አጠቃላይ ጉባኤ
መልሱ ሁልጊዜም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
የሚያዝያ 2023 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


መልሱ ሁልጊዜም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው

ምንም አይነት ጥያቄዎች ወይም ችግርች ቢኖሯችሁ፣ መልሱ ሁልጊዜም በኢየሱስ ክርስቶስ ህይወት እና ትምህርት ውስጥ ይገኛል።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ በእነዚህ ባለፉት ሁለት ቀናት በመንፈስ ተመግበናል። ዘማሪዎቹ አስደናቂ ነበሩ። ንግግር ያቀረቡትም ለጌታ መሳሪያዎች ነበሩ። ከዚህ መስበኪያ የተማራችሁትን እውነቶች ስታሰላስሉ መንፈስ ቅዱስ በጥናታችሁ መመሪያ እንዲሰጣችሁ እንድትሹ እጸልያለሁ። እነርሱም በእውነትም ከሰማይ የተላኩ ነበሩ።

ከዛሬ ቀን አንድ ሳምንት በኋላ የትንሳኤ ሰንበት ይሆናል። ለኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች ይህም ከሁሉም በላይ የሆነ የሀይማኖት በዓል ነው። ገናን የምናከብርበት ዋና ምክንያት ትንሳኤ ነው። የዚህ ሳምንት የኑ ተከተሉኝ ትምህርት አዳኙ ወደ ኢየሩሳሌም በድል የገባበትን፣ ቤተመቅደስን ያጸዳበትን፣ በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ የተሰቃየበትን፣ የተሰቀለበትን፣ ግርማዊ ትንሳኤውን፣ እና ያንንም ተከትሎ በተከታዮቹ የታየበትን እንድታጠኑ ያነሳሳችኋል።1

እነዚህን ቅዱስ ጥቅሶች አጣጥሟቸው እናም የሰማይ አባት ውድ አንድያ ልጁን በመላኩ2 የምታመሰግኑበትን ሁሉንም መንገዶች አግኙ። በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት፣ ንስሀ መግባት እና ለኃጢያቶቻችን ምህረትን ማግኘት እንችላለን። በእርሱም ምክንያት፣ እያንዳንዳችን ከሞት እንነሳለን።

አዳኙ በአሜሪካ ውስጥ በነበሩት ኔፋውያን የታየበትን በ3ኛ ኔፊ ውስጥ የሚገኘውን ታሪክ እንደገና እንድታጠኑት እጋብዛችኋለሁ። በዚያ ከመታየቱ በፊት፣ እነዚህን የማምለኪያ ቃላት ጨምሮ፣ ድምጹ በህዝቡ መካከል ተሰምቶ ነበር፦

“እፈውሳችሁ ዘንድ ንስሃ ገብታችሁ እናም ተለውጣችሁ አሁን ወደ እኔ አትመለሱምን?

“… እነሆ የምህረት ክንዴ ወደ እናንተ ተዘርግታለች፣ እናም ማንም ቢመጣ እቀበለዋለሁ።” 3

ውድ ወንድሚቼ እና እህቶቼ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን አይነት ግብዣ ዛሬም ለእናንተ ሰጥቷል። እርሱ እናንተን ይፈውሳችሁ ዘንድ ወደ እርሱ እንድትመጡ እለምናችኋለሁ። ንስሀ ስትገቡ ከኃጢያት ይፈውሳችኋል። ከሀዘን እና ፍርሃት ይፈውሳችኋል። ከዚህ አለም ቁስሎችም ይፈውሳችኋል።

ምንም አይነት ጥያቄዎች ወይም ችግርች ቢኖሯችሁ፣ መልሱ ሁልጊዜም በኢየሱስ ክርስቶስ ህይወት እና ትምህርት ውስጥ ይገኛል። ስለኃጢያት ክፍያው፣ ፍቅሩ፣ ምህረቱ፣ አስተምሮቱ፣ እና በዳግም ስለተመለሰችው የፈውስ፣ የእድገት፣ እና የማቀላቀል ወንጌሉ በተጨማሪ ተማሩ። ወደ እርሱ ዙሩ! ተከተሉት!

ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተመቅደሶችን የምንገነባበት ምክንያት ነው። እያንዳዱ የእርሱ ቤት ነው። በቤተመቅደስ ውስጥ ቃል ኪዳኖችን መግባት እና አስፈላጊ ስርዓቶችን መቀበል፣ እንዲሁም በዚያ ወደ እርሱ ለመቅረብ መፈለግ፣ ህይወታችሁን ሌላ የአምልኮ አይነት ሊያደርጓቸው በማይችሉ መንገዶች ይባርካል። ለዚህ ምክንያት፣ በአለም አቀፍ ለሚገኙ አባላቶቻችን የቤተመቅደስ በረከቶች እንዲገኙ ለማድረግ የምንችለውን ሁሉ እያደረግን ነን። በሚከተሉት ሥፍራዎች አዲስ ቤተመቅደሶችን ለመገንባት ዕቅዳችንን ዛሬ ሳስተዋውቅ አመስጋኝ ነኝ፦

  • ሬታልሁሉ ጓቲማላ

  • እኳይተስ ፔሩ

  • ቴሬሲና ብራዚል

  • ናታል ብራዚል

  • ቱጉጋሮ ሲቲ፣ ፊሊፒንስ

  • ኢሎይሎ ፊሊፒንስ

  • ጃካርታ ኢንዶኔዢያ

  • ሃምበርገር ጀርመን

  • ሌትብሪጅ አልበርታ ካናዳ

  • ሳን ሆሴ ካሊፎርንስ

  • ቤከርስፊልድ ካሊፎርንያ

  • ስፕሪንግፊልድ፣ ሚዙሪ

  • ሻርለት ኖርዝ ካሮላይና

  • ዊንቸስተር ቨርጂኒያ

  • ሃሪስበርግ፣ ፔንሴልቬኒያ

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የዚህችን ቤተክርስቲያን ጉዳዮች እንደሚመራ ምስክሬን እሰጣለሁ። እርሱን መከተል መጨረሻ የሌለው ደስታ የሚገኝበት ብቸኛ መንገድ እንደሆነ እመሰክራለሁ። ሀይሉ “ፅድቅንና የእግዚአብሔርን ኃይል በታላቅ ክብር [በታጠቁ]” 4 በቃል ኪዳን ጠባቂ ህዝቡ ላይ እየወረደ እንደሆነ አውቃለሁ። ለእያንዳንዳችሁ ያለኝን ፍቅር እና በረከት እየገልፅኩኝ ይህን የምመሰክረው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም ነው፣ አሜን።