“ሚያዝያ 25–ግንቦት 1 (እ.አ.አ)። ዘጸአት 24፤ 31–34፥ “እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፣’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]
“ሚያዝያ 25–ግንቦት 1 (እ.አ.አ)። ዘጸአት 24፤ 31–34፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2022 (እ.አ.አ)
ሚያዝያ 25–ግንቦት 1 (እ.አ.አ)
ዘጸአት 24፤ 31–34
“እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ”
በቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ትርጉማዊ መርሆች በእነዚህ ረቂቆች ውስጥ ለመጠቆም አይቻልም። የሚያስፈልጋችሁ እውነታዎች ላይ ለማተኮር መንፈስ ቅዱስን አዳምጡ።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
የእስራኤል ልጆች ህጉን ከገለጠላቸው በኋላ ለእግዚአብሔር ታማኝ ሆነው እንደሚኖሩ ተስፋ የሚሆንበት ምክንያት ነበር (ዘጸአት 20–23ን ይመልከቱ)። ምንም እንኳን ከዚህ በፊት ቢያጉረመርሙም እና ቢያንገራግሩም፣ በሲና ተራራ ስር ሙሴ ህጉን ሲያነብ፣ እነርሱ ይህንን ቃል ኪዳን ገቡ፥ “እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እናደርጋለን እንታዘዛለንም” (ዘጸአት 24፥7)። ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን ወደ ተራራው ጠራው፣ “በመካከላቸውም አድር ዘንድ” ብሎ መቅደስ እንዲሰራ ነገርው (ዘጸአት 25፥8፤ ምእራፎች 25–30 ይመልከቱ)።
ነገር ግን ሙሴ በተራራው አናት ላይ እያለ እስራኤላውያን በመካከላቸው የእግዚአብሔር መገኘት እንዲኖርባቸው ሲማር፣ እስራኤላውያን በምትኩ እንዲያመልኩ የወርቅ ጣዖት እየሠሩ በተራራው ታችኛው ክፍል ላይ ነበሩ። “ ሌሎች አማልክት” እንደማያመልኩ ቃል ገብተው ነበር፣ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ትእዛዛት “ፈጥነው ፈቀቅ አሉ” (ዘጸአት 20፥3፤ 32፥8፤ ደግሞም ዘጸአት 24፥3ን ይመልከቱ)። ይህ አስገራሚ ለውጥ ነበር፣ ግን እምነት እና ቁርጠኝነት አንዳንድ ጊዜ በትዕግስት ማጣት፣ በፍርሃት ወይም በጥርጣሬ ሊሸነፍ እንደሚችል ከልምድ አውቀናል። በሕይወታችን ውስጥ የጌታን መገኘት ስንፈልግ፣ ጌታ በጥንቷ እስራኤል ላይ ተስፋ እንዳልቆረጠ እና እኛንም ተስፋ እንደማይቆርጥብን ማወቁ የሚያበረታታ ነው—እርሱ “መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፣ ታጋሽም፣ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት” ነውና (ዘጸአት 34፥6)።
ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ቃል ኪዳኖቼ የእግዚአብሔርን ህግ ለማክበር ያለኝን ፍላጎት ያሳያሉ።
