ቅዱሳት መጻህፍት
ሞዛያ ፳፮


ምዕራፍ ፳፮

ብዙዎች የቤተክርስቲያኑ አባላት እምነት በሌላቸው ወደ ኃጢያት ተመሩ—አልማ የዘለዓለማዊ ሕይወት ቃል ተገብቶለታል—ንስሃ የሚገቡት እና የሚጠመቁ ይቅርታን ያገኛሉ—በኃጢያት ያሉት እና ኃጢአታቸውን ለአልማና ለጌታ የተናዘዙ የቤተክርስቲያን አባላት ይቅር ይባላሉ፤ አለበለዚያ ከቤተክርስቲያን አባላት ጋር አይቆጠሩም። ከ፻፳–፻ ም.ዓ. ገደማ።

አሁን እንዲህ ሆነ የንጉስ ቢንያምን ቃል መረዳት የማይችሉ በማደግ ላይ ያሉ ትውልዶች ነበሩ፣ እነርሱም እርሱ ለዚህ ህዝብ በተናገረበት ጊዜ ትንሽ ልጆች የነበሩ በመሆናቸው፤ እናም የአባቶቻቸውን ባህል አያምኑም ነበር።

የሙታን ትንሣኤንም ሆነ የክርስቶስን መምጣት በሚመለከት የተነገረውን አያምኑም ነበር።

እናም አሁን ባለማመናቸው የእግዚአብሔርን ቃል ሊረዱት አልቻሉም ነበር፤ ልባቸውም ጠጥሮ ነበር።

እናም አይጠመቁም ነበር፣ የቤተክርስቲያኗም አባል አይሆኑም ነበር። እናም እምነታቸውን በተመለከተ የተለዩ ነበሩ፣ ከእዚያም በኋላ እንደዚያው ሆነው ቀሩ፣ በስጋዊነታቸውና በኃጢአተኝነታቸውም ቢሆን፣ ወደ ጌታ አምላካቸው አይፀልዩም ነበርና።

እናም አሁን በሞዛያ የንግስና ዘመን እንደ የእግዚአብሔር ሰዎች ግማሽ ያህል አልበዙም ነበር፣ ነገር ግን በወንድሞች መካከል ጥል ምክንያት በጣም በርክተው ነበር።

እንዲህ ሆነ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ የነበሩትን ብዙዎችን በሸንጋይ ቃላቸው አታለሉአቸው፣ እናም ብዙ ኃጢአቶችን እንዲፈፅሙ አደረጉአቸው፣ ስለዚህ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ሆነው ኃጢያትን የፈፀሙ፣ በቤተክርስቲያኗ መገሰፃቸው አስፈላጊ ነበር።

እናም እንዲህ ሆነ ከካህናቱ ፊት አመጡአቸው፣ እናም በመምህራንም ለካህናቱ ተሰጡ፤ እናም ካህናቱ ሊቀ ካህን ከሆነው ከአልማ ፊት አመጧቸው።

አሁን ንጉስ ሞዛያ አልማን በቤተክርስቲያኗ ላይ ስልጣን ሰጥቶታል።

እናም እንዲህ ሆነ አልማ ስለእነርሱ አያውቅም ነበር፤ ነገር ግን በእነርሱ ላይ ብዙ ምስክሮች ነበሩ፣ አዎን፣ ህዝቡ ቆሙና ስለኃጢአታቸው በብዛት መሰከሩ።

አሁን በቤተክርስቲያኑ ፊት እንደዚህ ያለ ነገር ሆኖ አያውቅም፤ ስለዚህ አልማ በመንፈሱ ይጨነቅ ነበር፤ እናም ከንጉሱ ፊት እንዲመጡ አደረገ።

፲፩ እናም ለንጉሱ አለው፥ እነሆ ብዙዎቹን በወንድሞቻቸው የተከሰሱትን በአንተ ፊት አምጥተናል፤ አዎን፣ እናም በተለያዩ ክፋቶች የተያዙ ናቸው። እናም ስለኃጢአታቸው ንስሃ አይገቡም፤ ስለዚህ እንደወንጀላቸው ትፈርድባቸው ዘንድ በአንተ ፊት አምጥተናቸዋል።

