“ዘላለማዊው ቃል ኪዳን፣“ሊያሆና፣ ጥቅምት 2022 (እ.አ.አ)
ወርሀዊ የሊያሆና መልዕክት፣ ጥቅምት 2022 (እ.አ.አ)
ዘላለማዊው ቃል ኪዳኑ
ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን የገቡ ልዩ የሆነ ፍቅር እና ምህረትን ማግኘት ይችላሉ።
በጦርነቶች እና በጦርነት ወሬዎች በታመሰችው በዚህች ዓለም የእውነት፣ የብርሀን እና የኢየሱስ ክርስቶስ ንፁህ ፍቅር አስፈላጊነት ከምንጊዜውም በላይ ነው። የክርስቶስ ወንጌል የተከበረ ነው፣ ስለሆነም እንድናጠናው እና በትእዛዛቱ እንድንኖር ተባርከናል። እርሱን ለማካፈል እንዲሁም እውነታውን በየትኛውም ቦታ ለመመስከር በተሰጡን እድሎች እንደሰታለን።
ስለአብርሃም ቃልኪዳን እና ስለእስራኤል መሰብሰብ አስፈላጊነት በተደጋጋሚ ተናግሪያለሁ። ወንጌልን ስንቀበል እና ስንጠመቅ የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ስም በራሳችን ላይ እንወስዳለን። ጥምቀት በቅዱስ ቤተመቅደስ ለአብርሃም፣ ለይስሃቅ እና ለዘሮቻቸው ቃል እንደተገባው የዘላለም ቤተሰብ በረከቶች ጣምራ ወራሽ ወደመሆን የሚያመራ መግቢያ በር ነው።1
“አዲሱ እና ዘላለማዊው ቃል ኪዳን”2(ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች132:6) እነና የአብርሃም ቃል ኪዳን በመሰረቱ ተመሳሳይ ናቸው—እግዚአብሔር በተለያዩ ጊዜያት ከምድራዊ ወንዶችና ሴቶች ጋር የገባውን ቃል ኪዳን የመናገሪያ ሁለት መንገዶች።
ዘላለማዊየሚለው ቅጽል ይህ ቃል ኪዳን ከአለም መመስረት በፊት እንደነበረ ያመለከታል። በሰማይ ውስጥ ባነበረው በታላቁ ስብሰባ ላይ የተነደፈው እቅድ ሁላችንም ከእግዚአብሔር መገኘት የምንወገድ የመሆናችንን ጥልቅ ግንዛቤ ያካትታል። ሆኖም እግዚአብሄር የውድቀቱን ውጤቶች የሚቋቋም አዳኝ እንደሚያቀርብ ቃል ገብቶ ነበር። ከጥምቀቱ በኋላ እግዚአብሄር አዳምን ይህንን ነገረው፦
“አንተም ከዘለአለም እስከ ዘለአለም፣ ለቀናቱ የመጀመሪያ ወይም የመጨረሻ ከሌለው ከእርሱ ስርዓትም ሆነሀል።
“እነሆ፣ አንተ በእኔ አንድ ነህ፣ የእግዚአብሔርም ልጅ፤ እና እንደዚህ ሁሉም የእኔ ልጆች መሆን ይችላሉ፣ አሜን(ሙሴ 6:67–68)”።
አዳም እና ሄዋን የጥምቀትን ስርዓት ተቀበሉ እንዲሁም ከእግዚአብሄር ጋር አንድ የመሆንን ሂደት ጀመሩ። ወደቃል ኪዳኑ መንገድ ገብተው ነበር።
እናንተ እና እኔ ወደዚያ መንገድ ስንገባ አዲስ የአኗኗር መንገድ ይኖረናል። በዚህም እንዲባርከን እና እንዲለውጠን የሚያስችለውን ግንኙነት ከእግዚአብሔር ጋር እንፈጥራለን። የቃል ኪዳኑ መንገድ ወደእርሱ እንድንመለስ ይመራናል። እግዚአብሄር በህይወታችን እንዲያሸንፍ ብንፈቅድ ያ ቃልኪዳን የበለጠ ወደእርሱ ወደመቅረብ ይመራናል። ቃልኪዳኖች ሁሉ አስገዳጅ እንዲሆኑ የታለሙ ናቸው። ትስስሮቹ ዘላለማዊ የሆኑ ዝምድናን ይፈጥራሉ።
የተለየ ፍቅር እና ምህረት
