የጥናት እርዳታዎች
አገልግሎት


አገልግሎት

የጌታን ስራ በምድር ላይ ማከናወን። ለእግዚአብሔር እና ለሌሎች ጥቅም የተሰጠ እንክብካቤ ወይም የተፈጸመ ስራ። ሌሎችን ስናገለግል፣ እግዚአብሔርንም ማገልገላችን ነን። የጌታ የተመረጡ አገልጋዮች በስራው ውስጥ ለማገልገል በእግዚአብሔር መጠራት አለባቸው። እውነተኛ አገልጋዮች የጌታን ፍላጎት ሲያከናውኑ፣ በዋና ሀላፊነታቸው ጌታን ይወክላሉ እናም እንደ እርሱ ወኪሎችም ይሰራሉ (ት. እና ቃ. ፷፬፥፳፱)፣ በዚህም ለሰው ደህናነት አስፈላጊ ስራዎችን ያከናውናሉ። ጌታ ሐዋሪያት፣ ነቢያት፣ ወንጌልን ሰባኪዎች፣ ሊቀ ካህናት፣ ሰባዎች፣ ሽማግሌዎች፣ ኤጲስ ቆጶሳት፣ ካህናት፣ አስተማሪዎች፣ ዲያቆኖች፣ ረዳቶች፣ እና አስተዳዳሪዎች ቅዱሳንን ፍጹም ለማድረግ እና ለአገልግሎት ስራ ሰጥቷል (፩ ቆሮ. ፲፪፥፲፪–፳፰ኤፌ. ፬፥፲፩–፲፮ት. እና ቃ. ፳፻፯)።