የጥናት እርዳታዎች
ሲዖል


ሲዖል

የኋለኛው ቀን ራዕይ ስለሲዖል በሁለት አስተያየት አለው። መጀመሪያ፣ ይህ በሟችነት ትእዛዝ አክባሪ ያልሆኑት ለጊዜ የሚኖሩበት የመንፈስ አለም ነው። በዚህ አስተያየት፣ ሲዖል መጨረሻ አለው። በእዚያ ያሉት መንፈሶች ወንጌሉን ይማራሉ፣ እናም ንስሀ ከገቡ በኋላም ብቁ ወደ ሆኑበት የክብር ደረጃ በትንሳኤ ይነሳሉ። ንስሀ የማይገቡት፣ ግን የጥፋት ልጆች ያልሆኑት፣ በአንድ ሺህ አመት በሙሉ በሲዖል ይቆያሉ። ከእነዚህ አንድ ሺህ አመቶች ስቃይ በኋላ፣ ወደ ቲለስቲያል ክብር በትንሳኤ ይነሳሉ (ት. እና ቃ. ፸፮፥፹፩–፹፮፹፰፥፻–፻፩)።

ሁለተኛ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ያልዳኑት በቋሚነት የሚኖሩበት ቦታ ነው። በዚህ አስተያየት፣ ሲዖል ዘላቂ ነው። ይህም ለእነዚያ “ረክሰው ለቀሩት” ነው (ት. እና ቃ. ፹፰፥፴፭፣ ፻፪)። ይህም ሰይጣን፣ መላእክቱ፣ እና አብ ከገለጸው በኋላ ወልድን የካዱ የጥፋት ልጆች ለዘለአለም የሚኖሩበት ነው (ት. እና ቃ. ፸፮፥፵፫–፵፮)።

ቅዱሣት መጻህፍት አንዳንዴ ሲዖልን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ይገልጹታል።