ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፶፮


ክፍል ፶፮

በሰኔ ፲፭፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) ከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ፣ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። ይህም ራዕይ በሚኖርበት በፍሪድሪክ ጂ ዊልያምስ እርሻ ላይ ስላለው ሀላፊነት በተመለከተ ጆሴፍ ስሚዝ ለእርሱ የተቀበለለትን የቀድሞውን ራዕይ (በቁጥር ፰ “ትእዛዝ” ተብሎ የተጠቀሰው) ባለማክበሩ እዝራ ቴይርን ይገስጻል። የሚቀጥለው ራዕይ ደግሞም ከቶማስ ቢ ማርሽ ጋር ወደ ሚዙሪ እንዲጓዝ የተጠራበትን ይሰርዛል (ክፍል ፶፪፥፳፪ ተመልከቱ)።

፩–፪፣ ደህንነትን ለማግኘት ቅዱሳን መስቀሉን መሸከም እና ጌታን መከተል አለባቸው፤ ፫–፲፫፣ ጌታ ያዛል እናም ይሽራል፣ እና የማይታዘዙትም ይጣላሉ፤ ፲፬–፲፯፣ ድሀውን ለማይረዳው ባለጠጋም ወዮለት፣ እና ልባቸው ላልተሰበሩ ድሆችም ወዮላቸው፤ ፲፰–፳፣ በልባቸው ንጹሀን የሆኑ ድሆች ብፁዓን ናቸው፣ ምድርን ይወርሳሉና።

በስሜ የምትታወቁ ህዝቤ ሆይ፣ አድምጡ ይላል ጌታ አምላካችሁ፤ እነሆ ቁጣዬ በአማጸኞች ላይ ነዷል፣ እናም በአህዛብ ላይ በሚመጣው የጉብኝት እና የመዓት ቀን፣ ክንዴን እና ቁጣዬን ያውቃሉ።

መስቀሉን አንስቶ የማይከተለኝ፣ እና ትእዛዛቴን የማያከብረው፣ እርሱ አይድንም።

እነሆ፣ እኔ ጌታ አዛለሁ፤ እና ትእዛዝን ሰጥቼ እና ትእዛዜም ከተሰበረ በኋላም የማይታዘዘውም በራሴ ጊዜ ይቆረጣል

ስለዚህ፣ እኔ ጌታ መልካምም እንደመሰለኝ አዝዛለሁ እሽራለሁም፤ እናም፣ ጌታ እንዲህ ይላል፣ ይህም ሁሉ በሚያምጹት ራስ ላይ ይመለስላቸዋል።

ስለዚህ፣ ለአገልጋዮቼ ቶማስ ቢ ማርሽ እና እዝራ ቴይር የሰጠሁትን ትእዛዝ እሽራለሁ፣ እና ለአገልጋዬ ቶማስ ወደ ሚዙሪ አገር ፈጥኖ እንዲጓዝም አዲስ ትእዛዝን ሰጥቼዋለሁ፣ እና አገልጋዬ ሴላ ጄ ግርፍን አብሮት ይሄዳል።

ምክንያቱም እነሆ፣ ቶምሰን ውስጥ ባሉት ህዝቤ አንገተ ደንዳናነት እና በእነርሱ አመጽ ምክንያት ለአገልጋዮቼ ሴላ ጄ ግርፍን እና ኒውል ናይት የሰጠኋቸውን ትእዛዝ እሽራለሁ።

ስለዚህ፣ አገልጋዬ ኒውል ናይት ከእነርሱ ጋር ይቆይ፤ እና በፊቴ የሚጸጸቱ እና ወደ መረጥኩት ምድር በእርሱ ተመርተው የሚሄዱት ሁሉም ይሂዱ።

እና ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ እዝራ ቴይር ለኩራቱ እና ራሱን ለመውደዱ ንስሀ መግባት፣ እናም ስለሚኖርበት ስፍራ በፊት የሰጠሁትን ትእዛዝ ማክበር አለበት።