ከእግዚያብሄር ጋር አንዴ ቃል ኪዳን ከገባን ገለልተኛ ሃሳቦችን ለዘላለም እንተዋለን።፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዲህ ያለውን ግንኙነት የፈጠሩትን አይተውም። በርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን የገቡ ልዩ የሆነ ፍቅር እና ምህረትን ማግኘት ይችላሉ። በዕብራይስጥ ቋንቋ የቃል ኪዳን ፍቅር ሄሴድ (חֶסֶד).3ይባላል።
ሄሴድአቻ የእንግሊዝኛ ፍቺ የለውም። የኪንግ ጄምስ የመጽሃፍ ቅዱስ እትም ተርጓሚዎች ሄሴድየሚለውነን ቃል ወደእንግሊዝኛ ለመተርጎም ተቸግረው የነበረ መሆን አለበት። አብዛኛውን ጊዜ “ፍቅራዊ ደግነት“ የሚለውን መርጠዋል። ይህ የተወሰነውን የሄሴድፍቺ ይሰጣል ሆኖም ሙሉውን ፍቺ አይሰጥም። እንደ “ምህረት“ እና “መልካምነት“ ያሉ ሌሎች ፍቺዎችም ተሰጥተውት ነበር። ሄሴድሄሴድ ሁለት አካላት አንዳቸው የሌላውን ቃል አክባሪ እና እርስ በርስ የሚተማመኑ እንዲሆኑ የሚጠበቅባቸውን የቃል ኪዳን ግንኙነት የሚገልጽ ልዩ ቃል ነው።
የሴሌስቲያል ጋብቻ እንዲህ ዓይነት የቃል ኪዳን ግንኙነት ነው። ባልና ሚስት አንዳቸው የሌላውን ቃል አክባሪ እና እርስ በርስ የሚተማመኑ እንዲሆኑ ከእግዚአብሄር ጋር እና እርስ በርሳቸው ቃል ኪዳን ይገባባሉ ።
ሄሴድእግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን ለገቡት የሚሰማው እና የሚሰጣቸው ልዩ ፍቅር እና ምሕረት ነው። እኛምበሄሴድ እንመልስለታለን።
እኔ እና አናንተ አንዴ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ከገባን፣ ያለን ግንኙነት ቃል ኪዳን ከመግባታችን በፊት ከነበረው በጣም የቀረበ ይሆናል። አሁን አንድ ላይ ተጣምረናል።
ፎቶግራፍ በጄሪ ኤል. ጋምስ
ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን ለገቡትሄሴድስላለው ይወዳቸዋል። ከእነርሱ ጋር መስራቱን ይቀጥላል እንዲሁም መለወጥ የሚችሉባቸውን እድሎች ይሰጣቸዋል። ንስሃ ሲገቡ ይቅር ይላቸዋል። መንገዳቸውን ቢስቱም ወደእርሱ የሚመለሱበትን መንገድ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል።
እኔ እና አናንተ አንዴ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ከገባን፣ ያለን ግንኙነት ቃል ኪዳን ከመግባታችን በፊት ከነበረው በጣም የቀረበ ይሆናል። አሁን አንድ ላይ ተጣምረናል። ከእግዚአብሔር ጋር በገባነው ቃል ኪዳን ምክንያት እኛን ለመርዳት በሚያደርገው ጥረት አይታክትም እንዲሁም ለእኛ ያለውን የምሕረት ትዕግሥትም አንጨርሰውም። እያንዳንዳችን በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ልዩ ስፍራ አለን። ለኛ ትልቅ ተስፋ አለው፡፡
ጌታ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ስለሰጠው ታሪካዊ አዋጅ ታውቃላችሁ። የመጣው በራዕይ ነበር። ጌታ ለጆሴፍ ስሚዝ “ይህም ቃል ኪዳን ያንተም ነው፣ ምክንያቱም አንተ ከአብርሐም ነህና፣ እና ቃል ኪዳኑም ለአብርሐም ተሰርቶ ነበርና” አለው(ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132:31)።
