2010–2019 (እ.አ.አ)
በውስጡ ያለውን መለኮታዊነት ማግኘት
ኦክተውበር 2015


11:19

በውስጡ ያለውን መለኮታዊነት ማግኘት

በውስጣችን ያሉትን የመለኮታዊ ፍጥረት ፍሬዎችን ለመመገብ እና ለማግኘት ወደዚህች ምድር መጣን።

እህቶች፣ እወዳችኋለሁ! ሕይወት ስጦታ እንደሆነ እመሰክራለሁ። እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ዕቅድ አለው እንዲሁም የየግላችን የሕይወት አላማ ወደዚህ ምድር ከመምጣጣችን በፊት አስቀድሞ ጀመረ።

በቅርቡ የአንድ ሕፃን ልጅን እንደ ጌታ ዕቅድ ክፍል ወደ ምድር የውልደት ተአምርን ላስተውል ቻልኩኝ። እያንዳንዳችን በእናታችን መሃፀን ውስጥ ሆነን ለብዙ ወራት እራሳችንን ለማኖር በሰውነቷ ላይ ጥገኛ በመሆነ በአካል እንዳብራለን። ይሁን እንጂ፣ ከዛ በኋላ፣ ለእናትና ልጅ አስፈላጊ የሆነው የውልደት ሂደት ለየን።

አዲስ የተወለደ

አንድ ልጅ ከመሃፀን ውስጥ ወጥቶ ወደዚች አለም ሲገባ፣ የሙቀትና የብርሃን መለወጥ እንዲሁም በደረቱ ላይ የሚለቀቀው ድንገተኛ ጉልበት የመጀመሪያውን አየር እንዲወስድ ያደርገዋል። እነዛ ትንሽዬ ሳናባዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በድንገት በአየር ይሞላሉ ከዛ የሰውነት ክፍሎቹ ስራቸውን ማከናወን ይጀምራሉ እናም ልጁ መተንፈስ ይጀምራል። እትብቱ ሲታሰር፣ ያ በእናትና ልጅ መካከል ያለ የሕይወት መስመር ለዘላለም ይቆረጣል እናም የሕፃኑ ሕይወት በመድር ላይ ይጀምራል።

ኢዮብ እንድህ አለ፣ “የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፣ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ።”1

“ከሰማይን የተወሰነ ክብር ይዘን”2 ወደዚች ምድር መጣን። “ቤተሰብ፥ ለአለም አዋጅ” እያንዳንዳችን “የተወደድን የሰማይ ወላጆች የመንፈስ ወንድና ሴት ልጆች ነን” እናም “እያንዳንዳችን መለኮታዊ ፍጥረትና እጣ ፈንታ አለን።”3 የሰማይ አባት በደግነቱ የመለኮታዊነቱን የተወሰነ ክፍል አካፈለን። ያ መለኮታዊው ፍጥረት ወላጅ ብቻ ሊረዳው በሚችል መልኩ ከእርሱ በፍቅር እንደ ስጦታ ይመጣል።

በውስጣችን ያለውን የመለኮታዊ ፍጥረት ፍሬዎችን ለማግኘት ወደዚህች ምድር መጣን።

ለምን እንደተወለድን እናውቃለን

እሌኒ ካነን፣ የቀድሞ የወጣት ሴቶች አጠቃላይ ፕሬዘዳንት እንዲህ አሉ፣ “በሴት ሕይውት ውስጥ ሁለት አስፈላጊ ቀኖች አሉ፥ የተወለደችበት ቀንና ለምን እንደተወለደች ያወቀችበት ቀን።”4

ለምን እንደተወለድን እናውቃለን። በዚች ምድር ላይ መንግስቱን ለመገንባት ለመርዳት እና ለልጁ ለኢየሱስ ክርሰቶስ ሁለተኛ ምፅዓት ለመዘጋጀት ስንል መጣን። በምንወስደው በእያንዳንዱ እስትንፋሶች ውስጥ እርሱን ለመከተል እንጥራለን። ወደ አባታችንና ወደ ልጁ ለመቅረብ በምናደርገው ጥረት አማካኝነት በእያንዳንዳችን ውስጥ ያለው መለኮታዊው ፍጥረት ይጠራል እንዲሁም ይጎላል።

