ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፺፯


ክፍል ፺፯

በነሀሴ ፪፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዩ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ይህ ራዕይ፣ ነቢዩ ጌታን ለመረጃ በጠየቀበት መልስ፣ የፅዮን፣ የጃክሰን የግዛት ክፍል ሚዙሪ ቅዱሳን ጉዳዮችን የሚያመራምር ነበር። በዚህ ጊዜ በሚዙሪ የነበሩት የቤተክርስቲያኗ አባላት በጥልቅ እየተሰቃዩ ነበር እና በሐምሌ ፳፫፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) ከጃክሰን የግዛት ክፍል ወጥተው እንዲሄዱ ስምምነትን እንዲፈርሙ ተገድደው ነበር።

፩–፪፣ ብዙዎቹ የፅዮን (ጃክሰን የግዛት ክፍል፣ ሚዙሪ) ቅዱሳን በእምነታቸው ተባርከዋል፤ ፫–፭፣ ፓርሊ ፒ ፕራት በፅዮን ትምህርት ቤት እንዲያገለግል ታዝዟል፤ ፮–፱፣ ቃል ኪዳናቸውን የሚያከብሩትን ጌታ ይቀበላቸዋል፤ ፲–፲፯፣ ልበ ንጹ የሆኑት እግዚአብሔርን የሚያዩበት ቤት በፅዮን ይሰራ፤ ፲፰–፳፩፣ ፅዮን ልበ ንጹህ ነች፤ ፳፪–፳፰፣ ታማኝ ከሆነች ፅዮን የጌታን ቅጣት ታመልጣለች።

ባልንጀሮቼ እውነት እላችኋለሁ፣ በእውነት ትሁት ሆነው እና በቅንነት ጥበብን ለመማርና እውነትን ለማግኘት ስለሚጥሩት ብዙዎች፣ በፅዮን ምድር ስላሉት ወንድሞቻችሁ ያለኝን ፈቃድ አሳያችሁ ዘንድ በድምጼ፣ እንዲሁም በመንፈሴ ድምፅ እናገራችኋለሁ።

እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እንደነዚህ አይነቶች የተባረኩ ናቸው፣ ያገኙታልና፤ ፍርድንም ሳመጣባቸው ፅድቅ አደርግ ዘንድ፣ እኔ ጌታ ለቅን እና ለምፈልገው ሁሉ ምህረትን አሳያለሁና።

እነሆ፣ በፅዮን ስላለው ትምህርት ቤት እላችኋለሁ፣ እኔ ጌታ በፅዮን ትምህርት ቤት በመኖሩ፣ ደግሞም በአገልጋዬ ፓርሊ ፒ ፕራትም ተደስቻለሁ፣ እርሱም በእኔ ይኖራልና።

በእኔ በመኖር የሚቀጥል ቢሆን ሌላ ትእዛዛትን እስከምሰጠው ድረስ በፅዮን ምድር ትምህርት ቤት ውስጥ በመሪነት ይቀጥላል።

እናም ለትምህርት ቤቱ፣ እና ለፅዮን ውስጥ ቤተክርስቲያን መታነጽ ቅዱሳን መጻህፍትን ሁሉ እና ሚስጥራትን ለማብራራት በሚበዙ በረከቶች እባርከዋለሁ።

እና ለሚቀሩት ትምህርት ቤትም፣ እኔ ጌታ፣ ምህረትን ለማሳየት ፈቃደኛ ነኝ፤ ይህም ቢሆን፣ መገሰፅ የሚያስፈልጋቸው ሌሎችም አሉ፣ እና ስራዎቻቸውም እንዲታወቁ ይደረጋል።

ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እና መልካም ፍሬ የማይሰጥ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል እና ወደ እሳትም ይጣላል። እኔ ጌታ ተናግሬዋለሁ።

እውነት እላችኋለሁ፣ በመካከላቸው ልቦቻቸው ታማኝ እንደሆኑ፣ እና እንደተሰበሩ፣ እና መንፈሶቻቸው እንደተዋረዱ የሚያውቁ፣ እና ቃል ኪዳኖቻቸውን በመስዋዕት—አዎን፣ እኔ ጌታ በማዝዘው እያንዳንዱ መስዋእት—ለመከተል ፈቃደኛ የሆኑት ሁሉ፣ እኔ እቀበላቸዋለሁ

እኔ ጌታ በመልካም ምድር ውስጥ፣ በንጹህ ወንዝ አጠገብ እንደተተከለ፣ ውድ ፍሬዎች እንደሚሰጥ፣ በጣም ፍሬአማ እንደሆነ ዛፍ እንዲፈሩ አደርጋለሁ።

