ቅዱሳት መጻህፍት
ሔለማን ፫


ምዕራፍ ፫

ብዙ ኔፋውያን ወደ ሰሜን ምድር ተጓዙ—የስሚንቶ ቤቶችን ሰሩ፣ እና ብዙ መዛግብቶችን አስቀመጡ—በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ተለወጡ እናም ተጠመቁ—የእግዚአብሔር ቃል ሰዎችን ወደ ደህንነት ይመራል—የሔለማን ልጅ ኔፊ የፍርድ ወንበሩን ያዘ። ከ፵፱–፴፱ ም.ዓ. ገደማ።

እናም እንግዲህ እንዲህ ሆነ በመሣፍንቱ አርባ ሶስተኛ ዓመት የንግስ ዘመን በህዝቡ መካከል ጥቂት ልዩነት በፈጠረው ቤተክርስቲያን ካለው ጥቂት ኩራት በስተቀር በኔፊ ህዝብ መካከል ፀብ አልነበረም፤ ይህ ጉዳይም በአርባ ሶስተኛው ዓመት መጨረሻ ላይ ተስተካከለ።

እናም በአርባ አራተኛው ዓመት በህዝቡ መካከል ፀብ አልነበረም፤ በአርባ አምስተኛው ዓመትም ብዙ ፀብ አልነበረም።

እናም እንዲህ ሆነ በአርባ ስድስተኛው ዓመት፣ አዎን ብዙ ፀብና መገነጣጠሎች ነበሩ፤ ስለሆነም ከዛራሔምላ ምድር የወጡ እጅግ ብዙዎች ነበሩ፤ እናም በምድሪቱ ወደ ሰሜን በኩል ምድሪቱን ለመውረስ ሄዱ።

እናም በታላቁ ውሃ እንዲሁም ወንዝ እስከሚደርሱ ድረስ እጅግ ብዙ ተጓዙ።

አዎን፣ ቀደም ሲል በብዙ ሰዎች ተሰፍሮበት የነበረ በመሆኑም የተነሳ በሁሉም ስፍራ ባዶ ባልሆነው እንዲሁም ምንም ደን በሌለበት የምድሩ ክፍሎች ሁሉ ውስጥ በሙሉ ተበተኑ።

እናም እንግዲህ ከደኑ በስተቀር ባዶ የሆነ ስፍራ በምድሪቱ አልነበረም፤ ነገር ግን ቀደም ሲል ምድሪቱን ወርሰው በነበሩት ሰዎች ታላቅ ጥፋት የተነሳ ምድሪቱ የወደመች ተብላ ትጠራ ነበር።

እናም በምድሪቱ ገፅ ትንሽ ዛፍ ብቻ የነበረ በመሆኑ፣ ይሁን እንጂ፣ በምድሪቱ ለመኖር የሄዱ በስሚንቶ ሥራ ባለሙያዎች ሆኑ፤ ስለዚህ የሚኖሩበትንም ቤት ከስሚንቶ ሰርተዋል።

እናም እንዲህ ሆነ ተባዙና፣ ተሰራጩ፣ እንዲሁም ከምድሪቱ ከደቡብ በኩል ወደ ሰሜን ተጓዙ፣ እናም ከባህሩ በስተደቡብ እስከባህሩ በስተ ሰሜን፣ ከባህሩ በስተምዕራብ እስከ ባህሩ በስተምስራቅ ድረስ ምድሪቱን በሙሉ መሸፈን እስከሚጀምሩ ድረስ ተበተኑ።

እናም በምድሪቱ በስተሰሜን በኩል የነበሩት ሰዎች በድንኳንና፣ በስሚንቶ በተሰራው ቤት ውስጥ ኖሩ፣ እናም ከጊዜ በኋላም ቤቶቻቸውን መስሪያ፣ አዎን፣ ከተሞቻቸውንና፣ ቤተመቅደሶቻቸውንና፣ ምኩራቦቻቸውንና፣ ቅዱስ የሆኑ ቦታዎቻቸውንና ሁሉም ዓይነት ህንፃዎቻቸውን መስሪያ እንጨት ይኖራቸው ዘንድ በምድሪቱ ላይ ማንኛውንም ዓይነት ዛፍ እንዲያድግ አደረጉ።

እናም እንዲህ ሆነ በምድሪቱ በስተሰሜን በኩል እጅግ የእንጨት እጥረት ስለነበር፣ ከሌላ ስፍራ ብዙ በመርከብ ያስመጡ ነበር።

፲፩ እና በምድሪቱ በስተሰሜን በኩል ያለው ህዝብ ብዙ ከተሞችን ከእንጨትና ከስሚንቶ ይሰሩ ዘንድ አስቻሏቸው።

፲፪ እናም እንዲህ ሆነ በትውልዳቸው ላማናውያን የነበሩ ብዙ የአሞን ሰዎችም ደግሞ ወደዚህች ምድር ሄዱ።

፲፫ እናም እንግዲህ ስለዚህ ህዝብ ስራ የተቀመጡ፣ በብዙዎቹ በእነዚህ ሰዎች የተለዩ፣ እናም ትልቅ የሆኑ እነርሱን በተመለከተ የሚናገሩ ብዙ መዛግብት ተጠብቀዋል።

