ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፭


ክፍል ፭

መጋቢት ፲፰፻፳፱ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ፣ ፔንስልቬንያ፣ በማርቲን ሀሪስ ጥያቄ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ።

፩–፲፣ ይህ ትውልድ የጌታን ቃል በጆሴፍ ስሚዝ በኩል ይቀበላል፤ ፲፩–፲፰፣ ሶስቱ ምስክሮች ስለ መፅሐፈ ሞርሞን ይመሰክራሉ፤ ፲፱–፳፣ እንደ ቀድሞው ጊዜ የጌታ ቃል ይረጋገጣል፤ ፳፩–፴፭፣ ማርቲን ሀሪስ ንስሀ ይግባና ከምስክሮቹ አንዱ ይሁን።

እነሆ፣ እንዲህ እልሀለሁ፣ አንተ አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ፣ ምስክርነትህን የሰጠህባቸውን ሰሌዳዎችን ከእኔ እንደተቀበልህ አገልጋዬ ማርቲን ሀሪስ ከእኔ ምስክርነትን ፈልጓል፤

እናም አሁን፣ እነሆ፣ ለእርሱም እንዲህ ትለዋለህ—ለአንተ የተናገረህ፣ እንዲህ ብሎሀል፥ እኔ ጌታ አምላክ ነኝ፣ እናም እነዚህን ነገሮች ለአንተ፣ ለአገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ፣ ሰጥቻለሁ፣ እናም ለእነዚህም ነገሮች ምስክር ሆነህ እንድትቆም አዝዤሀለሁ፤

እናም እኔ ላዘዝኩህ ሰዎች ካልሆነ በስተቀር እንዳታሳያቸው ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን እንድትገባ አድርጌሀለሁ፤ በእነርሱም ላይ እኔ ካልሰጠሁህ በስተቀር ምንም አይነት ስልጣን የለህም።

እናም ሰሌዳዎቹን የመተርጎም ስጦታ አለህ፤ እናም ይህም በአንተ ላይ ካደረኩት የመጀመሪያው ስጦታ ነው፤ በዚህ አላማዬ እስኪሟላ ድረስ ሌላ ስጦታ እንዳለው እንዳታስመስል አዝዤሀለሁ፤ ይህም እስኪያልቅ ድረስ ሌላ ምንም ስጦታ አልሰጥህምና።

እውነት፣ እልሀለው፣ ቃላቴን የማያደምጡ ከሆነ በምድር ነዋሪዎች ላይ ዋይታ ይመጣል፤

ስለዚህ ከአሁን በኋላ ትሾማለህና ሂድ እናም ቃሌን ለሰዎች ልጆች አድርስ።

እነሆ፤ ቃላቴን የማያምኑ ከሆን፤ አገልጋዬ ጆሴፍ፣ የሚቻል ሆኖ ለአንተ የሰጠሁትን ነገሮች ሁሉ ብታሳያቸውም፣ አንተን አያምኑህም።

አቤቱ፣ ይህ የማያምን አንገተ ደንዳና ትውልድ—ቁጣዬ በእነርሱ ላይ ተቀጣጥሏል።

እነሆ፣ እውነት እልሀለሁ፣ አገልጋዬ ጆሴፍ፣ ለአንተ በአደራ የሰጠሁህን እነዚህን ነገሮች የጠበኩት በጥበብ አላማዬ ምክንያት ነው፣ እና ይህም ወደፊት ለሚመጡት ትውልዶች እንዲታወቅ ይደረጋል፤

ነገር ግን ይህ ትውልድ በአንተ አማካይነት ቃሌን ያገኛል፤

፲፩ እናም ከአንተ ምስክርነት በተጨማሪ ጠርቼም የምሾማቸው፣ እነዚህንም ነገሮች የማሳያቸው የሶስቱ አገልጋዬቼ ምስክርነት እናም በአንተ አማካይነት የተሰጡትን ቃሎቼን ይዘው ወደፊት ይጓዛሉ።

፲፪ አዎን፣ እነዚህ ነገሮች በእርግጥም እውነት እንደሆኑ ያውቃሉ፣ ምክንያቱም ከሰማይ እኔ አውጅላቸዋለሁና።

፲፫ እነዚህን ነገሮች እንዳሉ እና ማየት ይችሉ ዘንድ ሀይልን እሰጣቸዋለሁ፤

፲፬ እናም እንደጨረቃ የጠራች፣ እንደ ጸሀይ መልከ መልካም፣ ሰንደቅ ዓርማን እንዳነገበ ወታደር የምታስፈራው ቤተክርስቲያኔ ከምድረበዳ በምትነሳበት እና መምጣት በምትጀምርበት ጊዜ፣ ይህን አይነት ምስክርነት፣ ይህን ሀይል፣ በዚህ ትውልድ መካከል እንዲቀበል ለሌላ ለማንም አልሰጥም።

፲፭ እናም ስለቃሌ የሶስቱን ምስክሮችን ምስክርነት እልካለሁ።

፲፮ እናም እነሆ፣ ቃሌን የሚያምኑ ሁሉ በመንፈሴ መገለጥ እጎበኛቸዋለሁ፤ እናም ከእኔ፣ እንዲሁም ከውሀ እና ከመንፈስ ይወለዳሉ

፲፯ እናም ገና ስላልተሾማችሁ ለትንሽ ጊዜ መቆየት አለባችሁ—

፲፰ እናም በእነርሱ ላይ ልባቸውን ካደነደኑ ምስክርነታቸውም ይህንን ትውልድ ይኮንን ዘንድ ይሄዳል፤

፲፱ በምድር ነዋሪዎች መካከል ጥፋትና መከራ ይመጣል፣ ንስሀ ካልገቡም ምድር ባዶ እስክትሆን ድረስ ከጊዜ ወደ ጊዜ መውረዱ ይቀጥላል፣ እንዲሁም የምድር ነዋሪዎች በምፅዓቴም ብርሀን ይበላሉ እናም ፈጽሞ ይጠፋሉ።

