት በጥንቃቄ ይራመዳሉ፤ እናም በሙሴ ህግ መሰረትም ትዕዛዛቱንና ህግጋቱን እንዲሁም ፍርዱን ያከብራሉ።
፮ አዎን፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ አብዛኞቹ ይህንን ያደርጋሉ፤ እናም የተቀሩት ወንድሞቻቸውን ወደ እውነት ያመጡ ዘንድም ያለማቋረጥ ትጋትን ያደርጋሉ፤ ስለሆነም በየቀኑም ቁጥራቸውን ከፍ የሚያደርጉ ብዙዎች አሉ።
፯ እናም እነሆ፣ እናንተ በእራሳችሁ እንደምታውቁት፣ ምስክር ሆናችሁበታልና፣ ብዙዎች ወደ እውነት እውቀት የመጡት፣ እናም ክፉውንና የረከሰውን የአባቶቻቸውን ወግ ያውቁትና፣ ቅዱሳት መጻሕፍትንም እንዲያምኑ፤ አዎን፣ እምነትና ንስሃም በልባቸው ሀለውጥን ስለሚያመጣላቸው ስለተፃፉት ወደ ጌታ እምነትና ወደ ንስሃው ወደሚመሩት የነቢያት ቅዱስ ትንቢቶችም የተመሩት ሁሉ—
፰ ስለዚህ፣ ይህንን እንደሚያውቁ የመጡ ሁሉ፣ በእምነታቸውና ነፃ በተደረጉበትም ነገር ሀፅኑ እናም የማይነቃነቁ መሆናቸውን በእራሳችሁ አውቃችኋል።
፱ እናም ደግሞ የጦር መሳሪያዎቻቸውን ሀእንደቀበሩና፣ በሆነ አጋጣሚ ኃጢያትን እንሰራለን ብለው በመፍራታቸውም መሣሪያዎቻቸውን ለማንሳት እንደሚፈሩ ታውቃላችሁ፤ አዎን፣ ኃጢያትን ለመስራት መፍራታቸውን ለመመልከት ትችላላችሁ—እነሆም፣ በጠላቶቻቸው እንዲረገጡና እንዲገደሉ ይፈቅዳሉ፣ ጎራዴዎቻቸውንም በእነርሱ ላይ አያነሱም፣ እናም ይህ የሆነበት በክርስቶስ ባላቸው እምነት ነው።
፲ እናም እንግዲህ፣ በሚያምኑበት በዚያ ነገር ሲያምኑ፣ የማያወላውሉ በመሆናቸው፣ ምክንያቱም አንዴ በተገለፀላቸው ጊዜ ፅኑ በመሆናቸውም፣ እነሆ ጌታ ይባርካቸዋል፣ እናም ኃጢአተኞች ቢሆኑም ዘመናቸውን ያረዝምላቸዋል—
፲፩ አዎን፣ እምነት አጥተው ቢመነምኑም፣ በአባቶቻችን እንዲሁም ደግሞ በነቢዩ ሀዜኖስ፣ እንዲሁም በሌሎች ብዙ ነቢያት ወንድሞቻችን ላማናውያን ድጋሚ እውነትን ወደማወቅ ለመመለስን በተመለከተ የተናገሩበት ቀን እስከሚመጣ ድረስ ጊዜ ቀኖቻቸውን ጌታ ሐያረዝመዋል—
፲፪ አዎን፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ በኋለኞቹ ጊዜያት የጌታ ሀቃል ኪዳን ለወንድሞቻችን ለላማናውያንም ይቀርባል፤ እናም ብዙ ስቃዮችም የሚመጡባቸው ቢሆንምና፣ በምድር ገፅ ላይም ለመጠለያቸው ሥፍራን ሳያገኙ ለወዲህና ወዲያ ቢሰደዱም፣ ቢታደኑም፣ ቢመቱም፣ እናም ከሀገር ውጪ ቢባረሩም፤ ጌታ ለእነርሱ ሐመሃሪ ይሆናል።
፲፫ እናም ይህም የሚሆነው ታላቁና እውነተኛው ሀእረኛ ወደሆነው ወደ አዳኛቸው እውቀት ወደሆነው እውነታዊ እውቀት ለእንደሚመጡ፣ እናም ከእርሱ በጎችም ጋር አብረው እንደሚቆጠሩ በተተነበየው መሰረት ነው።
፲፬ ስለዚህ እንዲህ እላችኋለሁ፣ ንስሃ ካልገባችሁ ከእናንተ ይልቅ ለእነርሱ ሀየተሻለ ይሆናል።
፲፭ እነሆም፣ ለእናንተ የታዩት ኃያል ስራዎች ለእነርሱ፣ አዎን፣ በአባቶቻቸው ወግ አማካይነት እምነት አጥተው ለመነመኑት፣ ሀየታዩ ቢሆን ኖሮ በድጋሚ እምነት በማጣት እንደማይመነምኑ እራሳችሁ ለመመልከት ትችላላችሁ።
፲፮ ስለዚህ፣ ጌታ እንዲህ አለ፥ ፈፅሞ አላጠፋቸውም፣ ነገር ግን በጥበብ ቀኔ ወደ እኔ እንዲመለሱ አደርጋቸዋለሁ፣ ይላል ጌታ።
፲፯ እናም እንግዲህ እነሆ፣ ጌታ ስለኔፋውያን እንዲህ ይላል፥ ንስሃ ካልገቡና፣ እንደፈቃዴም ካላደረጉ፣ ምንም እንኳን ብዙ አስደናቂ ስራዎች በመካከላቸው ብሰራም እምነት ስለሌላቸው ፈፅሞ ሀአጠፋቸዋለሁ፣ ይላል ጌታ፤ እናም በእውነት ጌታ ህያው እንደሆነ እነዚህም ነገሮች ይሆናሉ ይላል ጌታ።