የጥናት እርዳታዎች
ባለራዕይ


ባለራዕይ

በመንፈሳዊ አይን እግዚአብሔር ከአለም የደበቃቸውን ነገሮች ለማየት እግዚአብሔር ስልጣን የሰጠው ሰው (ሙሴ ፮፥፴፭–፴፰)። እርሱም ገላጭ እና ነቢይ ነው (ሞዛያ ፰፥፲፫–፲፮)። በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ አሞን ባለራዕይ ብቻ ልዩ ማስተርጎሚያን፣ ወይም ኡሪምና ቱሚምን ለመጠቀም እንደሚችል አስተማረ (ሞዛያ ፰፥፲፫፳፰፥፲፮)። ባለራዕይ በፊት የነበረውን፣ አሁን ያለውን፣ እና ወደፊት የሚሆነውን ያውቃል። በጥንት ጊዜ፣ ነቢይ በብዙ ጊዜ ባለራዕይ ተብሎ ይጠራ ነበር (፩ ሳሙ. ፱፥፱፪ ሳሙ. ፳፬፥፲፩)።

ጆሴፍ ስሚዝ የኋለኛው ቀናት ታላቅ ባለራዕይ ነው (ት. እና ቃ. ፳፩፥፩፻፴፭፥፫)። በተጨማሪም፣ ቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሸንጎ እንደ ነቢያት፣ ባለራዕያት፣ እና ገላጮች ይደገፋሉ።