እውነት እላችኋለሁ፣ በፅዮን ምድር ውስጥ በሰጠኋችሁ ንድፍ መሰረት ቤት ይሰራልኝ ዘንድ ፍቃዴ ነው።

፲፩ አዎን፣ በቶሎም በህዝቤ አስራት ይሰራ።

፲፪ እነሆ፣ ለፅዮን ደህንነት ቤት ለእኔ ይሰራ ዘንድ፣ ከእጆቻቸው እኔ ጌታ የምጠብቅባቸው አስራትና መስዋዕት ይህ ነው—

፲፫ ለቅዱሳን ሁሉ ምስጋናን የማቅረቢያ ቦታ፣ እና በአገልግሎቱ ስራ በተለያዩት ጥሪአቸው እና ሀላፊነታቸው የተጠሩት ሁሉ የሚማሩበት ቦታ፤

፲፬ በአገልግሎታቸው፣ በአስተያየታቸው፣ በመሰረታዊ መርህ፣ እና በትምህርታቸው፣ እና በላያችሁ የተሰጣችሁ የመንግስቱ ቁልፍ፣ በምድር ላይ ያለው የእግዚአብሔር መንግስትን በሚመለከት ሁሉ፣ በዚህ ሁሉ ፍጹም መረዳት ይኖራቸው ዘንድ ነው።

፲፭ እና በጌታ ስም ቤትን ለእኔ እስከሰሩልኝ ድረስ፣ እና እንዳይረከስ፣ ማንኛውንም እርኩስ ነገር እንዲገባበት እስካልፈቀዱ ድረስ፣ ክብሬ ያርፍበታል፤

፲፮ አዎን፣ እና በዚያም እገኛልሁ፣ እመጣበታለሁና፣ እና የሚገባበት ንጹህ ልብ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያያል።

፲፯ ነገር ግን የረከሰ ቢሆን አልመጣበትም፣ እና ክብሬም አይገኝበትም፤ ቅዱስ ወዳልሆነ ቤተመቅደስ አልመጣምና።

፲፰ እሁንም እነሆ፣ ፅዮን እነዚህን ነገሮች ካደረገች ትበለፅጋለች፣ እና ታድጋለችም እናም በጣም የከበረች፣ በጣም ታላቅ፣ እና በጣም አስፈሪም ትሆናለች።

፲፱ እና የምድር ህዝብም ያከብሯታል፣ እና እንዲህም ይላሉ፥ በእርግጥም ፅዮን የእግዚአብሔር ከተማ ነች፣ እና በእርግጥም ፅዮን ልትወድቅ አትችልም፣ ወይም ከስፍራዋ አትወጣም፣ እግዚአብሔር በዚያ ነውና፣ እና የጌታም እጅ በዚያ ነው፤

እና በጉልበቱ ሀይል መድሀኒቷና ታላቅ ማማዋ እንደሚሆን መሀላ ገብቷል።

፳፩ ስለዚህ፣ በእውነት ጌታ እንዲህ ይላል፣ ፅዮን ትደሰት፣ ይህች ፅዮን ነውና—ልበ ንጹህ፤ ስለዚህ፣ ኃጥአን ሁሉ ሲያዝኑ ፅዮን ትደሰት።

፳፪ እነሆም፣ እና አስተውሉ፣ በኃጢአተኞቹ ላይ በቀል እንደ አውሎ ንፋስ ፈጥኖ መጥቷል፤ እና ማንስ ያመልጠዋል?

፳፫ የጌታ መከራም ቀንና ሌሊት ያልፋል፤ ወሬውንም መላውን ህዝብ ያስደነግጣል፤ አዎን፣ ጌታ እስከሚመጣም አይቆምም፤

፳፬ የጌታ ቁጣ በርኩሰታቸውና በክፉ ስራዎቻቸው ሁሉ ላይ ተቀጣጥሏልና።

፳፭ ይህም ቢሆን፣ ፅዮን ያዘዝኳትን ማንኛውም ነገሮች ሁሉ የምትከተል ከሆነችም ታመልጣለች

፳፮ ነገር ግን፣ ያዘዝኳትን ማንኛውም ነገሮች ሁሉ ባትከተል ግን፣ በሁሉም ስራዎቿ መሰረት በታላቅ ስቃይ፣ ቸነፈር፣ መቅሰፍት፣ በጎራዴ፣ በበቀልበምትበላም እሳት እጎበኛታለሁ

፳፯ ይህም ቢሆን፣ እኔ ጌታ መስዋዕቴን እንደተቀበልኩ በጆሮዋ ይህ አንድ ጊዜ ይነበብላት፤ እና ኃጢአት ከዚህ በኋላ የማትሰራ ቢሆን ከእነዚህ ነገሮች ማንኛቸውም አይደርሱባትም።

፳፰ እና በበረከቶች እባርካታለሁ፣ እና በእርሷና በትውልዶቿ ላይ ለዘለአለም የሚሆኑ በረከቶች አበዛላታለሁ፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ። አሜን።