2022 (እ.አ.አ)
ኢሳይያስ ስለኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሯል
መስከረም 2022 (እ.አ.አ)


“ኢሳይያስ ስለኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሩአል፣” ወርሃዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ መስከረም 2022 (እ.አ.አ)

“ኢሳይያስ ስለኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሯል”

ወርሃዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ መስከረም 2022 (እ.አ.አ)

ኢሳይያስ ስለኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሯል

ምስል
ኢሳይያስ እየጻፈ

ሥዕል በኤፕርል ስቶት

ኢሳይያስ ነቢይ ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወለዱ በፊት ይኖር ነበር። ነገር ግን ኢየሱስ እንደሚመጣ ያውቅ ነበር።

ምስል
ኢሳይያስ እየተናገረ

ኢሳይያስ ኢየሱስ እንደ እግዚአብሔር ልጅ እንደሚወለድ ተናገረ። ኢየሱስ ሌሎችን ይረዳል እናም ይፈውሳል።

ምስል
ዮሴፍ፣ ማርያም፣ እና ህጻኑ ኢየሱስ

ኢሳይያስ ደግሞም ኢየሱስ ወደምድር እንደሚመጣ ተናገረ። እርሱ የሰላም ልዑል ተብሎ ይጠራል። እኛን በጣም ስለሚወደን ህይወቱን ለእኛ አሳልፎ ይሰጣል።

ምስል
በትንሳኤ የተነሳ ኢየሱስ ክርስቶስ

ኢሳይያስ ያስተማራቸው ነገሮች ደረሱ። ከብዙ አመታት በኋላ፣ ኢየሱስ ወደምድር መጣ። መንገዱን አሳየን። ሞተ እና እንደገናም ኖረ። ዛሬም ህያው ነው!

ምስል
እናት ለልጆች ስለኢየሱስ ክርስቶስ ስታነብ።

ስለኢየሱስ ክርስቶስ ለመማር እችላለሁ። እርሱ ለእኔ ምን እንዳደረገ ሳስታውስ፣ ሰላም እና ተስፋ ሊሰማኝ ይችላል።

የሚቀባ ገፅ

ስለኢየሱስ ክርስቶስ ለመማር እችላለሁ

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስከአንድ ሴት ጋር ለመነጋገር ተንበርክኮ

ለማውረድ ስዕሉ ላይ ጠቅ ያድርጉ።

ሥዕል በኤፕርል ስቶት

ለኢየሱስ የምትወደው/የምትወጂው ታሪክ ምንድን ነው?