ቅዱሳት መጻህፍት
አልማ ፭


በእግዚአብሔር ቅዱሱ ስርዓት መሰረት ሊቀ ካህኑ የነበረው አልማ ለህዝቡ በከተማቸውና በምድሪቱ ባሉት መንደሮች በሙሉ የተናገረው ቃል።

ከምዕራፍ ፭ ጀምሮ።

ምዕራፍ ፭

ደህንነት ለማግኘት ሰዎች ንስሀ መግባትና ትዕዛዛቱን መጠበቅ፣ ዳግም መወለድ፣ በክርስቶስ ደም ልብሳቸውን ማፅዳት፣ ትሁት መሆንና፣ ከኩራትና ከምቀኝነት እራሳቸውን ማስወገድ እናም የፅድቅን ስራ መስራት አለባቸው—መልካሙ እረኛ ህዝቡን ይጠራል—ክፉ ስራ የሚሰሩ የዲያብሎስ ልጆች ናቸው—አልማ የትምህርቱን እውነተኛነት መሰከረ፣ እናም ሰዎች ንስሀ እንዲገቡ አዘዘ—የፃድቃኖች ስም በህይወት መዝገብ ይፃፋል። በ፹፫ ም.ዓ. ገደማ።

አሁን እንዲህ ሆነ አልማ በመጀመሪያ በዛራሔምላ ምድር እናም ከዚያም በምድሪቱ ላይ ሁሉ ለህዝቡ የእግዚአብሔርን ቃል መናገር ጀመረ።

እናም በእርሱ አመዘጋገብ መሠረት በዛራሔምላ ከተማ ለተመሰረተችው ቤተክርስቲያን ሰዎች የተናገራቸው ቃላት እነዚህ ናቸው።

እኔ አልማ በአባቴ በአልማ በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ላይ ሊቀ ካህን በመሆን በመቀባቴ፤ እርሱም ከእግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች ለመፈፀም ኃይልና ስልጣን ስላለው፣ እነሆ፣ እላችኋላሁ፣ እርሱም በኔፊ ምድር ወሰን ላይ ቤተክርስቲያንን ማቋቋም ጀመረ፤ አዎን፣ የሞርሞን ምድር ተብላ በምትጠራው ምድር ላይ፤ አዎን፣ እናም በሞርሞን ውሃ ወንድሞቹን አጠመቃቸው።

እናም እነሆ፣ እላችኋለሁ፣ እነርሱ ከንጉስ ኖህ ሰዎች እጅ በእግዚአብሔር ኃይልና ምህረት ድነው ነበር።

እናም እነሆ፣ ከዚያ በኋላ በምድረበዳው ውስጥ በላማናውያን እጅ ወደ ባርነት ገብተው ነበር፤ አዎን፣ እላችኋለሁ፣ በምርኮ ነበሩ፣ እናም በድጋሚ ጌታ በቃሉ ኃይል ከባርነት አውጥቷቸዋል፤ እኛም ወደዚህ ምድር ተወስደን ነበር፣ እናም ደግሞ በዚህ ምድር ላይ የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ማቋቋም ጀመርን።

እናም አሁን እነሆ፣ ወንድሞቼ እንዲህ እላችኋለሁ፣ ከዚህ ቤተክርስቲያን የሆናችሁ የአባቶቻችሁን በምርኮ መቆየት በሚገባ ታስታውሳላችሁን? አዎን፣ እናም ለእነርሱ ያለውንስ ምህረትና ታላቅ ፅናት በሚገባ ታስታውሳላችሁን? እናም ከዚህ በተጨማሪ፣ የእነርሱን ነፍስ ከሲዖል እንዳዳነ በሚገባ ታስታውሳላችሁን?