፲፬ ነገር ግን እነሆ፣ የዚህ ህዝብ ስራ መቶኛው ክፍል፤ አዎን፣ የላማናውያንና የኔፋውያንና፣ ጦርነታቸውና፣ ፀባቸው፣ እናም ጥላቸውና፣ ሰበካቸውም፣ ትንቢታቸውም፣ የመርከብ ጉዞአቸውና፣ የመርከብ አሰራራቸውንና፣ የቤተመቅደስ አሰራራቸውንና፣ የምኩራቡንና፣ የቅዱሳን ስፍራዎቻቸውንና፣ ፅድቃቸውንና፣ ኃጢአታቸውንና፣ የግድያቸውና፣ ስርቆታቸው፣ እናም የዝርፊያቸው፣ እንዲሁም የሁሉም ዓይነት እርኩሰትና ዝሙት ታሪክ በዚህ ስራ ውስጥ ሊጠቃለሉ አይችሉም።

፲፭ ነገር ግን እነሆ፣ ብዙ መጻሕፍትና ከሁሉም ዓይነት ብዙ መዛግብት አሉ፣ እናም በኔፋውያን በተለይ ተጠብቀዋል።

፲፮ እናም ኔፋውያን በመተላለፍ እስከሚወድቁና እስከሚገደሉ፣ እስከሚዘረፉና፣ እስከሚታደኑና፣ እስከሚባረሩ፣ እናም እስከሚታረዱና፣ በምድር ገፅ ላይ እስከሚበተኑ፣ እንዲሁም ኔፋውያን ተብለው መጠራት እስከሚያቆሙ ድረስ ከላማናውያን ጋር እስከሚቀላቀሉ፣ እነርሱ ኃጢአተኞችና፣ አረመኔዎች፣ እናም ኃይለኞች እስከሚሆኑ፣ አዎን፣ ላማናውያንም እንኳን እስከሚሆኑ ድረስ ከአንዱ ትውልድ ወደ ሌላኛው በኔፋውያን ተላልፈዋል

፲፯ እናም አሁን እኔም በድጋሚ ወደራሴ ታሪክ እመለሳለሁ፤ ስለዚህ የተናገርኳቸው የሆኑት ታላቁ ፀብና፣ ረብሻና፣ ጦርነት፣ እናም ጥል፣ በኔፋውያን መካከል ከተፈፀመ በኋላ ነበር።

፲፰ አርባ ስድስተኛው የመሣፍንቱ የንግስ ዘመንም ተፈፀመ፤

፲፱ እናም እንዲህ ሆነ በምድሪቱ አሁንም ታላቅ ፀብ ነበር፤ አዎን፣ እንዲሁም በአርባ ሰባተኛው ዓመትም፣ እናም ደግሞ በአርባ ስምንተኛውም ዓመት።

ይሁን እንጂ ሔለማን በፅድቅና በእኩልነት የፍርድ ወንበሩን ያዘ፤ አዎን የእግዚአብሔርን ስርዓትና፣ ህግጋት፣ እናም ትዕዛዛት ለመጠበቅ ጥረት አደረገ፤ እናም በእግዚአብሔር ፊት ትክክል የሆነውን ያለማቋረጥ ያደርግ ነበር፤ በምድሪቱም ላይ እስከሚበለፅግ ድረስ እንደ አባቱ ኖሯል።

፳፩ እናም እንዲህ ሆነ እርሱ ሁለት ወንድ ልጆች ነበሩት። ለታላቅየው የኔፊን ስምና፣ ለታናሽየው የሌሂን ስም ሰጣቸው። እናም በጌታ ማደግ ጀመሩ።

፳፪ እናም እንዲህ ሆነ በመሣፍንቱ በኔፊ ህዝብ ላይ በአርባ ስምንተኛው ዓመት የንግሥ ዘመን ማብቂያ ገደማ በኔፋውያን መካከል ጦርነቱ፣ እናም ፀቡ በመጠኑ መቆም ጀመረ።

፳፫ እናም እንዲህ ሆነ በመሣፍንቱ አርባ ዘጠነኛ ዓመት የንግስና ዘመን፣ እነርሱም በዚያን ጊዜም ቢሆን በመንግስት ከበላይ በነበሩት ከማይታወቁት፣ ሁሉም በተረጋጋው ስፍራ ቀማኛው ጋድያንቶን ካደራጀው የሚስጥር ሴራዎች በስተቀር በምድሪቱም የማያቋርጥ ሰላም ተመሰረተ፤ ስለዚህ ከምድሪቱም ፈፅሞ አልጠፉም ነበር።

፳፬ እናም እንዲህ ሆነ በዚሁ ዓመት በቤተክርስቲያኗ እጅግ ታላቅ ብልፅግና ሆነ፤ በሺዎች የሚቆጠሩትም ወደ ቤተክርስቲያኗ መጡ፣ እናም ንስሃ በመግባት ተጠመቁ።

