ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፻፳፬


ክፍል ፻፳፬

በጥር ፲፱፣ ፲፰፻፵፩ (እ.አ.አ.) በናቩ ኢለኖይ ውስጥ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ። በእነርሱ ላይ በመንግስት ባለስልጣናት በተደረጉባቸው ተጨማሪ ስደቶችና ህገ ወጥ ስራዎች ምክንያት፣ ቅዱሳን ሚዙሪን ለቅቀው ለመውጣት ተገድደው ነበር። በጥቅምት ፳፯፣ ፲፰፻፴፰ (እ.አ.አ.) በሚዙሪ አስተዳዳሪ ሊበርን ደብሊው ቧግስ በተሰጠው ዘር የማጥፋት ትእዛዝ ምንም ሌላ ምርጫ አልሰጣቸውም። በ፲፰፻፵፩ (እ.አ.አ.)፣ ይህ ራዕይ ሲሰጥ፣ በቀድሞ ኮመርስ መንደር፣ ኢለኖይ ስፍራ ላይ የተመሰረተው የናቩ ከተማ በቅዱሳኑ ተገንብቶ ነበር፣ እና በዚህም የቤተክርስቲያኗ ጠቅላይ መምሪያ ተመስርቶ ነበር።

፩–፲፬፣ ጆሴፍ ስሚዝ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘደንት፣ ለአስተዳዳሪዎች፣ እና ለሁሉም ሀገሮች መሪዎች ወንጌልን እንዲያውጅ ታዘዘ፤ ፲፭–፳፩፣ በህይወት ከሚኖሩትና ከሞቱት መካከል ሀይረም ስሚዝ፣ ዴቪድ ደብሊው ፓትተን፣ ጆሴፍ ስሚዝ ቀዳማዊ፣ እና ሌሎች ለቅንነታቸው እና ለምግባረ መልካምነታቸው ተባርከዋል፤ ፳፪–፳፰፣ ቅዱሳን እንግዳዎችን የሚቀበሉበትን ቤት እና ቤተመቅደስን እንዲገነቡ ታዝዘዋል፣ ፳፱–፴፮፣ የሙታን ጥምቀት በቤተመቅደስ ውስጥ ይፈጸም፤ ፴፯–፵፬፣ የጌታ ህዝብ ለቅዱስ ስርዓቶች ማከናወኛ ዘወትር ቤተመቅደስን ይገነባሉ፤ ፵፭–፶፭፣ ቅዱሳን በጠላቶቻቸው ክፋት ምክንያት በጃክሰን የግዛት ክፍል ቤተመቅደስን ባለመገንባታቸው ይሁንታን አግኝተዋል፤ ፶፮–፹፫፣ ለናቩ ቤት መገንቢያ መመሪያዎች ተሰጥተዋል፤ ፹፬–፺፮፣ ሀይረም ስሚዝ ፔትሪያርክ እንዲሆን፣ ቁልፎችን እንዲቀበል፣ እና በኦሊቨር ካውድሪ ስፍራ እንዲቆም ተጠርቷል፤ ፺፯–፻፳፪፣ ውልያም ሏው እና ሌሎች በአገልግሎታቸው ተመክረዋል፤ ፻፳፫–፻፵፭፣ አጠቃላይ እና የአካባቢ ባለስልጣናት ከሀላፊነታቸው እና ተባባሪ ግንኙነት ካላቸው ቡድኖች ጋር ተጠርተዋል።

በእውነት፣ ጌታ ለአንተ፣ አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ፣ እንዲህ ይላል፣ አንተ ባደረካቸው መስዋዕት እና እውቅናዎች በተቀበልክባቸው ተደስቼአለሁ፤ በምድር ደካማ ነገሮች ጥበቤን አሳይ ዘንድ፣ ለዚህም ምክንያት ነው ያስነሳሁህ።

ጸሎቶችህ በፊቴ ተቀብዬአቸዋለሁ፤ እና ለእነዚህም መልስ በመስጠት እንዲህ እልሀለሁ፣ አሁንም ወዲያው ወንጌሌን፣ እና በቤተመንግስት ምሳሌነት በመንጠር የምትብረቀረቀው የፅዮን የማዕዘን ራስ ድንጋይ እንድትሆን ስለተከልኳት ካስማ በቅድስና እንድታውጅ ተጠርተሀል።

ይህም እወጃ ለአለም ነገስታት ሁሉ፣ በዚህም አራት ማዕዘናት፣ ለተከበረው እንደ ፕሬዘደንት ለተመረጠው፣ እና ለተከበሩት ለምትኖርበት አገር እና በውጪ ለተበተኑት የምድር አገሮች አስተዳዳሪዎች ሁሉ ይደረግ።

ይህንም በትህትና መንፈስ እና፣ ይህን በምትፅፍበት ጊዜ በውስጥህ በሚገኘው በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ይጻፍ፤

ስለእነዚያ ነገስታት እና ባለስልጣናት፣ እንዲሁም ወደፊት በሚመጣው ጊዜ ስለሚደርስባቸው፣ ያለኝን ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስም አማካይነት ታውቅ ዘንድ ይሰጥሀል።

እነሆ፣ የፅዮንን ብርሀን እና ክብር እንዲመለከቱ ልጠራቸው ነውና፣ የመሞገሷ ዘመንም ቀርቧልና።

ስለዚህ በጎላ ድምፅ እወጃ፣ እና በምስክርህ ጥራቸው፣ እና አትፍራቸው፣ ደግሞም ያለምክንያት ይተዉ ዘንድ፣ እነርሱ እንደ ሣር ናቸው እና ክብራቸውም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ይረግፋልና—

እና አገልጋዮቼን እና የገለጥኩላቸውን ምስክሬን ቢቃወሙ፣ ጥርስ ማፋጨት በሚኖርበት የክፉዎችንም እድል ፈንታ ከግብዞች ጋር በማደርግበት ጊዜ፣ የፊቴንም መጋረጃ ሳወልቅ፣ በጉብኝት ቀን ይጎበኛሉ።

ደግሞም፣ ብዙዎቹንም ለእናንተ ጥቅም፣ ወደ እውነትም ብርሀን እና አህዛብም ወደ ዘለአለማዊነት ወይም ወደ ፅዮን ወደ ዘለአለማዊ ክብር ይመጡ ዘንድ በአይኖቻቸውም ፊት ጸጋን ታገኙ ዘንድ፣ እጎበኛቸዋለሁ እናም ልቦቻቸውንም አለሰልሳለሁ።

በማታስቡበት ሰዓት፣ የጉብኝቴ ቀን ፈጥኖ ይመጣል፤ እና የህዝቤ ደህንነት እና ከእነርሱም የሚቀሩት መሸሸጊያቸው የት ይሆናል?

