የጥናት እርዳታዎች
የሙሴ ህግ


የሙሴ ህግ

እግዚአብሔር ያላከበሩትን ታላቁን ህግ ለመተካት ለእስራኤል ቤት ህግጋትን በሙሴ በኩል ሰጠ (ዘፀአ. ፴፬ጆ.ስ.ት.፣ ዘፀአ. ፴፬፥፩–፪ጆ.ስ.ት.፣ ዘዳግ. ፲፥፪ [ተጨማሪ])። የሙሴ ህግ ሰዎችን ስለሀላፊነቶቻቸው እንዲያስታውሱ የሚያደርጉ ብዙ መሰረታዊ መርሆችን፣ ደንቦችን፣ ቅደም ተከተሎችን፣ እና ምልክቶችን የያዙ ናቸው። ይህም እነርሱን ስለእግዚአብሔርና ለእርሱ ስላላቸው ሀላፊነት እንዲያስታውሱ የሚያደርግ (ሞዛያ ፲፫፥፴) ስነምግባራዊ፣ ግብረገባዊ፣ ሀይማኖታዊ ህግን እና ስጋዊ ትእዛዛትንና እንደ መስዋዕት (ዘሌዋ. ፩–፯) አይነት ድርጊቶችን የያዘ ነው። አስሩ ትእዛዛት እና ብዙ ሌሎቹ የግብረገባዊና የስነምግባር ዋጋ ትእዛዛት እንደነበሩ፣ እምነት ንስሀ መግባት፣ በውሀ መጠመቅ፣ እና የኃጢያት ስርየት የህጉ ክፍሎች ናቸው። ብዙዎቹ የስርዓት ህጎች ደምን በማፍሰስ መስዋዕት ማድረግን በፈጸመው (አልማ ፴፬፥፲፫–፲፬) በኢየሱስ ሞት እና ትንሳኤ ተሟልተዋል። ህጉ የተፈጸመው በአሮናዊ ክህነት ስር ነበር እና ይህን የሚከተሉትን ወደክርስቶስ የሚያመጣ መዘጋጃ ወንጌል ነበር።