2023 (እ.አ.አ)
ኢየሱስ መንገዱን አሳይቶናል።
ነሐሴ 2023 (እ.አ.አ)


“ኢየሱስ መንገዱን አሳይቶናል፣” ጓደኛ፣ ነሐሴ 2023 (እ.አ.አ)፣ 4–5.።

ወርሃዊ የጓደኛ መልእክት፣ ነሐሴ 2023 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ መንገዱን አሳይቶናል።

ምስል
Alt ጽሑፍ

ስዕላዊ መግለጫዎች በዳን በር

ኢየሱስ ክርስቶስ የሰማይ አባት ልጅ ነው። አንድ ቀን ወደ ሰማይ አባት እንዴት እንደምንመለስ ሊያሳየን ወደ ምድር መጣ። ኢየሱስ ተጠምቆ ነበር። እኛም መጠመቅ እንደሚገባን አስተምሯል።

ምስል
alt ጽሑፍ

ኢየሱስ እንዴት እንደምንኖር አስተምሮናል። ሁላችንንም ወዶናል እንዲሁም ረድቶናል። እንድንከተለው ይፈልጋል።

ምስል
alt ጽሑፍ

ኢየሱስ ሕመማችን ሁሉ ተሰምቶታል እንዲሁም ስለሐጢያቶቻችን ተሰቃይቷል። ከዚያም ለእኛ ሲል ሞተ፡፡ ይህም የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ይባላል። ከሞት ተነሥቷል። ያ ማለት አሁንም በህይወት ይኖራል ማለት ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ከሞትን በኋላ እንደገና በህይወት እንኖራለን።

ምስል
alt ጽሑፍ

ኢየሱስ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ያደረገው ስለሚወደን ነው። በእርሱ ምክንያት አንድ ቀን ከሰማይ አባታችን እና ከቤተሰቦቻችን ጋር መኖር እንችላለን።

ምስል
alt ጽሑፍ

በመጠመቅ ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል እንችላለን። ሌሎችን በመውደድ እና በመርዳት እንዲሁም ትዕዛዛቱን በመጠበቅ በየቀኑ ልንከተለው እንችላለን።