በዚህም፣ ይህ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን የወንጌል ሙላት አካል ሆኖ በታላቁ የዳግም መመለስ ተመልሷል። አስቡበት! በቤተመቅደስ ውስጥ የሚካሄድ ጋብቻ በቀጥታ ከዚያ የአብርሀሃም ቃልኪዳን ጋር ይያያዛል። በቤተመቅደስ ውስጥ ጥንዶች ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ እና ለያዕቆብ ታማኝ ትውልዶች ከተዘጋጁት ከሁሉምበረከቶች ጋር ይተዋወቃሉ።
አዳም እንዳደረገው እናንተ እና አኔ ስንጠመቅ በግለሰብ ደረጃ ወደቃልኪዳነኑ መንገድ ገብተናል። ከዚያም በቤተመቅደስ ውስጥ ይበልጥ ሙሉለሙሉ ወደቃልኪዳነኑ መንገድ እንገበለን። የአብርሃም ቃልኪዳን በረከቶች የሚሰጡት በቤተመቅደስ ውስጥ ነው። እነዚህ በረከቶች፣ በትንሳኤ ስንነሳ “ዙፋናት[ን]፣ መንግስታት[ን]፣ ጌትነቶች[ን]፣ እና ሃይላት[ን]“‘[ለ]ዘላለማዊ ክብር እና [ለ]ክብራችን‘ እንድንወርስ ያስችሉናልትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132:194።
በብሉይ ኪዳን ጽሁፍ መደምደሚያ ላይ ኤሊያስ “የአባቶችን ልብ ወደልጆች፣ የልጆችንም ልብ ወደአባቶች ስለሚመልስበት” ሚልኪያ የሰጠውን ተስፋ እናነባለን። (ሚልኪያ 4) በጥንቷ እስራኤል ስለአባቶች የሚሰጡ እንዲህ ያሉ ማጣቀሻዎች አብርሃምን፣ ይስሐቅን እና ያዕቆብን ያካትታሉ። ሞሮኒ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተጠቀሰውን የተለየ አይነት ጥቅስ ስናነብ ይህ የተስፋ ቃል ግልጽ ይሆናል፦ “እርሱ [ኤልያስ] ለአባቶች የተገባውን የተስፋ ቃል በልጆች ልብ ይተክላል፣ እናም የልጆቹንም ልብ ወደ አባቶቻቸው ይመልሳል” (ጆሴፍ ስሚዝ— ታሪክ 1:39)። እነዚያ አባቶች በርግጠኝነት አብርሐምን፣ ይስሀቅን እና ያዕቆብን ያካትታሉ። (ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 27፥9–10 ይመልከቱ።)
ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን የሚያደርጉ እና የሚጠብቋቸው የዘላለም ህይወት እንደሚያገኙ እና ዘላለም ክብር እንደሚያገኙ ቃል ተገብቶላቸዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ የእነዚያ ቃልኪዳኖች ዋስትና ነው።
ማብራሪያ ከ Christ and the Rich Young Ruler በሄንሪክ ሆፍማን
ኢየሱስ ክርስቶስ፦ የቃልኪዳኑ ማዕከል ነው።
የአዳኙ የሃጢያት ክፍያ መስዋዕት አብ ለልጆቹ የሰጠውን ተስፋ እንዲፈጽም አስችሏል። ኢየሱስ ክርስቶስ “መንገድና እውነት ህይወትም [ስለሆነ]፤ [በእሱ] በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” (ዮሀንስ 14፥6)። የአብርሃም ቃል ኪዳን ሊፈጸም የሚችል የሆነው በአዳኛችን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ምክንያት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የአብርሃም ቃልኪዳን ማዕከልነው።