እነሆ፣ እርሱ ልባቸውን ለውጧል፣ አዎን፣ ከጥልቁ እንቅልፋቸው ቀስቅሶአቸዋል፣ እናም ወደ እግዚአብሔር ነቅተዋል። እነሆ፣ በጨለማው መካከል ነበሩ፣ ይሁን እንጂ ነፍሳቸው በዘለአለማዊው ቃል ብርሃን በርቷል፣ አዎን፣ በሞት እስራትና በሲኦል ሰንሰለት ተከበው ነበር፣ እናም ዘለአለማዊ ጥፋትም ይጠብቃቸው ነበር።

እናም አሁን ወንድሞቼ እነርሱ ጠፍተው ነበርን? ብዬ እጠይቃችኋለሁ፣ እነሆ፣ አይደለም አልጠፉም እላችኋለሁ።

እናም በድጋሚ እጠይቃለሁ፣ የሞት እስር ተስብሯልን፣ እናም እነርሱን የከበበው የሲኦል ሰንሰለትስ ተፈትቷል? እንዲህ እላችኋለሁ፥ አዎን፣ ተፈትቷልና፣ ነፍሳቸው ተስፋፋች፣ እንዲሁም በቤዛነት ፍቅር ዘምረዋል። እናም ድነዋል እላችኋለሁ።

እናም አሁን በምን ሁኔታ ነው የዳኑት? ብዬ እጠይቃችኋለሁ፣ አዎን፣ ለመዳንስ በምንድን ነው ተስፋ ያደረጉት? ከሞት እስራት፣ አዎን፣ እናም ደግሞ የሲዖሉ ሰንሰለት የሚፈቱበት መንስኤ ምንድን ነው?

፲፩ እነሆ፣ ልነግራችሁ እችላለሁ—አባቴ አልማ በአቢናዲ አንደበት የተነገሩትን አላመነምን? እናም እርሱስ ቅዱስ ነቢይ አልነበረምን? የእግዚአብሔርንስ ቃላት አልተናገረምን፣ እናም አባቴ አልማስ አላመናቸውምን?

፲፪ እናም በእምነቱ መሰረት በልቡ ታላቅ ለውጥ ነበር። እነሆ ይህ ሁሉ እውነት ነው እላችኋለሁ።

፲፫ እናም እነሆ፣ ለአባቶቻችሁ ቃሉን ሰብኳል፣ ታላቅ ለውጥም በልባቸው ውስጥ ሆነ፤ እራሳቸውንም ትሁት አደረጉ፣ እምነታቸውንም በእውነተኛውና በህያው አምላክ ላይ አደረጉ። እናም እነሆ፣ እስከመጨረሻው የታመኑ ነበሩ፣ ስለዚህም ድነው ነበር።

፲፬ እናም አሁን እነሆ፣ የቤተክርስቲያኗ ወንድሞቼ፣ በመንፈስ ከእግዚአብሔር የተወለዳችሁ ናችሁን? በፊታችሁስ ምስሉን ተቀብላችኋልን? በልባችሁስ ይህን ታላቅ ለውጥ ተለማምዳችኋልን? ብዬ እጠይቃችኋለሁ።

፲፭ እናንተን በፈጠረው ስለተደረገው ቤዛነት እምነትን ተለማምዳችኋልን? ወደፊትስ በእምነት አይን እየተመለከታችሁ፣ ይህ ሟቹ ሰውነት የማይሞት በመሆን እንደሚነሳ፣ እናም ይህ የሚበሰብሰው ባለመበስበስ ተነስቶ በእግዚአብሔር ፊት በሥጋ በተደረገው ስራዎች መሰረት ሊፈረድበት እንደሚቆም ትመለከታላችሁን?

፲፮ እኔ እላችኋለሁ፣ በዚያን ቀን የጌታ ድምፅ ለራሳችሁ፣ እናንተ የተባረካችሁ ወደ እኔ ኑ፣ እነሆ ሥራችሁ በምድር ፊት የፅድቅ ሥራ ነው እንደሚላችሁ ትገምታላችሁን?

