ቅዱሳት መጻህፍት
ሞዛያ ፳


ምዕራፍ ፳

አንዳንድ የላማናውያን ሴት ልጆች በኖህ ካህናት ተጠልፈው ነበር—ላማናውያን በሊምሂና በህዝቡ ላይ ጦርነት አደረጉ—የላማናውያን ሠራዊቶች አሸነፏቸውና አረጋጓቸው። ከ፻፵፭–፻፳፫ ም.ዓ. ገደማ።

አሁን በሻምሎን የላማናውያን ሴት ልጆች ለመዝፈንና ለመደነስ እናም እራሳቸውን ለማስደሰት በአንድነት የሚሰበስቡበት ስፍራ ነበር።

እናም እንዲህ ሆነ በጥቂት የሚቆጠሩ እራሳቸውን በአንድነት ለመዝፈንና ለመደነስ አንድ ቀን አሰባስበው ነበር።

እናም አሁን የንጉስ ኖህ ካህናት ወደ ኔፊ ከተማ ለመመለስ በማፈር፣ አዎን፣ እናም ደግሞ ህዝቡ ይገድለናል ብለው ስለፈሩ፣ ስለዚህ ወደ ሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው ለመመለስ አልደፈሩም።

እናም በምድረበዳ ውስጥ በመቅረታቸውና፣ የላማናውያን ሴት ልጆችን በማግኘታቸው ተኝተው ጠበቁአቸው፣

እናም ጥቂቶች ለመደነስ በአንድ ላይ በተሰበሰቡ ጊዜ፣ ከተደበቁበት ስፍራ ወጡና ጠለፉአቸው እናም ወደ ምድረበዳው ወሰዱአቸው፤ አዎን፣ የላማናውያን ሀያ አራት ሴት ልጆችን ወደ ምድረበዳው ወሰዱአቸው።

እናም እንዲህ ሆነ ላማናውያን የሴት ልጆቻቸውን መጥፋት ሲያውቁ፣ ይህን ያደረጉት የሊምሂ ህዝብ ናቸው ብለው በማሰብ በሊምሂ ህዝብ ተቆጡ።

ስለዚህ ወታደሮቻቸውን ላኩባቸው፣ አዎን፣ ንጉሱም ራሱ እንኳን ቢሆን ከህዝቡ ፊት ሄደ፤ እናም የሊምሂን ህዝብ ለማጥፋት ወደ ኔፊ ምድር ሄዱ።

እናም አሁን ሊምሂ ከግንቡ ላይ ተመለከታቸውና፣ ለጦርነት ሁሉንም ዝግጅታቸውን ተመለከተ፤ ስለዚህ ህዝቡን በአንድ ላይ ሰበሰበና፣ እናም በመስኩ ላይና በጫካው መሽገው ጠበቁ።

እናም እንዲህ ሆነ ላማናውያን በመጡ ጊዜ፣ የሊምሂ ህዝቦች ይጠብቁበት ከነበረበት ስፍራ ያጠቁአቸውና፣ ይገድሉአቸው ጀመር።

እናም እንዲህ ሆነ ጦርነቱ እጅግ አሰቃቂ ሆነ፤ ልክ አንበሳዎች ለአደኖቻቸው እንደሚጣሉም አይነት ነበርና።

፲፩ እናም እንዲህ ሆነ የሊምሂ ህዝብ ላማናውያንን ከፊታቸው ማባረር ጀመሩ፤ ይሁን እንጂ እንደ ላማናውያን ግማሹን እንኳን ያህል አይበዙም ነበር። ነገር ግን ለህይወታቸው፣ እናም ለሚስቶቻቸውና፣ ለልጆቻቸው ታገሉ፤ ስለዚህ ለራሳቸው እንደዘንዶው ለመዋጋት ጥረት አድርገዋል።

፲፪ እናም እንዲህ ሆነ ከሙታን መካከል የላማናውያንን ንጉስ አገኙ፤ ሆኖም እርሱ ገና አልሞተም ነበር፣ ቆስሎ ነበር፣ እናም የህዝቡም ሽሽት ፈጣን ስለነበር በመሬቱም ላይ ወድቆ ነበር።

፲፫ እናም ወሰዱትና ቁስሉን አሰሩለት፣ እንዲሁም ከሊምሂ ፊት አመጡት፣ እናም እንዲህ አሉ፤ እነሆ፣ የላማናውያን ንጉስ ይኸውና፣ በመቁሰሉም ከሙታኖቻቸው መካከል ወደቀና፣ ጥለውት ሄዱ፤ እናም እነሆ፣ በፊትህ አመጣነው፤ እናም አሁን እንግደለው።

፲፬ ነገር ግን ሊምሂ እንዲህ አላቸው፥ አትግደሉት፣ ነገር ግን እኔ እንዳየው ወደዚህ ስፍራ አምጡት። እነርሱም አመጡት። እናም ሊምሂ እንዲህ አለው፥ አንተን ከህዝቤ ጋር በጦርነት ለመምጣት ያነሳሳህ ምንድን ነው? እነሆ፣ ህዝቤ ለአንተ ያደረግሁትን መሃላ አላፈረሱም፤ ስለዚህ፣ ለምን አንተ ለህዝቤ ያደረግኸውን መሃላ ታፈርሳለህ?

