ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፴፬


ክፍል ፻፴፬

በነሀሴ ፲፯፣ ፲፰፻፴፭ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ በነበረው በቤተክርስቲያኗ አጠቃላይ ስብሰባ ላይ በአንድ ድምፅ ምርጫ የተቀበሉት ስለመንግስት እና በአጠቃላይም ስለህግጋት የሚመለከት የእምነት እወጃ። ብዙ ቅዱሳን የትምህርት እና ቃል ኪዳን የመጀመሪያው ቅጂ ውስጥ እንዲኖር የቀረበውን ለማመዛዘን ተሰብስበው ነበር። በዚያም ጊዜ፣ የሚቀጥለው መግቢያ ለዚህ እወጃ ተሰጠው፥ “የምድር መንግስታትን እና አጠቃላይ ህግጋትን በሚመለከት ያለን እምነት የስህተት ትርጉም ወይም የስህተት መረጃ እንዳይሆን፣ በዚህ መፅሀፍ መዝጊያ ላይ ይህን በሚመለከት አስተሳሰባችንን ማቅረብ ትክክለኛ እንደሆነ አስበናል።”

፩–፬፣ መንግስታት የህሊናን ነጻነት እና አምልኮን ይጠብቁ፤ ፭–፰፣ ሁሉም ሰዎች መንግስታቸውን መደገፍ እና ለህግም ታዛዥነት እና አክብሮት ሊኖራቸው ይገባል፤ ፱–፲፣ የሀይማኖት ህብረተሰቦች የህዝባዊ ሀይላት አይኑራቸው፤ ፲፩–፲፪፣ ሰዎች ራሳቸውን እና ንብረቶቻቸውን በመጠበቅ ከጥፋት ነጻ ይሆናሉ።

መንግስታት እግዚአብሔር ለሰው ጥቅም የመሰረታቸው እንደሆኑ እናምናለን፤ እና እነዚህን በሚመለከትም፣ ለህብረተሰብ ጥቅም እና ደህንነት በሚሰሩት አማካይነት ህግጋትን እና እነርሱንም በሚያስተዳድሩ ሰዎችን በተጠያቂነት ይይዟቸዋል።

ህግጋት ለእያንዳንዱ የህሊና ነጻነት ጥቅም፣ የንብረት መብትና ቁጥጥር፣ እና የህይወት ጥበቃን ለማግኘት ካልተመሰረቱ እና ተጥሰውም ካልተገኙ በስተቀር ምንም መንግስት በሰላም ለመኖር እንደማይችል እምነት አለን።

መንግስታት ሁሉ እነዚህን ህግጋት ለማስከበር ህዝባዊ ባለስልጣናት እና ዳኛዎች እንደሚያስፈልጋቸው እናምናለን፤ እና ህጉን በእኩልነት እና በፍትሀዊነት የሚያስተዳድሩም ሪፐብሊክ ከሆነ በህዝብ ድምፅ፣ ወይም በነገስታት ይፈለጉ፣ ይደገፉም።

ሀይማኖት በእግዚአብሔር እንዲመሰረት እናምናለን፤ እና የሀይማኖታቸው አስተያየት የሌሎችን መብት እና ነጻነት እስካልጣሰ ድረስ፣ ይህን ለመጠቀምም ሰዎች ለእርሱ እና ለእርሱ ብቻ መልስን ይስጡ፤ ነገር ግን የሰዎች ህግ የሰዎችን ህሊና በማስተሳሰር የማምለክን ደንብ በማዘዝ ጣልቃ ለመግባት፣ ወይም የህዝባዊ ወይም የግል የአምልኮ መንገድን ለማዘዝ መብት እንዳላቸው አናምንም፤ ዳኞች ወንጀሎችን ያስቁሙ፣ ነገር ግን ህሊናን አይቆጣጠሩ፤ ወንጀለኛነትን ይቅጡ፣ ነገር ግን የነፍስን ነጻነት አይጨቁኑ።

ሁሉም ሰዎች በሚኖሩባቸው መንግስታት ህግጋት የወረሱትን እና የማይነጠለውን መብቶቻቸውን የሚጠብቁላቸውን መንግስታት ለመቀበል እና ለመደገፍ ግዴታ እንዳላቸው እናምናለን፤ እና በእንደዚህ ከተጠበቁ ዜጎች ህዝብን ማሳመጽ እና መቃወም የሚጠበቅባቸው አይደለም፣ እና መቀጣትም ይገባቸዋል፤ እና መንግስታት ሁሉ የህዝብን ጥቅም በጥብቅ ለመያዝ የራሳቸውን ፍርድ በመልካምነት እንደሚያስቡት እንደዚህ አይነት ህግጋትን ለመስራት መብት አላቸው፤ በዚህም ጊዜ ግን፣ የህሊና ነጻነትን በቅድስና ይጠበቁ።

እያንዳንዱም ሰው በተመደበለት ስፍራ ውስጥ መከበር እንደሚገባው፣ የዋሆችን ለመጠበቅ እና ወንጀለኞችን ለመቅጣት የተመደቡት መሪዎች እና ዳኛዎችም እንደዚህ መከበር እንደሚገባቸው እናምናለን፤ እና ለህግጋትም ሁሉም ሰዎች ክብር እና አክብሮትን ይስጡ፣ ካለእርሱም ስርዓት የለሽነት እና ሽብር ሰላምንና ስምምነትን ይሰጣሉ፤ የሰዎች ህግጋት የሚመሰረቱት እንደግለሰቦች እና እንደህዝቦች፣ በሰዎች እና ሰው መካከል፣ የምንፈልገውን ለመቆጣጠር በሚኖር አላማ ነው፤ እና ከሰማይ የተሰጡት መለኮታዊ ህግጋትም በመንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ መመሪያዎችን ለመጠቀም፣ ለእምነትና ለአምልኮ፣ ሁለቱም በሰው እና በፈጣሪው ይመለሱ ዘንድ ነው።