፲፯ ወይንስ፣ ጌታ ሆይ፤ ስራችን በምድር ፊት ጻድቅ ስራ ነው፣ ብላችሁ በዚያን ቀን ለጌታ መዋሸት እንችላለን፣ እናም እኛን ያድነናል ብላችሁ ትገምታላችሁ?

፲፰ ወይስ አለበለዚያ፣ ጥፋታችሁን ሁሉ በማስታወስ፣ አዎን፣ የክፋታችሁን ሁሉ ፍፁም ትውስታ፣ እግዚአብሔርን ትእዛዛት ላይ ያመጻችሁትን ትውስታ እያላችሁ፣ ነፍሳችሁ በጥፋትና በፀፀት ተሞልታ በእግዚአብሔር ፍርድ ቤት ፊት መቅረባችሁን መገመት ይቻላችኋልን?

፲፱ እንዲህ እላችኋለሁ፣ በዚያን ቀን በንፁህ ልባችሁና በንፁህ እጃችሁ እግዚአብሔርን ለመመልከት ትችላላችሁን? የእግዚአብሔር ምስል በእናንተ ምስል ተቀርፆ ቀና ብላችሁ መመልከት ትችላላችሁን? እላችኋለሁ።

በዲያብሎስ ተገዢ ለመሆን ራሳችሁን አሳልፋችሁ በምትሰጡበት ጊዜ ለመዳን ለማሰብ ትችላላችሁን? እላችኋለሁ።

፳፩ በዚያን ቀን መዳን እንደማትችሉ ታውቃላችሁ እላችኋለሁ፤ ማንም ሰው ልብሱ ነጭ ሆኖ ካልታጠበ በቀር መዳን አይችልምና፤ አዎን፣ በአባቶቻችን በተነገረለት፣ ህዝቡን ከኃጢኣት ለማዳን በሚመጣው ደም ልብሱ ከሁሉም ኃጢኣት እስከሚፀዳ ድረስ ንፁህ መሆን አለበት።

፳፪ እናም አሁን፣ ወንድሞቼ እጠይቃችኋለሁ፣ ልብሳችሁ በደምና በማንኛውም ዓይነት ቆሻሻ ተበክሎ በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት የምትቆሙ ከሆነ ማንኛችሁም ምን ይሰማችኋል? እነሆ፣ እነዚህ ነገሮች በእናንተስ ላይ ምን ይመሰክራሉ?

፳፫ እነሆ ነፍሰ ገዳዮች፣ አዎን እናም ደግሞ በሁሉም ዓይነት ክፋት ጥፋተኛ እንደሆናችሁ አይመሰክሩምን?

፳፬ እነሆ፣ ወንድሞቼ፣ እንዲህ አይነቱ በእግዚአብሔር መንግስት ከአብርሃም ጋር፣ ከይስሀቅ ጋር፣ እናም ከያዕቆብ ጋር፣ እናም ደግሞ ልብሳቸው የነፃና እንከን የሌለው፣ ንፁህና ነጭ ከሆነው ከቅዱሳን ነቢያት ጋር ይቀመጣል ብላችሁ ትገምታላችሁን?

፳፭ አይደለም እላችኋለሁ፣ ፈጣሪያችንን ከመጀመሪያ ጀምሮ ሃሰተኛ ካላደረጋችሁት በስተቀር፣ ወይንም እርሱ ከመጀመሪያ ጀምሮ ሃሰተኛ ነው ብላችሁ ካልገመታችሁ በስተቀር እንደዚህ ዓይነቱ በመንግስተ ሰማይ ቦታ ይኖረዋል ብላችሁ ለመገመት አትችሉም፤ ነገር ግን እነርሱ የዲያብሎስ መንግስት ልጆች ናቸውና ይጣላሉ።

፳፮ እናም አሁን እነሆ፣ ወንድሞቼ እንዲህ እላችኋለሁ፣ የልብ መለወጥን የሚሰማችሁ ከሆነ፣ እናም የቤዛነት የፍቅር ዜማ ለመዘመር ከተሰማችሁ፣ አሁንም ሊሰማችሁ ይችላልን? በማለት እጠይቃችኋለሁ።

፳፯ ራሳችሁንስ በእግዚአብሔር ፊት እንከን የለሽ በማድረግ ትራመዳላችሁን? በዚህ ጊዜ ለመሞት ብትጠሩ በራሳችሁ፣ እኔ በሚገባ ትሁት ነኝ? ልብሳችሁ ህዝቡን ከኃጢአቶቻቸው ለማዳን በሚመጣው በክርስቶስ ደም ጠርቷልን፣ እናም ነጥቷል ለማለት ትችላላችሁን?