፲፩ ተነሱ፣ የምድር ነገስታት ሆይ! ከወርቃችሁና ከብራችሁ ጋር ህዝቤን ወደ መርዳት፣ ወደፅዮን ሴት ልጆች ቤት ኑ።

፲፪ ደግሞም፣ እውነት እልሀለሁ፣ አገልጋዬ ሮበርት ቢ ቶምሰን ይህን እወጃ ለመጻፍ ይርዳህ፣ እና ከአንተ ጋር ይሁን፣ በእርሱ ተደስቻለሁና፤

፲፫ ስለዚህ፣ ምክርህን ያድምጥ፣ እና በሚበዙ በረከቶች እባርከዋለሁ፤ ከዚህ ጀምሮ በሁሉም ነገሮች ታማኝ እና እውነተኛ ይሁን፣ እና በአይኖቼም ታላቅ ይሆናል።

፲፬ ነገር ግን በእጆቹ ስለምጠብቅበት መጋቢነትም ያስታውስ።

፲፭ ደግሞም፣ እውነት እልሀለሁ፣ አገልጋዬ ሀይረም ስሚዝ የተባረከ ነው፤ እኔ ጌታ በልቡ ቅንነት፣ እና በፊቴ ትክክል የሆነውን ስለሚወድ እወደዋለሁና፣ ይላል ጌታ።

፲፮ እንደገናም፣ አገልጋዬ ጆን ሲ በነት፣ ቃሌን ለነገስታት እና ለምድር ህዝቦች በመላክ ስራህ ይርዳህ፤ እንዲሁም ከአንተ ከአገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝም ጋር በስቃይህ ሰአት ከጎንህ ይቁም እና ምክርንም የሚቀበል ቢሆን ዋጋው አይወድቅም።

፲፯ እና ፍቅሩም ታላቅ ይሆናልና፣ ይህንም ቢያደርግ የእኔ ይሆናልና፣ ይላል ጌታ። ቢቀጥልም የምቀበለውን፣ የሰራውን ስራ ተመልክቻለሁ፣ እና በበረከቶችን እና ታላቅን የክብር አክሊል እጭንለታለሁ።

፲፰ ደግሞም፣ አገልጋዬ ላይመን ዋይት በፅዮን በትሁትነት መንፈስ፣ በአለም ፊት እየመሰከረልኝ በመስበክ እንዲቀጥል ፍቃዴ እንደሆነ ይህን እልሀለሁ፤ እና በንስርም ክንፍ ላይ እንደሚሆንም እሸከመዋለሁ፤ እና ግርማ እና ክብርንም ለእራሱ እና ለስሜ ያገኛል።

፲፱ ስራውንም ሲጨርስ፣ በዚህ ጊዜ ከእኔ ጋር እንዳለው እንደ አገልጋዬ ዴቪድ ፓትተን እና ደግሞም እንደ አገልጋዬ ኤድዋርድ ፓርትሪጅ፣ እና ደግሞም፣ እርሱም የእኔ ነውና፣ በአብርሐም ጋር ቀኝ እንደተቀመጠው፣ የተባረከው እና በቅድስና ያረጀው አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ፣ ቀዳማዊ ወደ እኔም ዘንድ እቀበለዋለሁ።

ደግሞም፣ እውነት እልሀለሁ፣ አገልጋዬ ጆርጅ ሚለር አታላይ አይደለም፤ በልቡ ቅንነትም ሊታመን ይቻላል፤ እና ለእኔ፣ ለጌታ፣ ለምስክሬ ባለው ፍቅር ምክንያትም እወደዋለሁ።

፳፩ ስለዚህ እልሀለሁ፣ እንደ አገልጋዬ ኤድዋርድ ፓርትሪጅ፣ የቤቴን ቅድስና ይቀበል ዘንድ፣ በድሀ ህዝቤ ራዕይ ላይ በረከቶችን ይሰጥ ዘንድ የኤጲስ ቆጶስ አመራር ሀላፊነትንም በራሱ ላይ አትምለታለሁ፣ ይላል ጌታ። አገልጋዬ ጆርጅን ማንም ሰው አይጥላው፣ እኔን ያከብረኛልና።

፳፪ አገልጋዬ ጆርጅ፣ እና አገልጋዬ ላይመን፣ እና አገልጋዬ ጆን ስናይደር፣ እና ሌሎችም አገልጋዬ ጆሴፍ እንደሚያሳያቸው አይነት፣ ደግሞም ለእነርሱ በሚያሳያቸው ስፍራ ለስሜ ቤት ይገንቡ።

፳፫ እና ይህም ለማረፊያ ቤት፣ እንግዶች ከሩቅ ስፍራ መጥተው የሚያርፉበት ይሁን፤ ስለዚህ የደከመው ተጓዥ የጌታን ቃል፣ እና ለፅዮን የመደብኩትን የማዕዘን ራስ ድንጋይ ሲያሰላስል ጤና እና ደህንነትን ያገኝ ዘንድ መልካም፣ ለተቀባይነትም ያለው ብቁ ቤት ይሁን።

፳፬ ይህ ቤት በስሜ ቢገነባ እና የተመደበበት አስተዳዳሪ ምንም የሚያረክሰውን ነገር እንዲገባበት እስካልፈቀደ ድረስ የጤና መኖሪያ ይሆናል። ቅዱስ ይሆናል፣ አለዚያ ጌታ አምላካችሁ አይኖርበትም።

፳፭ ደግሞም፣ እውነት እልሀለሁ፣ ቅዱሳኔ ከእሩቅ ስፍራዎች ይምጡ።

፳፮ እና ፈጣን መልእክተኞች ላኩ፣ አዎን፣ ምርጥ መልእክተኞችንም፣ እና እንዲህም በሏቸው፥ ከሁሉም ወርቆቻችሁ እና ከብሮቻችሁ፣ እና ከውድ ድንጋዮቻችሁ፣ እና ከሁሉም ጥንታዊ ንብረታችሁ ጋር ኑ፤ እና እውቀት ካላቸውም ከጥንቶቹ ጋር የሚመጡትም ይምጡ፣ እና የባርሰነቱን ዛፍ፣ እና የጥዱን ዛፍ፣ እና የአስታውን ዛፍ ከምድር ውድ ዛፎች ሁሉ ጋር አምጡ፤

፳፯ እና ከብረት፣ ከመዳብ፣ እና ከነሀስ፣ እና ከዚንክ፣ እና ከምድር ውድ ነገሮች ሁሉ ጋር፤ እና ከሁሉም በላይ ልዑል እንዲኖርበት፣ በስሜም ቤት ስሩ።

፳፰ ከእናንተ የጠፋውን ወይም የወሰደውን፣ እንዲሁም የክህነት ሙላትን፣ ደግሞ የሚመልስበት እና የሚመጣበት በምድር ላይ ምንም ስፍራ የለምና።