፲፪ ነገር ግን ንጉስ ሞዛያ አልማን እንዲህ አለው፥ እነሆ፣ እኔ አልፈርድባቸውም፣ ስለዚህ አንተ እንድትፈርድባቸው በእጅህ አሳልፌ አሰጥሃለሁ።

፲፫ እናም አሁን የአልማ መንፈስ በድጋሚ ታወከ፣ እናም ምክንያቱም በእግዚአብሔር ዐይን የተሳሳተ ነገርን እፈፅማለሁ በማለት ስለፈራ ወደጌታ ሄዶ ይህንን በተመለከተ ምን ማድረግ እንዳለበት ጠየቀ።

፲፬ እናም እንዲህ ሆነ ነፍሱን ሁሉ ለእግዚአብሔር ካፈሰሰ በኋላ፣ የጌታ ድምፅ ወደ እርሱ እንዲህ ሲል መጣ፥

፲፭ አልማ አንተ የተባረክ ነህ፣ እና በሞርሞን ውሃ የተጠመቁት የተባረኩ ናችው። የእኔ አገልጋይ በሆነው በአቢናዲ ቃል ብቻ እጅግ በማመንህ የተባረክህ ነህ።

፲፮ እናም እነሆ አንተ በተናገርካቸው ቃላት ብቻ እጅግ ስላመኑም የተባረኩ ናቸው።

፲፯ እናም በዚህ ህዝብ መካከል ቤተክርስቲያኗን በመመስረትህ አንተ የተባረክህ ነህ፤ እናም እነርሱም ይቋቋማሉ፣ የእኔም ሰዎች ይሆናሉ።

፲፰ አዎን፣ ስሜን ለመቀበል ፈቃደኛ የሆነ ይህ የተባረከ ህዝብ ነው፤ በስሜም ይጠራሉና፣ እናም እነርሱ የእኔ ናቸው።

፲፱ እናም እኔን ህጉን ስለተላለፉት በተመለከተ ስለጠየከኝ አንተ የተባረክህ ነህ።

አንተ የእኔ አገልጋይ ነህ፤ እናም ዘለዓለማዊ ሕይወት ይኖርህ ዘንድ ካንተ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ እናም ታገለግለኛለህም፣ በስሜም ትሄዳለህ፣ እናም በጎቼን በአንድነት ትሰበስባለህ።

፳፩ እናም ድምጼን የሰማ የእኔ በግ ይሆናል፣ እናም እናንተ በቤተክርስቲያኗ ትቀበሉታላችሁ፤ እኔም ደግሞ እቀበለዋለሁ።

፳፪ እነሆም ይህች የእኔ ቤተክርስቲያን ናት፣ ማንም የሚጠመቅ ንሰሃ በመግባት ይጠመቃል፤ እናም እናንተ የተቀበላችሁት ማንም ቢኖር በስሜ ያምናል፤ እናም እርሱን በነፃ ይቅር እለዋለሁ።

፳፫ እኔ የዓለምን ኃጢያት በራሴ ያደረግሁ ነኝና፤ እነርሱን የፈጠርኳቸው እኔ ነኝና፤ እናም እስከመጨረሻው ለሚያምነው በቀኜ ያለውንም ስፍራ የምሰጠው እኔ ነኝ።

፳፬ እነሆም፣ በስሜም ተጠርተዋል፤ እናም የሚያውቁኝ ከሆነም ወደ እኔ ይመጣሉ፣ እናም በቀኝ እጄ በኩል ዘለዓለማዊ ስፍራ ይኖራቸዋል።

፳፭ እናም እንዲህ ይሆናል ሁለተኛው መለከት ሲነፋ እኔን በፍፁም ያላወቁ መጥተው በፊቴ ይቆማሉ።

፳፮ እና ከእዚያም እኔ ጌታ አምላካቸው፣ አዳኛቸው መሆኔን ያውቃሉ፤ ነገር ግን አይድኑም።

፳፯ እናም ከዚያ በኋላ እኔ በጭራሽ እንደማላውቃቸው እናዘዝላቸዋለሁ፣ እናም ለዲያብሎስና ለመላዕክቱ ወደተዘጋጀው ወደ ዘለዓለማዊ እሳት ይሄዳሉ