የኛ መለኮታዊ ፍጥረት ከግላዊ ክንውኖቻችን፣ ከምናሳካው መሃበራው ማንነታችን፣ ከምንሮጣቸው የማራቶን እሩጫዎች ብዛት ወይም ከዝንኝነታችን እና ከግል ክብራችን ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም። የእኛ መለኮታዊ ፍጥረት ከእግዚአብሔር ነው የሚመጣው። ከውልደታችን በፊት በነበረ ሕይወት ነበር የተመሰረተው እንዲሁም ለዘላለም ይቀጥላል።

ተወደናል

የሰማይ አባታችንን ፍቅር ሲሰማን እና ስንሰጥ ከመለኮታዊ ፍጥረታችን ጋር በሚስማማ መልኩ እናከናውናል። ለመመገብ፣ ለማልማትና ለማሳደግ ምርጫው አለን። ጴጥሮስ “ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች”5 እንሆን ዘንድ “ታላቅ የሆነ ተስፋ” ተሰጥቶናል አለ። ማን እንደሆንን ማለትም የእግዚአብሔር ሴት ልጆች እንደሆንን ስንረዳ፣ እነዛን ታላቅ የሆኑ ተስፋዎች መሰማት እንጀምራለን።

መስታወት ውስጥ ሳይሆን፣ በመስኮት ባሻገር ወደ ውጭ መመልከት፣ እራሳችንን የእርሱ አድርገን እንድንመለከት ይረዳናል። በተፈጥሮ በፀሎት ወደ እርሱ እንዞራለን እንዲሁም ቃሎቹን ለማንበብና ፈቃዱን ለመፈፀም እንጓጓለን። ስልጣናችንን በዙሪያችን ካለው አለም በጎንዮሽ ወይም በፊት ገፅ( ፌስ ቡክ ) ወይም በኢንስታግራም ውስጥ ካሉት ሰዎች ሳይሆን ቀጥተኛ በሆነ መንገድ ከእርሱ እንወስዳለን።

በውስጣችሁ ያለውን የመለኮታዊነት ብልጭታ የትጠራጠሩ ከሆነ፣ በጉልበታችሁ ተንበርኩና የሰማይ አባትን “በእርግጥ እኔ ያንተ ሴት ልጅ ነኝን እናም ትወደኛለህን?”ብላችሁ ጠይቁ። ሽማግሌ ኤም. ረስል ባላርድ እንዲህ አሉ፣ “መንፈስ ቅዱስ ከሚነግራችሁ ጣፋች ከሆኑት መልዕክቶች መካከል አንዱ ጌታ ስለእናንተ እንዴት እንደሚሰማው የሚነግራችሁ ነው።”6

የእርሱ ነን። ጳውሎስ እንዲህ አለ፣ “የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።”7 ብዙውን ጊዜ የመጀመሪያ የምንማረው የሕፃናት ክፍል መዝሙር “እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ” የሚለውን ነው።8 አሁን ያንን የሚወደድ “እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ” የሚለውን ሐረግ ወስደን “ስለዚህ ምን?”የሚሉትን ቃሎች የምንጨምርበት ሰአት ነው። ምንአልባት እንደነዚህ አይነት ጥያቄዎችን መጠየቅ እንችል ይሆናል፥ “እንደ እግዚአብሔር ልጅ ሕይወቴል ለመኖር ምን ላድርግ?” “በውስጤ ያለውን መለኮታዊ ተፈጥሮ እንዴት ማዳበር እችላለው?”

ፕሬዘዳንት ዲይተር ኤፍ ኡክዶርፍ እንዲህ አሉ፣ “እግዚአብሔር ማሰብ ከምትችሉት ነገር በላይ እጅግ ድንቅ ለሆነ ወደፊት ሊያዘጋጃችሁ ላካችሁ።”9 ያ ወደፊት የ8 አመት ሆናችሁም የ108 አመት ዝምብላችሁ ከመኖር በላይ ስታደርጉ ህያው ይሆናል፥ የተፈጠራችሁበትን አላማ ለማሟላት ሕይወታችሁን ስትኖሩ ይመጣል። ይህ ጌታን ወደ ሕይወታችሁ ይጋባዛል እና የእርሱን ፍቃድ የራሳችሁ እንዲሆን መፍቀድ ትጀምራላችሁ።