ብሉይ ኪዳን ቅዱስ ጽሁፍ ብቻ አይደለም፤ የታሪክ መጽሃፍም እንጂ። ስለሳራ እና አብርሃም ጋብቻ ስለማንበባችሁ ታስታውሳላችሁ። ልጅ ስላልነበራቸው፣ በእግዚአብሔር መመሪያ መሰረት ሦራ ባሪያዋን አጋርን ለአብራም ሚስት እንድትሆነው ሰጠችው። አጋር እስማኤልን ወለደች።5 አብራም እስማኤልን ይወደው ነበር ሆኖም ቃል ኪዳኑን የሚቀበል ልጅ አይሆንም ነበር ( ዘፍጥረት 11:29–30፤ 16:1, 3, 11፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥34.ይመልከቱ)
እንደእግዚአብሄር በረከት እና ለሳራ እምነት እንደተሰጠ ምላሽ6እድሜዋ ከገፋ በኋላ አረገዘች፤ ይኸውም ቃልኪዳኑበእርሷልጅ በይስሃቅ በኩል እንዲተላለፍ ነበር።(ዘፍጥረት 17:19ይመልከቱ) በቃልኪዳኑ ውስጥ ነበር የተወለደው።
እግዚአብሄር ለሦራ እና ለአብራም አዲስ ስሞች ሰጣቸው—ሳራእናአብርሃም(ዘፍጥረት 17:5, 15)። የእነዚያ አዳዲስ ስሞች መሰጠት የአዲስ ህይወት ጅማሬን እና የዚህን ቤተሰብ አዲስ እጣ ፈንታ በግልጽ ያሳያል።
አብርሃም እስማኤልን እና ይስሃቅን ሁለቱንም ይወዳል። እስማኤል እንደሚበዛ እና ታላቅ ሕዝብ እንደሚሆን እግዚአብሔር ለአብርሃም ነገረው(ዘፍጥረት 17:20ይመልከቱ)። በዚያኑ ወቅትም፣ የዘላለም ቃል ኪዳን በይስሐቅ በኩል እንደሚደረግ እግዚአብሔር ግልጽ አደረገ።(ዘፍጥረት 17:19ይመልከቱ)።
ወንጌልን የተቀበሉ ሁሉ የአብርሃም ዘር አካል ይሆናሉ። በገላትያ ውስጥ እንደምናነበው፦
“ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።
“… ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።
“እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሐም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።”(ገላትያ 3:27–29)።
ስለዚህ፣ በመወለድ ወይም በማደጎ የቃል ኪዳኑ ወራሾች መሆን እንችላለን።
ከእግዚያብሄር ጋር አንዴ ቃል ኪዳን ከገባን ገለልተኛ ሃሳቦችን ለዘላለም እንተዋለን። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዲህ ያለውን ግንኙነት የፈጠሩትን አይተውም።
ይስሃቅ እና የርብቃ ልጅ ያዕቆብ በቃልኪዳኑ ውስጥ ነበር የተወለዱት። እንዲሁም፣በራሱ ፈቃድ መግባትን መርጧል። እንደምታውቁት የያዕቆብ ስምእስራኤልወደሚል ተቀይሮ ነበር(ዘፍጥረት 32:28ይመልከቱ) ትርጉሙም “እግዚአብሄር ያሸንፍ“ ወይም “በእግዚአብሔር ፊት የሚያሸንፍ“ ማለት ነው።7
በዘጸዓት “እግዚአብሄርም ከአብርሃምና ከይስሃቅ ከያዕቆብም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን እንዳሰበ“ እናነባለን።(ዘጸዓት 2:24) እግዚአብሄር ለእስራኤል ልጆች “ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ” ሰሲለል ተናገረ (ዘጸአት 19፥5)።