፳፰ ስለዚህ እንዲህም እላችኋለሁ፣ ቃሌን የማይሰማ፣ እርሱ በቤተክርስቲያኔ አትቀበሉት፣ በመጨረሻውም ቀን እርሱን አልቀበለውምና።

፳፱ ስለዚህ እላችኋለሁ ሂዱ፣ እናም እኔን የተላለፈ ማንኛውንም እንደፈፀመው ኃጢያት መሰረት ፍረድበት፤ እናም በእኔና በአንተ ፊት ኃጢአቱን ከተናዘዘ፣ እናም ከልቡ ንስሃ ከገባ እርሱን ይቅር ትለዋለህ፣ እኔም ደግሞ ይቅር እለዋለሁ።

አዎን፣ እናም ህዝቤ ንስሃ እንደገባው መጠን በእኔ ላይ ያደረጉትን መተላለፍ ይቅር እላቸዋለሁ።

፴፩ እናም እያንዳንዳችሁ መተላለፋችሁን ይቅር ተባባሉ፤ እውነት እላችኋለሁ ጎረቤቱ ንስሃ በሚገባበት ጊዜ የጎረቤቱን መተላለፍ ይቅር የማይል እርሱ ራሱን ወደኩነኔ ያመጣል።

፴፪ አሁን እልሀለሁ፣ ሂድ፣ ለኃጢአቱ ንስሃ የማይገባ እርሱ ከህዝቤ ጋር አብሮ አይቆጠርም፤ እናም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ይህ ደንብ ይጠበቃል።

፴፫ እናም እንዲህ ሆነ አልማ ይህንን ቃል በሰማ ጊዜ፣ እንዲኖሩት፣ እና በእግዚአብሔር ትዕዛዝ መሰረት የቤተክርስቲያን ሰዎችን ይፈረድባቸው ዘንድ ጻፋቸው።

፴፬ እናም እንዲህ ሆነ አልማ ሄደና፣ እነዚያ በክፋት የተወሰዱትን በጌታ ቃል መሰረት ፈረደባቸው።

፴፭ እና ማንኛውም ለኃጢአታቸው ንስሃ የገቡ የተናዘዙ፣ እነርሱ ከቤተክርስቲያኗ ሰዎች መካከል ቆጠራቸው።

፴፮ እናም ኃጢአታቸውን ያልተናዘዙና ለክፋታቸው ንስሃ ያልገቡ፣ እነርሱ ከቤተክርስቲያኗ ሰዎች መካከል አልተቆጠሩም፣ ናም ስማቸውም ተሰርዟል

፴፯ እናም እንዲህ ሆነ አልማ የቤተክርስቲያኗን ጉዳዮች ሁሉ መራ፤ እናም ለቤተክርስቲያኑ ጉዳዮች ሰላምና ብልፅግና በድጋሚ እጅግ መሳካት ጀመሩ፣ በጥንቃቄም በእግዚአብሔር ፊት በመራመድ ብዙዎችን ተቀበሉ፣ ብዙዎችን አጠመቁ።

፴፰ እናም አሁን፣ በማንኛውም ትጋት በመራመድ፣ በሁሉም ነገር የጌታን ቃል በማስተማር፣ በሁሉም መከራ በመሰቃየት፣ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን አባል ባልሆኑት ሁሉ በመሳደድ፣ እነዚህ ነገሮች በሙሉ አልማና በቤተክርስቲያኗ ላይ ያሉት ተከታይ አገልጋዮች ይህንን አደረጉ።

፴፱ እናም ወንድሞቻቸውን ገሰፁ፤ እናም በእግዚአብሔር ያለማቋረጥ እንዲፀልዩና በሁሉም ነገር ምስጋናን እንዲሰጡም በመታዘዝ፣ እያንዳንዱ እንደ ኃጥያቱ፣ ወይም እንደፈፀመው ኃጢአቱ መሰረት በእግዚአብሔር ቃል ተገስጿል።