ቅዱሳት መጻህፍት
ሙሴ ፯


ምዕራፍ ፯

[ታህሳስ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.)]

ሔኖክ ሕዝብን አስተማረ፣ መራ፣ እና ተራሮችንም አንቀሳቀሰ—የጽዮን ከተማም ተቋቋመ—ሔኖክ የሰው ልጅ መምጣትን፣ የኃጢአት ክፍያ መስዋዕቱን፣ እና የቅዱሳንን ትንሳኤን አስቀድሞ አየ—ዳግሞ መመለስን፣ መሰብሰብን፣ የክርስቶስን ዳግም ምፅዓት፣ እና የፅዮንን መመለስ አስቀድሞ አየ።

እናም እንዲህ ሆነ ሔኖክ ንግግሩን እንዲህ በማለት ቀጠለ፥ እነሆ፣ አባታችን አዳም እነዚህን ነገሮች አስተማረ፣ እና ብዙዎችም አመኑና የእግዚአብሔር ልጆች ሆኑ፣ እና ብዙዎችም አላመኑምና በኃጢአታቸውም ሞቱ፣ እና በፍርሀት፣ በስቃይ፣ የእግዚአብሐርን እሳት አይነት ቁጣ እስከሚፈስባቸው ድረስ ይጠብቃሉ።

ከዚህም ጊዜ ጀምሮ ሔኖክ መተንበይ ጀመረ፣ ለህዝቡም እንዲህ አለ፥ እየተጓዝኩ በማሁጃ ላይ ስቆም፣ እና ወደ እግዚአብሔር ስጮኽ፣ ከሰማይ ድምጽ መጣ እንዲህም አለኝ—ተመለስ፣ እና ወደ ስምዖን ተራራ ውጣ።

እናም እንዲህ ሆነ ተመለስኩ፣ እና በተራራውም ላይ ወጣሁ፤ እና በተራራው ላይ ቆሜ ሳለሁ፣ ሰማያት ሲከፈቱ አየሁ፣ እና ክብርንም ለብሼም ነበር፤

እና ጌታንም አየሁ፤ በፊት ለፊቴም ቆሞ፣ እና ሰው ከሌላው ሰው ጋር እንደሚነጋገርም ፊት ለፊት አነጋገረኝ፤ እናም እንዲህም አለኝ፥ ተመልከት፣ እና ለብዙ ትውልዶች ለሚሆን ጊዜ አለምን አሳይሀለሁ።

እናም እንዲህ ሆነ፣ እናም አስተውሉ፣ በሹም ሸለቆ ውስጥ በድንኳኖች ውስጥ የሚኖሩትንም የሹምን ህዝብ አየሁ።

ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፥ ተመልከት፤ እና ወደ ሰሜን ተመለከትኩኝ፣ እና በድንኳኖች ውስጥ የሚኖሩትን የከነዓንን ህዝብ አየሁ።

ጌታም ተንብይ አለኝ፤ እና እኔም እንዲህ ብዬ ተነበይኩ፥ እነሆ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ የከነዓን ሰዎች ለጦርነት ተዘጋጅተው ወደ ሹም ህዝብ ይሄዳሉ፣ እናም ፈጽመው እስኪጠፉ ድረስ ይገድሏቸዋል፤ እና የከነዓን ህዝብም በመሬቱ ራሳቸውን ይከፋፍላሉ፣ እናም መሬቱም ዳተኛና ፍሬ ቢስ ይሆናል፣ እና ከከነዓን ህዝብ ሌላ ማንም በዚያ መኖር አይችልም።

እነሆም፣ ጌታ መሬቱን በብዙ ሙቀት ይረግመዋል፣ በዳተኛነትም ለዘለአለም በእዚያ ይሆናል፤ እና በሁሉም ህዝብ ይጠሉ ዘንድ፣ በከነዓን ልጆች ላይ ሁሉ ጥቁርነት መጣባቸው።