፳፱ እነርሱ፣ ቅዱሳኔ፣ ለሙታን ይጠመቁ ዘንድ፣ በምድርም ላይ የማጥመቂያ ገንዳ የለምና—

ይህ ስነ ስርዓት በቤቴ ውስጥ ተገቢ ነውና፣ እና ቤት ለእኔ ለመገንባት በማትችሉበት በድህነታችሁ ቀናቶች በስተቀር፣ እኔ ልቀበልበት አልችልም።

፴፩ ነገር ግን ቅዱሳኔ ሁሉ በስሜ ቤት እንድትገነቡ አዛችኋለሁ፤ እና ለእኔ ቤት የምትገነቡበት ብቁ ጊዜም እሰጣችኋለሁ፤ እና በዚህም ጊዜ ጥምቀቶቻችሁ በእኔ ተቀባይ ይሆናሉ።

፴፪ ነገር ግን፣ እነሆ፣ ከዚህ ምደባ በኋላ ለሙታን የምታደርጉት ጥምቀት በእኔ ዘንድ ተቀባይነት የለውም፤ እና እነዚህንም ነገሮች በተመደበላቸው ጊዜ መጨረሻ ላይ ባታደጉት ከሙታኖቻችሁ ጋር እንደ ቤተክርስቲያን ትወገዳላችሁ፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ።

፴፫ እውነት እላችኋለሁ፣ ለሙታን የጥምቀት ስርዓት የሚገባበት፣ እና አለም ከመመስረቷ በፊት ጀምሮ ለዚህም አላማ የዋለውን ቤቴን ለመገንባት ብቁ ጊዜ ካገኛችሁ በኋላ፣ ለሙታኖቻችሁ የምትጠመቁት በእኔ ዘንድ ተቀባይነትን አያገኝም።

፴፬ ክብር እና ግርማ ትቀበሉ ዘንድ፣ ለቅዱስ ክህነት ስልጣን ቁልፎች የሚሾሙት በዚህም ውስጥ ነውና።

፴፭ ከዚህ ጊዜም በኋላ፣ በመካከላችሁ በየአካማቢው የተበተኑት የሙታን ጥምቀቶቻችሁ በእኔ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው አይደሉም፣ ይላል ጌታ።

፴፮ በፅዮን እና ካስማዎቼ፣ እና በኢየሩሳሌም፣ ለመሸሸጊያነት በመደብኳቸው በእነዚያ ስፍራዎች ውስጥም ለሙታኖቻችሁ ጥምቀት ስፍራ እንዲሆኑ ተመድበዋል።

፴፯ ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በስሜ በተሰራው ቤት ውስጥ ካልፈጸማችሁት በስተቀር፣ መታጠባችሁንስ ለእኔ ዘንድ እንዴት ተቀባይነት ይሆራቸዋል?

፴፰ በዱር ተሸክመው ይወስዱት ዘንድ ነው ሙሴን ታቦት እንዲሰራ ያዘዝኩት፣ እና ከአለም ፍጥረት በፊት ተደብቀው የነበሩት ስርዓቶችን ይገልጥም ዘንድ ነው በቃል ኪዳን ምድርም ቤት እንዲሰራ ያዘዝኩት።

፴፱ ስለዚህ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ መቀባታችሁ፣ እና መታጠባችሁ፣ እና ለሙታን መጠመቃችሁ፣ እና የክብር ስብሰባዎቻችሁ፣ እና ለሌዊ ልጆች መስዋዕት እና ንግግርን በምትቀበሉበት ቅዱስ ስፍራዎቻችሁ ውስጥ ለሚኖራችሁ የእግዚአብሔር ቃላት መታሰቢያ፣ እና ለደንቦቻችሁ እና ለፍርዶቻችሁ፣ ለራዕያት መጀመሪያ እና ለፅዮን መመስረት፣ እና ለእርሷም ማዘጋጃ ቤት ግርማ፣ ክብር፣ እና መንፈሳዊ ስጦታ፣ ለቅዱስ ስሜ ህዝቤ ሁልጊዜ እንዲገነቡ በሚታዘዙበት በቅዱስ ቤቴ ስነስርዓት የተሾሙ ናቸው።

እና እውነት እላችኋለሁ፣ ስነ ስርዓቶቼን ለህዝቤ በዚህ ውስጥ እገልጥ ዘንድ፣ ይህም ቤት በስሜ ይሰራ፤

፵፩ ከአለም መመስረት በፊት ተሰውረው የነበሩትን ነገሮች፣ ስለዘመን ፍጻሜ የሚመለከቱትን ነገሮች፣ ለቤተክርስቲያኔ እገልጥ ዘንድ አላማ አለኝና።

፵፪ እና ለአገልጋዬ ጆሴፍ ይህን ቤት፣ እና በዚህም ክህነትን፣ እና ይህም የሚገነባበትን ስፍራ በሚመለከት ሁሉንም ነገሮች አሳየዋለሁ

፵፫ እና ለመገንባት ስታሰላስሉበት በነበረው ስፍራም ትገነቡታላችሁ፣ እናንተ እንድትገነቡበት የመረጥኩት ስፍራ ነውና።

፵፬ በሙሉ ሀይላችሁ ታገለግሉ ዘንድ፣ ይህም ቅዱስ ይሆን ዘንድ ስፍራውን እቀድሰዋለሁ።

፵፭ እና ህዝቤ ድምጼን እና ህዝቤን እንዲመሩ የመደብኳቸውን የአገልጋዮቼን ድምፅ ቢያደምጡ፣ እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ከስፍራቸውም አይወጡም።

፵፮ ነገር ግን ድምጼን ወይም እነዚህን የመደብኳቸውን የአገልጋዮቼን ድምፅ ባያደምጡ፣ ቅዱስ መሬቴን፣ እና ቅዱስ ስርዓቶቼን፣ እና ህገ መንግስቴን፣ እና የሰጠኋቸውን ቅዱስ ቃላቴን ስለሚያረክሱ አይባረኩም።

፵፯ እና እንዲህም ይሆናል በስሜ ቤቴን ብትሰሩ፣ እና ያልኳቸውንም ነገሮች ባታደርጉ፣ ለእናንተ የገባሁትን መሀላ አልፈፅምም፣ ከእጄም የምትጠብቁትን ቃል ኪዳንም አላሟላም፣ ይላል ጌታ።

፵፰ እናንት በስራችሁ በረከቶች ሳይሆን፣ በሞኝነታችሁና በፊቴ በምታደርጉት በአጸያፊ ስራዎቻችሁ እርግማንን፣ ቁጣን፣ ንዴትን፣ እና ፍርድን በራሳችሁ ላይ ታመጣላችሁና፣ ይላል ጌታ።