“የተመረጠ ርስት“ የሚለው ሃረግ የተተረጎመውሴጉላህከሚለው የእብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጠው ይዞታ—“ርስት” ማለት ነው።8
የዘዳግም መጽሐፍም የቃልኪዳኑን አስፈላጊነት ይገልጻል። የአዲስ ኪዳን ሃዋርያት ስለዚህ ቃልኪዳን ያውቁ ነበር። ጴጥሮስ በቤተመቅደስ ደረጃ ላይ አንካሳውን ሰው ከፈወሰው በኋላ ተመልካቾቹን ስለኢየሱስ ክርስቶስ አስተ።ማራቸው። ጴጥሮስም እንዲህ አለ “የአብርሃምና የይስሃቅ የያዕቆብም አምላክ የአባቶቻችን አምላክ ኢየሱስን አከበረው(ሥራ 3:13)።
ጴጥሮስ የሚከተለውን ለአድማጮቹ በመናገር መልዕክቱን ደመደመ “እናም እነሆ፣ እናንተ የነቢያት ልጆች ናችሁ፤ እናም የእስራኤል ቤት ናችሁና፣ እግዚአብሔር ለአብርሃም በዘርህ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ከአባቶቻችሁ ጋር ያደረገው የኪዳን ልጆች ናችሁ(ሥራ 3:25)።. የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን መፈጸም የክርስቶስ ተልዕኮ አካል እንደሆነ ጴጥሮስ ግልጽ አደረገላቸው።
ጌታ በጥንት አሜሪካ ለነበሩ ህዝቦች ተመሳሳይ ትምህርት ሰጠ። በዚያም፣ ከሞት የተነሳውክርስቶስ በርግጥ እነርሱ ማን እንደሆኑ ለህዝቡ ነገራቸው። እንዲህ አለ፦
እናም እነሆ፣ እናንተ የነቢያት ልጆች ናችሁ፤ እናም የእስራኤል ቤት ናችሁና፣ እግዚአብሔር ለአብርሃም በዘርህ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ከአባቶቻችሁ ጋር ያደረገው የኪዳን ልጆች ናችሁ፤
“አብም ወደእናንተ በመጀመሪያ እንድነሳ አደረገኝ፣ እናም ከክፋቶቹ እያንዳንዳችሁን እንዳርቅ እናንተን እንድባርክ ላከኝ፤ እናም ይህም የሆነው እናንተ የቃል ኪዳን ልጆች ስለሆናችሁ ነው” (3 ኔፊ 20:25–26).
የዚህን አስፈላጊነት ታያላችሁ? ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን ቃል ኪዳኖች የሚጠብቁ የኃጢአትን ሃይል የሚቋቋሙ ነፍሳት ይሆናሉ! ቃል ኪዳናቸውን የሚጠብቁ የማያቋርጠውን የአለም ተጽእኖ የመቋቋም ጥንካሬ ይኖራቸዋል።
ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን ቃል ኪዳኖች የሚጠብቁ የኃጢአትን ሃይል የሚቋቋሙ ነፍሳት ይሆናሉ! ቃል ኪዳናቸውን የሚጠብቁ የማያቋርጠውን የአለም ተጽእኖ የመቋቋም ጥንካሬ ይኖራቸዋል።
የሚስዮናዊ ስራ፦ ስለቃልኪዳኑ ማጋራት
ጌታ ወንጌሉን እንድናሰራጭ እና ስለቃልኪዳኑ እንድናካፍል አዟል። ለዚህም ነው ሚስዮናውያን ያሉን። እያንዳንዱ ልጆቹ የአዳኙን ወንጌል እንዲመርጡ እና ወደቃል ኪዳኑ መንገድ እንዲገቡ እድል እንዲኖራቸው ይመኛል። እግዚአብሔር፣ ሰዎች ሁሉ ከአብርሃም ጋር በጥንት ጊዜ ከገባው ቃል ኪዳን ጋር ህብረት እንዲኖራቸው ይሻል።
