ምዕራፍ ፮
ጌታ እስራኤልን በመጨረሻው ቀን ይሰበስባል—ዓለም በእሳት ትቃጠላለች—ከእሳቱ ባህርና ከዲኑ ለመዳን ሰዎች ክርስቶስን መከተል ይኖርባቸዋል። ከ፭፻፵፬–፬፻፳፩ ም.ዓ. ገደማ።
፩ እናም አሁን፣ እነሆ፣ ወንድሞቼ እተነብያለሁ ብዬ ለእናንተ እንደተናገርኩት እነሆ፣ ትንቢቴ ይህ ነው—የእስራኤልን ቤት በተመለከተ ከለማው ወይራ ዛፍ ጋር በማመሳሰል ነቢዩ ሀዜኖስ የተናገራቸው ነገሮች በእርግጥ ይሆናሉ።
፪ እናም በድጋሚ ለሁለተኛ ጊዜ ህዝቡን ሀለማዳን እጁን የሚያነሳበት ቀን፣ አዎን፣ ለመጨረሻው ጊዜ እንኳን፣ የጌታ ለአገልጋይ ወደፊት በመቀጠል ሐበኃይሉ መየወይኑን ስፍራ ሠየሚንከባከብበትና፣ የሚከረክምበት ቀን ነው፤ እናም ከዚያ በኋላ ረመጨረሻው በፍጥነት ይመጣል።
፫ እናም በወይኑ ስፍራ በትጋት የሰሩት እንዴት የተባረኩ ናቸው፤ እናም ወደ ራሳቸው ስፍራስ የሚጣሉት እንዴት የተረገሙ ናቸው! እናም ዓለም በእሳት ሀትቃጠላለች።
፬ እናም ሀየእስራኤልን ቤት ስሮችና ቅርንጫፎች ያስታወሰው አምላካችን እንዴት መሀሪ ነው፤ እናም ለእነርሱ ቀኑን ሙሉ ለክንዱን ይዘረጋል፤ እነርሱም ሐአንገተ ደንዳና እና ተቃዋሚ ህዝብ ናቸው፤ ነገር ግን አብዛኞቹም ልባቸውን ባያጠጥሩ በእግዚአብሔር መንግስት ይድናሉ።
፭ ስለሆነም፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ንስሀ እንድትገቡም፣ በልባችሁም ሙሉ ዓላማ እንድትመጡና፣ እግዚአብሔር ለእናንተ ሀእንደፀና እናንተም እንድትፀኑ በጥሞና ቃላት እለምናችኋለሁ። እናም በቀን ብርሃን የምህረት ለክንዱ ወደ እናንተ በተዘረጋ ጊዜ ልባችሁን አታጠጥሩ።
፮ አዎን፣ ዛሬ፣ ድምፁን ብትሰሙ፣ ልባችሁን አታጠጥሩ፤ ለምንስ ሀትሞታላችሁ?
፯ እነሆም፣ ቀኑን ሁሉ በመልካሙ የእግዚአብሔርን ቃል ከተመገባችሁ በኋላ፣ መጥፎ ፍሬን አፍርታችሁ ሀበመቆረጥ ወደ እሳት መጣል ይገባችኋልን?
፰ እነሆ፣ እነዚህን ቃላት ትቃወማላችሁን? የነቢያቱን ቃላትስ ትቃወማላችሁን፤ ስለእርሱ ብዙዎች ከተናገሩ ከተባለ በኋላ፣ ክርስቶስን በተመለከተስ የተነገሩትን ቃላት ሁሉ ትቃወማላችሁን፤ እናም የክርስቶስን መልካም ቃል፣ የእግዚአብሔርን ኃይልና፣ የመንፈስ ቅዱስን ሀስጦታን ትክዳላችሁን፣ የቅዱስ መንፈስ እርካታንም ታጠፋላችሁን፣ እናም ለእናንተ የተመሰረተውን ታላቁን የቤዛነት ዕቅድ ትሳለቁበታላችሁን?
፱ እነዚህን ነገሮች ካደረጋችሁ፣ በክርስቶስ ያለው የቤዛነትና የትንሳኤ ኃይል ሀበእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት በእፍረትና በመጥፎ ለጸጸት እንደሚያቆማችሁ አታውቁምን?
፲ እናም ሀበፍርድ ኃይል መሰረት፣ ፍርድ ሊካድ አይችልምና፣ እናንተ በነበልባሉ ወደ ማይጠፋው፣ እናም ጢሱም ለዘለዓለም እስከዘለዓለም ወደሰማይ ወደሚወጣው፣ ለየእሳቱ ባህርና ዲን ሐመጨረሻ የሌለው መስቃይ ወደሆነው፣ የእሳት ባህርና ዲን መሄድ ይገባችኋል።
፲፩ እንግዲህ አቤቱ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ንስሀ ግቡ፣ ሀበጠባቡም ደጅ ግቡ፣ እናም ዘለዓለማዊ ህይወትን እስከምታገኙ ድረስ በቀጥተኛ ጎዳና ቀጥሉ።
፲፪ አቤቱ ሀብልህ ሁኑ፤ ከዚህ የበለጠ ምን ማለት እችላለሁ?
፲፫ በመጨረሻም ኃጢአተኞችን ሀበመጥፎ ስጋትና ፍርሃት በሚመታው በአስደሳቹ በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት እስከምንገናኝ ድረስ ደህና ሁኑ እላችኋለሁ። አሜን።