2022 (እ.አ.አ)
ሩት እና ኑኃሚን
ሰኔ 2022 (እ.አ.አ)


“ሩት እና ኑኃሚን፣” ወርሀዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ የካቲት 2022 (እ.አ.አ)

“ሩት እና ኑኃሚን”

ወርሃዊ የጓደኛ መልእክቶች፣ ሰኔ 2022 (እ.አ.አ)

ሩት እና ኑኃሚን

ምስል
ሩት ከኑኃሚን ቤተሰብ ጋር ጋብቻ ስትፈጽም

ሥዕል በኤፕርል ስቶት

ኑኃሚን እና ቤተሰቧ በድርቅ ምክንያት ወደአዲስ አገር መጡ። ሩት ከተባለች ወጣት ጋር ተገናኙ። ሩት የኑኃሚንን ወንድ ልጅ አገባች።

ምስል
ሩት በሞት ጣር ላይ ካለው ባለቤቷ ጋር

ከዚያም የሩት ባለቤት ሞተ። ሩት በጣም አዘነች።

ምስል
ኑኃሚን

ኑኃሚንም በጣም አዘነች። የሚንከባከባት አንድም የቀራት ቤተሰብ አልነበራትም። ወደመጣችበት አገር ተመልሳ ለመሄድ ወሰነች፡፡

ምስል
ኑኃሚን እና ሩት

ኑኃሚን ወደ ቤተሰቧ እንድትመለስ ለሩት ነገረቻት። ነገር ግን ሩት ኑኃሚንን ትወዳት ነበር። ከኑኃሚን ጋር ለመምጣት እና እርሷን ለመንከባከብ ቃል ገባች።

ምስል
ሩት እየቃረመች

ሩት እና ኑኃሚን ድሆች ነበሩ። ስለዚህ ሩት ምግባቸውን ለማግኘት ጠንክራ ትሰራ ነበር።

ምስል
ቦዔዝ እና ሩት በእርሻ ውስጥ

አንድ ቀን ቦዔዝ የተባለ ሰው ከእርሻዎቹ በአንዱ የተራረፈ እህል ስትበስብ አያት።

ምስል
ቦዔዝ ከአገልጋዩ ጋር

ቦዔዝ ደግ ነበር። ተጨማሪ እህል ለሩት እንዲተው ለአገልጋዮቹ ነገራቸው።

ምስል
ሩት፣ ቦዔዝ፣ እና ኑኃሚን ከህጻን ጋር

በኋላም ሩት እና ቦዔዝ ተጋቡ። ወንድ ልጅም ወለዱ። ኑኃሚን ልጁን በመንከባከብ ረዳች።

ምስል
ቤተሰብ ምግብ እየበሉ

ሌሎችን በመንከባከብ መርዳት እችላለሁ። ለተቸገሩ ደግ ለመሆን እችላለሁ።

የሚቀባ ገፅ

ሌሎችን መንከባከብ እችላለሁ

ምስል
ልጆች ከወንድ ቅድመአያታቸው ጋር

ለማውረድ ስዕሉ ላይ ጠቅ ያድርጉ።

ሥዕል በኤፕርል ስቶት

ማንን መርዳት ትችላላችሁ?