፳፰ እነሆ፣ ከኩራታችሁስ ተገፍፋችኋልን? ካልሆናችሁ እግዚአብሔርን ለመገናኘት ዝግጁ አይደላችሁም እላችኋለሁ። እነሆ በፍጥነት መዘጋጀት አለባችሁ፤ መንግስተ ሰማይ ቀርባለችና፣ እናም እንደዚህ ዓይነቱ ዘለአለማዊ ህይወት አይኖረውም።

፳፱ እነሆ፣ እላለሁ፣ ከእናንተ መካከል ከምቀኝነት ያልተገፈፈ አንድ እንኳን አለን? እንደዚህ ዓይነቱ አልተዘጋጀም እላችኋለሁ፤ እናም ጊዜው ቀርቧልና በፍጥነት እንዲዘጋጅ እፈልገዋለሁ፣ እናም ጊዜው መቼ እንደሚመጣ አያውቅም፤ እንደዚህ ዓይነቱ እንከን የሌለው ሆኖ አልተገኘምና።

እናም በድጋሚ እላችኋለሁ፣ በወንድሙ ላይ ከእናንተ መካከል የሚሳለቅ፣ ወይም ስደትን የሚያበዛ አለን?

፴፩ ለእንደዚህ ዓይነቱ አልተዘጋጀምና ወዮለት፣ እናም ጊዜው ቀርቧልና ንስሀ መግባት አለበት፣ አለበለዚያም መዳን አይችልም!

፴፪ አዎን፣ እናንተ ክፋትን ለምትሰሩ ሁሉ ወዮላችሁ፣ ንስሀ ግቡ፣ ንስሀ ግቡ፣ ጌታ እግዚአብሔር ተናግሮታልና!

፴፫ እነሆ፣ ለሰው ሁሉ ግብዣን ልኳል፣ የምህረት ክንድ ወደእነርሱ ተዘርግቷልና፣ እናም እንዲህ ይላል፥ ንስሀ ግቡ፣ እናም እኔ እቀበላችኋለሁ።

፴፬ አዎን፣ እንዲህም ይላል፥ ወደ እኔ ፣ እናም ከህይወት ዛፍም ፍሬ ትካፈላላችሁ፤ አዎን የህይወትን ዳቦና ውኃ በነፃ ትመገባላችሁ እናም ትጠጣላችሁ፤

፴፭ አዎን፣ ወደ እኔ ኑና፣ የፅድቅንም ስራ አቅርቡ፣ እናም አትቆረጡም በእሳት ውስጥም አትጣሉም—

፴፮ እነሆ፣ መልካም ያልሆነውን ፍሬ የሚያመጣ፣ ወይም የፅድቅን ስራ የማይሰራ እንዲያዝንና እንዲያለቅስ የሚሆንበት ጊዜው ቀርቧልና።

፴፯ እናንተ የተንኮል ሰራተኞች ሆይ፤ በዓለም ከንቱ ነገሮች በኩራት የተሞላችሁ፤ የፅድቅን መንገድ ማወቃችሁን የምትናገሩ ነገር ግን እረኛ እንደሌለው በግ በተሳሳተው የምትጓዙ፤ ሆኖም እረኛው ጠርቷችኋል እናም አሁንም እናንተን ይጣራል፣ ነገር ግን እናንተ ድምፁን አትሰሙም!

