የጥናት እርዳታዎች
መሰቀል


መሰቀል

በብሉይ ኪዳን ጊዜዎች ውስጥ ልምድ የነበረ፣ ሮሜ የምትጠቀምበት የመግደያ ዘዴ፣ በዚህም ሰው እጆቹን እና እግሮቹን በመስቀል ላይ በማሰር ወይም በምስማር በመምታት ይገደላል። ይህም በልምድ የሚደረገው ለባሪያዎችና ለትንሽ ወንጀለኞች ነው። ከመሰቀል አስቀድሞ በልምድ መገረፍ ነበር (ማር. ፲፭፥፲፭)። የሚሰቀለው ሰው በልምድ የእራሱን መስቀል ወደ ሚሰቀልበት ቦታ እንዲሸከም ይደረጋል (ዮሐ. ፲፱፥፲፮–፲፯)። በልምድም ልብሱን ፍርዱን የሚፈፅሙ ወታደሮችም ይወስዱታል (ማቴ. ፳፯፥፴፭)። የሰውየው እግሮች ከምድር ሰላሳ ሰንቲ ሜትር ወይም ስልሳ ሰንቲ ሜትር በላይ እንዲሆን ዘንድ መስቀሉም በመሬት ውስጥ ይቀበራል። በመስቀሉ ላይ ያለው ሰው እስከሚሞትም ድረስ መስቀሉ በወታደሮች ይጠበቃል፣ ይህም አንዳንዴ እስከ ፫ ቀናት ይፈጃል (ዮሐ. ፲፱፥፴፩–፴፯)።

ኢየሱስ የተሰቀለው የማያምኑ ቡድኖች በቄሳር ላይ እንዳመጸና የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላለም እንደተሳደበ በሀሰት በመክሰሳቸው ምክንያት ነበር። ቀይ ልብስ(ዮሐ. ፲፱፥፪)፣ የእሾኽ አክሊል፣ እና ሌሎች ስድቦች በኢየሱስ ላይ ተደርገው ነበር (ማቴ. ፳፮፥፷፯ማር. ፲፬፥፷፭)።