፵፱ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ለስሜ ስራን እንዲሰሩ ለየትኞቹም የሰዎች ልጆች ትእዛዝን ስሰጥ፣ እነዚያም የሰዎች ልጆች ሁሉ በሙሉ ሀይላቸውና ባላቸው ሁሉ ያንን ስራ ቢፈጽሙ፣ እና ቅንነታቸውን ባያጎድሉ፣ እና ጠላቶቻቸው ቢመጡባቸው እና ያንንም ስራ እንዳያከናውኑ እንቅፋት ቢሆኑባቸው፣ እነሆ፣ ከእነዚያ የሰዎች ልጆች እጆች ላይ ያንንም ስራ በተጨማሪም ላለመጠየቅ፣ ነገር ግን መስዋዕታቸውን እቀበል ዘንድ ፍቃዴ ነው።

እና ንስሀ እስካልገቡ እና እስከጠሉኝም ድረስ፣ ክፋትን እና የቅዱስ ህግጋቴን እና ትእዛዛቴን ስራ የሚያደናቅፉትን፣ እስከ ሶስት እና አራት ትውልዶችእጎበኛቸዋለሁ፣ ይላል ጌታ አምላክ።

፶፩ ስለዚህ፣ በጃክሰን የግዛት ክፍል ሚዙሪ ውስጥ ከተማ እና ቤት በስሜ እንዲገነቡ ካዘዝኳቸው፣ እና በጠላቶቻቸውም ከተደናቀፉት መካከል መስዋዕታቸውን የተቀበልኩት በዚህ ምክንያት ነው፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ።

፶፪ እና ንስሀ እስካልገቡ እና እስከጠሉኝ ድረስ፣ ፍርድን፣ ቁጣን፣ ንዴትን፣ ልቅሶን፣ እና ስቃይን፣ እና ጥርስ ማፏጨትን በራሳቸው ላይ፣ እስከ ሶስት እና አራት ትውልድ እመልስላቸዋለሁ፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ።

፶፫ እና እነዚያ ስራ እንዲሰሩ ታዝዘው እና በጠላቶቻቸው እጆች እና በግፍ ተደናቅፈው የነበሩትን ሁሉ በሚመለከት ትፅናኑበት ዘንድ ይህን ለእናንተ ምሳሌ አደርጋለሁ፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ።

፶፬ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝና፣ እና በልባቸው ንጹህ የሆኑትን፣ እና በሚዙሪ ምድር ውስጥ የተገደሉትን ወንድሞቻችሁንም አድናለሁ፣ ይላል ጌታ።

፶፭ ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በማዝዛችሁ ማንኛቸውም ነገሮች እናንተ ታማኝ መሆናችሁን ለእኔ ታረጋግጡ ዘንድ፣ እና እኔም እባርካችሁ እና በክብር፣ ህያውነት፣ እና በዘለአለማዊ ህይወትንም አጎናጽፋችሁ ዘንድ በስሜ ቤትን እንድትገነቡ፣ በዚህም ስፍራ ይህን ታደርጉ ዘንድ፣ ደግሜ አዛችኋለሁ።

፶፮ አሁንም ለእንግዶች ማረፊያ እንድትገነቡት ያዘዝኳችሁ ማረፊያ ቤትን በሚመለከት እላችኋለሁ፣ በስሜም ይሰራ፣ ስሜም በእርሱ ላይ ይሁን፣ እና አገልጋዬ ጆሴፍ እና ቤቱም በዚህ ውስጥ ከትውልድ እስከ ትውልድ ስፍራ ይኑራቸው።

፶፯ ለዚህም ራሱን ቀብቼዋለሁ፣ ከእርሱ በኋላ ያለው ትውልድ የእርሱን በረከት በላያቸው ይቀበላሉ።

፶፰ እና ለአብርሐም ስለምድር ነገዶች እንዳልኩትም፣ ለአገልጋዬ ጆሴፍም እንዲሁም እለዋለሁ፥ በአንተ እና በዘርህ የምድር ነገዶች ይባረካሉ።

፶፱ ስለዚህ፣ አገልጋዬ ጆሴፍ እና ከእርሱም በኋላ ዘሮቹ በዚያ ቤት ከትውልድ እስከ ትውልድ፣ ለዘለአለም ስፍራ ይኑራቸው፣ ይላል ጌታ።

የቤቱም ስም የናቩ ቤት በመባል ይታወቅ፤ እና ለሰውም የሚያስደስት መኖሪያ እና የፅዮንን ክብር እና የዚህ የማዕዘን ድንጋይ ክብርን ያሰላስል ዘንድ ለደከመውም ተጓዢ ማረፊያ ስፍራ ይሁን፤

፷፩ እንደዝነኛ አትክልት እና እንደ ጠባቂዎች በግድግዳዋ ላይ ካስቀመጥኳቸው ምክር ደግሞም ይቀበል ዘንድ።

፷፪ እነሆ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ ጆርገ ሚለር እና አገልጋዬ ላይመን ዌይት፣ እና አገልጋዬ ጆን ስናይደር፣ እና አገልጋዬ ፒተር ሀውስ ራሳቸውን ያደራጁ እና ቤቱን ለመገንባትም ባላቸው አላማም በመካከላቸው አንዱን እንደ ቡድናቸው ፕሬዘደንት ይመድቡ።

፷፫ እና እነርሱም ያን ቤት ለመስራትም ሸቀጥ የሚቀበሉበት ህገ መንግስትን ይመስርቱ።

፷፬ እና በዚያ ቤት ውስጥ የድርሻቸውን ሸቀጥ ከሀምሳ ዶላር በላይ አይቀበሉ፣ እና ለዚያ ቤት ሸቀጥም ከእያንዳንዱ ሰው አስራ አምስት ሺህ ዶላሮች እንዲቀበሉ ይፈቀድላቸው።

፷፭ ነገር ግን ከማንም አንድ ሰው ከአስራ አምስት ሺህ ዶላሮች በላይ እንዲቀበሉ አይፈቀድላቸውም።

፷፮ እና ከማንም ሰው ለዚያ ቤት ሸቀጥ የድርሻውን ከአስራ አምስት ሺህ ዶላሮች በታች እንዲቀበሉ አይፈቀድላቸውም።

፷፯ እና ሸቀጡን በሚቀበልበት ጊዜ ለሸቀጡ ካልከፈለ በስተቀር፣ ማንንም ሰው እንደዚህ ቤት ሸቀጥ ድርሻ ያዥ ለመቀበል አይፈቀድላቸውም።

፷፰ በእጆቻቸው በሚከፍለው የሸቀጡ ክፍያው በዚያ ቤት ውስጥ ሸቀጥን ይቀበል፤ ነገር ግን በእጆቻቸው ምንም ካልከፈለ በእዚያ ቤት ውስጥ ምንም ሸቀጥ አይቀበል።

