አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
መጋቢት 20–26 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 13፤ ሉቃስ 8፤ 13፦ “የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ”


“መጋቢት 20–26 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 13፤ ሉቃስ 8፤ 13፦ ‘የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ’” ኑ፣ ተከተሉኝን—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፣ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“መጋቢት 20–26 (እ.አ.አ)። ማቴዎስ 13፤ ሉቃስ 8፤ 13፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ለመሰብሰብ የደረሰ ስንዴ

መጋቢት 20–26 (እ.አ.አ)

ማቴዎስ 13ሉቃስ 8፤ 13

“የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ”

ማቴዎስ 13 እና ሉቃስ 8፤ 13ን ስታነቡ እነዚህን የአዳኙን ምስላሌያዊ አስተምሮቶች “[ለመስማት]” እና ለማድነቅ ራሳችሁን አዘጋጁ። እነዚህን አስተምሮቶች በህይወታችሁ ለመተግበር ምን ታደርጋላችሁ?

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

አንዳንዱ የአዳኙ የማይረሱ አስተምሮቶች ምሳሌ በሚባሉ ቀለል ባሉ ታሪኮች ነበር። እነዚህ ስለተለመዱ እቃዎች ወይም ክስተቶች ደስ ከሚሉ ተረቶች በላይ ነበሩ። በመንፈስ ለተዘጋጁት ስለ እግዚአብሔር መንግስት ታላቅ እውነቶችን የያዙ ናቸው። በአዲስ ኪዳን ላይ ከተመዘገቡ ምሳሌዎች የመጀመርያው የሆነው የዘሪው ምሳሌ የእግዚአብሔር ቃልን ለመቀበል ዝግጁነታችንን እንድንፈትን ይጋብዘናል (ማቴዎስ 13፥3–23ን ተመልከቱ)። “ለሚቀበል ሁሉ ይሰጠዋል እና ይበዛለትማል” በማለት ኢየሱስ አወጀ (የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ማቴዎስ 13፥10 [በማቴዎስ 13፥12፣ የግርጌ ማስታወሻ  ])። ስለዚህ የአዳኙን ምሳሌዎች—ወይም የትኞቹንም አስተምሮቶቹን—ለማጥናት ስንዘጋጅ ልባችንን መመርመር እና የእግዚአብሔር ቃል እንዲያድግ፣ እንዲያብብ፣ እንዲበቅል እና እኛን እና ቤተሰባችንን በብዙ የሚባርክ ፍሬ እንዲያፈራ “መልካም መሬት” እየሰጠን እንደሆነ ማወቅ ጥሩ ጅማሬ ነው (ማቴዎስ 13፥8)።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ማቴዎስ 13፥3–23ሉቃስ 8፥4–1513:6–9

የእግዚአብሔርን ቃል ለመቀበል ልቤ መዘጋጀት አለበት።

አንዳንድ ጊዜ ልባችን እውነትን በቀላሉ የሚቀበል ሌላ ጊዜ ደግሞ ለመቃወም የሚፈታተነን ለምንድነው? የዘሪውን ምሳሌ ማንበብ ከጌታ እውነትን እንዴት እንደምትቀበሉ እንድታስቡ እድል ሊሰጣችሁ ይችላል። የማቴዎስ 13 ቁጥር 3–8 ን በ ቁጥር 18–23፣ ላይ ከሚገኙ ማብራርያዎች ጋር ማዛመድ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። በራሳችሁ ውስጥ “መልካም መሬት” ለማልማት ምን ማድረግ ትችላላችሁ? የእግዚአብሔርን ቃል በእውነት እንዳትሰሙ እና እንዳትከተሉ የሚከለክሏችሁ አንዳንድ “[እሾሆች]” ምን ሊሆኑ ይችላሉ? እነዚህን “[እሾሆች]” እንዴት ማሸነፍ ትችላላችሁ?

