አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
መለወጥ ግባችን ነው


“መለወጥ ግባችን ነው፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“መለወጥ ግባችን ነው፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
ቅዱሳት መጻህፍትን የምታጠና ሴት

መለወጥ ግባችን ነው

ሁሉም የወንጌል መማርና ማስተማር አላማ በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ በጥልቅ እንድንለወጥ እና እነርሱን እንድንመስል እኛን መርዳት ነው። በዚህ ምክንያት፣ ወንጌልን በምናጠናበት ጊዜ፣ እኛ አዲስ መረጃን ብቻ የምንፈልግ አይደለንም፤ “አዲስ ፍጡር” ለመሆን እንፈልጋለን (2 ቆሮንቶስ 5፥17)። ይህም ልባችንን፣ አመለካከታችንን፣ ድርጊቶቻችንን፣ እና ተፈጥሮአችንን ለመለወጥ ይረዳ ዘንድ በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ መታመን ማለት ነው።

ነገር ግን እምነታችንን የሚያጠናክር እና ወደ ለውጥ ተዓምር የሚመራው አይነት የወንጌል ትምህርት በሙሉ በአንድ ጊዜ አይከሰትም። ከመማሪያ ክፍል በላይ ወደ ልባችን እና ቤታችን ይሰፋል። ወንጌልን መረዳት እና መኖር የማይቋረጥ የእለት ተለት ጥረትን ይጠይቃል። ወደ ትክክለኛ መለወጥ የሚመራ የወንጌል ትምህርት የመንፈስ ቅዱስን ተፅዕኖ ይፈልጋል።

መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት ይመራናል እናም ስለዚያ እውነት ይመሰክራል (ዮሐንስ 16፥13ን ይመልከቱ)። እርሱ አዕምሯችንን ያበራል፣ ግንዛቤያችንን ያፋጥናል እናም የእውነት ሁሉ ምንጭ በሆነው በእግዚአብሔር ራዕይ ልባችንን ይነካል። መንፈስ ቅዱስ ልባችንን ያነጻል። በእውነት የመኖር ፍላጎትን በውስጣችን ያነቃቃል፣ እንዲሁም ይህን የምናደርግባቸውን መንገዶች በጸጥታ ይነግረናል። በእውነትም፣ “መንፈስ ቅዱስ … ሁሉንም ያስተምረናል” (ዮሐንስ 14፥26)።

በእነዚህ ምክንያቶች፣ ወንጌልን ለመኖር፣ ለመማር፣ እና ለማስተማር በምናደርገው ጥረት፣ በመጀመሪያ እና ከሁሉም በላይ የመንፈሱን አብሮ መሆን መፈለግ አለብን። ይህ ግብ ምርጫዎቻችንን መምራት እና ሀሳባችንን እና ድርጊቶቻችንን መምራት ይገባዋል። የመንፈስን ተጽዕኖ የሚጋብዘውን ማንኛውንም ነገር ሁሉ መፈለግ እና የእሱን ተጽዕኖ ከሚያርቁ ነገሮች መራቅ አለብን—እኛ ለመንፈስ ቅዱስ መገኘት ብቁዎች ለመሆን ከቻልን፣ እንዲሁ ከሰማያዊ አባት እና ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብረን ለመኖር ብቁ ለመሆንም እንደምንችል እናውቃለንና።