እናም እንዲህ ሆነ ጌታም እንዲህ አለኝ፥ ተመልከት፤ እና ተመለከትኩኝ፣ እና የሼረንን ምድር፣ እና የሔኖክን ምድር፣ እናም የኦምነርን ምድር፣ እናም የሄኒን ምድር፣ እናም የሴምን ምድር፣ እናም የሃነርን ምድር፣ እናም የሃናአኒሀህን ምድር፣ እናም እዚያ የሚኖሩትን ሁሉ አየኋቸው።

እናም ጌታ እንዲህ አለኝ፥ ወደነዚህ ህዝቦች ሂድ፣ እና እንዲህም በላቸው—ንስሀ ግቡ፣ አለበለዚያም መጥቼ በርግማን አጠፋቸዋለሁ፣ እና ይሞታሉ።

፲፩ እናም በአብ፣ እና በጸጋና በእውነት በተሞላው በወልድ፣ እና ስለአብና ወልድ ምስክር በሚሰጠው በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዳጠምቅ ትእዛዝም ሰጠኝ።

፲፪ እና እንዲህ ሆነ ሔኖክ ከከነዓን ህዝቦች በስተቀር ህዝቦችን በሙሉ ንስሀ እንዲገቡ መጥራትን ቀጠለ።

፲፫ እና የሔኖክ እምነት ታላቅ ስለነበረ የእግዚአብሔር ህዝቦችን መራ፣ እና ጠላቶቻቸውም ለጦርነት መጡባቸውም፣ የጌታን ቃል ተናገረ፣ እና መሬትም ተንቀጠቀጠች፣ እና ተራሮችም በትእዛዙ ምክንያት ሸሹ፤ እና የወንዝ ውሀዎችም መንገዳቸውን ቀየሩ፤ እና የአምበሶችም ግሳት ከዱር ይሰማ ነበር፤ እና የሔኖክም ቃላት በጣም ሀይለኛ ስለነበሩና እግዚአብሔር የሰጠው ቋንቋ በጣም ሀይለኛ ስለነበር ሁሉም ህዝቦች ታላቅ ፍርሀት ነበረባቸው።

፲፬ ከጥልቅ ባህር ውስጥም የደረቀ መሬትም ወጣ፣ እና የእግዚአብሔር ህዝብ ጠላቶች ፍርሀትም ታላቅ ስለነበር ሸሹ እና በሩቅም ቆሙ እና ከባህር ውስጥ ወደ ወጣው መሬትም ሄዱ።

፲፭ ደግሞም የሀገሩ ግዙፍ ሰዎችም በሩቅ ቆሙ፤ እናም ከእግዚአብሔር ጋር በተዋጉት ህዝቦች ሁሉ ላይ እርግማን መጣ።

፲፮ እና ከዚያም ጊዜ በኋላ በመካከላቸው ጦርነቶችና ደም ማፋሰስ ነበር፤ ነገር ግን ጌታ መጣ እና ከህዝቡም ጋር ኖረ፣ እና እነርሱም በፅድቅ ኖሩ።

፲፯ በህዝቡ ላይ ያረፈው የጌታ ክብር ታላቅ ስለነበር፣ የእግዚአብሔርም ፍርሀት በሁሉም ህዝብ ላይ ነበር። እግዚአብሔርም ምድሪቱን ባረከ፣ እና በተራራውና በታላቅ ስፍራዎችም ተባረኩ፣ እና በለጸጉም።

፲፰ እነርሱ አንድ ልብ እና አንድ አእምሮ ስለነበሩ፣ እና በጽድቅም ስለኖሩ፣ ጌታ ህዝቡን ፅዮን ብሎ ጠራቸው፤ እና በመካከላቸውም ማንም ድሀ አልነበረም።

፲፱ እና ሔኖክም በጽድቅ ለእግዚአብሔር ህዝብ መሰበክን ቀጠለ። በእርሱም ቀናት እንዲህ ሆነ፣ የቅድስና፣ እንዲሁም ፅዮን፣ ተብሎ የተጠራ ከተማም መሰረተ።

