ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፳፱


ክፍል ፳፱

መስከረም ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በፈየት ኒው ዮርክ በስድስት ሽማግሌዎች ፊት በነቢዩ ጆሴፍ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ይህ ራዕይ የተሰጠው ከጉባዔው ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ፣ ከመሰከረም ፳፮፣ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) ጀምሮ ነው።

፩–፰፣ ክርስቶስ የመረጣቸውን ይሰበስባል፤ ፱–፲፩፣ ምፅአቱ አንድ ሺህ ዘመን እንዲጀምር ያደርጋል፤ ፲፪–፲፫፣ አስራ ሁለቱ መላው እስራኤልን ይፈርዳሉ፤ ፲፬–፳፩፣ ምልክቶች፣ መቅሰፍቶች፣ እና ውድመቶች ዳግም መፅአትን ይቀድማሉ፣ ፳፪–፳፰፣ የመጨረሻው ትንሳዔ እና የመጨረሻው ፍርድ አንድ ሺህ ዘመንን ይከተላሉ፤ ፳፱–፴፭፣ ሁሉም ነገሮች ለጌታ መንፈሳዊ ናቸው፤ ፴፮–፴፱፣ ሰይጣን እና ተከታዮቹ የሰውን ልጅ እንዲፈትኑ ከሰማይ ተወርውረዋል፤ ፵–፵፭፣ ውድቀቱ እና የኃጢአት ክፍያው መዳንን ያመጣሉ፤ ፵፮–፶፣ ህፃናት ልጆች በሀጢይት ክፍያው ድነዋል።

ታላቁ እኔ ነኝ ያለውን፣ የምህረቱ ክንድ ለኃጢአታችሁ ክፍያ የሆንውን፣ የአዳኛችሁን የኢየሱስ ክርስቶስን ድምጽ አድምጡ፤

ድምጼን የሚያደምጡ እና ራሳቸውን በፊቴ ዝቅ የሚያደርጉ፣ እና ወደ እኔም በታላቅ ጸሎት የሚጣሩትን ህዝቦቹንም ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ የሚሰበስበውን የእነርሱን ድምጽ አድምጡ።

እነሆ እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ በዚህ ጊዜ ለኃጢአታችሁ ይቅርታን አግኝታችኋል፣ ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ትቀበላላችሁ፤ ነገር ግን ከዚህ የሚብስ ነገር እንዳይመጣባችሁ ዳግመኛ ኃጢአት እንዳትሰሩ አስታውሱ።

እውነት እላችኋለሁ፣ ልክ እንደ መለከትም ድምጽ፣ በደስታ ድምጽ ወንጌሌን ለማወጅ ከአለም ውስጥ ተመርጣችኋልና።

እኔ በመካከላችሁ ስላለሁ እና በአብም ዘንድ ስለማማልዳችሁ፣ ልባችሁን አንሱ እናም ተደሰቱ፤ እናም መንግስቱን ሊሰጣችሁ መልካም ፈቃዱ ነው።

እናም፣ እንደተጻፈው—እንደ ትእዛዜ በጸሎት አንድ ሆናችሁ በእምነት የምትጠይቁትን ማንኛውንም ነገር ትቀበላላችሁ።

እናም በእኔ የተመረጡትን ለመሰብሰብ ተጠርታችኋል፣ ምክንያቱም በእኔ የተመረጡት ድምጼን ይሰማሉ እና ልባቸውንም አያደነድኑም፤

ስለዚህ ልባቸውን ለማዘጋጀት እና በክፉዎች ላይ በሚላክበትን መከራ እና ጭንቀት ቀን ለመቃወም እንዲዘጋጁ፣ በዚህ ምድር ላይ በአንድ ስፍራ እንዲሰበሰቡ አዋጁ ከአብ ዘንድ ወጥቷል።

እነሆ ሰዓቱ ተቃርቧል፣ ምድርም የምትጠፋበትም ዳርሷል፤ እናም ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሰሩ ሁሉ ገለባ የሚሆኑበት ይሆናሉ፤ በምድር ላይ ኃጢአት እንዳይኖር አቃጥላቸዋለሁ ይላል የሰራዊት ጌታ፤

ሰዓቱ ተቃርቧል፣ እናም በኃዋሪያቴ የተነገረው መፈጸም አለበት፤ እንደተናገሩት እንዲሁ ይፈጸማልና፤

፲፩ ራሴን ከሰማይ በኃይል እና በታላቅ ክብር፣ በሰማይ ሰራዊት ጋር እገልጣለሁ፣ እና በጽድቅም ከሰዎች ጋር በምድር ላይ ለአንድ ሺህ አመታት እኖራለሁ፣ እናም ኃጢአተኞችም መቆም አይችሉም።