እና ይህን ቢያደርግ፣ በምድሩም ላይ መከፋፈል ስለማይኖር፣ ወደ ሚዙሪ አገር እንዲሄድም ይመረጣል፤

አለበለዚያም፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ የከፈለውን ገንዘብ ይቀበላል፣ እናም ከስፍራው ይሄዳ፣ ከቤተክርስቲያኔም ይቆረጣል

፲፩ እና ምንም እንኳን ሰማይ እና ምድር ቢያልፉም፣ እነዚህ ቃላት አያልፉም፣ ነገር ግን ሁሉም ይፈጸማሉ።

፲፪ እናም አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊም ገንዘቡን መክፈል ቢኖርበትም፣ እነሆ፣ እኔ ጌታ መልሼ በሚዙሪ አገር ውስጥ እከፍለዋለሁ፣ እና እርሱ የሚቀበላቸውም ባደረጉት መጠን ደግመው ዋጋቸውን ይቀበላሉ፤

፲፫ በውርስ መሬቶቻቸውም እንኳ ቢሆን ባደረጉት መጠን ይቀበላሉ።

፲፬ እነሆ፣ ጌታ ለህዝቤ እንዲህ ይላል—እናንት ብዙ የምታደርጉት እና ንስሀ የምትገቡባቸው ነገሮች አሉአችሁ፤ እነሆ፣ ኃጢአቶቻችሁ ወደ እኔ መጥተዋል፣ እና ይቅርታም አልተሰጣቸውምና፣ ምክንያቱም በገዛ መንገዳችሁ ምክርን ስለምትሹ ነው።

፲፭ እናም ልባችሁም አልረኩም። እናም እውነትን አታከብሩም፣ ነገር ግን ፅድቅ ባልሆነው ትደሰታላችሁ

፲፮ ንብረታችሁን ለድሆች የማትሰጡ እናንት ባለጠጎች ወዮላችሁ፣ ሀብቶቻችሁም ነፍሳችሁንያዝላሉና፤ እና በጉብኝት እና በፍርድ እና በቁጣም ቀንም ለቅሶአችሁ ይህ ይሆናል፥ የአዝመራ ወቅት አለፈ፣ በጋም አለቀ፣ እና ነፍሴም አልዳነም!

፲፯ ልባችሁ ያልተሰበሩ፣ መንፈሶቻችሁም ያልተዋረዱ፣ እና ሆዳችሁ ያልሞላና፣ የሌሎች ሰዎች ንብረቶችን ከመያዝ እጆቻችሁን ያላቆማችሁ፣ አይኖቻችሁ በስግብግብነት የተሞላና፣ በእጆቻችሁ የማትሰሩ ድሀ ሰዎችም ወዮላችሁ!

፲፰ ነገር ግን ልባቸው ንጹህ የሆኑ፣ ልቦቻቸው የተሰበሩ፣ እና መንፈሶቻቸው የተጸጸቱ ድሆች ግን ብፁዓን ናቸው፣ ምክንያቱም ለደህንነታቸው የእግዚአብሔር መንግስት በሀይልና በታላቅ ክብር ሲመጣ ይመለከታሉና፤ የምድርም ስብ ለእነርሱ ይሆናልና።

፲፱ እነሆ፣ ጌታ ይመጣል፣ እናም ሽልማቱም ከእርሱ ጋር ይሆናል፣ እና ለእያንዳንዱን ሰውም ዋጋውን ይሰጠዋል፣ እና ድሀውም ይደሰታልና፤

ትውልዶቻቸውም ምድርን ከትውልድ እስከ ትውልድ፣ ከዘለአለም እስከ ዘለአለም ድረስ ይወርሳሉ። እና አሁን የምነግራችሁን እፈፅማለሁ። እንዲሁም ይሁን። አሜን።