እንዲህም ሆነ ሔኖክ ከጌታ ጋር ተነጋገረ፤ እና ለጌታም እንዲህ አለው፥ ፅዮን በእርግጥም በደህንነት ለዘለአለም ትኖራለች። ነገር ግን ጌታ ለሔኖክ እንዲህ አለው፥ ፅዮንን ባርኬአለሁ፣ የሚቀሩትን ህዝቦች ግን ረግሜአለሁ።

፳፩ እንዲህም ሆነ ጌታ ለሔኖክ የምድርን ነዋሪዎችን በሙሉ አሳየው፤ ፅዮን ከጊዜ በኋላ ወደ ሰማይ እንደምትወሰድም ተመለከተ አስተዋለም። እና ጌታም ለሔኖክ እንዲህ አለው፥ እነሆ ለዘለአለም መኖሪያዬ ትሆናለች።

፳፪ ሔኖክም ደግሞም የቀሩትን የአዳም ልጆች የሆኑትን ህዝቦች አየ፤ እና እነርሱም ከቃየን ዘሮች በስተቀር ሁሉም የአዳም ልጆች ድብልቆች ነበሩ፣ የቃየን ዘሮች ጥቁር ነበሩ፣ እና ከእነርሱ መካከል ስፍራ አልነበራቸውምና።

፳፫ ከዚያም በኋላ ፅዮን ወደ ሰማይ ተወሰደች፣ እናም የምድርም ሀገሮች ሁሉም ከእርሱ ፊት እንደነበሩ ሔኖክ አየ አስተዋለም፤

፳፬ እና በትውልድ ላይ ትውልድም መጣ፤ እና ሔኖክም ከፍ ብሎ ወደላይ ተነስቶ ነበር፣ እንዲሁም በአብና በሰው ልጅ እቅፍ ውስጥም ነበር፤ እና እነሆ፣ የሰይጣን ሃይል በምድር ፊት ሁሉ ላይ ነበር።

፳፭ እና መላእክት ከሰማይ ሲወርዱም አየ፤ እና ታላቅ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማ፥ በምድር ለሚኖሩት ወዮ፣ ወዮ።

፳፮ ሰይጣንንም አየ፤ እና በእጁም ታላቅ ሰንሰለት ነበረው፣ እና ይህም ምድርን በሙሉ በጭለማ ሸፈነ፤ እርሱም ቀና ብሎ ሳቀ፣ እና የእርሱም መላእክት ተደሰቱ።

፳፯ እና ሔኖክ መላእክት የአብና ወልድ ምስክር ይዘው ከሰማይ ሲወርዱ አየ፤ እና መንፈስ ቅዱስ በብዙዎች ላይ አረፈ፣ እና እነርሱም በሰማይ ሀይሎች ወደ ፅዮን አረጉ።

፳፰ እንዲህም ሆነ እግዚአብሔር የቀሩትን ህዝቦች ተመለከተ፣ እናም አለቀሰ፤ ስለዚህም ሔኖክ እንዲህ ብሎ መሰከረ፥ ለምንድን ነው ሰማያት የሚያለቅሱት፣ እና እምባቸውን እንደ ዝናብ በተራራው ላይ እንደሚፈስ የሚያደርጉት?

፳፱ እና ሔኖክ ለጌታ እንዲህ አለ፥ ቅዱስ እና ከዘለአለም ሁሉ እስከ ዘለአለም ሆነህ፣ ለምንድን ነው የምታለቅሰው?