፷፱ እና ማንም ሸቀጥን በእጆቻቸው ቢከፈል በቤቱ ውስጥ እና ለእርሱና ከእርሱ በኋላ ለመጡት ትውልዶችም፣ ከትውልድ እስከትውልድ፣ እርሱ እና የእርሱ ወራሾች ሸቀጡን እስከያዙ ድረስ እና በራሳቸው ነጻ ፈቃድ ወይም ስራ ሸቀጡን ከእጆቻቸው አውጥቶ ካላስተላለፈ ወይም ካልሸጠው በስተቀር፣ ፈቃዴን ብታደርጉ ለሸቀጥ ይሆንለታል፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ።

ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ ጆርጀ ሚለር እና አገልጋዬ ላይመን ዋይት እና አገልጋዬ ጆን ስናይደር፣ እና አገልጋዬ ፒተር ሀውስ በገንዘቦች ወይም የእውነት ዋጋ ያለው ገንዘብ በሚቀበሉበት ንብረቶች ምንም ሸቀጥ በእጆቻቸው ቢቀበሉ፣ በቤቱ ውስጥ እንጂ ያንን ሸቀጥ የትኛውንም ክፍል ለምንም አላማ አይመድቡ።

፸፩ እና ከቤቱ ላይ በስተቀር የሸቀጡን ማንኛውንም ክፍል በሌላ ስፍራ ሸቀጡን ከያዙት ሳይፈቅዱ ከመደቡት እና በየትኛውም ስፍራ የመደቡትን ሸቀጥ በአራት እጥፍ መልሰው ባይከፍሉ፣ ይረገማሉ፣ እና ከስፍራቸውም ይወጣሉ፣ ይላል ጌታ አምላክ፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ እና በእነዚህ በማንኛቸውም ነገሮች አይዘበትብኝምና

፸፪ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ ጆሴፍ፣ መልካም እንደሚመስለው፣ ቤቱ ከመገንባቱ በፊት ለሸቀጡ በእጆቻቸው ይክፈል፤ ነገር ግን አገልጋዬ ጆሴፍ ለዚያ ቤት ሸቀጥ ከአስራ አምስት ሺህ በላይ ወይም ከአምስት ሺህ በታች መክፈል አይችልም፤ ወይም ሌላም ሰው ይህን ማድረግ አይችልም፣ ይላል ጌታ።

፸፫ እና ፈቃዴን ለማወቅ ፈቃድ ያላቸው ሌሎችም አሉ፣ ከእጆቼ ጠይቀውታልና።

፸፬ ስለዚህ፣ ስለአገልጋዬ ቪንሰን ናይት እላችኋለሁ፣ ፈቃዴን ቢያደርግ በዚያ ቤት ላይ ለራሱ እና ከእርሱ በኋላ ለሚመጡ ትውልዶቹ፣ ከትውልድ እስከ ትውልድ ሸቀጥን ያስገባ።

፸፭ እና በህዝብ መካከል፣ የድሆች እና እርዳታን ለሚሹ ለመለመን፣ ድምጹን ረጅም እና ጉልህ በማድረግ ያንሳ፤ አይውደቅ፣ ወይም ልቡም ተስፋ አይቁረጥ፤ እና መስዋዕቶቹን እቀበላቸዋለሁ፣ እንደ ቃየን መስዋእቶች አይደሉምና፣ እርሱም የእኔ ይሆናልና፣ ይላል ጌታ።

፸፮ ቤተሰቡም ይደሰቱ እና ከስቃይም ልባቸውን ይመልሱ፤ እኔ መርጬው እና ቀብቼዋለሁና፣ እና በቤቱም መካከልም ይከብራል፣ ለኃጢአቶቹ ሁሉ ምህረትን እሰጠዋለሁና፣ ይላል ጌታ። አሜን።

፸፯ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ ሀይረም ስሚዝ ለእራሱ እና ከእርሱ በኋላ ለሚመጡት ትውልዶች፣ ከትውልድ እስከ ትውልድ፣ መልካም እንደሚመስለው በቤቱ ላይ ሸቀጥን ያስቀምጥ።

፸፰ አገልጋዬ አይዛክ ጋላንድ በቤቱ ላይ ሸቀጥ ያስገባ፤ እኔ ጌታ ለሰራው ስራም እወደዋለሁና እና ለኃጢአቶቹ በሙሉ ምህረትን እሰጠዋለሁና፤ ስለዚህ፣ በዚህም ቤት ውስጥ ሸቀጥ እንዳለውም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይታወስ።

፸፱ አገልጋዬ አይዛክ ጋለንድም በመካከላችሁ ይመደብ፣ እና ከአገልጋዬ ሀይረም ስሚዝ ጋር አገልጋዬ ጆሴፍ የሚጠቁምላቸውን ስራ ለማከናወን በአገልጋዬ ዊልያም ማርክስም ይሾም፣ እና በእርሱም ይባረክ፣ እና እነርሱም በታላቅ በረከትም ይባረካሉ።

አገልጋዬ ውልያም ማርክስም መልካም እንደሚመስለው ለራሱ እና ለትውልዱ፣ ከትውልድ እስከ ትውልድ፣ በቤቱ ላይ ለሸቀጥ ይክፈል።

፹፩ አገልጋዬ ሄንሪ ጂ ሸርውድ መልካም እንደሚመስለው ለራሱ እና ከእርሱ በኋላ ለዘሩ፣ ከትውልድ እስከ ትውልድ፣ በቤቱ ላይ ለሸቀጥ ይክፈል።

፹፪ አገልጋዬ ውልያም ሎው መልካም እንደሚመስለው ለራሱ እና ከእርሱ በኋላ ለዘሩ፣ ከትውልድ እስከ ትውልድ፣ በቤቱ ላይ ለሸቀጥ ይክፈል።

፹፫ ፈቃዴን የሚያደርግ ቢሆን፣ ቤተሰቡን ወደ ምስራቅ ምድር፣ እንዲሁም ወደ ከርትላንድ አይውሰድ፤ ይህ ቢሆን፣ እኔ ጌታ ከርትላድን እገነባለሁ፣ እና እኔ ጌታ በዚያ ለሚኖሩትም የሚመቱበትን ጅራፍ አዘጋጅቼላቸዋለሁ።

፹፬ እና ከአገልጋዬ አልሞን ባቢት ያልተደሰትኩበት ብዙ ነገሮች አሉ፤ እነሆ፣ ከመደብኩለት ምክር፣ እንዲሁም ከቤተክርስቲያኔ አመራር በላይ የእራሱን ምክር ለመመስረት ተነሳስቷል፤ እና ህዝቤም ያመልኩት ዘንድ የወርቅ ጥጃን ያቆማል።

፹፭ ትእዛዛቴን በመሻት የመጣ ማንም ሰው ከዚህ ስፍራ አይሂድ

፹፮ እዚህም የሚኖሩ ቢሆን፣ በእኔ ይኑሩ፤ እና ቢሞቱም፣ በእኔ ይሙቱ፤ ከስራዎቻቸው ሁሉ በዚህ ያርፋሉና፣ እና ስራዎቻቸውንም ይቀጥላሉና።

