ቅዱሳት መጻህፍት
ሞዛያ ፭


ምዕራፍ ፭

ቅዱሳን በእምነታቸው የክርስቶስ ወንዶች እና ሴቶች ልጆች ይሆናሉ—ከዚያም በክርስቶስ ስም ይጠራሉ—ንጉስ ቢንያም በመልካም ስራቸው እንዲፀኑ እናም የማይነቃነቁ እንዲሆኑ መከራቸው። በ፻፳፬ ም.ዓ. ገደማ።

እናም አሁን፣ እንዲህ ሆነ ንጉስ ቢንያም ለህዝቡ እንደዚህ በተናገረ ጊዜ፣ ለእነርሱ የተናገረውን አምነው እንደሆነ ከህዝቡ ለማወቅ በመፈለጉ በመካከላቸው ሰው ላከ።

እናም ሁሉም በአንድ ድምፅ እንዲህ በማለት ጮኹ፥ አዎን፣ ለእኛ የተናገርካቸውን ቃላት በሙሉ እናምናለን፤ እናም ደግሞ ያለማቋረጥ መልካምን መስራት እንጂ ከእንግዲህ ኃጢያት ለመፈፀም ምንም ፍላጎት እንዳይኖረን ታላቅ ለውጥ ለእኛ ወይንም በልባችን ውስጥ በሰራው ሁሉን በሚገዛው በጌታ መንፈስ አማካኝነት እርግጠኝነታቸውን እና እውነተኛነታቸውን አውቀናል።

እናም እኛ፣ እራሳችን ደግሞ በማይወሰነው የእግዚአብሔር ቸርነትና፣ በመንፈሱ መገለጥ ስለሚመጣው ታላቅ አመለካከት አለን፤ እናም የሚያስፈልግ ቢሆን እንኳን፣ ስለ ሁሉም ነገሮች መተንበይ እንችላለን።

እናም እጅግም ታላቅ በሆነ ደስታ ወደምንደሰትበት ወደዚህ ታላቅ እውቀት ያመጣን፣ የእኛ ንጉስ በተናገራቸው ነገሮች አንፃር ያለን እምነት ነው።

እናም ከእግዚአብሔር ጋር ፈቃዱን ለማድረግ እናም በቀረው ጊዜአችን ሁሉ እኛን ባዘዘን በሁሉም ነገር ለትዕዛዛቱ ታዛዦች ለመሆን፣ መጨረሻ የሌለው ቅጣት በራሳችን ላይ እንዳናመጣ፣ በመልአኩ እንደተነገረው ከእግዚአብሔር የቁጣ ዋንጫ እንዳንጎነጭ ከአምላካችን ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት ፈቃደኞች ነን።

እናም አሁን፣ ንጉስ ቢንያም ከእነርሱ የፈለጋቸው ቃላት እነዚህ ናቸው፤ እናም ስለዚህ እንዲህ አላቸው፥ እናንተ እኔ የፈለኳቸውን ቃላት ተናግራችኋል፤ እናም የገባችሁት ቃል ኪዳን የጽድቅ ቃል ኪዳን ነው።

እናም አሁን፣ በገባችሁት ቃል ኪዳን የተነሳ የክርስቶስ ልጆች፣ ወንዶችና ሴት ልጆቹ፣ ተብላችሁ ትጠራላችሁ፤ እነሆም በዚህ ቀን እናንተን በመንፈስ ወልዷችኋልልባችሁ በስሙ በማመን ተለውጧል ብላችኋልና፤ ስለዚህ እናንተ ከእርሱ ተወልዳችኋል እናም የእርሱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ሆናችኋል።

እናም በዚህ ራስ ስር ነፃ ተደርጋችኋል እናም በራሱ ነፃ መሆን የምትችሉበት ሌላ ምንም የለም። ደህንነት ሊመጣበት የሚችል ሌላ ስም የለም፤ ስለዚህ የክርስቶስን ስም እንድትወስዱ እፈልጋለሁ፣ ሁላችሁም ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን የገባችሁ እስከህይወታችሁ መጨረሻ ታዛዥ እንድትሆኑ እመኛለሁ።

እናም እንዲህ ይሆናል፣ ማንም ይህንን ያደረገ በእግዚአብሔር ቀኝ ይገኛል፣ የሚታወቅበትን ስም ያውቃልና፤ በክርስቶስ ስም ይጠራልና።

እናም አሁን እንዲህ ይሆናል፣ የክርስቶስን ስም ያልለበሰ ማንኛውም በሌላ ስም መታወቅ አለበት፤ ስለዚህ፣ እራሱን በእግዚአብሔር ግራ በኩል ያገኛል።

፲፩ እናም ይህን ደግሞ እንድታስታውሱ እፈልጋለሁ፣ በመተላለፍ ካልሆነ በቀር ለእናንተ መስጠት አለብኝ ያልኩት የማይደመሰሰው ስም ይህ ነው፤ ስለዚህ፣ ስሙም ከልባችሁ እንዳይጠፋ ዘንድ እንዳትተላለፉ አስተውሉ።

፲፪ በእግዚአብሔር ግራ እንዳትገኙ፣ ነገር ግን የምትጠሩበትን ድምፅ፣ እናም ደግሞ በእርሱ የምትጠሩበትን ስም እንድታዳምጡና እንድታውቁ፣ በልባችሁ የተፃፈውን ስም ሁልጊዜ እንድትጠብቁ እፈልጋለሁ እላችኋለሁ።

፲፫ ያላገለገለውን አለቃ፣ እና ለእርሱ እንግዳ የሆነውን፣ ከልቡ ስሜትና ሀሳብ የራቀውን፣ አንድ ሰው እንዴት ያውቃል?

፲፬ እናም ሰው እንደገና የጎረቤቱ የሆነውን አህያ ወስዶ የእርሱ ያደርገዋልን? አያደርግም እላችኋለሁ፣ ከመንጋዎቹ ጋር እንኳን እንዲመገብ አይፈቅድም፣ ነገር ግን ያስወጣታል እናም ያሳድዳታል። እላችኋለሁ፣ የምትጠሩበትን ስም የማታውቁ ከሆነ በእናንተ መካከል እንኳን እንዲህ ይሆናል።

፲፭ ስለዚህ፣ ሁሉን የሚገዛ ጌታ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ትመጡ ዘንድ፣ ከሁሉም በላይ አምላክ የሆነው በሰማይና በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ በፈጠረ፣ ጥበብ፣ ሀይል፣ እና ፍርድ፣ እንዲሁም በምህረቱ ዘለዓለማዊ ደህንነትና ዘለዓለማዊ ህይወት እንዲኖራችሁ የእርሱ እንድትሆኑ ያትምላችሁ ዘንድ እናንተ ፅኑ እናም የማትነቃነቁ፣ ሁልጊዜም በመልካም ስራ የተሞላችሁ እንድትሆኑ እፈልጋለሁ። አሜን።