ገዢዎች፣ ስቴቶች፣ እና መንግስታት መብት እንዳላቸው፣ እና ዜጎች የሀይማኖት እምነታቸውን በነጻነት ለማምለክ እንዲጠብቋቸው ህግጋትን ለማሳለፍ የሚገባቸው እንደሆኑ እናምናለን፤ ነገር ግን ለህግጋት ትኩረትና ክብር እስከ ተሰጠ ድረስ እና እንደዚህ አይነቶቹ የሀይማኖት አስተያየቶች ህዝብን ማሳመጽንና አድማን እንደ ጥፋት የማያዩ እስካልሆነ ድረስ በፍትህ ይህን መብት ለመውሰድ፣ ወይም በአስተያየታቸው እነዚህን ከህግ ውጪ ለማድረግ መብት እንዳላቸው አናምንም።

ወንጀል መስራት እንደ ጥፋቱ መሰረት መቀጣት እንደሚገባው እናምናለን፤ መግደል፣ አገር መክዳት፣ መዝረፍ፣ መስረቅ፣ እና ሰላምን ማፍረስ፣ በሁሉም ሁኔታዎች፣ በወንጀልነታቸው መሰረት እና በሰዎች መካከል ጥፋት ለማድረግ ባላቸው ፍላጎት መሰረት ጥፋቱ በተደረገበት መንግስት ህግጋት ይቀጡ፤ እና ለህዝባዊ ሰላም እና እርጋታ ሁሉም ሰዎች ወደፊት በመሄድ በመልካም ህግጋት ላይ የሚያጠፉትን ለቅጣት ለማምጣት ችሎታቸውን ይጠቀሙበት።

የሀይማኖት ተፅእኖ ከህዝባዊ መንግስት ጋር በመቀላቀል አንድ የሀይማኖት ህብረተሰብን በማበረታታት እና ሌላን በመንፈሳዊ መብት ከህግ ወጪ በማድረግ፣ እና የእያንዳንዱ አባላት መብቶችም እንደ ዜጋ መካዳቸው ትክክል እንደሆነ አናምንም።

የፅድቅ ህብረተሰቦች ሁሉ አባሎቻቸው በሚረብሹበት ጊዜ በህብረተሰቦች መመሪያዎችና መቆጣጠሪያዎች መሰረት ለመቅጣት መብት እንዳላቸው እናምናለን፤ እነዚህ ቅጣቶች ለማህበርተኛነት እና ለመልካም አቋም እስከሆነ ድረስ፤ ነገር ግን ምንም የሀይማኖት ህብረተሰብ ሰዎችን በንብረት ወይም በህይወት መብት ላይ፣ የዚህ አለም ቁሳቁሶችን ሊወስዱባቸው፣ ወይም በህይወታቸው ይሁን በሰውነታቸው ላይ አደጋን ሊያደርሱባቸው፣ ወይም ምንም የሰውነት ቅጣት በእነርሱ ላይ ለማድረግ ስልጣን እንዳላቸው አናምንም። ከህብረተሰቦቻቸው ይወገዙ ዘንድ ህብረታቸውን ለመውሰድ ብቻ ነው የሚችሉት።

፲፩ ሰዎች በህዝባዊ ህግ ለደረሰባቸው አግባብ ላልሆኑ ነገሮች እና ለቅሬታ፣ ለግል መጎሳቆልን፣ ወይም የንብረት ወይም የህሊና መብት መጣስን፣ እና እነዚህን ለመጠበቅ ህግጋት ባሉበት ይግባኝ መጠየቅ እንደሚገባቸው እናምናለን፤ ነገር ግን መንግስትን ከህጋዊ ካልሆነ ወረራ እና ሁሉንም ሰዎች በአስቸኳይ ሁኔታ የመብትን መጣስ እና በህግጋት ይግባኝ ለመጠየቅ በማይቻልበት ጊዜ ርጋታን ለማግኘት ሁሉም ሰዎች ራሳቸውን፣ ባልንጀሮቻቸውን፣ እና ንብረቶቻቸውን በመጠበቅ ጥፋተኞች እንደማይሆኑ እናምናለን።

፲፪ ወንጌልን ለምድር ህዝቦች መስበክ፣ እና በፅድቅ ራሳቸውን ከአለም ክፋት እንዲያድኑ ማስጠንቀቅ ትክክል እንደሆነ እናምናለን፤ ነገር ግን በባሪያዎች ላይ ጣልቃ በመግባት፣ ወይም ለእነርሱ የአለቆቻቸው ፈቃድ ባለማክበር ወንጌልን መስበክ ወይም ማጥመቅ፣ ወይም ጣልቃ በመግባት ወይም ተጽእኖ በማድረግ በዚህ ህይወት ሁኔታቸው እንዳይደሰቱ ማድረግ፣ በዚህም የሰዎችን ህይወት አደጋ ላይ መጣል ትክክለኛ እንደሆነ አናምንም፤ እንደዚህ አይነት ጣልቃ መግባት ህጋዊ ያልሆነ እና ፍትሀዊ እንዳልሆነ እንደሆነ፣ እና በአገልጋይነት ሰዎች በግድ እንዲያዙ ለሚፈቅደው መንግስት ሰላም አደገኛ እንደሆነም እናምናለን።