የወሲብ ድርጊቶችን የሚያሳይ ፎቶ ወይም ፊልም
ስለ ጤናማ ወሲባዊነት ለልጄ እንዴት መናገር እችላለሁ?


“ስለ ጤናማ ወሲባዊነት ለልጄ እንዴት መናገር እችላለሁ?” እርዳታ ለወላጆች [2021 (እ.አ.አ)]

“ስለ ጤናማ ወሲባዊነት ለልጄ እንዴት መናገር እችላለሁ?” እርዳታ ለወላጆች

ምስል
ቤተሰብ በውጪ ሲራመዱ

ስለ ጤናማ ወሲባዊነት ለልጄ እንዴት መናገር እችላለሁ?

ብዙ ወላጆች ስለ ወሲባዊነት ከልጆቻቸው ለመነጋገር ጥርጣሬ ወይም እፍረት ይሰማቸዋል፣ ወይም ስለ ወሲባዊነት ከልጆቻቸው ጋር ከተነጋገሩ የወሲብ ባህሪያቸውን ያስነሳል ብለው ይፈራሉ። እውነታው ግን፣ ስለ ወሲባዊነት ከልጆቻችሁ ጋር ካልተነጋገራችሁ፣ ስለ እሱ ነገር ከሌላ ምንጭ ይማራሉ። ከልጆቻችሁ ጋር እንደ ጤናማ ወሲባዊነት ቀጣይነት ያለው አስፈላጊ ርዕሶች ንግግር ስታደርጉ፣ እናንተ ለመቅረብ የምትቻሉ እንደሆናችሁ እንዲገነዘቡ ትረዷቸዋላችሁ።

ብዙ ልጆች በተፈጥሮ ለማወቅ ጉጉት ያድርባቸዋል፣ እና የሚለማመዱትን ተፈጥሮአዊ ከእግዚአብሔር የተሰጡ ስሜቶችን ለመረዳት ይፈልጋሉ። በእነርሱ እድሜ በነበራችሁ ወቅት እንዴት እንደነበራችሁ በማስታወስ ስለ ወሲባዊነት ከልጆቻችሁ ጋር ለመነጋገር እራሳችሁን ማዘጋጀት ትችላላችሁ። የተለማመዳችሁት የተወሰኑ ስሜቶች ምን ነበሩ? ምን አስተሳሰቦች፣ ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች ነበሯችሁ? መረጃን ከየት ነው የፈለጋችሁት? ምን ብትሰሙ ወይም ብትማሩ ትመርጡ ነበር?

እነዚህን ንግግሮች በጥሩ ሁኔታ ለማድረግ እርግጠኛ ካልሆናችሁ ምንም ችግር የለም። ተጋላጪነታችሁን በመጠቀም ከልጆቻችሁ ጋር ያላችሁን ግንኙነት መገንባት ትችላላችሁ። ምንም እንኳን አመቺ ባይሆንም ከእነሱ ጋር በመነጋገር ሃቀኛ እና ትሁት ስትሆኑ ልጆች ፍቅራችሁ ሊሰማቸው ይችላል።

ግልፅ ንግግሮችን ለማዳበር የሚከተሉትን ማድረግ ትችላላችሁ፦

  • ልጆቻችሁ ትንሽ ሆነው ሳሉ የሰውነት ክፍሎችን በትክክለኛው ስማቸው መጥራት ጀምሩ። ይህ ልጆችን ስለ ሰውነታቸው ያስተምራል እንዲሁም ጤናማ እና መረጃ ያገኙ እንዲሆኑ የሚረዳቸውን ትርጉም ይሰጣቸዋል።

  • ልጆቻችሁ ማንኛውንም ጥያቄዎች ሊጠይቋችሁ እንደሚችሉ አሳውቋቸው፣ ከዚያም ለጥያቄዎቻቸው ወይም ኑዛዜያቸው ላለበሳጨት ወይም ላለማሳፈር ሞክሩ። ከእናንተ ጋር ስለተነጋገሩ ደስ በመሰኘት ፍቅር እና እርዳታ አሳዩአቸው፣ እናም በተደጋጋሚ ለመነጋገር የተቻላችሁን አድርጉ።

