ምዕራፍ ፭
ቅዱሳን በእምነታቸው የክርስቶስ ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ይሆናሉ—ከዚያም በክርስቶስ ስም ይጠራሉ—ንጉስ ቢንያም በመልካም ስራቸው እንዲፀኑ እናም የማይነቃነቁ እንዲሆኑ መከራቸው። በ፻፳፬ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም አሁን፣ እንዲህ ሆነ ንጉስ ቢንያም ለህዝቡ እንደዚህ በተናገረ ጊዜ፣ ለእነርሱ የተናገረውን አምነው እንደሆነ ከህዝቡ ለማወቅ በመፈለጉ በመካከላቸው ሰው ላከ።
፪ እናም ሁሉም በአንድ ድምፅ እንዲህ በማለት ጮኹ፥ አዎን፣ ለእኛ የተናገርካቸውን ቃላት በሙሉ እናምናለን፤ እናም ደግሞ ያለማቋረጥ መልካምን መስራት እንጂ ከእንግዲህ ሀኃጢያት ለመፈፀም ምንም ፍላጎት እንዳይኖረን ታላቅ ለለውጥ ለእኛ ወይንም በልባችን ውስጥ በሰራው ሁሉን በሚገዛው በጌታ መንፈስ አማካኝነት እርግጠኝነታቸውን እና እውነተኛነታቸውን አውቀናል።
፫ እናም እኛ፣ እራሳችን ደግሞ በማይወሰነው የእግዚአብሔር ቸርነትና፣ በመንፈሱ መገለጥ ስለሚመጣው ታላቅ አመለካከት አለን፤ እናም የሚያስፈልግ ቢሆን እንኳን፣ ስለ ሁሉም ነገሮች መተንበይ እንችላለን።
፬ እናም እጅግም ታላቅ በሆነ ደስታ ወደምንደሰትበት ወደዚህ ታላቅ እውቀት ያመጣን፣ የእኛ ንጉስ በተናገራቸው ነገሮች አንፃር ያለን እምነት ነው።
፭ እናም ከእግዚአብሔር ጋር ፈቃዱን ለማድረግ እናም በቀረው ጊዜአችን ሁሉ እኛን ባዘዘን በሁሉም ነገር ለትዕዛዛቱ ታዛዦች ለመሆን፣ መጨረሻ የሌለው ሀቅጣት በራሳችን ላይ እንዳናመጣ፣ ለበመልአኩ እንደተነገረው ከእግዚአብሔር የቁጣ ዋንጫ እንዳንጎነጭ ከአምላካችን ጋር ሐቃል ኪዳን ለመግባት ፈቃደኞች ነን።
፮ እናም አሁን፣ ንጉስ ቢንያም ከእነርሱ የፈለጋቸው ቃላት እነዚህ ናቸው፤ እናም ስለዚህ እንዲህ አላቸው፥ እናንተ እኔ የፈለኳቸውን ቃላት ተናግራችኋል፤ እናም የገባችሁት ቃል ኪዳን የጽድቅ ቃል ኪዳን ነው።
፯ እናም አሁን፣ በገባችሁት ቃል ኪዳን የተነሳ የክርስቶስ ሀልጆች፣ ወንዶችና ሴት ልጆቹ፣ ተብላችሁ ትጠራላችሁ፤ እነሆም በዚህ ቀን እናንተን በመንፈስ ለወልዷችኋል፤ ሐልባችሁ በስሙ በማመን ተለውጧል ብላችኋልና፤ ስለዚህ እናንተ ከእርሱ መተወልዳችኋል እናም የእርሱ ሠወንዶችና ሴቶች ልጆች ሆናችኋል።
፰ እናም በዚህ ራስ ስር ሀነፃ ተደርጋችኋል እናም በራሱ ነፃ መሆን የምትችሉበት ለሌላ ምንም የለም። ደህንነት ሊመጣበት የሚችል ሌላ ሐስም የለም፤ ስለዚህ የክርስቶስን ስም መእንድትወስዱ እፈልጋለሁ፣ ሁላችሁም ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን የገባችሁ እስከህይወታችሁ መጨረሻ ታዛዥ እንድትሆኑ እመኛለሁ።
፱ እናም እንዲህ ይሆናል፣ ማንም ይህንን ያደረገ በእግዚአብሔር ቀኝ ይገኛል፣ የሚታወቅበትን ስም ያውቃልና፤ በክርስቶስ ስም ይጠራልና።
፲ እናም አሁን እንዲህ ይሆናል፣ የክርስቶስን ስም ያልለበሰ ማንኛውም ሀበሌላ ስም መታወቅ አለበት፤ ስለዚህ፣ እራሱን በእግዚአብሔር ለግራ በኩል ያገኛል።
፲፩ እናም ይህን ደግሞ እንድታስታውሱ እፈልጋለሁ፣ በመተላለፍ ካልሆነ በቀር ለእናንተ መስጠት አለብኝ ያልኩት የማይደመሰሰው ሀስም ይህ ነው፤ ስለዚህ፣ ስሙም ከልባችሁ እንዳይጠፋ ዘንድ እንዳትተላለፉ አስተውሉ።
፲፪ በእግዚአብሔር ግራ እንዳትገኙ፣ ነገር ግን የምትጠሩበትን ድምፅ፣ እናም ደግሞ በእርሱ የምትጠሩበትን ስም እንድታዳምጡና እንድታውቁ፣ በልባችሁ የተፃፈውን ስም ሁልጊዜ ሀእንድትጠብቁ እፈልጋለሁ እላችኋለሁ።
፲፫ ያላገለገለውን አለቃ፣ እና ለእርሱ እንግዳ የሆነውን፣ ከልቡ ስሜትና ሀሳብ የራቀውን፣ አንድ ሰው እንዴት ሀያውቃል?
፲፬ እናም ሰው እንደገና የጎረቤቱ የሆነውን አህያ ወስዶ የእርሱ ያደርገዋልን? አያደርግም እላችኋለሁ፣ ከመንጋዎቹ ጋር እንኳን እንዲመገብ አይፈቅድም፣ ነገር ግን ያስወጣታል እናም ያሳድዳታል። እላችኋለሁ፣ የምትጠሩበትን ስም የማታውቁ ከሆነ በእናንተ መካከል እንኳን እንዲህ ይሆናል።
፲፭ ስለዚህ፣ ሁሉን የሚገዛ ጌታ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ትመጡ ዘንድ፣ ከሁሉም በላይ አምላክ የሆነው በሰማይና በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ ሀበፈጠረ፣ ጥበብ፣ ሀይል፣ እና ፍርድ፣ እንዲሁም በምህረቱ ዘለዓለማዊ ደህንነትና ዘለዓለማዊ ህይወት እንዲኖራችሁ የእርሱ እንድትሆኑ ለያትምላችሁ ዘንድ እናንተ ፅኑ እናም የማትነቃነቁ፣ ሁልጊዜም በመልካም ስራ የተሞላችሁ እንድትሆኑ እፈልጋለሁ። አሜን።