እነሆ፣ በኢየሩሳሌም መጥፊያ ጊዜ እንደነገርኳቸው ህዝብ፣ እነዚህን ነገሮች እነግርሀለሁ፤ በዚያም ጊዜ ቃሌ እንደተረጋገጠ ሁሉ በዚህም ጊዜ ይረጋገጣል።

፳፩ እናም አሁን አገልጋዬ ጆሴፍ በፊቴ በቅንነት እንድትራመድ፣ ንሰሀ እንድትግባ፣ እናም ከዚህ በኋላ በሰዎች ሀሳብ እንዳትወሰድ አዝሀለሁ፤

፳፪ እናም ያዘዝኩህ ትእዛዛት በመጠበቅ ጠንካራ እንድትሆን አዝሀለሁ፤ እናም ይህንን ካላደረግህ ብትገደልም እንኳን ዘለአለማዊ ህይወትን እሰጥሀለሁ።

፳፫ እናም አሁን፣ ዳግም፣ አገልጋዬ ጆሴፍ፣ ምስክርነትን ስለሚፈልገው ሰው እናገርሀለሁ—

፳፬ እነሆ እንዲህ እለዋለሁ፣ ራሱን ከፍ ከፍ ያደርጋል እና እራሱን በብቃት በፊቴ ዝቅ አያደርግም፤ ነገር ግን እራሱን በታላቅ ጸሎት እና እምነት ከልብ በሆነ ፈቃድ ዝቅ የሚያደርግ ከሆነ ማየት የሚሻውን ነገሮች እይታ አሰጠዋለሁ።

፳፭ እናም ለዚህ ትውልድ እንዲህ ይላል፥ እነሆ ጌታ ለጆሴፍ ስሚዝ፣ ዳግማዊ፣ ያሳየውን ነገሮች አይቻለሁ እናም በእርግጥም እውነት እንደሆኑ አውቃለሁ፣ ምክንያቱም ተመልክቻቸዋለሁና፣ በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር ሀይል አይቻቸዋለሁና።

፳፮ እናም እኔ ጌታ አገልጋዬን ማርቲን ሀሪስን እነዚህን ነገሮች በተመለከተ ተመልክቻቸዋለሁ፣ በእግዚሐብሔር ሀይል አይቻቸዋለሁ ከማለት በስተቀር ምንም ተጨማሪ ነገር እንዳይነግራቸው አዝዘዋለሁ፤ እናም የሚናገራቸው ቃላት እነዚህን ናቸው።

፳፯ ነገር ግን ይህን ከካደ ቀደም ብሎ ከእኔ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ያፈርሳል እናም እነሆ፣ ይኮነናል።

፳፰ እናም እራሱን ዝቅ አድርጎ እናም የሰራውን ስህተት ካልተቀበለ እና ትእዛዛቴን ለመጠበቅ ከእኔ ጋር ቃል ካልገባ፣ እና በእኔ ካላመነ በስተቀር፣ እነሆ፣ እንዲህ እለዋለሁ ምንም አይነት እይታ አይኖረውም፣ የተናገርኳቸውን ነገሮች እይታ አልሰጠውምና።

፳፱ እናም ነገሩ ይህ ከሆነ፣ አገልጋዬ ጆሴፍ ካሁን በኋላ ምንም ነገር እንደማይሰራ እንዲሁም ስለዚህም ነገር ካሁን በኋላ እንዳያታክተኝ እንድትነግረው አዝሀለሁ።

ነገሩ እንዲህ ከሆነ፣ እነሆ እንዲህ እልሀለሁ ጆሴፍ፣ ጥቂት ገጾችን ከተረጎምህ በኋላ፣ ዳግም ትተረጉም ዘንድ ዳግመኛ እስከማዝህ ድረስ ለጥቂት ጊዜ ታቆማለህ።

፴፩ እናም ይህንን ካላደረግህ በስተቀር፣ ምንም ስጦታ አይኖርህም እናም የሰጠሁህን ነገሮች እወስዳቸዋለሁ።

፴፪ እናም፣ ምክንያቱም አንተን ለማጥፋት የታለመውን ዕቅድ አስቀድሜ ማየት ስለምችል፣ አዎን አገልጋዬ ማርቲን ሀሪስ ራሱን ዝቅ የማያደርግ ከሆነ እና ምስክርነትን ከእጄ የማይቀበል ከሆነ ወደመተላለፍ እንደሚወድቅ አስቀድሜ አይቻለሁ፤

፴፫ እናም ሌሎች ብዙ አንተን ከምድር ላይ ለማጥፋት የሚያቅዱ አሉ፤ እናም በዚህ ምክንያት ቀኖችህ ይራዘሙ ዘንድ ለአንተ እነዚህን ትእዛዛት ሰጥቻለሁ።

፴፬ አዎን፣ በዚህ ምክንያት እንዲህ ብያለሁ፣ እስከማዝህ ድረስ አቁም እናም ባለህበት ሁን፣ እናም ያዘዝኩሁን ነገሮችን የምታከናውንበትን ሁኔታዎች አዘጋጃለሁ

፴፭ እናም ትእዛዛቴን በመጠበቅ ታማኝ ከሆንህ፣ በመጨረሻው ቀን ከፍ ትላለህ። አሜን።