የዚህ ምሳሌ ጥናታችሁ በሉቃስ 13፥6–9፣ ላይ ያለውን ምሳሌ አጠናናችሁ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። እግዚአብሔር ከኛ የሚፈልገው “ፍሬ” ምንድነው? “ፍሬ [እንድናፈራ]” መሬታችንን የምንንከባከበው እንዴት ነው?

በተጨማሪም ሞዛያ 2፥9አልማ12፥10–1132፥28–43፤ ዳለን ኤች. ኦክስ “የዘሪው ምሳሌ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ) 32–35ን ተመልከቱ።

ማቴዎስ 13፥24–35፣ 44–52ሉቃስ 13፥18–21

የኢየሱስ ምሳሌዎች የእርሱን ቤተክርስትያን እድገት እና እጣ ፈንታ አንድረዳ ይረዳኛል።

ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ በ ማቴዎስ 13 ያሉ ምሳሌዎች በኋለኛው ቀናት የቤተክርስትያኑን እድገት እና እጣ ፈንታ እንደሚያስረዱ አስተምሯል። የሚከተሉት ምሳሌዎች ስለ ጌታ ቤተክርስትያን የሚያስተምሩትን ስታስቡ የነብዩን ቃላት በ የቤተክርስቲያኗ ፕሬዝዳንቶች ትምህርቶች፦ ጆሴፍ ስሚዝ (2007(እ.አ.አ))፣ 293–303፣ ላይ መቃኘት ትችላላችሁ፦

እነዚህን ምሳሌዎች ካሰላሰላችሁ በኋላ በክርስቶስ የኋለኛው ቀን ቤተክርስትያን ስራ ላይ በሙላት እንድትሳተፉ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ይሰማችኋል?

በተጨማሪም የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ “የእግዚአብሔር መንግስት ወይም የሰማይ መንግስት፣” “ምሳሌ፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

ዕንቁ

የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል “[የታላቅ ዋጋ ዕንቁ]” (ማቴዎስ 13፥46) ነው።

ማቴዎስ 13፥24–30፣ 36–43

የአለም መጨረሻ እስኪደርስ ጻድቁ በሃጢያተኞች መሃል ማደግ አለበት።

ይህን ምሳሌ ማጥኛ አንዱ መንገድ ስዕል መሳል እና በ ማቴዎስ 13፥36–43 እና ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 86፥1–7፣ ላይ ካለው ትንታኔ ጋር በመለጠፍ ነው። እንክርዳድ “አትኩሮት ካልተሰጠው በቀር ከስንዴ ጋር የሚመሳሰል መርዛማ አረም” ነው (የመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ “እንክርዳድ”)። በአለም ላይ ክፋት ቢኖርም ታማኝ ሆናችሁ እንድትቀጥሉ የሚያነሳሳችሁ እውነት በዚህ ምሳሌ የትኛው ነው?

ሉቃስ 8፥1–3

“አንዳንድ ሴቶች” በምን አይነት መንገድ አዳኙን አገለገሉ?

“ሴት ደቀመዛሙርት [ከኢየሱስ] በመንፈስ እየተማሩ እና ለእርሱ ምድራዊ አገልግሎት እየሰጡ ከኢየሱስ እና ከአስራ ሁለቱ ጋር ይጓዙ ነበር። … የወንጌሉን የምስራች እና የእርሱን ፈውስ ሃይል በረከት፤ የኢየሱስን አገልግሎት ከመቀበል በተጨማሪ እነዚህ ሴቶች እቃቸውን በመለገስ እና በመስጠት እርሱን አገልግለውታል (ሴት ልጆች በመንግስቴ ውስጥ [2017 (እ.አ.አ)]፣ 4)። ክርስቶስን የተከተሉ ሴቶች ስለ እርሱ ጠንካራ ምስክርነትም ሰጥተዋል (ሊንዳ ኬ. በርቶን “አንዳንድ ሴቶች፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 12–15ን ተመልከቱ)።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ማቴዎስ 13ቤተሰባችሁ የአዳኙን ምሳሌዎች ሲያነብ ቁሶችን ወይም ለእነሱ የተለመዱ ሁኔታዎችን በመጠቀም ስለ ሰማይ መንግስት (ስለ ቤተክርስትያን) ተመሳሳይ እውነቶችን በራሳቸው ምሳሌ ለማስተማር ማሰብ ሊያስደስታቸው ይችላል።