፲፪ እናም ዳግም፣ እውነት፣ እውነት፣ እላችኋለሁ፣ በኢየሩሳሌም በአገልግሎቴ ከእኔ ጋር የነበሩት አስራ ሁለቱ ሐዋሪያቴበእሳት አምድ በምመጣበት ቀን የጽድቅን ልብስ ለብሰው፣ አክሊልን በራሳቸው ላይ ደፍተው፣ ልክ እንደ እኔው በክብር፣ መላው እስራኤልን ለመፍረድ፣ እንዲሁም የወደዱኝ እና ትእዛዛቴን የጠበቁትን ብቻ ለመፍረድ፣ ከእኔ ጋር በቀኝ በኩል ይቆሙ ዘንድ በአብ ፈቃድ የጸና አዋጅ ወጥቷል።

፲፫ እነሆ ልክ እንደ ሲና ተራራ መለከትም በረጅም እና በጉልህ ይሰማል፣ እናም መላው ምድርም ይናወጣል፣ እናም አዎን በእኔ የሞቱትም ሙታን የጽድቅን አክሊል ሊቀበሉ እናም ልክ እንደ እኔ ሊለብሱ፣ አንድ እንሆን ዘንድ ከእኔ ጋር እንዲሆኑ ወደፊትም ይመጣሉ

፲፬ ነገር ግን፣ እነሆ እውነት እልሀለሁ ይህ ታላቅ ቀን ከመምጣቱ በፊት ፀሀይ ትጨልማለች፣ እናም ጨረቃም ወደ ደምነት ትለወጣለች፣ እናም ከዋክብትም ከሰማይ ይረግፋሉ፣ እናም በላይ በሰማይና በታች በምድርም ታላቅ ምልክቶችም ይሆናሉ፤

፲፭ እናም በስዎች መካካልም ለቅሶ እና ሐዘን ይሆናል፤

፲፮ እናም ታላቅ የበረዶ አውሎነፋስም የምድርን ሰብል ለማጥፋት ይላካል።

፲፯ እንዲህም ይሆናል፣ በአለም ኃጢአት የተነሳ፣ ንስሀም ስለማይገቡ፣ በኃጢአተኞች ላይ በቀልን አደርጋለሁ፣ የቁጣ ጽዋዬም ሞልቷልና፤ ስለሆነም እነሆ፣ ካልሰሙኝ ደሜ አያነጻቸውም።

፲፰ ሰለዚህ፣ እኔ ጌታ አምላክ በውስጧ የሚኖሩትን ይይዙ ዘንድ በምድር ላይ ዝንቦችን እልካለሁ፣ እናም ስጋቸውንም ይበላሉ፣ በውስጣቸውም እጭ እንዲያዝ አደርጋለሁ፤

፲፱ እናም እኔን በመቃወም እንዳይናገሩ ምላሳቸው እንዳይንቀሳቀስ አደርገዋለሁ፤ ስጋቸው ከአጥንታቸው እናም አይኖቻቸው ከአይን ጉድጓዶቻቸው ላይ ይረግፋሉ።

እናም የጫካ አውሬዎች እናም የሰማይ አዕዋፋት ይበሏቸዋል።

፳፩ እናም ታላቋና የርኩሰት ቤተክርስቲያን፣ እነዚህ ገና ያልተፈጸሙትን ነገሮች ግን መፈጸም የሚገባቸውን ነገሮች ነቢዩ ሕዝቅኤል እንደተናገረው፣ እና እኔ ህያው እንደሆንኩ፣ የምድር ሁሉ ጋለሞታ የሆነችው ወደምትበላ እሳት ትጣላለች፣ ምክንያቱም የረከሰ አይነግስምና።

፳፪ እናም ዳግም፣ እውነት፣ እውነት፣ እላችኋለሁ አንድ ሺህ አመት ሲጠናቀቅ፣ እናም ሰዎች ዳግም አምላካቸውን መካድ ሲጀምሩ፣ ምድርንና የምተዋት ለጥቂት ጊዜ ይሆናል።

