ጓደኛ
ሩት እና ኑኃሚን
መስከረም 2026 (እ.አ.አ)


“ሩት እና ኑኃሚን፣” ጓደኛ፣ መስከረም 2026 (እ.አ.አ)፣ 46–48።

ወርሃዊ የጓደኛ መልዕክት፣ መስከረም 2026 (እ.አ.አ)

ሩት እና ኑኃሚን

ኑኃሚን እና ቤተሰቧ

የኑኃሚን ቤተሰብ በይሁዳ ይኖሩ ነበር። በረሃብ ምክንያት በቂ ምግብ ስላልነበራቸው ወደ ሞዓብ ተጓዙ።

ኑኃሚን፣ ሩት፣ እና ዖርፋ እርስ በርሳቸው ሲጸጸናኑ

በሞዓብም፣ የኑኃሚን ባል ሞተ እናም ልጆቿ ዖርፋ እና ሩት የተባሉ ሴቶችን አገቡ። እነርሱም ኑኃሚንን ለአስር አመታት ተንከባከቡ። ከዚያም የዖርፋ እና የሩት ባለቤቶች ሞቱ። አሁን ሴቶቹ ብቻቸውን ነበሩ።

ኑኃሚን የተቀመጠችበትን ግመል ሩት እየመራች

ዖርፋ ወደ ቤቷ ተመለሰች። ነገር ግን ሩት ለመቆየትና ኑኃሚንን ለመንከባከብ ፈለገች። ሩት እና ኑኃሚን በይሁዳ ምድር እንደገና ሰብሎች እንዳሉ ስለሰሙ ወደዚያ ተጓዙ።

ሩት በእርሻ ውስጥ እህል ስትቃርም

እነርሱም በመከሩ ወቅት ደረሱ። ቦዔዝ የተባለ የኑኃሚን ዘመድ እርሻዎች ነበሩት። ሩት የተረፈውን እህል ከእርሻው ውስጥ እንድትወስድ ፈቀደላት። ይህም ከባድ ስራ ነበር።

ሩት እና ቦዔዝ ሲነጋገሩ

ቦዔዝ ሩት ጠንክራ ስለሰራች እና ለኑኃሚን እና ለጌታ ታማኝ በመሆኗ አክብሯት ነበር።

ሩት እና ቦዔዝ

ሩት ቦዔዝ እንዲያገባት ጠየቀችው። ቦዔዝም ሩት ታማኝ እና በጎ ሴት እንደነበረች ያውቅ ነበር። እርሱም ተስማማ።

ሩት፣ ቦዔዝ፣ እና ኑኃሚን ከህጻን ጋር

ሩት እና ቦዔዝ ተጋቡ እና ወንድ ልጅም ወለዱ። ከብዙ አመታት በኋላ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ቤተሰብ ዘር ተወልዶ ነበር።

የሚቀለም ገፅ

በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት፣ ንስሐ ገብቼ ንጹህ መሆን እችላለሁ

አንድ ወጣት ወንድ በአግዳሚ ወንበሩ ላይ ለተቀመጠች ወጣት ሴት ቅዱስ ቁርባንን ሲያስተላልፍ የሚያሳይ የሚቀለም ገጽ

ስዕል በኦድሪ ደይ። ለቤተክርስቲያኗ ጥቅም ብቻ መባዛት ይችላል።

መልካም ምርጫን እንድታደርጉ ለማስታወስ ምን ይረዳችኋል?