እና የዚህን ምድር፣ አዎን፣ እንደዚህ አይነት ሚልዮን ምድሮችን፣ ታናሽ መጠንን ሰው ለመቁጠር የሚችሉ ቢሆንም፣ አንተ ለፈጠርካቸው የመቆጠሪያ መጀመሪያም አይሆንም፤ እና መጋረጃህ አሁንም ተወጥሯል፤ ነገር ግን አንተ እዚህ አለህ፣ እና እቅፍህም እዚህ አለ፤ ደግሞም አንተ ጻድቅ ነህ፤ ለዘለአለምም ሩህሩህና ደግ ነህ፤

፴፩ እና ከዘለአለም እስከ ዘለአለም፣ ከፍጥረታትህ ሁሉ፣ ወደ እቅፍህም ፅዮንን ወስደሀል፤ እና የዙፋንህ ነዋሪዎችም ከሰላምከፍትህ፣ እና ከእውነት ሌላ ነዋሪዎች የላቸውም፤ ምህረት በፊት ለፊትህ ይሄዳል እና መጨረሻ የለውም፤ አንተ ለማልቀስ እንዴት ትችላለህ?

፴፪ ጌታም ለሔኖክ እንዲህ አለው፥ እነሆ፣ እነዚህ ወንድሞችህን እይ፤ እነርሱ የእጅህ ስራዎች ናቸው፣ እና በፈጠርኳቸው ቀንም እውቀታቸውን ሰጠኋቸው፤ እና በዔደን ገነትም ለሰው ነጻ ምርጫውን ሰጠሁት።

፴፫ እና ለወንድሞችህም ይህን ብያለሁ፣ እና ደግሞም እርስ በርስ እንዲዋደዱ፣ እና እኔ አባታቸውን ይመርጡ ዘንድ ትእዛዝን ሰጠኋቸው፤ ነገር ግን እነሆ፣ እነርሱ ፍቅር የላቸውም፣ እና የራሳቸውንም ደም ይጠላሉ፤

፴፬ የእሳት አይነት ቁጣዬም እነርሱ ላይ ተቀጣጥሏል፤ እና በእነርሱም ላይ ቁጣዬ ታላቅ ስለሆነ፣ በቅያሜዬም የጥፋት ውሀ እልክባቸዋለሁ፣ ጥብቅ ቁጣዬም በእነርሱ ላይ ተቀጣጠላለችና።

፴፭ እነሆ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜም የቅድስና ሰው ነው፤ የምክር ሰውም ስሜ ነው፤ እና መጨረሻ የሌለውና ዘለአለማዊም ደግሞ ስሜ ነው።

፴፮ ስለዚህ፣ እጆቼን እዘረጋለሁ እና የፈጠርኳቸውን ፍጥረታት ሁሉ ልይዛቸውም እችላለሁ፤ እና ደግሞም አይኔ ሊበሳቸው ይችላል፣ እና በእጆቼ ከሰራኋቸው ፍጥረታት ሁሉ ከወንድሞችህ ውስጥ እንዳለው እንደእነዚህ አይነት ጥፋቶች አልነበሩም።

፴፯ ነገር ግን እነሆ፣ ኃጢአታቸው በአባቶቻቸው ጭንቅላት ላይ ይሆናል፤ ሰይጣንም አባታቸው ይሆናል፣ ጣርም እጣቸው ይሆናል፤ እናም ሰማያትም በሙሉ ለእነርሱ፣ እንዲሁም በእጆቼ ለሰራኋቸው በሙሉ፣ ያለቅሳሉ፤ ስለዚህ እነዚህ እንደሚሰቃዩ ሲያዩ፣ ሰማያት አያለቅሱም?

፴፰ ነገር ግን እነሆ፣ እነዚህ በአይንህ ያየሀቸውም በጎርፍ ይጠፋሉ፤ እና እነሆ፣ እኔ እዘጋቸዋለሁ፤ እስር ቤት ለእነርሱ አዘጋጅቼላቸዋለሁ።

፴፱ እና የመረጥኩትም በፊቴ ለምኗል። ስለዚህ፣ ለኃጢአታቸው ተሰቃየ፤ ንስሀ ከገቡም በዚያ ቀን የመረጥኩት ወደ እኔ ይመለሳሉ፣ እና እሰከዚያም ቀን ድረስ በስቃይ ውስጥም ይሆናሉ፤

