2023 (እ.አ.አ)
ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሳ
ሚያዝያ 2023 (እ.አ.አ)


“ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሳ፣” ጓደኛ፣ ሚያዝያ 2023 (እ.አ.አ)፣ 46–47።

ወርሃዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ ሚያዝያ 2023 (እ.አ.አ)

ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት አስነሳ

ምስል
ኢየሱስ ከማርያም፣ ማርታ እና አልዓዛር ጋር ተቀምጦ

ሥዕል በኤፕርል ስቶት

ማርያም እና ማርታ አልዓዛር የሚባል ወንድም ነበራቸው። የኢየሱስ ክርስቶስ ጓደኖች ነበሩ።

ምስል
ክርስቶስ ማርያምን እና ማርታን ሲያቅፍ

አልዓዛር በጣም ታመመ። ከዚያም ሞተ። ማርያም እና ማርታ አዘኑ። ኢየሱስ ሲመጣ አብሯቸው አለቀሰ።

ምስል
ኢየሱስ በአልዓዛር መቃብር ውስጥ ቆሞ

ከዚያም ኢየሱስ ወደ አልዓዛር መቃብር አብሯቸው ሄደ። እንዲህ አለ፣ “አልዓዛር ሆይ፣ ወደ ውጭ ና።”

ምስል
ኢየሱስ አልዓዛርን ከመቃብር ውስጥ እንዲወጣ ሲያግዘው

አልዓዛርም ቆመ እና ከመቃብሩ ወጣ። እንደገና ህያው ሆነ። በኢየሱስ አማካኝነት እኛም በድጋሜ መኖር እንችላለን።

የሚቀባ ገፅ

ኢየሱስ ክርስቶስ ህያው ነው

ምስል
የኢየሱስን ፎቶ የያዘ ልጅ የሚያሳይ የሚቀባ ገፅ

ሥዕል በኤፕርል ስቶት

በፋሲካ ጊዜ ኢየሱስን እንዴት ነው የምታስታውሱት?