ዘጸአት 24፥3–8 እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ህግ ለመታዘዝ ቃል መግባታቸውን ስታነቡ፣ ሃሳባችሁ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ወደገባችሁት ቃል ኪዳኖች ሊዞር ይችላል። የእስራኤል ቃል ኪዳን እግዚአብሔር ዛሬ ከሚጠብቀው የተለዩ ሥነ ሥርዓቶችን አካትቶ ነበር፣ ነገር ግን በተለይም በእነዚህ ሥነ ሥርዓቶች የተወከሉ ዘለአለማዊ እውነቶችን ካሰባችሁ፣ አንዳንድ ተመሳሳይነቶችን ታስተውሉ ይሆናል።
ለምሳሌ፣ ቁጥሮች 4፣ 5፣ እና 8 መሰዊያን፣ የእንስሳት መስዋእትን፣ እና ደምን ይጠቁማሉ። እነዚህ ነገሮች የሚወክሉት ምንድን ነው፣ እና ከእናንተ ቃል ኪዳኖች ጋር እንዴት ይያያዛሉ? ቃል ኪዳኖቻችሁ እንዴት ነው “እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ” እንድታደርጉ የሚረዷችሁ? (ቁጥር 7)።
በተጨማሪም ሙሴ 5፥4–9፤ ቤኪ ክሬቨን፣ “ጥንቃቄ ያለው ወይስ የሌለው፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 9–11 ይመልከቱ።
ኃጢያት ከእግዚአብሔር መዞር ነው፣ ነገር ግን እርሱ መመለሻ መንገዱን ያዘጋጃል።
እስራኤላዊያን እንዴት ቃል ኪዳኖቻቸውን በመስበር በፍጥነት “ፈቀቅ [እንዳሉ]” (ዘጸአት 32፥7) በማሰብ፣ ተመሳሳይ ስህተቶችን ማስወገድ እንችላለን። ዘጸአት 32፥1–8ን ስታነቡ፣ ራሳችሁን በእስራኤላውያን ቦታ ለማስቀመጥ ሞክሩ—በምድረ በዳ ናችሁ፣ ሙሴ ለ 40 ቀናት ሄዷል፣ መቼ እንደሚመለስ ወይም ይመለስ እንደሆነም አታውቁም፣ እና በተስፋው ምድር ላይ ከከነዓናውያን ጋር ውዝግቡ ከፊት ትጠብቃላችሁ (በተጨማሪም ዘጸአት 23፥22–31ን ይመልከቱ)። እስራኤላውያን ለምን የወርቅ ጣዖት የፈለጉ ይመስላችኋል? የእስራኤላዊያን ኃጢያት በጣም ከባድ የነበረው ለምንድን ነው? እነዚህ ጥቅሶች በአዳኝ ካልሆነ በቀር በሌላ ሰው ወይም በሌላ ነገር ላይ እምነት ለመጣል የምትፈተኑባቸውን መንገዶች ለማሰላሰል ሊረዷችሁ ይችላሉ። እግዚአብሔርን ይበልጥ ሙሉ ለሙሉ በህይወታችሁ ለማድረግ ምን ተነሳሽነት ይሰማችኋል? በዘጸአት 33፥11–17 ውስጥ ሙሴ ጌታን ስለተማጸነው ምን ተነሳሳሽነት ይሰማችኋል?
የእስራኤላውያን ኃጢአት ከባድ ቢሆንም፣ ይህ ታሪክ የእግዚአብሔር ምህረት እና ይቅር ባይነት መልእክትንም ያካትታል። ዘጸአት 34፥1–10 ስለአዳኝ ምን ያስተምራችኋል? እስራኤላውያንን ወክሎ ሙሴ ያደረገው ኢየሱስ ክርስቶስ ለህዝብ ሁሉ ስላደረገው ምን ያስታውሳችኋል? ( ዘጸአት 32፥30–32፤ ሞዛያ 14፥4–8፤ 15፥9፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥3–5ን ይመልከቱ)።
የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ዘጸአት 34፥1–2 (ከመፅሐፍ ቅዱስ መግለጫ ውስጥ)
ሙሴ ከሰራቸው ሁለት የድንጋይ ጽላቶች መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