ስለዚህ፣ ለዚህም ሰማያት፣ አዎን፣ እና በእጆቼ የሰራኋቸውም ሁሉ ያለቅሳሉ።

፵፩ እንዲህም ሆነ ጌታ ሔኖክን አነጋገረው፣ እና ስለሰው ልጆች ድርጊቶች ሁሉም ነገረው፤ ስለዚህ ሔኖክ አወቀ፣ እና ጥፋታቸውንና ስቃያቸውን አየ፣ እና አለቀሰ እናም ክንዶቹን ዘረጋ፣ ልቡም እንደ ዘለአለም ተጉረበረበ፤ እና አንጀቱም በጥልቅ ተነካ፤ እናም ዘለአለምም ተንቀጠቀች።

፵፪ ሔኖክም ኖህንና ቤተሰቡን አየ፤ የኖህ ልጆች ዘሮችም በጊዜያዊ ደህንነት ይድናሉ፤

፵፫ ስለዚህ ሔኖክ ኖህ መርከብን እንደሰራም አየ፤ እና ጌታም ፈገግ አለበት፣ እና በእጁም ያዘው፤ ነገር ግን በቀሩት ጥፋተኞች ላይ ጎርፎቹ መጡ እና አጥለቀለቋቸው።

፵፬ ሔኖክም ይህን ተመለከተ፣ የነፍስ መራራነት ተሰማው፣ እና ለወንድሞቹ በማልቀስ ለሰማያት እንዲህ አለ፥ ለመጽናናት እምቢ እላለሁ፤ እግዚአብሔር ግን ሔኖክን አለው፥ ልብህን አንሳ፣ ተደሰትም፤ እና ተመልከት።

፵፭ እንዲህም ሆነ ሔኖክ ተመለከተ፤ እና ከኖህ ጀምሮ የምድርን ቤተሰቦች አየ፤ እና ለጌታ እንዲህ ብሎ ጮኸ፥ የጌታ ቀን መቼ ይመጣል? የሚያለቅሱት ሁሉ እንዲቀደሱና ዘለአለማዊ ህይወት ይኖራቸው ዘንድ፣ የጻድቁ ደምስ መቼ ነው የሚፈሰው?

፵፮ ጌታም እንዲህ አለ፥ ይህም በመካከለኛው ዘመን፣ በጥፋትና በበቀል ቀናት ነው።

፵፯ እና እነሆ፣ ሔኖክም የሰው ልጅ በስጋ የሚመጣበትን ቀን አየ፤ እና መንፈሱም በመደሰት እንዲህ አለ፥ ጻድቁ ወደላይ ተነስቷል፣ እናም ከምድር መሰረት ጀምሮም በጉ ተገድሏል፤ እና በእምነትም በኩል በአብ እቅፍ ውስጥ ነኝ፣ እና እነሆ፣ ፅዮንም ከእኔ ጋር ነች።

፵፰ እንዲህም ሆነ ሔኖክ ምድርን ተመለከተ፤ እና ከጥልቁም እንዲህ የሚል ድምጽ ሰማ፥ ወዮ፣ ለእኔም ለሰው እናት ወዮለኝ፤ በልጆቼ መጥፎነት ምክንያት አሞኛል፣ ደክሞኛልም። መቼ አርፋለሁ፣ እና ከእኔ ውስጥ ከወጡት እድፍ እነጻለሁን? አርፍስ ዘንድ ፈጣሪዬ መቼ ይቀድሰኛል፣ ለዘመንም በፅድቅ በፊቴ መቼ ይኖራል?

፵፱ ሔኖክ ምድር ስታለቅስ ሲሰማም አለቀሰ፣ እና ለጌታም እንዲህ ብሎ ጮኸ፥ ጌታ ሆይ፣ በምድር ላይ ርህራሄ አይኖርህምን? የኖህንን ልጆችንስ አትባርክም?