ስለዚህ የሚስዮናዊ ስራ የታላቁ እስራኤልን የመሰብሰብ ስራ አስፈላጊ አካል ነው። ያ መሰባሰብ አሁን በምድር ላይ ከሚሰሩት ካሉት ስራዎች እጅግ አስፈላጊው ነገር ነው። ሌላ ምንም ይህን ያህል ክብደት የሚሰጠው ነገር የለም። ሌላ ምንም ይህን ያህል ክብደት የሚሰጠው ነገር የለም። የጌታ ሚስዮናውያን—ደቀ መዛሙርቱ—ዛሬ በትልቁ ፈታኝ ሁኔታ፣ በታላቁ ምክንያት፣ በምድር ላይ ባለው በታላቁ ስራ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ነገር ግን የበለጠ ነገርም አለ—ብዙ ተጨማሪ ነገር። የመጋረጃ በሌላኛው በኩል ላሉ ሰዎች ወንጌልን ለማዳረስ ከፍተኛ ፍላጎት አለ። እግዚአብሔር በመጋረጃው በሁለቱም በኩል ያሉት እያንዳንዱ ሰው ከእርሱ የቃል ኪዳን በረከቶች እንዲካፈሉ ይፈልጋል። የቃል ኪዳኑ መንገድ ለሁሉም ክፍት ነው። ሁሉም ሰው በዚያ መንገድ ከእኛ ጋር እንዲጓዝ እንማጸናለን። ያን ያህል ሁሉን የሚያካትት ሌላ ምንም ሥራ የለም። ስለዚህ “ጌታ ከልብ በመሆን ቅዱስ ስሙን ለሚጠሩ ሁሉ እርሱ መሀሪ [ነው]”(ሄለማን 3:27)።
የመልከጼዴቅ ክህነት በመመለሱ ምክንያት ፣ ቃል ኪዳኑን የሚጠብቁ ሴቶች እና ወንዶች “የወንጌልን መንፈሳዊበረከቶች ሁሉ” መቋደስ ይችላሉ(ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 107:18፤ አትኩሮት ተጨምሮበታል ).።
በ1836 እ.አ.አ) በከርትላንድ ቤተመቅደስ ምረቃ ስነስርዓት ላይ፣ በጌታ መሪነት፣ ኤልያስ ተገለጠ። አላማው? “የልጆችን ወደ አባቶች… ለመመለስ(ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110:15)። ኤልያም ደግሞ ተገለጠ። አላማው? ለጆሴፍ ስሚዝ እና ለኦሊቨር ካውደሪ ሲል“ከዚህ በኋላ፣ ኤልያ መጣ፣ እና በእኛና በዘራችን ከእኛም በኋላ የሚመጡ ትውልዶች ሁሉ ይባረካሉ በማለት የአብርሐም ወንጌል የዘመን ፍጻሜን ሰጠን”(ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 110:12)። ስለዚህ፣ መምህሩ ለጆሴፍ ስሚዝ እና ለኦሊቨር ካውደሪ የክህነት ስልጣን እና የአብርሃምን ቃል ኪዳን ልዩ በረከቶች ለሌሎች የማድረስ መብት ሰጣቸው።9
በቤተክርስቲያን ውስጥ፣ የቃልኪዳኑን መንገድ በግል እና በጋራ እንጓዛለን። ትዳር እና ቤተሰብ ልዩ ፍቅርን የሚፈጥር የተለየ የጎንዮሽትስስር እንደሚጋሩ ሁሉ፣ እኛም በቃል ኪዳን ከአምላካችን ጋር ከታች ወደላይ ስንተሳሰር የሚፈጠረው አዲስ ግንኙነትም እንዲሁ ነው!
ኔፊ “[ጌታ] አምላካቸው አድርገው የሚቀበሉትን ሰዎች ይወዳቸዋል” ባለ ጊዜ ይህንን ማለቱ ሊሆን ይችላል(1 ኔፊ 17:40)። በትክክል ለዚህ ነው እንደቃልኪዳኑ ክፍል፣ ልዩ ምህረት እና ፍቅር—ወይም ሄሴድሄሴድ—ከእግዚአብሔር ጋር ወደዚህ አስገዳጅ እና የቅርብ ግንኙነት ለሚገቡ ሁሉ “እስከ ሺህ ትውልድ” ድረስ ያለው(ዘዳግም 7:9)።
ከእግዚያብሄር ጋር ቃል ኪዳን መግባት ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ለዘለለም ይቀይረዋል። በተጨማሪ የፍቅር እና የምህረት ብዛት ይባርከናል።10 የአሁኑን ማንነታችንን እና እግዚያብሄር መሆን የምንችለውን እንድንሆን በሚረዳን መንገድ ላይ ተጽዕኖ ያደርጋል። በተጨማሪም የእርሱ “የተመረጠ ርስት” ልንሆን እንደምንችልም ተስፋ ተሰጥቶናል(መዝሙር 1354)።