፳፫ እናም መጨረሻው ይመጣል፣ እናም ሰማይ እና ምድር ይጠፋሉ እናም ያልፋሉ፣ እንዲሁም አዲስ ሰማይ እና አዲስ ምድርም ይሆናል።

፳፬ እነሆ ሁሉም አሮጌ ነገሮች ያልፋሉ፣ ሁሉም ነገሮች፣ እንዲሁም ሰማይ እና ምድር እናም በውስጣቸው ያሉት ሁሉ፣ ሰዎች እና አራዊት፣ የሰማይ አዕዋፋት፣ እናም የባህር አሳዎች ሁሉ አዲስ ይሆናሉ፤

፳፭ እናም አንድ ጸጉርም ሆነ ጉድፍ ከፊታችሁ እንኳን አይጠፋም፣ የእጄ ስራ ነውና።

፳፮ ነገር ግን እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ምድር ከማለፏ በፊት፣ የመላእክቴ አለቃ ሚካኤል መለከቱን ይነፋል፣ ከዚያም በኋላ የሞቱት ሁሉ ይነሳሉ፣ መቃብራቸው ይከፈታልና፣ እናም ወደፊትም ይመጣሉ—አዎን ሁሉም ወደፊት ይመጣሉ።

፳፯ እናም ጻድቃን ለዘለአለም ህይወት በቀኜ ይሰበሰባሉ፤ እናም በግራዬ የሚገኙትን ኃጢአተኞችም በአባቴ ፊት የእኔ እንደሆኑ ለመናገር ያሳፍረኛል፤

፳፰ ስለዚህ እንዲህም እላችኋለሁ—እናንት የተረገማችሁ ለዲያብሎስ እና ለመላእክቱ ወደተዘጋጀው ዘለአለማዊ እሳት ከፊቴ ሂዱ

፳፱ እናም አሁን፣ እነሆ፣ እላችኋለሁ፣ በፍጹም በማንኛው ጊዜ እንዲመለሱ በአፌ ተናግሬ አላውቅም፣ እኔ ወዳለሁበት መምጣት አይችሉም፣ ሀይል የላቸውምና።

ነገር ግን አስታውሱ ሁሉም ፍርዶቼ ለሰዎች አልተሰጡም፤ ከአፌ ቃላት እንደወጡ እንዲሁ ይፈጸማሉ፣ የመንፈሴ ኃይል በሆነው በቃሌ ኃይል ከፈጠርኳቸው ነገሮች ፊተኞችም ኋለኞች፣ ኋለኞቸም ፊተኞች ይሆናሉ።

፴፩ በመንፈሴ ሀይል ፈጥሬአቸዋለሁና፤ አዎን፣ መንፈሳዊ እንዲሁም ስጋዊ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ—

፴፪ የስራዬ ጅማሬ የሆነው በቅድሚያ መንፈሳዊ፣ ሁለተኛ ጊዜአዊዊ፤ እናም ደግሞ የስራዬ ማብቂያ የሆነውን፣ በቅድሚያ ጊዜአዊው፣ እና ሁለተኛም መንፈሳዊው—

፴፫ ለእናንተ ስናገር በተፈጥሮ ትረዱ ዘንድ ነው፤ ነገር ግን ለእኔ ለስራዬ መጨረሻም ሆነ መጀመሪያ የለውም፤ ነገር ግን ለእናንተ ተረዱት ዘንድ ተሰጥቷችኋል፣ ምክንያቱም እኔን ጠይቃችኋል እናም ተስማምታችኋልና።

፴፬ ስለዚህ፣ እውነት እላችኋለሁ ሁሉም ነገሮች ለእኔ መንፈሳዊ ናቸው፣ እናም በማንኛውም ጊዜ ቢሆን፣ ለሰው ወይም ለሰው ልጆች፣ ወይም እኔ ለፈጠርኩት ለአባታችሁ አዳምም፣ ጊዜያዊ የሆነ ህግ አልሰጠኋቸውም።

፴፭ እነሆ፣ ለእርሱ ራሱን እንዲወክል ሰጥቸዋለሁ፣ እናም ትእዛዛትን ሰጠሁት ነገር ግን ጊዜአዊ ትእዛዝን አልሰጠሁትም፣ ትእዛዛቴ መንፍሳዊ ናቸውና፤ ተፍጥሯዊ ሆነ ጊዜያዊ፣ እንዲሁም ስጋዊ ወይም ስሜታዊ አይደሉም።