፹፯ ስለዚህ፣ አገልጋዬ ውልያም እምነቱን በእኔ ላይ ያድርግ፣ እና በምድሩ ላይ ባለው ህመም ምክንያትም ስለቤተሰቡ መፍራቱን ያቁም። ብትወዱኝ ትእዛዛቴን ጠብቁ፤ እና የምድሩም ህመም ለክብራችሁ ይቀየራል

፹፰ አገልጋዬ ውልያም ይሂድ እና በጎላ ድምፅም እና በታላቅ ደስታ፣ በመንፈሴም እንደተነሳሳ፣ ዘለአለማዊውን ወንጌሌን ለዋርሶ ነዋሪዎች፣ እና ደግሞም ለካርቴጅ ነዋሪዎች፣ እና ደግሞም ለበርሊንግተን ነዋሪዎች፣ እና ደግሞም ለማድሰን ነዋሪዎች፣ ያውጅ፣ እና በትእግስትና በቅንነት በአጠቃላይ ጉባኤ ላይ መመሪያን ይጠብቅ፣ ይላል ጌታ።

፹፱ ፈቃዴን የሚያደርግ ቢሆን፣ የአገልጋዬ ጆሴፍን ምክር ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ያድምጥ፣ በችሎታውም ድሆችን ይርዳ፣ እና ለምድርም ነዋሪዎች ቅዱስ ቃሌን አዲስ ትርጉም ያውጅ።

እና ይህንንም ቢያደርግ በሚበዙ በረከቶች እባርከዋለሁ፣ እርሱ አይተውም፣ ወይም ዘሩም ዳቦ እየለመኑ አይገኙም።

፺፩ ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ ሀይረም በአባቱ እና በበረከት፣ እና ደግሞም በመብት የተመደበለትን ክህነት እና የፓትሪያርክ ሀላፊነት ይወስድ ዘንድ፣ አገልጋዬ ውልያም በአገልጋዬ ሀይረም ምትክ ለአገልጋዬ ጆሴፍ አማካሪ እንዲሆን ይመደብ፣ ይሾም፣ እናም ይቀባ፤

፺፪ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በህዝቤ ሁሉ ላይ የፓትሪያርክ በረከት ቁልፎችን ይያዝ፣

፺፫ ማንም እርሱም የሚባርክ ይባረካል፣ እና ማንም የሚረግመውም ይረገማል፤ በምድር የሚያስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፣ በምድርም የሚፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።

፺፬ እና ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ለአገልጋዬ ጆሴፍ ለቤተክርስቲያኔ ነቢይ፣ ባለራዕይ፣ እናም ገላጭ እንዲሆን መድቤዋለሁ፤

፺፭ ከአገልጋዬ ጆሴፍ ጋር በአንድነት ይሰራም ዘንድ፤ እና የሚጠይቀውን እና የሚቀበልበትን ቁልፎች የሚያሳየውን የአገልጋዬን የጆሴፍን ምክር ይቀበል፣ እና በዚህም አይነት በረከት፣ እና አገልጋዬ በነበረው ኦሊቨር ካውድሪ ላይ ተጭኖ የነበረውን ግርማ፣ እና ክብር፣ እና ክህነት፣ እና የክህነት ስጦታም ይጎናጸፋል፤

፺፮ አገልጋዬ ሀይረምም ስለማሳየው ነገሮች ምስክነትን ይሰጥ ዘንድ፣ ስሙም በክብር ማስታወሻ ከትውልድ እስከ ትውልድ፣ ለዘለአለም ይሆን ዘንድ መድቤዋለሁ።

፺፯ አገልጋዬ ውልያም ሎውም በረከቶችን በመጠየቅ የሚቀበልበትን ቁልፎች ይቀበል፤ በፊቴም ትሁት፣ እና ያለነቀፋም ይሁን፣ እና የሁሉንም ነገር እውነትነት የሚገልፅ፣ እና በዚያችም ሰዓት እንዴት እንዲናገር የሚሰጠው መንፈሴን፣ እንዲሁም አፅናኝን ይቀበል።

፺፰ እና እነዚህም ምልክቶች ይከተሉታል—የታመሙትን ይፈውሳል፣ አጋንንትን ያወጣል፣ ገዳይ መርዝንም ከሚሰጡትም ከእነርሱም ይድናል፤

፺፱ እና መርዛማም እባብ ተረከዙን በማይነክስበት መንገድ ይመራል፣ እና በሀሳቡም አይነ ህሊናው የንስር ክንፍ እንደሚበር ወደላይ ይብረር።

እና የሞተውን እንዲያነሳ ብፈቅድ፣ ድምጹን አይሰብስብ።

፻፩ ስለዚህ፣ አገልጋዬ ውልያምም በደስታ እና በሀሴት በዙፋኑ ላይ ለዘለአለም ለተቀመጠው ሆሳዕና በማለት፣ በታላቅ ድምጽ ይጩህ እናም አይከልከል፣ ይላል ጌታ አምላክህ።

፻፪ እነሆ፣ እላችኋለሁ፣ ለአገልጋዬ ውልያም እና ለአገልጋዬ ሀይረም፣ እና ለእርሱም ብቻ ተልዕኮን አዘጋጅቼላቸዋለሁ፤ እና አገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝም በቤት ይቆይ፣ ይፈለጋልና። የሚቀረውን ከዚህ በኋላ አሳያችኋለሁ። እንዲህም ይሁን። አሜን።

፻፫ ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ ስድኒ ቢያገለግለኝ እና ለአገልጋዬ ጆሴፍ ስሚዝ አማካሪ ቢሆን፣ ይነሳ እና ወደፊትም ይምጣ እና በተጠራበት ሀላፊነትም ይቁም፣ እና በፊቴም ትሁት ይሁን።

፻፬ እና ተቀባይነት ያለውን መስዋዕትና እውቀትን ቢያቀርብልኝ፣ እና ከህዝቤም ጋር ቢቆይ፣ እነሆ እኔ ጌታ አምላክህ የሚፈወሰውን እፈውሳለሁ፤ እና በተራሮችም ላይ ድምጹን ከፍ ያደርጋል፣ እና በፊቴም የሚናገርልኝ ይሆናል።

፻፭ ይምጣ እና አገልጋዬ ጆሴፍ በሚኖርበት አካባቢም ቤተሰቡንም በዚያ ያኑር።

፻፮ እና በጉዞዎቹም ሁሉ እንደመለከት ድምጽ ድምጹን ከፍ ያድርግ፣ እና የምድር ነዋሪዎችንም ስለሚመጣው ከሚመጣው ቍጣ እንዲሸሹ ያስጠንቅቃቸው።

