2023 (እ.አ.አ)
ለኢየሱስ ስጦታዎች
ጥር 2023 (እ.አ.አ)


“ለኢየሱስ ስጦታዎች፣” ወርሃዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ ጥር 2023 (እ.አ.አ)

“ለኢየሱስ ስጦታዎች”

ወርሃዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ ጥር 2023 (እ.አ.አ)

ለኢየሱስ ስጦታዎች

ምስል
ማርያም ከህፃኑ ኢየሱስ ጋር

ሥዕል በኤፕርል ስቶት

ምስል
ሰብዓ ሰገል እየተጓዙ

ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ጊዜ አዲስ ኮከብ በሰማይ ላይ ወጣች። ሰብዓ ሰገል የኮከቧ ትርጉም ኢየሱስ ተወልዷል ማለት እንደሆነ አውቀዋል። ኮከቧን ተከተሉ። ለብዙ ቀናት ተጓዙ።

ምስል
ሰብዓ ሰገል ለኢየሱስ ስጦታ እየሰጡ

ሰብዓ ሰገል ኢየሱስን ባገኙት ጊዜ ስጦታዎችን ሰጡት። በፊቱ ተንበርክከው ሰገዱለት። እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አወቁ።

ምስል
ልጆች በበረዶ አካፋ እየዛቁ።

እኔም ለኢየሱስ ስጦታ መስጠት እችላለሁ። የእሱን ምሳሌ በመከተል እና ለሌሎች ፍቅር በማሳየት ለእርሱ ያለኝን ፍቅር ማሳየት እችላለሁ።

የሚቀባ ገፅ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለኢየሱስ ያስተምራል።

ምስል
አባት እና ሴት ልጅ ቅዱሳት መጻህፍትን እያነበቡ

ለማውረድ ስዕሉ ላይ ጠቅ ያድርጉ።

ሥዕል በኤፕርል ስቶት

ኢየሱስን ለመምሰል እየሞከራችሁ ያላችሁት እንዴት ነው?