የጥናት እርዳታዎች
መናዘዝ


መናዘዝ

ቅዱሣት መጻህፍት መናዘዝን በሁለት መንገዶች ተጠቅመውበታል። በሌላ አባባል፣ መናዘዝ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ መናዘዝ አይነት በአንድ ነገር የእራስን እምነት ሁኔታ መግለፅ ነው (ማቴ. ፲፥፴፪ሮሜ ፲፥፱፩ ዮሐ. ፬፥፩–፫ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፬)።

መናዘዝ፣ እንደ ኃጢያት መናዘዝ አይነት፣ ለራስ ወንጀለኛነት ተቀባይ መሆን ማለት ነው። ሁሉም ሰው ኃጢያቶቻቸውን ሁሉ ለጌታ መናዘዝ እና የእርሱን ምህረት የማግኘት ሀላፊነት አላቸው (ት. እና ቃ. ፶፰፥፵፪–፵፫)። አስፈላጊም ሲሆን፣ ኃጢያቶች ለተሰራበት ወይም ለተሰራባቸው ሰዎች መናዘዝ ያስፈልጋል። ሀይለኛ ኃጢያቶች ለቤተክርስቲያኗ ባለስልጣናት (በብዙም ጊዜ ለኤጲስ ቆጶስ) መናዘዝ ይገባል።