ስርዓቶች እና አዋጆች
ቤተሰብ፧ ለአለም የተላለፈ አዋጅ


ቤተሰብ

ለአለም የተላለፈ አዋጅ

የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን ቀዳሚ አመራር እና አስራ ሑለት ሐዋሪያት ሸንጎ

እኛ፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን ቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁልቱ ሐዋርያት ሸንጎ፣ በእርጋታ በወንድ እና በሴት መካከል ያለ ጋብቻ የእግዚአብሔር ስርዓት እንደሆነ እና ቤተሰብም ፈጣሪው ለልጆቹ ላለው ዘላለማዊ እጣ አላማ ዋና ክፍል እንደሆነም እንገልጻለን።

የሰው ልጆች በሙሉ —ወንድና ሴቶች —በእግዚአብሔር አምሳል ነው የተፈጠሩት። እያንዳንዱም በሰማይ ወላጆች የተወደዱ የመንፈስ ሴት እና ወንድ ልጆች ናቸው፣ እናም ይህ ስለሆነም፣ እያንዳንዱ መለኮታዊ ተፈጥሮ እና ፍጻሜም አላቸው። ጾታም አስፈላጊ የሆነ የግለሰብ ቅድመ ምድራዊ፣ ሟች፣ እና ዘለአለማዊ መለያ እና አላማ እና ባህሪ ነው።

በቅድመ ምድራዊ ህይወት ውስጥ፣ የመንፈስ ወንድ እና ሴት ልጆች እግዚአብሔርን እንደ ዘላለማዊ አባታቸው ያውቁትም ያመልኩትም ነበር፣ እናም ልጆቹ ስጋዊ አካልን አግኝተው ምድራዊ አጋጣሚዎችን በማግኘት ወደ ፍጹምነት ለመሻሻል እና በመጨረሻም እርሱ ወይም እርሷ እንደ መለኮታዊ እጣቸው ዘላለማዊ ህይወትን ወራሽ እንዲሆኑ የሚያደርገውን አላማውን ተቀብለው ነበር። መለኮታዊው የደስታ እቅድ የቤትሰብ ግንኙነት ከመቃብር ባሻገር እንዲቀጥልም ያስችላል። በቅዱስ ቤተ መቅደሶች የሚገኙትም ቅዱስ ስነ ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖችም ግለሰቦች ወደ እግዚአብሔር ፊት ለመመለስ እና ቤተሰቦችም ለዘላለም እንዲጣመሩ ያስችላቸዋል።

እግዚአብሔር ለአዳም እና ለሔዋን የሰጠው የመጀመሪያው ትእዛዝ እንደባልና ሚስት ስላላቸው የወላጅነት አቅም ነበር። እግዚአብሔር ልጆቹን እንዲባዙ እና ምድርን እንዲሞሉ ዘንድ የሰጠው ትእዛዝ አሁንም ተግባራዊ ነው ብለን እናውጃለን። የተቀደሱት የመዋለድ ሀይሎች እንደ ባልና ሚስት በህግ በተጋቡት ወንዶች እና ሴቶች መካከል ብቻ መፈጸም እንዳለበትም እግዚአብሔር እንዳዘዘ ጨምረንም እናውጃለን።

ሟች ህይወትን የሚፈጠሩበት መንገድም በመለኮታዊ የተወሰኑ እንደሆኑም እንገልጻለን። የህይወትን ቅድስና እና በእግዚአብሔር ዘላለማዊ እቅድ ውስጥ ያለውን አስፈላጊነትንም እናረጋግጣለን።

ባል እና ሚስት እርስ በራሳቸው እና ከልጆቻቸው ጋር ለመፈቃቀር እና ለመንከባከብ ሀላፊነት አለባቸው። ‘ልጆች የጌታ ወራሽ ናቸው።’ (መዝሙር 127፧3) ወላጆች ልጆቻቸውን በፍቅር እና በጻድቅነት የማሳደግ፣ እናም የስጋዊ እና የመንፈሳዊ ፍላጎታቸውን የማሟላት፣ እርስ በራስ እንዲዋደዱ እና እንዲያገለግሉ፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንዲያከብሩ እና በሚኖሩበት ቦታ ህግ አክባሪ ዜጎች እንዲሆኑ የማስተማር ሀላፊነት አለባቸው። ባሎች እና ሚስቶችም፣ እንዲሁም እናቶች እና አባቶች፣ ለእነዚህ ሀላፊንቶች በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂዎች ይሆናሉ።

ቤተሰብ በእግዚአብሔር የተሰጠ ነው። በወንዶች እና ሴቶች መካከል ያለው ጋብቻም ለዘላለማዊ እቅድ ውስጥ በጣም አስፈላጊው ነው። ልጆችም በጋብቻ ጥምረቶች ውስጥ የመውለድ፣ እናም የጋብቻ ቃል ኪዳናቸውን በሙሉ ታማኝነት በሚያከብሩ አባት እና አናት የማደግ መብት አላቸው። በቤተሰብ ህይወት ውስጥ ደስታ የሚገኘው ቤተሰብ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት በኩል ሲገነባ ነው። የተሳኩ ጋብቻዎች እና ቤተሰቦች የሚመሰረቱት እና የሚጸኑት በእምነት፣ በጸሎት፣ ንስሀ በመግባት፣ በምህረት፣ በክብር፣ በፍቅር፣ በርህራሄ፣ በስራ፣ እና በመልካም መዝናኛ እንቅስቃሴዎች መሰረት በኩል ነው። በመለኮታዊ እቅድ፣ አባቶች በፍቅር እና በጻድቅነት ቤተሰቦቻቸውን ያስተዳድራሉ እና ለቤተሰቦቻቸው የህይወት መሰረታዊ ፍላጎት የማሟላት እና ጥበቃ ሀላፊነት አለባቸው። እናቶች በቀደምትነት ልጆቻቸውን የመንከባከብ ሀላፊነት አለባቸው። በእነዚህ ቅዱስ ሀላፊነቶችም፣ አባቶች እና እናቶች በእኩል አጋርነታቸው የመረዳዳት ሀላፊነት አለባቸው። በአካል ጉዳት፣ በሞት፣ ወይም በሌሎች ሁኔታዎች ምክንያትም እነዚህን ሀላፊነቶችን ማመጣጠን ያስፈልጋል። ለቅርብ ዘመዶችና ቤተሰቦችም አስፈላጊ ሲሆን እርዳታ መስጠት ይገባቸዋል።

የንፅህና ቃል ኪዳንን የሚሰብሩ፣ ባለቤቶቻቸውን ወይም ልጅቻቸውን የሚበድሉ፣ ወይም የቤተሰብ ሀላፊነታቸውን የማያከናውኑ ሁሉ አንድ ቀን በእግዚአብሔር ፊት በተጠያቂነት እንድሚቆሙም እናስጠነቅቃለን። በተጨማሪም፣ የቤተሰብ መፈራረስ በግለሰብ፣ በህብረተሰብ፣ እናም በአገሮች ላይ በጥንት እና በዘመኑ ቀድመው የተነገሩት ጥፋቶች እንደሚያመጡባቸውም እናስጠነቅቃለን።

በየትም ስፍራ ላሉት ሀላፊነት ላላቸው ዜጎች እና የመንግስት ባለስልጣኖች ቤተሰብ የማህብረሰብ ዋና መሰረታዊ ክፍል እንዲሆን እና እንዲጠናከር እርምጃዎች እንዲወስዱም ጥሪ እናቀርባለን።