፴፰ እነሆ፣ መልካሙ እረኛ እናንተን ይጣራል እላችኋለሁ፤ አዎን፣ እናም በክርስቶስ ስም በሆነው በስሙ ይጠራችኋል፤ እናም በምትጠሩበት ስም የመልካሙን እረኛ ድምፅ የማትሰሙ ከሆነ፣ እነሆ፣ እናንተ የመልካሙ እረኛ በግ አይደላችሁም!

፴፱ እናም አሁን የመልካሙ እረኛ በግ ካልሆናችሁ፣ ከየትኛው በረት ናችሁ? እነሆ፣ ዲያብሎስ እረኛችሁ ነው እላችኋለሁ፣ እናም እናንተም ከእርሱ በረት ናችሁ፣ እናም አሁን ይህንን ማን ሊክደው ይቻለዋል? እነሆ ይህን የካደ ውሸታም እንዲሁም የዲያብሎስ ልጅ ነው እላችኋለሁ።

ማንኛውም መልካም የሆነ የሚመጣው ከእግዚአብሔር ነው፣ ማንኛውም ክፉ የሆነው የሚመጣው ከዲያብሎስ ነው እላችኋለሁ።

፵፩ ስለዚህ፣ መልካም ስራዎችን የሚያመጣ የመልካሙን እረኛ ድምፅ ይሰማል፣ እና እርሱንም ይከተለዋል፤ ነገር ግን ክፉ ስራዎች የሚያመጣ፣ ያም የዲያብሎስ ልጅ ይሆናል፣ ድምፁን ይሰማዋል፣ እናም ይከተለዋልና።

፵፪ እናም ይህን ያደረገ ደምዎዙን ከእርሱ መቀበል ይገባዋል፤ ስለዚህ፣ የፅድቅ ስራዎችን በተመለከተ፣ ለመልካም ስራዎች ሁሉ ሙት በመሆን፣ ለደሞዙ የሚያገኘው ሞት ነው።

፵፫ እናም አሁን፣ ወንድሞቼ፣ እንድታዳምጡኝ እፈልጋለሁ፣ በነፍሴ ሀይል እናገራለሁና፤ እነሆ ልትሳሳቱ በማትችሉበት ሁኔታ በግልፅ ተናግሬአችኋለሁና፣ ወይም በእግዚአብሔር ትዕዛዛት መሰረት ተናግሬአችኋለሁ።

፵፬ እኔም ክርስቶስ ኢየሱስ በሆነው፣ በእግዚአብሔር ቅዱሱ ስርዓት መሰረት በዚህ ሁኔታ እንድናገር ተጠርቻለሁ፤ አዎን፣ የሚመጡትን ነገሮች በሚመለከት በአባቶቻችን የተነገሩትን ነገሮች ለዚህ ህዝብ ቆሜ እንድመሰክር ታዝዤአለሁ።

፵፭ እናም ይህ ብቻም አይደለም። እነዚህን ነገሮች እኔ ራሴ እንደማውቃቸው አትገምቱምን? እነሆ፣ እነዚህ የምናገራቸው ነገሮች እውነት መሆናቸውን እንደማውቅ እመሰክርላችኋለሁ። እናም እርግጠኝነታቸውን እንዴት እንዳወቅሁ ትገምታላችሁ?

፵፮ እነሆ፣ እነዚህ እንዲታወቁኝ የሆኑት በእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ነው። እነሆ፣ እነዚህን ነገሮች ለራሴ ለማወቅ ለብዙ ቀናት ፆሜአለሁ እንዲሁም ፀልያለሁ። እናም አሁን እውነት መሆናቸውን ለራሴ አውቄአለሁ፤ ጌታ እግዚአብሔር በቅዱስ መንፈሱ እንዲገለፅልኝ አድርጓልና፤ እናም ይህ በእኔ ውስጥ ያለው የራዕይ መንፈስ ነው።