እንዲህም ሆነ ሔኖክ ወደጌታ መጮሁን እንዲህ በማለት ቀጠለ፥ ጌታ ሆይ፣ በአንድያ ልጅህ፣ እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስም ለኖህና ለዘሩ ርህራሄ ይኖርህ ዘንድ፣ መሬትም በመጥፊያው ውሀ ደግሞም እንዳትሸፈን ዘንድ እጠይቅሀለሁ።

፶፩ ጌታም ይህን ሊከለክለው አልቻለም፤ ከሔኖክ ጋር ቃል ገባ፣ እና ከእርሱም ጋር ቃለ መሀላ ጎርፉን እንደሚያቆም፤ የኖህ ልጆችንም እንደሚጠራቸው ማለለት።

፶፪ ከዚያም ምድር እስካለች ድረስ የእርሱ የሚቀሩት ዘሮችም በሁሉም ህዝቦች መካከል ይገኙ ዘንድ የማይቀየር አዋጅን ሰደደ።

፶፫ እና ጌታም እንዲህ አለ፥ በዘሩ በኩል መሲህ የሚመጣበት የተባረከ ነው፤ ምክንያቱም እንዳለው—እኔ የፅዮን ንጉስ፣ እንደ ዘለአለም ሰፊ የሆነው የሰማይ አለት፣ መሲህ ነኝ፣ እና ማንም በበሩ ገብተው ወደ እኔ የሚወጡትም አይወድቁም፤ ስለዚህ፣ የተናገርኩባቸውም የተባረኩ ናቸው፣ ከዘለአለም ደስታ መዝሙር ጋር በደስታ ይመጣሉና።

፶፬ እንዲህም ሆነ ሔኖክ ወደጌታ እንዲህ ብሎ ጮኸ፥ የሰው ልጅ በስጋ ሲመጣ፣ ምድርም ታርፋለችን? እነዚህን ነገሮች እንድታሳየኝ እለምንሀለሁ።

፶፭ ጌታም ለሔኖክ አለው፣ ተመልከት፣ እና ተመለከተ፣ እና የሰው ልጅን እንደ ሰው በመስቀል ላይ ሲሰቀልም አየ እና ተመለከተ።

፶፮ የደመቀ ድምጽንም ሰማ፤ እና ሰማያት ተሸፍነው ነበር፤ እና የእግዚአብሔር ፍጥረታት ሁሉ አዘኑ፤ ምድርም አቃሰተች፤ ድንጋዮችም ተሰነጠቁ፤ ቅዱሳንም ተነሱ፣ እና በሰው ልጅ ቀኝ እጅም በክብር ዘውዶች ተጫኑ።

፶፯ እና በእስር ቤት የነበሩትም ሁሉ መንፈሶች መጡ፣ እና በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ በኩል ቆሙ፤ እና የቀሩትም እስከ ታላቁ የፍርድ ቀን ድረስ በጭለማ ሰንሰለቶች ታሰሩ።

፶፰ ሔኖክም እንደገና አለቀሰ እና ለጌታ እንዲህ ብሎ ጮኸ፥ ምድር መቼ ታርፋለች?

፶፱ ሔኖክም የሰው ልጅ ወደአብ ሲያርግ ተመለከተ፤ እና ወደ ጌታም እንዲህ ብሎ ጠራ፥ በምድር እንደገና አትመጣምን? አምላክም እስከሆንክ ድረስ፣ እና አውቅሀለሁ፣ እና ምለህልኛል፣ እና በአንድያ ልጅህ ስም እጠይቅህ ዘንድ አዝዘኸኛል፤ ሰርተኸኛል፣ እና ለዘውድህ መብትም በራሴ ሳይሆን በጸጋህ ሰጥተኸኝ፤ ስለዚህ፣ ወደ ምድር እንደገና የምትመለስ እንዳልሆነም እጠይቅሃለሁ።

እና ጌታ ለሔኖክ እንዲህ አለ፥ እንደምኖርም፣ እንዲህም በመጨረሻዎቹ ቀናት፣ መጥፎነትንና በበቀልም ቀናት፣ የኖህ ልጆችን በሚመለከት ቃለ መሀላ ላንተ የገባሁትን ለማሟላት ተመልሼ እመጣለሁ፤

