ቅዱሳት መጻህፍት
ሞዛያ ፲፮


ምዕራፍ ፲፮

እግዚአብሔር ሰዎችን ከጥፋትና ከውድቀት ሁኔታቸው ያድናል—በስጋ ያሉ ቤዛነት እንደሌለ ሆነው ይቀራሉ—ክርስቶስ መጨረሻ የሌለው ህይወትን ወይንም መጨረሻ የሌለው ኩነኔ ትንሳኤን አመጣው። በ፻፵፰ ም.ዓ. ገደማ።

እናም አሁን እንዲህ ሆነ፣ አቢናዲ እነዚህን ቃላት ከተናገረ በኋላ ክንዱን ዘረጋና አለ፥ ሁሉም የጌታን ደህንነት የሚያዩበት ቀን ይመጣል፤ ሁሉም ሀገር፣ ነገድ፣ ቋንቋና ህዝብ ዐይን ለዐይን ይተያያሉ እናም በእግዚአብሔር ፊት ፍርዱ ትክክል እንደሆነ ይናዘዛሉ

እና ከእዚያም ኃጢአተኞች ይጣላሉ፣ እናም ዋይ እያሉ የሚያለቅሱበትና በትካዜ የሚጮሁበት፣ እናም ጥርሳቸውን የሚፋጩበት ምክንያት ይኖራቸዋል፣ ይህም የሚሆነው የጌታን ድምፅ ስለማያዳምጡ ነው፤ ስለዚህ ጌታ አያድናቸውም።

ስጋዊና አጋንንታዊ ናቸው፣ እናም ዲያብሎስ፣ አዎን፣ እንዲሁም ያ የቀደመው እባብ እንዲያውም የመጀመሪያ ወላጆቻችንን ያሳተውየውድቀታቸው መንስኤ የሆነውን፣ ለሰው ዘር በሙሉ ስጋዊነት፣ ስሜታዊነት፣ ዲያብሎሳዊነት፣ መጥፎን ከጥሩ ለይተው በማወቅ ራሳቸውን ለዲያብሎስ የሚያስገዙበት ምክንያት የሆነው በእነርሱ ላይ ኃይል አለውና።

የሰው ዘር ሁሉ ጠፍቷል፣ እናም እነሆ፣ እግዚአብሔር ህዝቡን ከጠፋበትና ከውድቀት ባያድነው ኖሮ እስከመጨረሻው በጠፋ ነበር።

ነገር ግን አስታውሱ በስጋዊ ተፈጥሮው የቆየ፣ እናም በኃጢያትና በእግዚአብሔር እያመፀ የተጓዘ፣ ወድቆ ይቀራል እናም ዲያብሎስ ሙሉ ስልጣን በእርሱ ላይ ይኖረዋል። ስለዚህ ለእግዚአብሔር ጠላት ሆኖ፣ እርሱ ቤዛነት እንዳልተደረገለት ይሆናል፣ እናም ደግሞ ዲያብሎስም የእግዚአብሔር ጠላት ነው።

እናም፣ ስለነገሮች መምጣት እንደመጡ በመናገር፣ እንግዲህ ክርስቶስ ወደ ዓለም ባይመጣ ኖሮ ቤዛ ሊሆን አይችልም ነበር።

እናም ክርስቶስ ከሞት ባይነሳ ኖሮ፣ ወይም መቃብርም ድል እንዳይኖረውና ሞትም መውጊያ እንዳይኖረው፣ የሞትን እስር ባይበጣጥስ ኖሮ፣ ትንሣኤም ሊኖር አይችልም ነበር።

ነገር ግን ትንሳኤ አለ፤ ስለዚህ ሞት ድል አይኖረውም፤ እናም የሞት መውጊያ በክርስቶስ ተውጧል።

እርሱ የዓለም ብርሃንና ህይወት ነው፤ አዎን፣ መጨረሻ የሌለው፣ ሊጨልም የማይችል ብርሃን፤ አዎን እናም ደግሞ መጨረሻ የሌለው ህይወት፣ እናም ከእንግዲህ ሞት ሊሆን የማይችልበት።

እንዲሁም ይህ የሚሞተው የማይሞተውን ይለብሳል፣ እናም ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ይለብሳል፣ እናም መጥፎም ይሁን መልካም እንደስራቸው መሰረት እንዲፈረድባቸው በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት ይቆማሉ

፲፩ መልካም ከሆኑ መጨረሻ ለሌለው ህይወትና ደስታ ትንሳኤ፤ እናም መጥፎ ከሆኑ፣ ኩነኔ ወደሆነው የእርሱ ላደረጋቸው ለዲያብሎስ በመሰጠት መጨረሻ ለሌለው የኩነኔ ትንሳኤ—

፲፪ እና በስጋዊ ፍቃዳቸውና ፍላጎታቸው መሰረት በመሄዳቸው፣ እናም የምህረት ክንዶች ወደ እነርሱ ተዘርግተው ሳለ፣ ጌታን በጭራሽ ባለመጥራታቸው፤ የምህረት ክንዶች ወደ እነርሱ ተዘርግተዋልና፣ እነርሱም አልተቀበሉትም፤ ለጥፋታቸው ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም እነርሱ ግን ከእነዚህ አልሸሹም፤ እናም ንስሃ እንዲገቡ ታዘው ነበር ነገር ግን ንስሃ አልገቡም።

፲፫ እናም አሁን፣ ልትንቀጠቀጡና፣ ለኃጢአታችሁ ንስሃ ልትገቡ አይገባችሁምን፤ እናም በክርስቶስ ብቻ ልትድኑ እንደምትችሉ አታስታውሱምን?

፲፬ ስለዚህ፣ የሙሴን ህግ የምታስተምሩ ከሆነ፣ ደግሞ የሚመጣው ነገር ጥላ እንደሆነ አስተምሩ—

፲፭ ቤዛነት ዘለዓለማዊ አባት በሆነው በጌታ በክርስቶስ እንደሚመጣ አስተምሯቸው። አሜን።