በመለኮታዊ ፍጥረታችን ምክንያት እንማራለን

መለኮታዊ ፍጥረት እነዚህን ዘላለማዊ እውነታዎችን የማወቅ ምኞት ወደእኛ ይተነፍሳል።

ኤሚ የምትባል ወጣት ሴት በቅርቡ እንደዚህ ብላ ስትፅፍ ይህን ትምህርት አስተማረችኝ፥ “በነዚህ ዘመናት ወጣት መሆን ከባድ ነው። መንገዱ እየጠበበ ነው። ሴጣን በእውነት እየጣረ ነው። ትክክለኛ ወይም ስህተተኛ መሆን ነው እንጂ መካከል ላይ መሆን አይቻልም።”

እንዲህ በማለትም ቀጠለች፥ “መልካም ጓደኞችን ማግኘት አንድአንድ ጊዜ ከባድ ነው። የማይለዩኝ ጥሩ ጓደኞች አሉኝ ብላችሁ ስታስቡ እንኳን በማንኛውም መንስኤ ሊቀየር ይችላል። ነገሮች ከጓደኞቼ ጋር ሲበላሹ ጓደኞች የሚሆኑኝ ቤተሰብ፣ የሰማይ አባት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እና መንፈስ ቅዱስ ስላሉኝ ለዚህ ነው በጣም ደስተኛ የሆንኩት።”

ኤሚ መናገሯን ቀጠለች፣ “አንድ ምሽት ተረብሼ ነበርና ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንዳላወቅኩኝ ለእህቴ ነገርኳት።”

በዛ ምሽት ወደ በኋላ ላይ የኤሚ እህት ሽማግሌ ጀፍሪ አር ሆላንድን ያሉትን በመጥቀስ አጭር የጽሑፍ መልዕክት ላከችላት፥ “ተስፋ እትቁረጡ።… እንዳታቆሚ። መራመዳችሁን ቀጥሉ። መሞከራችሁን ቀጥሉ። ወደፊት እርዳታና ደስታ አለና። … መጨረሻ ላይ ሁሉም መልካም ይሆናል። በእግዚአብሔር ተማመኑ እናም በሚመጡት መልካም ነገሮች እመኑ።”10

ኤሚ እንዲህ አስረዳች፣ “ያንን ማንበቤንና በእርግጥ እግዚአብሔር ለእኔ ካለ ከእርሱ ፍቅር እንደሚሰማኝ እየፀለይኩኝ እንደነበር አስታውሳለሁ።”

እንዲህ አለች፥ “እዛ እንዳለ ልክ እንደጠየቅኩኝና እንዳመንኩኝ እጅግ ድንቅ የሆነ ፍቅር ያለው የደስታ ስሜት ተሰማኝ።” ቃላቶች አይገልፁትም። እሱ እዛ እንደነበር እና እንደወደደኝ አወቅኩኝ።

የእርሱ ልጅ ስልሆናችሁ፣ ምን መሆን እንደምትችሉ ያውቃል። ፍርሃታችሁንና ህልማችሁን ያውቃል። በእምቅ አቅማችሁ ይደሰታል። በፀሎት ወደ እርሱ እንድትመጡ ይመኝላችኋል። የእርሱ ልጅ ስለሆናችሁ፣ እናንተ ብቻ አትፈልጉትም፣ነገር ግን እርሱም ይፈልጋችኋል። አሁን በዚህ ስብሰባ ውስጥ በዙሪያችሁ አብረዋችሁ የተቀመጡት ሁሉ ይፈልጓችኋል። አለም ይፈልጋችኋል እንዲሁ የእናንተ መለኮታዊ ተፈጥሮ ለእርሱ ልጆች በሙሉ የእርሱ ታማኝ ደቀ መዝሙር እንድትሆኗቸው ይፈቅዱላችኋል። በራሳችን መለኮታዊነትን ማየት ስንጀምር በሌሎችም ማየት እንችላለን።

