ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፶፪


ክፍል ፶፪

በሰኔ ፮፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ለቤተክርስቲያኗ ሽማግሌዎች የተሰጠ ራዕይ። በሰኔ ፫ ተጀምሮ በሰኔ ፮ የተዘጋ ጉባኤ ከርትላንድ ውስጥ ተካሂዶ ነበር። በዚህ ጉባኤ ውስጥም የመጀመሪያው ልዩ የሊቀ ካህን ሀላፊነት ሹመቶች ተደርገው ነበር፣ እናም የሀሰት እና የሚያታልሉ መናፍስትም ተገልጠው እና ተገስጸውም ነበር።

፩–፪፣ የሚቀጥለው ጉባኤ በሚዙሪ ውስጥ እንዲሆን ተወስኗል፤ ፫–፰፣ አንዳንድ ሽማግሌዎች አብረው እንዲጓዙም ተመድበዋል፤ ፱–፲፩፣ ሽማግሌዎችም ሐዋርያት እና ነቢያት የጻፉትን ያስተምሩ፤ ፲፪–፳፩፣ በመንፈስ የሚታነጹት የምስጋና እና የጥበብ ፍሬ ያመጣሉ፤ ፳፪–፵፬፣ ወደ ሚዙሪ ለጉባኤው እየተጓዙ እያሉ፣ ወንጌልን እየሰበኩ እንዲሄዱ የተለያዩ ሽማግሌዎች ተመድበዋል።

እነሆ፣ ጌታ በእነዚህ በመጨረሻው ቀናት ለጠራቸው እና ለመረጣቸው ሽማግሌዎች በመንፈሱም ድምፅ፣ እንዲህ ይላል—

እንዲህም አለ፤ እኔ ጌታ በቃል ኪዳን ወራሾች ለሆኑት፣ እና ለያዕቆብ ቅሪት ለሆኑት ህዝቤ፣ በቀደስኩላቸው ምድር ላይ፣ በሚዙሪ ውስጥ የሚቀጥለው ጉባኤ እስከሚጠራ ድረስ ምን እንደምታደርጉ አስታውቃችኋለሁ።

ስለዚህ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ቤታቸውን ትተው ለመሄድ ለመዘጋጀት በሚችሉበት፣ አገልጋዮቼ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግማዊ፣ እና ስድኒ ሪግደን ወዲያው ይጓዙ፣ እና ወደ ሚዙሪ ምድርም ይጓዙ።

እናም ለእኔ ታማኝ እስከሆኑም ድረስ፣ ምን እንደሚያደርጉ እንዲያውቁም ይደረግላቸዋል፤

እናም ደግሞ፣ ታማኝ እስከሆኑም ድረስ፣ የውርሳችሁን ምድር እንዲያውቁት ይደረጋል።

እና ታማኝ እስካልሆኑም ድረስ፣ በእኔ ፈቃድ፣ እና መልካም እንደሚመስለኝምይገለላሉ።

እና ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ ላይመን ዋይት እና አገልጋዬ ጆን ኮርል ፈጥነው ይጓዙ፤

እና አገልጋዬ ጆን መርዶክ፣ እና አገልጋዬ ሀይረም ስሚዝ በድትሮይት በኩል ወደዚያ ይጓዙ።

ከዚያም ስፍራ፣ ነቢያት እና ሐዋርያት ከጻፉት፣ እና በእምነት ጸሎት አማካይነት አፅናኙ ካስተማራቸው ሌላ ምንም ሳይሉ፣ ቃሉን በሚያልፉበት ስፍራዎች እየሰበኩ ይጓዙ።

ሁለት በሁለት ሆነውም ይጓዙ፣ እና በዚህም በሚያልፉበትም ስፍራዎች፣ በውሀ በማጥመቅ እና በውሀውም አጠገብ እጃቸውን በመጫን፣ በእያንዳንዱ ስብሰባዎች ውስጥ ይስበኩ።