ማርቆስ 13፥3–23ሉቃስ 8፥4–15የዘሪውን ምሳሌ በአንድነት ካነበባችሁ በኋላ ቤተሰባችሁ እንደዚህ አይነት ጥያቄዎችን ሊወያይ ይችላል፤ “[መሬታችንን]” (ልባችንን) “ድንጋያማ” ወይም ቃሉን “[የሚያንቅ]” እንዲሆን የሚያደርገው ምንድነው? መሬታችን መልካም እና ፍሬያማ እንደሆነ እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን?

ቤተሰባችሁ ውስጥ ትንሽ ልጆች ካሉ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ልባችንን የምናዘጋጅበት የተለያዩ መንገዶችን የቤተሰብ አባላት እንዲተውኑ መጋበዝ እና ሌሎች የቤተሰብ አባላት ደግሞ ምን እያደረጉ እንደሆነ እንዲገምቱ ማድረግ አስደሳች ሊሆን ይችላል።

ማቴዎስ 13፥13–16የቤተሰብ አባላት የክርስቶስን ቃል በፈቃደኝነት የመቀበልን አስፈላጊነት እንዲረዱ እንዴት መርዳት ትችላላችሁ? “ጆሮአቸውም ደንቁሮአል” የሚለውን ለማሳየት የቤተሰብ አባልን ጆሮ ልትሸፍኑ እና በዝምታ ማቴዎስ 13፥13–16ን ልታነቡ ትችላላችሁ። የቤተሰብ አባሉ ከእነዚህ ቁጥሮች ምን ያህል ተረዳ? ለእግዚአብሔር ቃል አይናችንን፣ ጆሮአችንን እና ልባችንን የምንከፍትባቸው መንገዶች ምንድናቸው?

ማቴዎስ 13፥44–46በዚህ ምሳሌ ላይ ያሉ ሁለቱ ሰዎች ምን ተመሳሳይ ነገር አላቸው? በግል እና እንደ ቤተሰብ በህይወታችን የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስቀደም ተጨማሪ ማድረግ ያለብን ነገሮች ምንድናቸው?

ሉቃስ 13፥11–17የቤተሰብ አባላት “[ቀንተው መቆም]” እንደማይችሉ ሆኖ የተሰማቸው አጋጣሚዎች አሉ? እንደዚህ የሚሰማቸውን ሌሎች ሰዎችን እናውቃለን? እንዴት መርዳት እንችላለን? አዳኙ ከድካማችን እንዴት ነው “[የሚፈታን]”?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልን ይመልከቱ።

በሀሳብ የሚቀርብ መዝሙር፦ “እኛ እየዘራን ነው፣” መዝሙር፣፣ ቁጥር 216።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

የቅዱሳት መጻህፍት ጥቅሶችን በቃል ያዙ። ለቤተሰብዎ ትርጉም ያለው የቅዱስ ፅሁፍ ምንባብ ምረጡ እና የቤተሰብ አባላቱ እንዲያስታውሱ ጋብዟቸው። ሽማግሌ ሪቻርድ ዲ.ስካት “በቃል የተያዘ ቅዱስ ጽሁፍ በጊዜ ሂደት የማይደበዝዝ ዘላቂ ጓደኛ ይሆናል“ በማለት አስተምረዋል (“የቅዱሳት መጻህፍት ሃይል፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2011(እ.አ.አ)፣6)፡፡

ሰው ዘር እየዘራ

የዘሪው ምሳሌ፣ በጆርጅ ሶፐር