የጥናት እርዳታዎች
ቅዱሳት መጻህፍት


ቅዱሳት መጻህፍት

የተቀደሱ የእግዚአብሔር ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ በተነሳሱ ጊዜ የተጻፉ እና የሚነገሩ ቃላት። ይፉ የሆኑ የቤተክርስቲያኗ የቀኖና ቅዱሳት መጻህፍት መፅሐፍ ቅዱስ፣ መፅሐፈ ሞርሞን፣ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች፣ እና የታላቅ ዋጋ ዕንቁ ናቸው። ኢየሱስ እና የአዲስ ኪዳን ጸሀፊዎች የብሉይ ኪዳን መጻህፍትን እንደ ቅዱሣት መጻህፍት ይቆጥሯቸው ነበር (ማቴ. ፳፪፥፳፱ዮሐ. ፭፥፴፱፪ ጢሞ. ፫፥፲፭፪ ጴጥ. ፩፥፳–፳፩)። ደግሞም የዘመን ቅድመ ተከተልን ተመልከቱ።

የጠፉ ቅዱሣት መጻህፍት

በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ የተጠቀሱ ዛሬ የሌሉን ብሱ ቅዱስ ፅሁፎች ነበሩ፣ ከእነዚህ መፅሐፎች እና ጸሀፊዎች መካከል፥ የቃል ኪዳን መፅሐፍ (ዘፀአ. ፳፬፥፯)፣ የእግዚአብሔር የጦርነት መጽሐፍ (ዘኁል. ፳፩፥፲፬)፣ የያሻር መጽሐፍ (ኢያ. ፲፥፲፫፪ ሳሙ. ፩፥፲፰)፣ የሰሎሞን ታሪክ መጽሐፍ (፩ ነገሥ. ፲፩፥፵፩)፣ የሳሙኤል ታሪክ (፩ ዜና ፳፱፥፳፱)፣ ነቢዩ ናታን፥ (፪ ዜና ፱፥፳፱)፣ ነቢዩ ሸማያ (፪ ዜና ፲፪፥፲፭)፣ ነቢዩ በአዶ (፪ ዜና ፲፫፥፳፪)፣ ኢዩ (፪ ዜና ፳፥፴፬)፣ ባለ ራእዩ ታሪክ (፪ ዜና ፴፫፥፲፱)፣ ሄኖክ (ይሁዳ ፩፥፲፬)፣ እናም የዜኖቅ፣ ኔዩም፣ እና ዜኖስ ቃላት (፩ ኔፊ ፲፱፥፲)፣ ዜኖስ (ያዕቆ. ፭፥፩)፣ ዜኖቅ እና ኤፅያስ (ሔለ. ፰፥፳)፣ የመታሰቢያ መፅሐፍ (ሙሴ ፮፥፭)፣ ወደ ቆሮንቶስ መልእክት (፩ ቆሮ. ፭፥፱)፣ ወደ ኤፌሶን መልእክት (ኤፌ. ፫፥፫)፣ ከሎዶቅያም መልእክት (ቄላ. ፬፥፲፮)፣ እና ከይሁዳ (ይሁዳ ፩፥፫)።

የሚጠበቁ ቅዱስ መጻፍህት

የቅዱሣት መጻህፍት ዋጋዎች

እንደሚመጡ የተተነበዩ ቅዱሣት መጻህፍት