፲፩ ጌታም እንዲህ ይላል፣ በፅድቅም ስራዬን በአጭር እቆርጣለሁ፣ ድል ለመንሣት ፍርድን የማመጣበት ቀን ይመጣልና።

፲፪ አገልጋዬ ላይመን ዋይትም ይጠንቀቅ፣ ሰይጣን እንደ ገለባ ሊያበጥረው ይፈልጋልና።

፲፫ እናም እነሆ፣ ታማኝ የሆነው እርሱ በብዙ ነገሮች ላይ ገዢ ይሆናልና።

፲፬ እና ደግሞም፣ እንዳትታለሉም ለሁሉም ነገሮች ንድፍን እሰጣችኋለሁ፤ ሰይጣን በምድር ላይ አለና፣ እና አገሮችን እያሳታቸውም ይሄዳል—

፲፭ ስለዚህ የሚጸልየው፣ መንፈሱ የተዋረደውምስርዓቴን ካከበረ፣ እርሱም በእኔ ዘንድ ተቀባይነትን ያገኛል።

፲፮ መንፈሱ ትሁት፣ ቋንቋውም ቅንና የሚያንፅ የሆነው፣ የሚናገረውም፣ ስርዓቶቼን ቢያከብር፣ እርሱ ከእግዚአብሔር ነው።

፲፯ እና ደግሞም፣ በሀይሌ የሚንቀጠቀጠውም እርሱ ጠንካራ እንዲሆን ይደረጋል፣ እና በምሰጣችሁ ራዕዮች እና እውነቶች በኩልም የምስጋና እና የጥበብ ፍሬዎችን ያመጣል።

፲፰ እና ደግሞም የተሸነፈውም እና በዚህም ንድፍ አማካይነት፣ ፍሬ የማያመጣውም ከእኔ አይደለም።

፲፱ ስለዚህ፣ ከሰማይ በታች ሁሉ በዚህ ንድፍ አማካይነት መናፍስትን በሁሉም ጉዳዮች ታውቃላችሁ

ቀኖቹም ቀርበዋል፤ ሰዎችም እንደ እምነታቸው ይከናወንላቸዋል

፳፩ እነሆ፣ ይህ ትእዛዝ ለመረጥኳቸው ሽማግሌዎች ሁሉ የተሰጠው ነው።

፳፪ እና ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ ቶማስ ቢ ማርሽ እና አገልጋዬ እዝራ ቴይርም ቃሉን በየመንገዳቸው እየሰበኩ ወደ እዚያ ምድር ደግመውም ይጓዙ።

፳፫ እና ደግሞም፣ አገልጋዬ አይዛክ ሞርሊ እና አገልጋዬ እዝራ ቡዝ፣ ቃሉን በዚያም ምድር እግረ መንገዳቸውን እየሰበኩ፣ ደግመው ይጓዙ።

፳፬ እና ደግሞም፣ አገልጋዮቼ ኤድዋርድ ፓርትሪጅ እና ማርቲን ሀሪስ ከአገልጋዮቼ ስድኒ ሪግደን እና ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ ጋር ይጓዙ።

፳፭ አገልጋዮቼ ዴቪድ ዊትመር እና ሀርቪ ውትሎክም፣ ደግመውም እግረ መንገዳቸውን እየሰበኩ ወደ እዚያው ምድር ይጓዙ።

፳፮ እናም አገልጋዮቼ ፓርሊ ፒ ፕራት እና ኦርሰን ፕራትም፣ እግረ መንገዳቸውን፣ እንዲሁም ወደ እዚያው ምድር እየሰበኩ ይጓዙ።

፳፯ እናም አገልጋዮቼ ሰለሞን ሀንኮክ እና ሰሚየን ካርተርም ወደ እዚያ ምድርም ደግመውም ይጓዙ፣ እናም እግረ መንገዳቸውን ይስበኩ።