ተስፋዎች እና እድሎች
ቅዱስ ቃል ኪዳኖችን የሚያደርጉ እና የሚጠብቋቸው የዘላለም ህይወት እንደሚያገኙ እና “ከእግዚአብሄር ስጦታዎች ሁሉ ታላቅ ስጦታ የሆነውን“ የዘላለም ክብር እንደሚያገኙ ቃል ተገብቶላቸዋል(ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 14:7)። ኢየሱስ ክርስቶስ የእነዚያ ቃልኪዳኖች ዋስትና ነው( ሄለማን 7:22፤ 8:6)። እግዚአብሄርን የሚወዱ እንዲሁም በሕይወታቸው ውስጥ በሁሉም ነገሮች ላይ እንዲያሸንፍ የሚፈቅዱ ቃል ኪዳን ጠባቂዎች በሕይወታቸው ውስጥ ያለ እጅግ በጣም ኃይለኛ ተጽዕኖ ያደርጉታል።
በዘመናችን የፓትርያርክ በረከቶችን ለመቀበል እና ከቀደምት ፓትርያርኮች ጋር ስላለን ግንኙነት ለመማር እድል ተሰጥቶናል። በተጨማሪም እነዚያ በረከቶች ወደፊት ስለሚመጣው ነገር ፍንጭ ይሰጣሉ።
ከእግዚአብሔር ጋር በገባነው ቃል ኪዳን ምክንያት እኛን ለመርዳት በሚያደርገው ጥረት አይታክትም።
ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን? በዴቪድ ሊንድስሊ
እንደ ቃልኪዳን እስራኤል የተሰጠን ጥሪ ሁሉም የቤተክርስቲኗ አባል ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ከመግባት ጋር የተያያዙት ደስታዎችን እና ልዩ ልዩ እድሎችን እንዲገነዘቡ ማድረግ ነው። እያንዳንዱ ቃልኪዳን የሚጠብቅ ወንድና ሴት፣ ወጣት ወንድ ልጅና ወጣት ሴት ልጅ፣በስራቸው ለሚገኙት ወንጌልን እንዲያካፍሉ ለማበረታታት የተሰጠ ጥሪ ነው። በአንድነት የእግዚአብሔር ሰዎች እንድንሆን እና እርሱም አምላካችን ይሆንልን ዘንድ፣ የማጥመቅ እና እስራኤልን የመሰብሰብ መመሪያ ተቀብለው የተላኩትን ሚስዮናውያኖቻችንን የመደገፍ እና የማበረታታት ጥሪ ነው(ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42:9ይመልከቱ)።
እያንዳንዳቸው በክህነት ስርዓቶች ውስጥ የሚሳተፉ እንዲሁም ከእግዚአብሄር ጋር ቃል ኪዳኖችን የሚገቡ እና እነርሱንም የሚጠብቁ ወንዶች እና ሴቶች ሁሉ የእግዚአብሔርን ኃይል መጠቀም ይችላሉ። እንደግለሰብ እያንዳንዳችን የጌታን ስም በላያችን ላይ እንወስዳለን። እንደህዝብም እያንዳንዳችን የጌታን ስም በላያችን ላይ እንወስዳለን። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የሚለውን ትክክለኛ ስም ለመጠቀም ቀናኢ መሆን እኛ እንደህዝብ ስሙን በእኛ ላይ የምንወስድበት ወሳኝ መንገድ ነው። በእውነት፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እና አባላቶቿ እያንዳንዱ ደግነት የእግዚአብሔርን ሄሴድ.መገለጫ ነው።
እስራኤል የተበተነው ለምንድነ ነው? ህዝቡ ትእዛዛትን በመጣሱ እና ነቢያትን በድንጋይ በመውገሩ ምክንያት ነው። አፍቃሪ የሆነው ነገር ግን ያዘነው አባት እስራኤላውያንን አርቆ በተናቸው።11
ነገር ግን፣ ሲበትናቸው አንድ ቀን እስራኤል እንደገና ወደመንጋው እንደሚሰበሰብ የተስፋ ቃል በመስጠት ነበር።