  • ለወሲባዊነት ምሳሌዎችን መጠቀም አስወግዱ። ልጆች በግልፅ እና በሃቀኝነት የሚነገሩ መረጃን ይፈልጋሉ። ለምሳሌ፣ የተወሰኑ ወጣቶች የንፅህና ህግን መስበር ማለት የታኘከ ማስቲካን ወይም ምግብን በክፍል ውስጥ ከሰው ወደ ሰው ከማዘዋወር ጋር እንደሚነፃፀር እናም ስለሆነም ካሁን በኋላ እንደማይፈለግ የሚናገር ትምህርቶችን እንደተማሩ ይናገራሉ። ምንም እንኳን በጎ ለማድረግ የታሰበበት ቢሆንም፣ እነዚህ ዓይነት ምሳሌዎች ብዙውን ጊዜ የወሲባዊነት ፍርሃትን ወይም የማይስተካከል ዝቅ ያለ የራስ ክብር ስሜቶችን ሊጭሩ ይችላሉ።

  • የቤተሰብ ምሽት ትምህርቶችን ከወሲባዊነት ጋር የሚዛመዱ ርዕሶች ላይ አድርጉ እና ልጆቻችሁ ዝግጁ ሲሆኑ እንዲያስተምሩ ፍቀዱላቸው። ርዕሶቹ ጉርምስናን፣ የሰውነት ምስልን እና የወሲባዊነት አወንታዊ ገፅታዎችን ሊያካትቱ ይችላሉ።

  • የወሲባዊ ስሜቶች እና ወሲባዊ መነሳሳትን መሰማት የተለመደ እንደሆነ ተወያዩ። ልጆች በእነዛ ስሜቶች እና መነሳሳቶች ላይ ሊተገብሩ አይገባቸውም ነገር ግን ስለ እነሱ ማወቅ ይችላሉ። ይህ ማለት ወሲባዊነት ስሜቶችን መገንዘብ ነገር ግን በአሉንታዊ ሁኔታ እነሱ ላይ አለመፍረድ ማለት ነው። መጠንቀቅን መለማመድ ልጆች ከዋጋቸው እና ግባቸው ጋር የሚዛመዱ የተሻለ ምርጫዎችን እንዲያደርጉ መርዳት እንደሚችል ምርምር አሳይቷል።

  • ልጆች እራሳቸውን በመንካት ነገር ላይ ሲሳተፉ ወይም ወጣቶች እራሳቸውን እንዳረኩ ሲያምኑ በመጠየፍ ወይም በንዴት ለመመለስ አትሞክሩ። ወላጆች ለእነዚህ ባህሪዎች ምላሽ የሚሰጡበት መንገድ ልጆች እና ወጣቶች ስለራሳቸው እና ስለ ወሲባዊነታቸው የሚሰማቸው ስሜት ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል።

  • ከግንኙነቶች እና ወሲባዊነት አቋሞች በስተጀርባ ያለውን ምክንያት ለልጆቻችሁ አስተምሩ። እነዚህን አቋሞች እና ጠቃሚ የሆኑበትን ምክንያቶች ስታስተምሩ፣ ይህንንም እፍረትን ወይም ፍርሃትን ያለመጨመር ማድረጋችሁ ጠቃሚ እንደሆነ አስታውሱ።1

ማስታወሻ

  1. ነጥቦቹ የተጠቀሱት ከሎራ ኤም. ፓዲላ‑ዋከር እና ሜግ ኦ. ጃንኮቪች፣ “How, When, and Why: Talking to Your Children about Sexuality [እንዴት፣ መቼ እና ለምን፦ ስለ ወሲባዊነት ከልጆችዎ ጋር መነጋገር]፣” ሊያሆና፣ ነሐሴ 2020 (እ.አ.አ)።