፳፰ አገልጋዮቼ ኤድሰን ፉለር እና ጄከብ ስኮትም እንዲሁ ይጓዙ።

፳፱ አገልጋዮቼ ሊቫይ ደብሊው ሀንኮክ እና ዘበዲ ኮልትርንም እንዲሁ ይጓዙ።

አገልጋዮቼ ሬኖልድዝ ካሁን እና ሳሙኤል ኤች ስሚዝም እንዲሁ ይጓዙ።

፴፩ አገልጋዮቼ ዊለር ቦልድውን እና ውልያም ካርተርም እንዲሁ ይጓዙ።

፴፪ እናም አገልጋዮቼ ኑወል ናይት እና ሴላ ጄ ግርፍንም ይሾሙ፣ እናም እንዲሁ ይጓዙ።

፴፫ አዎን፣ እውነት እላለሁ፣ እነዚህ ሁሉ ወደ አንድ ስፍራ በተለያዩ መንገዶቻቸው ይጓዙ እናም አንድ በሌላው ሰው መሰረት ላይ አያንጽም፣ ወይም በሌላ ሰውም መንገድ አይጓዝም።

፴፬ ታማኝ የሆነው፣ እርሱ ይጠበቃል እና ብዙ ፍሬ በማፍራትም ይባረካል።

፴፭ እና ደግሞም፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ አገልጋዮቼ ጆሴፍ ዌክፊልድና ሰለሞን ሀምፍሪ ወደ ምስራቅ አገሮች ይጓዙ፤

፴፮ ትንቢቶቹ እንዲሟሉ፣ ካዩት እና ከሰሙት እናም በእርግጥ ከሚያምኑት፣ ከነቢያትና ከሐዋርያት በቀር ምንም ነገሮችን ሳያውጁ፣ ከቤተሰቦቻቸው ጋርም ያገልግሉ።

፴፯ በኃጢአት ምክንያትም፣ ለሂምን በሰት የተሰጠውም ይወሰድበት፣ እናም ለሳይመንድስ ራይደር ይሰጥ።

፴፰ እና ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ጀርድ ካርተር እንደ ካህን ይሾም፣ ጆርጅ ጄምስም እንዲሁ እንደ ካህን ይሾም።

፴፱ የሚቀሩት ሽማግሌዎችም ቤተክርስቲያኖችን ይጠብቁ፣ እና በአካባቢያቸውም ቃሉን ያውጁ፤ እናም የጣኦት አምላኮም እንዳይኖር እና ጥፋት እንዳይሰራም በገዛ እጆቻቸው ይስሩ።

እናም በሁሉም ነገሮችም ድሀውን እና ችግረኛውን፣ የታመመውን እና የተሰቃየውን አስታውሱ፣ ይህን የማያደርግም፣ እርሱ ደቀ መዝሙሬ አይደለምና።

፵፩ እና ደግሞም፣ አገልጋዮቼ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ፣ እና ስድኒ ሪግደን እና ኤድዋርድ ፓርትሪጅ ከቤተክርስቲያኗ ማስተዋወቂያ ይውሰዱ። እና አንድ ደግሞ ለአገልጋዬ ኦሊቨር ካውድሪ ይሰጠው።

፵፪ እና በዚህም፣ እንዲሁም እንዳልኩት፣ ታማኝ ከሆናችሁ፣ የውርሳችሁ ምድር በሆነው፣ እና አሁንም የጠላቶቻችሁ ምድር በሆነው፣ በሚዙሪ ምድር ለመደሰት ራሳችሁን ትሰበሰባላችሁ።

፵፫ ነገር ግን፣ እነሆ፣ እኔ ጌታ ከተማውን በጊዜው አፈጥነዋለሁ፣ እና ታማኝ የሆነውንም በደስታ እና በሀሴት አነግሰዋለሁ።

፵፬ እነሆ፣ እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፣ እናም በኋለኛው ቀን አነሳቸዋለሁ። እንዲሁም ይሁን። አሜን።