፷፩ ምድር የምታርፍበትም ቀን ይመጣል፣ ነገር ግን ከዚያ ቀን በፊት ሰማያት ይጠቁራሉ፣ የጭለማም መጋረጃ ምድርን ይሸፍናል፤ እና ሰማያትም ይንቀጠቀጣሉ፣ ዳግም በምድርም፤ በሰው ልጆችም መካከልም ታላቅ ስቃይ ይኖራል፣ ነገር ግን ህዝቤን አተርፋቸዋለሁ

፷፪ እና ፅድቅን ከሰማያት እሰዳለሁ፤ እና ስለ አንድያ ልጄ፣ ከሙታን ትንሳኤውን፣ አዎን፣ እና ስለሁሉም ሰዎች ከሞት ስለመነሳት እንዲመሰክርም እውነትን ከምድር እልካለሁ፤ እና እንደ ጥፋት ውሀ ፅድቅና እውነት ምድርን አንድታጸዳት፣ የእኔ ተመራጮችን ከምድር አራት ማእዘናት ወደ አዘጋጀሁት ስፍራ፣ ቅዱስ ከተማ፣ ወገባቸውን እንዲታጠቁ እና ለእኔ መመለሻ ወደፊት ይጠብቁ ዘንድ እንዲሰበሰቡ አደርጋለሁ፤ በዚያም ድንኳኔም ይገኛልና፣ እና ይህችም ፅዮን፣ አዲስቷ ኢየሩሳሌም ተብላ ትጠራለች።

፷፫ ጌታም ለሔኖክ እንዲህ አለው፥ አንተና ከተማህ ሁሉ በዚያ ትገናኛቸዋለህ፣ እናም በእቅፋችንም እንቀበላቸዋለን፣ እነርሱም ያዩናል፤ እና አንገታቸውን እናቅፋለን፣ እና እነርሱም አንገታችንን ያቅፋሉ፣ እና እንሳሳማለን፤

፷፬ እኔም በዚያ መኖሪያዬ ይሆናል፣ እና ከፈጠርኳቸው ሁሉ ውስጥ የምትመጣው ፅዮን ትሆናለች፤ እና ለአንድ አመታትም ምድር ታርፋለች

፷፭ እንዲህም ሆነ ሔኖክ በኋለኛዎቹ ቀናት ለአንድ ሺህ አመታት በፅድቅ በምድር ለመኖር የሰው ልጅ የሚመጣበትን ቀናት አየ፤

፷፮ ከዚያ ጊዜ በፊት ግን ከመጥፎዎቹ መካከል ታላቅ ስቃይን አየ፤ እና ባህርም እንደተቸገረ አየ፣ እና በመጥፎው ላይ የሚመጣውን የሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔርን ፍርድ በመፍራት ወደፊት እየተመለከቱ የሰዎች ልብ ሲወድቁባቸው ተመለከተ።

፷፯ ጌታም ለሔኖክ ሁሉንም ነገሮች፣ እንዲሁም እስከ አለም መጨረሻ ድረስ አሳየው፤ እና የፅድቅን ቀን፣ የቤዛነታቸውንም ሰአት አየ፣ እና የደስታ ሙላትን ተቀበለ፤

፷፰ እና የፅዮን ቀናት ሁሉ፣ በሔኖክ ቀናት፣ ሶስት መቶ ስልሳ አምስት ነበሩ።

፷፱ እና ሔኖክና ሁሉም ህዝቡ ከእግዚአብሔር ጋር ተራመዱ፣ እና እርሱም በፅዮን መካከል ኖረ፤ እንዲህም ሆነ ፅዮንም አልነበረችም፣ እግዚአብሔር ወደ እቅፉ ተቀብሏታልና፤ እና ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ፅዮን ጠፋች የሚል አባባል ነበር።