ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፵፮


ክፍል ፵፮

በመጋቢት ፰፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ለቤተክስቲያኗ የተሰጠ ራዕይ። በዚህ በቤተክርስቲያኗ ቀደምት ጊዜያት፣ የቤተክርስቲያኗን ስርዓቶች ለማከናወን አንድ ወጥ የሆነ የአሰራር ሁኔታ አልነበረም። ነገር ግን፣ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎች እና በሌሎች ጉባዔዎች የቤተክርስቲያኗን አባላትና በትጋት ቤተክርስቲያኗን እየመረመሩ ያሉትን የመቀበል ልምድ በመጠኑም ቢሆን ነበር። ይህ ራዕይ የስብሰባዎችን አካሄድና አመራር እና የመንፈስ ስጦታዎችን ስለመፈለግ እና ለይቶ ስለማወቅ ስላለው መመሪያ በተመለከተ የጌታን ፈቃድ ይገልጣል።

፩–፪፣ ሽማግሌዎች ሰብሰባዎችን መንፈስ ቅዱስ እንደመራቸው ማከናወን አለባቸው፤ ፫–፮፣ እውነትን የሚሹ ከቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎች መገለል የለባቸውም፤ ፯–፲፪፣ እግዚአብሔርን ጠይቁ እናም የመንፈስ ስጦታዎችን ፈልጉ፣ ፲፫–፳፮፣ ከእነዚህም ስጦታዎች የጥቂቶቹ ዝርዝር፤ ፳፯–፴፫፣ የቤተክርቲያን መሪዎች የመንፈስን ስጦታዎች የመለየት ሀይል ተሰጥቷቸዋል።

የቤተክርቲያኔ ህዝብ ሆይ፣ አድምጡ፤ እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች ለእናንተው የሚነገሯችሁ ለእናንተ ጥቅም እና ትምህርት ነውና።

ነገር ግን ምንም እንኳን እነዚህ ነገሮች ቢጻፉም፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ እንዲሁም ፍጻሜ እስከሚሆንበት ወቅት፣ ሁሉንም ስብሰባዎች በመንፈስ ቅዱስ ምሪትና አመራር እንዲያካሂዱ በሁሉም ጊዜያት ለቤተክርስቲያኔ ሽማግሌዎች ተሰጥቷቸዋል።

ሆኖም፣ በአለም ፊት ከሚደረጉት የህዝብ ስብሰባዎቻችሁ ውስጥ በፍጹም ማንንም እንዳታስወጡ ታዛችኋል።

እንዲሁም ማንንም የቤተክርስቲያኗ አባል ከቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎች እንዳታስወጡ ታዛችኋል፤ ሆኖም፣ ማንም በደልን ያደረገ ቢኖር እስኪያስተሰርይ ድረስ ቅዱስ ቁርባንን እንዲወስድ አትፍቀዱለት።

ደግሞም እንዲህ እላችኋለሁ፣ ማናቸውንም መንግስትን በትጋት እየፈለጉ ያሉትን ከቅዱስ ቁርባን ስብሰባዎቻችሁ አታስወጧቸው—ይህንን የምናገረውም በቤተክርቲያኗ አባል ስላልሆኑት ነው።

ደግሞም እንዲህ እላችኋለሁ፣ በማረጋገጫ ስብሰባዎቻችሁ ውስጥ የቤተክርቲያን አባል ያልሆኑ፣ በፅኑ መንግስትን የሚሹ፣ የሚገኙ ቢሆን አታስወጧቸው።

ነገር ግን በልግስና የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ስለሁሉም ነገሮች እንድትጠይቁት ታዛችኋል፤ እናም መንፈስ የሚመሰክርላችሁንም ሁሉ በልብ ቅድስና፣ በፊቴ በቅንነት በመራመድ፣ የደህንነታችሁን ፍጻሜ እያሰባችሁ፣ ሁሉንም ነገሮች በጸሎትና በምስጋና በማድረግ፣ በክፉመናፍስት ወይም በአጋንንት ትምህርት ወይም በሰዎች ትእዛዛት እንዳትወሰዱ የእኔ ፈቃድ ነው፤ አንዳንዶቹ ከሰዎች ሌሎቹ ደግሞ ከአጋንንት ናቸውና።

ስለዚህ፣ እንዳትታለሉ ተጠንቀቁ፤ እና ዘወትር ለምን እንደተሰጧችሁ እያስታወሳችሁ፣ እንዳትታለሉም የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በፅኑ ፈልጉ

በእውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ለሚወዱኝ እና ሁሉንም ትእዛዛቴን ለሚጠብቁ እናም ይህን ለማድረግ ፈቃድ ላላቸው ለእነርሱ ጥቅም የተሰጡ ናቸው፤ ለምኞቶቻችሁ ማስፈፀሚያ በክፉ ለምልክት ሳይጠይቁ፣ ከእኔ የሚሹት ወይም ይጠየቁበት ዘንድ እንዲጠቀሙበት ነው።