በመለኮታዊ ፍጥረታችን ምክንያት እናገለግላለን

መለኮታዊ ፍጥረት ሌሎችን የማገልገል ፍላጎት ይተነፍስብናል።

በኢትዮጵያ ርሀብ ዘመን የነብሩ እናት እና ልጅ

በቅርቡ ሼረን ኢውባንክ የበጎ አድራጎት አገልግሎትና የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ልግስናዎች መሪ በሽማግሌ ግሌን ኤል ፔስ የተካፈለ ልምድን ተናገረ። በኢትዮጵያ (እ.አ.አ) በ1980ዎቹ አጋማሽ ላይ የተንሰራፋ ድርቅ እና የከፋ ረሀብ ነበረ። በቦታው ላይ መድረስ ለሚችሉት ሰዎች ሁሉ እርዳታ ለመስጠት ውኃና ምግብ ያላቸው የመመገቢያ ጣቢያዎች ተቋቋሙ። አንድ የተራቡ አዛውንት ወደ መመገቢያው ጣቢያ ለመድረስ እረጅም መንገድ እየተጓዙ ነበር። የአንድን ሕፃን ልጅ ለቅሶ ሲሰሙ በአንድ መንደር ውስጥ እያለፉ ነበር። ከሞተች እናቱ አጠገብ መሬት ላይ ተቀምጦ የነበረውን ህፃን ልጅ እስከሚያገኙት ድረስ ፈለጉት። ልጁን ከመሬት በማንሳት አዛውንቱ ወደ መመገቢያ ጣቢያው 25 ማይልስ (40 ኪ.ሜ.) መራመዳቸውን ቀጠሉ። ሲደርሱ፣ የእርሳቸው የመጀመሪያ ቃላቶች “እርቦኛል” ወይም “እርዱኝ” አልነበሩም። “ለዚህ ሕፃን ልጅ ምን መደረግ ይችላል?”11 የሚሉ ነበሩ።

በውስጣችን ያለው መለኮታዊ ፍጥረት ለሌሎች ለመድረስ ፍላጎታችንን ይጨምራል እንዲሁም ተግባራዊ እንድናደርገው ያሳስበናል። የሰማይ አባትና ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ለማድረግ ጥንካሬን እንድናገኝ ሊረዱን ይችላሉ። ጌታ እንዲህ እያለ እየጠየቀን ይሆን፣ “ለዚህች ሴት ልጅ፣ ለዚህ ወንድም፣ ለዚህ አባት ወይም ለዚህ ጓደኛ ምን መደረግ ይቻላል?”

በመንፈስ ቅዱስ ሹክሹክታ አማካኝነት ነው የተጠራጣሪ መለኮታዊ ፍጥረት ከአየር መቆራረጥ በኋላ እንደገና ለመተንፈስ ሰላምን የሚያገኘው።

ነብዩ ሲናገር ቃሎቹ መለኮታዊ ፍጥረታችን ጋር ይደርሳሉ እናም ለመከተል ጥንካሬ ይሰጡናል።

በእያንዳንዱ ሳምንት ቅዱስ ቁርባን መካፈል በውስጣችን ላለው መለኮታዊነት ተስፋ ይተነፍስበታል እናም አዳኛችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እናስታውሳለን።

በውስጣችሁ ያለውን መለኮታዊ ፍጥረት ጥልቀት ለማግኘት ስትሹ፣ ውድ ስጦታዎቻችሁን የበለጠ ማሟላት እንደምትጀምሩ ቃል እገባላችኋለሁ። “ወደ እግዚአብሔር እስትንፋስ [ወደሰጠን] [ወደምንመለስበት]”12 ወደ እርሱ መመለሻ መንገድን በመጓዝ የእርሱ ሴት ልጆች እንድትሆኑ እንዲመራችሁ ፍቀዱለት። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ያዕቆብ 33፥4

  2. “Ode፥ Intimations of Immortality from Recollections of Early Childhood፣” The Complete Poetical Works of William Wordsworth (1924)፣ 359።

  3. “ቤተሰብ፥ ለአለም አዋጅ፣” Ensign or Liahona፣ ህዳር 2010፣ 129።

  4. እሌይን ካነን፣ Elaine Cannon፣ በ “‘Let Me Soar፣’ Women Counseled፣” Church News፣ ውስጥ ጥቅምት 17፣ 1981፣ 3።

  5. 2 ጴጥሮስ 1፥4

  6. ኤም. ራስል ባለርድ፣ “Women of Righteousness፣” Ensign፣ ሚያዝያ 2002፣ 72; Liahona፣ ታህሳስ 2002፣ 42።

  7. ሮሜ 8፥16

  8. “የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፣” Hymns፣ no. 301 ተመልከቱ።

  9. ዲየትር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “Living the Gospel Joyful፣” Ensign or Liahona፣ ህዳር 2014፣ 121።

  10. ጀፍሪ አር. ሆላንድ፣ “An High Priest of Good Things to Come፣” Ensign፣ ህዳር 1999፣ 38፤ Liahona፣ ጥር 2000፣ 45።

  11. ግለን ኤል. ፔስ፣ “Infinite Needs and Finite Resources፣” Ensign፣ ሰኔ 1993፣ 52፤ Tambuli፣ መጋቢት 1995፣ 18–19።

  12. 2 ኔፊ 9፥26