የይሁዳ ነገድ አለምን ለጌታ የመጀመሪያ ጊዜ ምፅዓት ለማዘጋጀት ሃላፊነት ተሰጥቶት ነበር። ከዚያ ነገድ፣ ማርያም የእግዚአብሔር ልጅ እናት እንድትሆን ተጠርታ ነበር።
የዮሴፍ ነገድ በእርሱና በአስናት ወንዶች ልጆች በኤፍሬም እና በምናሴ በኩል እስራኤልን የመሰብሰብ ስራን የመምራት ሃላፊነት ተሰጥቶት ነበር(ዘፍጥረት 41:50–52፤46:20ይመልከቱ)።
በእንደዚህ አይነቱ ዘመን የማይሽረው የሄሴድግንኙነት፣ እግዚአብሔር እስራኤልን ለመሰብሰብ መፈለጉ ተፈጥሯዊ ነው። እርሱ የሰማይ አባታችን ነው! በመጋረጃው በሁለቱም በኩል ያሉት—እያንዳንዱ ልጆቹ—ዳግም የተመለሰውን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መልእክት እንዲሰሙ ይፈልጋል።
የፍቅር መንገድ
የቃልኪዳን መንገዱ የፍቅር መንገድ ነው—ያ የማይታመን ሄሴድ፣ ያ አዛኝ አሳቢ እንዲሁም እርስ በርስ መደጋገፍ ያለበት ነው። ያንን ፍቅር ማጣጣም ነፃ የሚያወጣ እና የሚያንጽ ነው።። እስከዛሬ ተሰምቷችሁ ከሚያውቀው የበለጠ ደስታ የሚሰማችሁ በእግዚአብሔር እና በሁሉም ልጆቹ ፍቅር ስትዋጡ ነው።
ከማንም ወይም ከምንም ነገር በላይ እግዚአብሔርን መውደድ እውነተኛ ሰላም፣ መጽናኛ፣ መተማመን እና ደስታን የሚያመጣ ሁኔታ ነው።
የቃል ኪዳኑ መንገድ ከእግዚአብሔር ጋር ስላለን ግንኙነት —ከእርሱ ጋር ስላለንየሄሴድግንኙነት ይገልጻል። ከእግዚያብሄር ጋር ቃልኪዳን ስናደርግ ሁልጊዜ ቃሉን ከሚጠብቅ ጋር ቃልኪዳን አድርገናል ማለት ነው። የመምረጥ ነጻነታችንን ሳይጥስ ቃልኪዳናችንን እንድንጠብቅ ለመርዳት ማድረግ የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል።
መፅሐፈ ሞርሞን የሚጀምረው እና የሚያበቃው ስለዚህ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን በመጥቀስ ነው። ከርዕስ ገጹ ጀምሮ እስከ ሞርሞን እና ሞሮኒ መዝጊያ ምስክርነቶች ድረስ፣ መፅሐፈ ሞርሞን ስለቃልኪዳኑ ይጠቅሳል(ሞርሞን፤9:37ይመልከቱ)። “የመፅሐፈ ሞርሞን መምጣት ጌታ እስራኤልን ለመሰብሰብ እና ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ እና ለያዕቆብ የገባላቸውን ቃልኪዳን ለመፈፀም መጀመሩን ለዓለም ሁሉ ምልክት ነው።“12
ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ስለዘላለማዊው ቃልኪዳን ውበት እና ሀይል ለአለም እንድናስተምር በምድር ታሪክ በዚህ ወሳኝ ወቅት ተጠርተናል። የሰማይ አባታችን ይህንን ታላቅ ስራ መስራት እንደምንችል ሙሉ በሙሉ ያምነናል።
ይህ መልእክት በመጋቢት 31 ቀን 2022(እ.አ.አ) በተካሄደው የጠቅላላ ጉባኤ አመራር ስብሰባ ላይም ተላልፏል።
© 2022 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. በዩ.ኤስ.ኤ ውስጥ የታተመ። እንግሊዘኛ የተፈቀደበት፦ 6/19። ትርጉም የተፈቀደበት፦ 6/19። Monthly Liahona Message, October 2022 ትርጉም። Amharic። 18317 506