2021 (እ.አ.አ)
በመጥምቁ ዮሐንስ የተደረገ ጉብኝት
የካቲት 2021 (እ.አ.አ)


“በመጥምቁ ዮሐንስ የተደረገ ጉብኝት፣” ጓደኛ፣ የካቲት 2021 (እ.አ.አ)

ወርሃዊ የጓደኛ መልእክት፣ የካቲት 2021 (እ.አ.አ)

በመጥምቁ ዮሐንስ የተደረገ ጉብኝት

ምስል
ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውድሪ ሲጸልዩ

ስእል በአፕርይል ስቶት

አንድ ቀን ጆሴፍ ስሚዝ እና ኦሊቨር ካውድሪ አንድ ጥያቄ ነበራቸው። ለመጠመቅ ትክክለኛው መንገድ ምን ነበር? መልሱን ለማወቅ ጸለዩ።

ምስል
መጥምቁ ዮሐንስ

አንድ መልአክም መጣ። መጥምቁ ዮሐንስ ነበር። እርሱም ኢየሱስን አጥምቆ ነበር። ሰዎችን ለማጥመቅ የክህነት ስልጣን እንደሚያስፈልጋቸው ነገራቸው።

ምስል
መጥምቁ ዮሐንስ ለጆሴፍ ስሚዝ የአሮናዊ ክህነትን ሲሰጠው

ዮሐንስ ጆሴፍን እና ኦሊቨርን ባረካቸው። የክህነትን ስልጣንም ሰጣቸው። አሁን ኢየሱስ በተጠመቀበት መንገድ ሰዎችን ማጥመቅ ይችላሉ።

ምስል
ኦሊቨር ካውድሪ ጆሴፍ ስሚዝን እያጠመቀው

ጆሴፍ ኦሊቨርን በወንዝ ውስጥ አጠመቀው። ከዚያም ኦሊቨር ጆሴፍን አጠመቀው። በኋላም ሌሎች ብዙዎች ተጠመቁ።

ምስል
አባት ሴት ልጁን እያጠመቀ

የሰማይ አባት የጆሴፍ ስሚዝን ጸሎት ስለመለሰ፣ ክህነት በምድር ላይ ተመልሷል! እኔ እንደ ኢየሱስ መጠመቅ እችላለሁ።

የሚቀባ ገፅ

መጠመቅ እንችላለን

ምስል
A pencil drawing of Joseph baptizing Oliver Cowdery.

ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ምን ማድረግ ትችላላችሁ?