፲፭ እናም አሁን ንጉሱ እንዲህ አለ፥ ህዝብህ የህዝቤን ሴቶች ልጆችን ስለወሰዱ መሃላዬን አፈረስሁ፤ ስለዚህ፣ በቁጣዬ ህዝቤ ከህዝብህ ላይ በጦርነት እንዲመጡ አድርጌአለሁ።

፲፮ እናም አሁን ሊምሂ ይህንን በተመለከተ ምንም አልሰማም ነበር፤ ስለዚህ እንዲህ አለ፥ ከህዝቤ መካከል እፈልጋለሁ እናም ይህንን ያደረገ ይጠፋል። ስለዚህ በህዝቡ መካከል እንዲፈልጉ አደረገ።

፲፯ አሁን ጌዴዎን እነዚህን ነገሮች በሰማ ጊዜ፣ እርሱ የንጉሱ ካፒቴን በመሆኑ፤ ሄዶም ለንጉሱ እንዲህ አለው፥ እባክህን እማፀንሃለሁ፣ እናም ይህን ህዝብ አትፈትሽ፣ ህዝቡንም በዚህ ሀላፊ አታድርጋቸው።

፲፰ ይህ ህዝብ ሊያጠፏቸው የፈለጓቸውን የአባትህን ካህናት አታስታውስምን? እናም በምድረበዳስ አይደሉምን? እናስ የላማናውያንን ሴት ልጆች የሰረቁት እነርሱ አይደሉምን?

፲፱ እናም አሁን፣ እነሆ እናም ለህዝቡ እንዲነግራቸውና ወደ እኛ እንዲረጋጉ እነዚህን ነገሮች ለንጉሱ ንገር፤ እነሆም በእኛ ላይ ለመምጣት ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፤ እነሆም፣ ደግሞ ከእኛ ጥቂቶቹ ነንና።

እናም እነሆ፣ ከብዙ ሰራዊቶቻቸው ጋር መጡ፣ እናም ንጉሱ ካላረጋጋቸው በስተቀር እኛ እንጠፋለን።

፳፩ አቢናዲ በእኛ ላይ የተነበያቸው ቃላት አልተፈፀሙምን—እናም ይህ ሁሉ የሆነበት ምክንያት የጌታን ቃል ባለመስማታችን፣ እናም ከክፋታችንስ ባለመመለሳችን አይደለምን?

፳፪ እናም እንግዲህ ንጉሱን እናረጋጋው እናም የገባውን መሃላ እንፈፅም፤ ምክንያቱም ህይወታችንን ከምናጣ በባርነት ሥር ብንሆን ይሻለናል፤ ስለዚህ የብዙ ደም መፋሰሱን እናቁመው።

፳፫ እናም እንግዲህ ሊምሂ ስለአባቱና ወደ ምድረበዳው ስለሸሹት ካህናት ለንጉሱ ነገረው፣ እናም ሴቶች ልጆቻቸው የመውሰድ ጥፋተኛነትን በተመለከተ በእነርሱ ላይ ጣለው።

፳፬ እናም እንዲህ ሆነ ንጉሱ ወደ ህዝቡ ተረጋጋ፣ እንዲህም አላቸው፥ ከህዝቤ ጋር ለመገናኘት መሳሪያዎችን ሳንይዝ እንሂድ፤ እናም ህዝቤ ህዝባችሁን እንደማይገድልም መሃላ እምልላችኋለሁ።

፳፭ እናም እንዲህ ሆነ ንጉሱን ተከተሉትና፣ መሳሪያቸውን ሳይዙ ላማናውያንን ለማግኘት ሄዱ። እናም እንዲህ ሆነ ላማናውያንን አገኙአቸው፤ የላማናውያንም ንጉስ ከፊታቸው በመስገድ ስለሊምሂ ህዝብ ለመነ።

፳፮ እናም ላማናውያን የሊምሂን ህዝብ ያለ ጦር መሳሪያ መሆናቸውን በተመለከቱ ጊዜ፣ አዘኑላቸውና፣ ወደ እነርሱ ተረጋጉ፣ ከንጉሳቸውም ጋር በሰላም ወደ ራሳቸው ምድር ተመለሱ።