ሙሴ ከተራራው ሲወርድ፣ በድንጋይ ጽላቶች ላይ የተጻፈውን ሕግ አመጣ። እስራኤላውያን ቃል ኪዳናቸውን እንደጣሱ ካወቀ በኋላ ሙሴ ጽላቶችን ሰባበረ (ዘጸአት 31፥18፤ 32፥19ን ይመልከቱ)። በኋላም፣ እግዚአብሔር ሙሴን ሌሎች የድንጋይ ጽላቶች ሠርቶ ወደ ተራራው እንዲወስዳቸው አዘዘው ( ዘጸአት 34፥1–4ን ይመልከቱ)። የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ዘጸአት 34፥1–2 (ከመፅሐፍ ቅዱስ መግለጫ ውስጥ) የመጀመሪያው የድንጋይ ጽላቶች የእግዚአብሔርን “የቅዱስ ትዕዛዝ” ወይም የመልከ ጼዴቅ ክህነትን ስርአቶች ያካተተ መሆኑን ያብራራል። ሁለተኛው ጽላቶች “የሥጋዊ ትእዛዝት ሕግ” ያካተቱ ነበሩ። ይህም እስራኤላውያንን ወደ እግዚአብሔር ፊት ይበልጥ በተሟላ ሁኔታ እንዲገቡ ለከፍተኛ ሕግ እና ለከፍተኛ ክህነት ለማዘጋጀት የታቀደ አነስተኛ ህግ ሆኖ በ“አነስተኛ ክህነት” የሚተዳደር ነበር (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥17–27)።
ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ዘጸአት 31፥12–13፣ 16–17።እነዚህን ጥቅሶች ካነበባችሁ በኋላ፣ ምናልባት ስለ ሰንበት ቀን ባህሪያችን ፕሬዝዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን “ፍቅራችሁን ለእርሱ ለማሳየት ምን ምልክቶችን ለጌታ ትሰጣላችሁ?” ብለው የጠየቁትን ጥያቄ ቤተሰቦቻችሁ ለመወያየት ይችላሉ። (“ሰንበት ደስታ ነው፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ.)፣ 130)። ቤተሰባችሁ በቤታችሁ ዙሪያ ምልክቶችን ሰርተው በማድረግ በሰንበት ቀን እንዴት ለጌታ ፍቅርን እንደምናሳይ ሊያስታውሷችሁ ይችላሉ። (ደግሞም እነዚህን የቪድዮ ስብስብ ይመልከቱ “Sabbath Day—At Home” [ChurchofJesusChrist.org]።)
-
ዘጸአት 32፥1–8።እስራኤላዊያን እንዴት ከእግዚአብሔር መንገድ እንደዞሩ በቤተሰባችሁ ለመወያየት እንዲረዳችሁ፣ በወለል ላይ የመንገድ መስመር ለመፍጠር አስቡበት (ወይም በቤታችሁ አቅራቢያ ይህን አግኙ)። የቤተሰቡ አባላት በመንገድ ላይ ሲጓዙ “[ጌታ] ካዘዘው መንገድ እንድንርቅ” ስለሚገጥሙን ፈተናዎች ማውራት ይችሉ ይሆናል። እንዴት በመንገዱ ልንቆይ እንችላለን? ብንጠፋ፣ እንዴት ወደ እርሱ ልንመለስ እንችላለን? አዳኝ የሚረዳን እንዴት ነው?
-
ዘፀአት 32፥26።እስራኤላውያን ጣዖትን ሲያመልኩ ከተገኙ በኋላ ሙሴ “ የእግዚአብሔር ወገን [ማን ነው?]” ሲል ጠየቀ። የእግዚአብሔር ወገን መሆናችንን እንዴት ነው የምናሳየው?
-
ዘጸአት 33፥14–15።እግዚአብሔር ለሙሴ “እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፥ አሳርፍህማለሁ” ሲል የገባውን ቃል ኪዳን እንደገባለት አይነት ስሜት ካላቸው ተሞክሮውን ሊያካፍሉ ይችላሉ። በእግዚአብሔር ላይ ስላለን ጥገኝነት መዝሙር ልትዘምሩ ትችላላችሁ፣ እንዲሁም “ከእኔ ጋር ሁን!” የሚለው አይነትን (መዝሙሮች፣ ቁጥር 166)።
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት ዝርዝር በኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ውስጥ ይመልከቱ።
በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፥ “የእግዚአብሔር ወገን ማን ነው?” መዝሙሮች፣ ቁጥር 260።