፳፭ እናም የቤተክርስቲያኗ ብልፅግናም ታላቅ ሆኖ፣ እናም በጣም ብዙ በረከት በህዝቡ ላይ ስለወረደ፤ ታላላቅ ካህናትና፣ መምህራንም እራሳቸው ከልክ በላይ ተገርመው ነበር።

፳፮ እናም እንዲህ ሆነ የጌታ ስራ ብዙ ነፍሳትን፣ አዎን አስር ሺዎችን ያህል፣ በማጥመቅ፣ እናም ወደ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያኗ በማምጣት በለጸገ።

፳፯ ስለዚህ ጌታ ከልብ በመሆን ቅዱስ ስሙን ለሚጠሩ ሁሉ እርሱ መሀሪ እንደሚሆን እንደዚህ እንመለከታለን።

፳፰ አዎን፣ የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለሚያምኑ፣ የሰማይ በር ለሁሉም ክፍት እንደሆነም እንደዚህ እንመለከታለን።

፳፱ አዎን፣ ማንም ቢሆን ህያው የሆነውንና ኃያል የሆነውን፣ የዲያብሎስን ዕቅድ፣ ብልጠትና ወጥመድ የሚበታትነውን፣ እናም የክርስቶስ የሆኑትን ሰዎች በቀጭኑና ጠባብ በሆነው ጎዳና፣ ኃጢአተኞችንም ሊውጣቸው ከተዘጋጀው ከዘለዓለማዊው ጉስቁልና ባሻገር የሚመራቸውን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቆ የያዘ—

ነፍሳቸውም፣ አዎን የማይሞተው ነፍሳቸው በመንግስተ ሰማያት በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ፣ ከአብርሃምና፣ ከይስሀቅ፣ እናም ከያዕቆብና፣ ከቅዱሳን አባቶቻችን ጋር ለማስቀመጥ፣ ከእንግዲህም ወደውጭ አይሄዱ ዘንድ እንደሚያደርግ እንመለከታለን።

፴፩ እናም በዚህ ዓመት በዛራሔምላ ምድር፣ እናም በዙሪያው ሁሉ፤ በኔፋውያን በተያዙት ቦታዎች እንኳን ሁሉ የማያቋርጥ ደስታ ነበር።

፴፪ እናም እንዲህ ሆነ በአርባ ዘጠነኛው ዓመት ሰላምና እጅግ ታላቅ ደስታ ነበር፤ አዎን፣ እናም ደግሞ በመሣፍንቱም ሀምሳኛ ዓመት የንግስ ዘመን የማያቋርጥ ሰላምና ታላቅ ደስታ ነበር።

፴፫ እናም በቤተክርስቲያኗ—ወደ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ሳይሆን፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ተብለው እራሳቸውን ከሚጠሩት ሰዎች ልብ ውስጥ—መግባት ከጀመረው ኩራት በስተቀር በመሣፍንቱ ሀምሳ አምስተኛ ዓመት የንግስ ዘመንም ሰላም ነበር

፴፬ እናም ብዙዎች ወንድሞቻቸውን እስከሚያሳድዱአቸው ድረስ በኩራት ተወጠሩ። አሁን ይህ ታላቅ ክፋት ትሁት የሆኑትን ሰዎች ይበልጥ ለታላቅ ስደት እናም ስቃይ እንዲገፉ የሚያደርግ የነበረው።

፴፭ ይሁን እንጂ ዘወትር ፆሙ፣ እንዲሁም ፀለዩ፣ እናም ነፍሳቸውን በደስታና በመፅናናት እስከሚሞሉ ድረስም፣ አዎን፣ ልቦቻቸውን ለእግዚአብሔር በፍቃድ በመስጠት በሚመጣው ቅድስና ልቦቻቸው እንዲጸዱና እንዲቀደሱ እስከሚያደርጉ ድረስ በትህትና እየጠነከሩ፣ እናም በክርስቶስ እምነታቸውን እየጸኑ ሄዱ።

፴፮ እናም እንዲህ ሆነ በህዝቡ ልብ ውስጥ ከገባው ታላቅ ኩራት በቀር ሀምሳ ሁለተኛው ዓመትም በሰላም ደግሞ ተፈፀመ፤ እናም የዚህ መንስኤ በምድሪቱ ከነበራቸው እጅግ ታላቅ ሀብትና ብልፅግና ነበር፤ ይህም በእነርሱ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ሄደ።

፴፯ እናም እንዲህ ሆነ በመሣፍንቱ ሀምሳ ሶስተኛ ዓመት የንግስ ዘመን ሔለማን ሞተ፤ ታላቁ ልጁ ኔፊም በእርሱ ምትክ መንገስ ጀመረ። እናም እንዲህ ሆነ የፍርድ ወንበሩንም በጽድቅና በእኩልነት ያዘው፤ አዎን የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ጠበቀና፣ በአባቱ መንገድ ተራመደ።