፻፯ አገልጋዬ ጆሴፍን ይርዳ፣ እና አገልጋዬ ውልያም ሎውም ከዚህ በፊት እንዳልኳችሁ ለምድር ነገስታት የክብር አዋጅን በማድረግ አገልጋዬ ጆሴፍን ይርዳ።

፻፰ አገልጋዬ ስድኒ ፈቃዴን ቢያደርግ፣ ቤተሰቡን ወደ ምስራቅ ምድር አይውሰዳቸው፣ ነገር ግን እንዳልኩት መኖሪያቸውን ይቀይር።

፻፱ እነሆ፣ ለእናንተ ከመደብኩላችሁ ከተማ፣ እንዲሁም ከናቩ ከተማ፣ ውጪ ደህንነትን እና መሸሸጊያን ለማግኘት መሻቱ ፍቃዴ አይደለም።

፻፲ እውነት እላችኋለሁ፣ አሁንም ድምጼን ብታደምጡ፣ መልካም ይሆንላችኋል። እንዲህም ይሁን። አሜን።

፻፲፩ ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ ኤመስ ዴቪስ የማረፊያ ቤት፣ እንዲሁም የናቩን ቤት፣ እንዲገነቡ ለመደብኳቸው ሰዎች በእጆቻቸው ላይ ሸቀጥ ይክፈል።

፻፲፪ ፍላጎቱም ቢሆን ይህንን ያድርግ፤ እና የአገልጋዬ ጆሴፍን ምክር ያድምጥ፣ እና የሰዎችንም እምነት ያገኝ ዘንድ በእጆቹ ይስራ።

፻፲፫ እና እንዲንከባከባቸው በተሰጡት ነገሮች ሁሉ፣ አዎን እንዲሁም በጥቃቅን ነገሮች፣ ታማኝ እንደሆነ ራሱን ሲያረጋግጥ፣ በብዙ ነገሮች አስተዳዳሪ ይሆናል።

፻፲፬ ስለዚህ፣ የላቀ ክብር ይኖረውም ዘንድ እራሱን ያዋርድ። እንዲህም ይሁን። አሜን።

፻፲፭ ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ ሮበርት ዲ ፎስተር ድምጼን ቢታዘዝ፣ ከእርሱ ጋርም በገባው ስምምነት መሰረት ለአገልጋዬ ጆሴፍ ቤት ይስራ፣ ከጊዜ ወደጊዜም በሮች ይከፈቱለታልና።

፻፲፮ እና ለሞኝነት ስራውም ንስሀ ይግባ፣ እና በልግስና እራሱን ያልብስ፤ እና ክፉ ማድረግንም ያቁም፣ እና የክፉ ንግግሮቹንም ያቁም።

፻፲፯ እና ከትውልድ ወደ ትውልድ፣ ለራሱ እና ከእርሱ በኋላ ለሚመጡት ትውልዶች፣ ለናቩ ቤት ቡድኖችም ሸቀጥን ይክፈል፤

፻፲፰ እና አገልጋዮቼን የጆሴፍን፣ እና ሀይረምን፣ እና የውልያም ሎው፣ እና የፅዮንንም መሰረት ይገነቡ ዘንድ የጠራኋቸውን ባለስልጣናት ምክሮችንም ያድምጥ፤ እና ለዘለአለም መልካም ይሆንለታል። እንዲህም ይሁን። አሜን።

፻፲፱ ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በመፅሐፈ ሞርሞን፣ እና በሰጠኋችሁ ራዕዮች የሚያምን ካልሆነ በስተቀር ማንም ሰው ለናቩ ቤት ቡድኖች ሸቀጥን አይክፈል፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ፤

፻፳ ከእነዚህም የበዛ ወይም ያነሰ ከክፉው የሚመጣ ነውና፣ እና በበረከቶች ሳይሆን እርግማኖች ይከተሏቸዋልና፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ። እንዲህም ይሁን። አሜን።

፻፳፩ ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ የናቩ ቤት ቡድኖች የናቩ ቤትን ለመገንባት ለሚያደርጉት አገልግሎታቸው ሁሉ በቂ ደመወዝ ይከፈላቸው፤ እና ደሞዛቸውም፣ ስለዋጋው በሚመለከት፣ በመካከላቸው የሚስማሙበት ይሁን።

፻፳፪ እና እያንዳንዱ ሸቀጥን የሚከፍለውም የድርሻ ደሞዙን፣ አስፈላጊም ከሆነ የሚደገፉበትን ይክፈል፣ ይላል ጌታ፤ አለበለዚያም፣ አገልግሎታቸው በዚያ ቤት እንደ ሸቀጥ ይቆጠርላቸዋል። እንዲህም ይሁን። አሜን።

፻፳፫ እውነት እላችኋለሁ፣ ለእናንተ ለክህነት ስልጣኔ አባል ለሆናችሁት ባለስልጣናትቁልፎቹንም ትይዙ ዘንድ፣ እንዲሁም በአንድያ ልጅ ስርዓት የሆነውን የመልከ ጼዴቅን ስርዓት ክህነት አሁን እሰጣችኋለሁ።

፻፳፬ መጀመሪያ፣ ሀይረም ስሚዝን ለእናንተ ፓትሪያርክ እንዲሆን፣ የሚመጡባችሁን፣ የፈተና ሰአታትን በመቋቋም እንዳትወድቁ ለቤዛም ቀን የምትታተሙባቸውን የቤተክርስቲያኔን ማስተሳሰሪያ በረከቶችን፣ እንዲሁም ቅዱስ የተስፋ መንፈስን እንዲይዝ እሰጠዋለሁ።

፻፳፭ አገልጋዬ ጆሴፍ በቤተክርስቲያኔ ሁሉ አስተዳዳሪ ሽማግሌ፣ ተርጓሚ፣ ገላጭ፣ ባለራዕይ፣ እና ነቢይ እንዲሆን እሰጣችኋለሁ።

፻፳፮ ለእርሱም አገልጋዬን ስድኒ ሪግደንን እና አገልጋዬን ውልያም ሎውን እንደ አማካሪዎቹ እሰጠዋለሁ፣ እነዚህም ለቤተክርስቲያኗ የእግዚአብሔርን ቃላት ለመቀበል ቡድንን እና ቀዳሚ አመራርን ያቋቁማሉ።

፻፳፯ አገልጋዬ ብሪገም ያንግን የአስራ ሑለቱ ተጓዥ ሸንጎ ፕሬዘደንት እንዲሆን እሰጣችኋለሁ፤

፻፳፰ አስራ ሁለቱም በምድር አራቱ ማዕዘናት ላይ የመንግስቴን ስልጣን ለመክፈት፣ እና ከዚያም በኋላ ቃሌን ለሁሉም ፍጥረቶች ይልኩ ዘንድ ቁልፎችን ይዘዋል።