እና ደግሞም በእውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ለቤተክርቲያኗ የተሰጡት ስጦታዎች ምን እንደሆኑ፣ ሁል ጊዜም እንድታስታውሷቸውና በአዕምሮአችሁ እንድትጠብቋቸው ፍቃዴ ነው።

፲፩ ብዙ ስጦታዎች አሉ፣ ሁሉም ስጦታዎች ለሁሉም አልተሰጡም፤ እያንዳንዱም ሰው አንድ ስጦታ በእግዚአብሔር መንፈስ ተስጥቶታል።

፲፪ ሁሉም በዚህም እንዲጠቀሙበት፣ ለአንዳንዶቹ አንድ ተሰጥቷል፣ እና ለሌሎችም ሌላ ተሰጥቷል።

፲፫ ለአንዳንዶቹ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ፣ እና ለአለምም ኃጢአት እንደተሰቀለ እንዲያውቁ በመንፈስ ቅዱስ ተሰጥቷቸዋል።

፲፬ በታማኝነትም ቢቀጠሉ ዘለአለማዊ ህይወት እንዲኖራቸው፣ ለሌሎችም በእነርሱ ቃላት እንዲያምኑ ተሰጥቷቸዋል።

፲፭ እናም ደግሞም፣ ለአንዳንዶቹ፣ አንዱን ጌታ እንደሚያስደስተው፣ እንደ ጌታ ፈቃድ፣ እንደ ሰው ልጆች ሁኔታዎች ምህረቱን በማመቻቸት፣ በመንፈስ ቅዱስ የአስተዳደርን ልዩነት እንዲያውቁ ተስጥቷቸዋል።

፲፮ ደግሞም፣ ለሌሎችም ስለ አሰራር ልዩነት፣ ከእግዚአብሔርም እንደሚመጡ፣ መንፈስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም እንደሚሰጠው፣ እንዲያውቁ በመንፈስ ቅዱስ ይሰጣቸዋል።

፲፯ እናም ዳግም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ለአንዳዶቹ በእግዚአብሔር መንፈስ፣ የጥበብ ቃል ተስጥቷቸዋል።

፲፰ ለሌላም፣ ሁሉም ብልህ እንዲሆኑ እና እውቀት እንዲኖራቸው ይማሩ ዘንድ፣ የእውቀት ቃል ተስጥቷቸዋል።

፲፱ ደግሞም፣ ለአንዳንዶቹ ለመፈወስ እምነት እንዲኖራቸው ተሰጥቷቸዋል፤

እናም ለሌሎች ይፈውሱ ዘንድ እምነት እንዲኖራቸው ተስጥቷቸዋል።

፳፩ ደግሞም፣ ለአንዳንዶቹ ተዓምራትን ማድረግ ተሰጥቷቸዋል።

፳፪ እና ለሌሎችም ትንቢትን መናገር ተሰጥቷቸዋል።

፳፫ እና ለሌሎችም መናፍስትን ለመለየት ተሰጥቷቸዋል።

፳፬ ደግሞም፣ ለአንዳንዶች በልሳን መናገር ተሰጥቷቸዋል።

፳፭ እና ለሌላውም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ተሰጥቶታል።

፳፮ እናም እነዚህ ስጦታዎች ሁሉ፣ ለእግዚአብሔር ልጆች ጥቅም፣ ከእግዚአብሔር የመጡ ናቸው።

፳፯ ለቤተክርቲያኗ ኤጲስ ቆጶስ፣ እናም ቤተክርቲያኗን እንዲጠብቁና የቤተክርቲያኗ ሽማግሌዎች እንዲሆኑ በእግዚአብሔር ለተመደቡት እና ለተሾሙትም፣ ከመካከላችሁ ከእግዚአብሔር የመጣ ያልሆኑትን ነገሮች ናቸው እንዳይሉ እነዚህን ስጦታዎች ለይተው እንዲያውቁ ተሰጥቷቸዋል።

፳፰ እናም እንዲህ ይሆናል፣ በመንፈስ የሚጠይቅ እርሱ በመንፈስም ይቀበላል፤

፳፱ ለአንዳንዶቹ እነዚህ ሁሉ ስጦታዎች የሚሰጧቸውም፣ መሪም እንዲኖር፣ እያንዳንዱ አባላት በዚህ ይጠቀሙበት ዘንድ ነው።

በመንፈስ የሚጠይቀው እርሱ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይጠይቃል፤ ስለዚህ እንደጠየቀውም ተደርጓለታል።

፴፩ ደግሞም፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ በመንፈስ ምንም ስታደርጉ፣ ሁሉም ነገሮች በክርስቶስ ስም መደረግ አለባቸው፤

፴፪ እናም ለማንኛውም የተባረካችሁባቸው በረከቶች ምስጋናን በመንፈስ ለእግዚአብሔር መስጠት አለባችሁ።

፴፫ እና በፊቴም መልካምነትንና ቅድስናን ሁል ጊዜ መለማመድ አለባችሁ። እንዲህም ይሁን። አሜን።