፴፮ እናም እንዲህም ሆነ፣ አዳም በዲያብሎስ በመፈተን—እነሆ፣ ዲያብሎስም በአዳም ፊት ነበርና፣ ምክንያቱም ኃይሌ የሆነውን ክብርህን ስጠኝ በማለት በእኔ ላይ አምጿልና፤ እንዲሁም አንድ ሶስተኛውን የሰማይ ሰራዊት በነጻ ምርጫቸው እኔን እንዲተው አደረገ፤

፴፯ እናም ወደታች ተጥለዋል፣ በዚህም የተነሳ ዲያብሎስ እና መላእክቱ መጥተዋል፤

፴፰ እናም፣ እነሆ፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ ለእነርሱ ስፍራ ተዘጋጅቶላቸዋል፣ ይህም ስፍራ ሲኦል ነው።

፴፱ እናም ሰይጣን የሰዎችን ልጆች ይፈትን ዘንድ ግድ ነው፣ ይህ ካልሆነ በራሳቸው መምረጥ አይችሉምና፤ ምክንያቱም መራራውን ካላወቁ ጣፋጩን ማወቅ አይችሉም ነበር—

ስለዚህ፣ እንዲህም ሆነ ዲያብሎስ አዳምን ፈተነው፣ እናም የተከለከለውን ፍሬ በላ እናም ትእዛዙን ተላለፈ፣ በዚህም ለፈተና ራሱን አሳልፎ በመስጠቱ ምክንያት በሰይጣን ፈቃድ ተገዢ ሆነ።

፵፩ ስለዚህ፣ እኔ፣ ጌታ አምላክ በመተላለፉ ምክንያት ከፊቴ ከዔደን ገነት እንዲወጣ አደረግሁ፣ በዚህም የተነሳ የመጀመርያ ሞት በሆነው እንዲሁም የመጨረሻ ሞት በሚሆነው መንፈሳዊ በሆነው በኃጢአተኞችም ላይ እናንት የተረገማችሁ ወደዚያ ሂዱ በምልበት ጊዜ በሚከሰተው የመንፈስ ሞት ሞተ።

፵፪ ነገር ግን፣ እነሆ፣ እንዲህ እላችኋለሁ እኔ፣ ጌታ አምላክ፣ ንስሀ እና በአንድያ ልጄ ስም በእምነት መዳንን እንዲያውጁላቸው እኔ ጌታ አምላክ መላእክትን እስከምልክላቸው ድረስ በጊዜያው ሞት አዳም እና ዘሮቹ እዳይሞቱ አደረግሁኝ።

፵፫ እናም በዚህም የተነሳ እኔ ጌታ እግዚአብሔር የሰው ልጅ የሚሞከርበት ቀናቱን መደብኩኝ፣ በዚህም የሚያምኑትም ሁሉ፣ በስጋዊ ሞቱ ወደ አለሟችነት እና በዘለአለማዊ ህይወት ለመነሳት እንዲችል እኔ ጌታ እግዚአብሔር ይህን አደረግሁ።

፵፬ እናም የማያምኑት ወደ ዘለአለማዊ ጥፋት፣ ንስሀ ባለመግባታቸው ከመንፈሳዊ ውድቀታቸው አይድኑምና፤

፵፭ እነሆ ከብርሀን ይልቅ ጭለማን ይወዳሉ፣ እናም ስራቸውም እርኩስ ነው፣ እናም ለሚታዘዙለት ለዚያ ደሞዛቸውን ይቀበላሉ።

፵፮ ነገር ግን፣ እላችኋለሁ፣ ህጻናት ልጆች ከአለም መጀመሪያ ጀምሮ በአንድያ ልጄ ድነዋል

፵፯ ስለዚህ፣ ኃጢአትን ሊሰሩ አይችሉም፣ በእኔ ፊት ተጠያቂ እስኪሆኑ ድረስ ህጻናት ልጆችን ለመፈተን ሰይጣን ሀይል አልተሰጠውምና፤

፵፰ ስለዚህ እንደ ፈቃዴ፣ እንደወደድሁ ከአባቶቻቸው እጅ ታላላቅ ነገሮችን እጠብቅባቸው ዘንድ ይህ ተሰጥቷቸዋል።

፵፱ እናም፣ ዳግም፣ እላችኋለሁ፣ እውቀት ያለው ሁሉ ንስሀ ይገባ ዘንድ አላዘዝሁምን?

እናም መረዳት ለሌለው እርሱ፣ እንደተጻፈው ያደርግ ዘንድ ሀላፊነቱ የእኔ ነው። እናም አሁን በዚህ ጊዜ ለእናንተ ተጨማሪ ነገርን አላውጅም። አሜን።