፻፳፱ እነዚህም ሂበር ሲ ኪምባል፣ ፓርሊ ፒ ፕራት፣ ኦርሰን ፕራት፣ ኦርሰን ሀይድ፣ ውልያም ስሚዝ፣ ጆን ቴይለር፣ ጆን ኢ ፔጅ፣ ዊልፈርድ ዉድረፍ፣ ዊለርድ ርቻርድስ፣ ጆርጅ ኤ ስሚዝ ናቸው፤

፻፴ ዴቪድ ፓትንን ወደ እኔም ዘንድ ወስጄዋለሁ፤ እነሆ፣ የእርሱን ክህነት ማንም ሰው አይወስድበትም፤ ነገር ግን፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በዚያ ጥሪ ሌላ ሊመደብ ይቻላል።

፻፴፩ ደግሞም፣ እላችኋለሁ፣ ለፅዮን የማእዘን ራስ ድንጋይ እንዲሆን ከፍተኛ ሸንጎን ሰጠኋችሁ—

፻፴፪ በስምም፣ ሳሙኤል ቤንት፣ ሔንሪ ጂ ሸርውድ፣ ጆርጅ ደብሊው ሀሪስ፣ ቻርልስ ሲ ሪች፣ ቶማስ ግሮቨር፣ ኒወል ኒይት፣ ዴቪድ ዶርት፣ ዱንባር ዊልሰን—ሲሞር ብረንሰንን ወደ እኔ ወስጃለሁ፤ የእርሱን ክህነት ማንም ሰው አይወስድበትም፤ ነገር ግን በዚያ ክህነት ስልጣን ላይ ሌላ በእርሱ ምትክ ሊመደብ ይቻላል፣ እና እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋዬ አሮን ጆንሰን በእርሱ ምትክ ለዚህ ጥሪ ይሾም—ዴቪድ ፉልመር፣ አልፊየስ ከትለር፣ ውልያም ሀንቲንግተን።

፻፴፫ ደግሞም፣ ዶን ሲ ስሚዝን በሊቀ ካህናት ቡድን ላይ ፕሬዘደንት እንዲሆን እሰጣችኋለሁ፤

፻፴፬ ይህም ስርዓት የማይጓዙ ፕሬዘደንቶች ወይም በውጪ በተበተኑት በተለያዩ ካስማዎች አገልጋዮች እንዲሆኑ የተመደቡ ብቁ ለሚሆኑበት አላማ የተመሰረተ ነው፤

፻፴፭ እና ቢፈለጉም መጓዝ ይችላሉ፣ ነገር ግን በአንድ ስፍራ እንደሚያገለግሉ ፕሬዘደንቶች ይሾሙ፤ ይህም የጥሪአቸው ሀላፊነት ነው፣ ይላል ጌታ አመላካችሁ።

፻፴፮ በቤተክርስቲያኔ ሊቀ ካህናት ቡድኖችን ያስተዳድሩ ዘንድ አማሳ ላይማንን እና ኖዋ ፓከርድን እንደአማካሪዎቹ እሰጠዋለሁ፣ ይላል ጌታ።

፻፴፯ ደግሞም፣ እላችኋለሁ፣ የክህነት ስልጣናቸው የሽማግሌዎች ቡድኖችን እንዲያስተዳድሩ የሆነውን ጆን ኤ ሂክስን፣ ሳሙኤል ዊልያምስን፣ እና ጀሲ ቤከርን እሰጣችኋለሁ፣ ያም ቡድን የተመሰረተው ለማይጓዙ አገልጋዮች ነው፤ ይህም ቢሆን መጓዝ ይችላሉ፣ ነገር ግን የተሾሙት በቤተክርስቲያኗ የማይጓዙ አገልጋዮች እንዲሆኑ ነው፣ ይላል ጌታ።

፻፴፰ ደግሞም፣ ጆሴፍ ያንግን፣ ጆሳያ በተርፊእልድን፣ ዳንኤል ማይልስን፣ ሄንሪ ሀሪማንን፣ ዜራ ፑልሲፈርን፣ ሊቫይ ሀንኮክን፣ ጄምስ ፎስተርን የሰባዎቹን ቡድን እንዲያስተዳድሩ እሰጣችኋለሁ።

፻፴፱ ይህም ቡድን የተመሰረተው የሚጓዙ ሽማግሌዎች በአለም ሁሉ፣ የሚጓዙ ከፍተኛ ሸንጎ፣ ሐዋሪያቴ በፊቴ መንገዶችን ለማዘጋጀት በሚልኳቸው በማናቸውም ስፍራዎች ስለ ስሜ እንዲመሰክሩ ነው።

፻፵ በዚህ ቡድን እና በሽማግሌዎች ቡድን ልዩነት ቢኖር አንዱ ዘወትር ይጓዛል እና ሌላው በቤተክርስቲያኔ ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲያስተዳድር ነው፤ አንዱ ከጊዜ ወደ ጊዜ የማስተዳደር ሀላፊነት አለው፣ እና ሌላውም የማስተዳደር ምንም ሀላፊነት የለውም፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ።

፻፵፩ ደግሞም፣ እላችኋለሁ፣ ቪንሰን ናይትን፣ ሳሙኤል ኤች ስሚዝን፣ እና የሚቀበለው ቢሆን ሻድራክ ራውንዲን የኤጲስ ቆጶስ አመራርን እንዲያስተዳድር እሰጣችኋለሁ፤ የዚህ ኤጲስ ቆጶስ አመራር እውቀት በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች መፅሀፍ ውስጥ ተሰጥቷችኋል።

፻፵፪ ደግሞም፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ሳሙኤል ሮልፍ እና አማካሪዎቹ እንደ ቄሶቹ ፕሬዘደንት፣ እና የመምህራን ፕሬዘደንት እና አማካሪዎች፣ እና ደግሞም የዲያቆናት ፕሬዘደንትና አማካሪዎች፣ እና ደግሞም የካስማ ፕሬዘደንቶችና አማካሪዎች እንዲሆኑ እሰጣችኋለሁ።

፻፵፫ የበላይ ሀላፊዎችን እና እነዚህን ቁልፎች ለእርዳታ እና ለማስተዳደር፣ ለአገልግሎቱ ስራዎችና ለቅዱሳኔ ፍጹምነት ሰጥቻችኋለሁ።

፻፵፬ እና እነዚህን ሀላፊነቶች በሙሉ እና የጠቀስኳቸውን ስሞች በአጠቃላይ ጉባኤዬም ላይ ታሟሏቸው እና ታጸድቋቸው ዘንድ ትእዛዝን እሰጣችኋለሁ፣ አለበለዚያም በአጠቃላይ ጉባኤዬም ላይ አታፅድቋቸውም።

፻፵፭ እና በቤቴ ውስጥም ለስሜ ስትገነቡት ለእነዚህ ሀላፊነቶች ክፍሎች አዘጋጁላቸው፣ ይላል ጌታ አምላካችሁ። እንዲህም ይሁን። አሜን።