፵፯ እናም ከዚህ በተጨማሪ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ መገለጫ በሆነው፣ በእኔ ውስጥ ባለው የትንቢት መንፈስም መሠረትም፣ በአባቶቻችን የተነገሩት ቃላት እውነት መሆናቸው እንደተገለፀልኝ እነግራችኋለሁ።

፵፰ የሚመጣውን በተመለከተ ማንኛውም ለእናንተ የምናገረው እውነት እንደሆነ እኔ ራሴ እንደማውቀው እነግራችኋለሁ፤ እናም እላችኋለሁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ አዎን፣ በጸጋና፣ በመሀሪነት፣ እንዲሁም በእውነት የተሞላው የአብ አንድያ ልጅ፣ እንደሚመጣ አውቃለሁ። እናም እነሆ የዓለምን ኃጢያት፣ አዎን፣ በፅናት በስሙ የሚያምኑ ሰዎች ሁሉ ኃጢያትን ለመውሰድ የሚመጣው እርሱ ነው።

፵፱ እናም አሁን እላችኋለሁ ይህ እኔ፣ አዎን፣ ለውድ ወንድሞቼ እንድሰብክ፤ አዎን፣ እናም በምድሪቱ ላይ ለሚኖሩ ሁሉ፣ አዎን፣ ለወጣትና ለሽማግሌዎች፣ ለታሰሩትና ነፃ ለሆኑት ሁሉ እንድሰብክ፤ አዎን፣ እላችኋለሁ፣ ለሽማግሌዎችና፣ ደግሞ መካከለኛ ዕድሜ ላላቸው፣ እናም በማደግ ላይ ላለው ትውልድ፤ አዎን፣ ንስሀ እንዲገቡና ዳግም እንዲወለዱ ወደ እነርሱ እንድጮህ የተጠራሁበት ሥርዓት ነው።

አዎን፣ መንፈስ እንዲህ ይላል፥ በአለም ዳርቻዎች ያላችሁ ሁሉ ንስሀ ግቡ፣ መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና፣ አዎን፣ የእግዚአብሔር ልጅ በኃይሉ፣ በግርማ ሞገሱ፣ በአገዛዙና በስልጣኑ፣ በክብሩ ይመጣል። አዎን፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ መንፈስ እንዲህ ይላል እላችኋለሁ፤ የምድር ንጉስ ሁሉ ክብር ተመልከቱ፤ እናም ደግሞ የሰማይ ንጉስ በቅርቡ በሰው ልጆች ሁሉ መካከል ያበራል።

፶፩ እናም ደግሞ መንፈስ እንዲህ አለኝ፣ አዎን፣ በከፍተኛ ድምፅ ወደ እኔ እንዲህ በማለት ጮኸ፤ ሂድና ለህዝቡ እንዲህ በል—ንስሀ ግቡ፣ ንስሀ ካልገባችሁ በስተቀር በምንም ዓይነት መንገድ መንግስተ ሰማያትን አትወርሱም።

፶፪ እናም በድጋሚ እንዲህ እላችኋለሁ፣ መንፈስ እንዲህ ይላል፥ እነሆ፣ ምሳር በዛፉ ስር ተቀምጧል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማይሰጥ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም፣ አዎን፣ ወደማይቆም እሳት፣ ወደማይጠፋ እሳት ይጣላል። እነሆ፣ እናም አስታውሱ፣ ይህን ቅዱሱ ተናግሮታል።

፶፫ እናም አሁን የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ ይህንን አባባል ልትቃወሙት ትችላላችሁን፤ አዎን፣ እነዚህ ነገሮችን ችላ ልትሉአቸው ትችላላችሁን፣ እናም ቅዱሱንስ በእግራችሁ ስር ትረግጡታላችሁን፤ አዎን፣ በልባችሁ ኩራትስ ለመወጠር ይቻላችኋልን፤ አዎን፣ ውድ የሆኑ ልብሶችን በመልበስ እናም ልባችሁን በከንቱ ምድራዊ ነገሮች እንዲሁም በሀብት ላይ ማድረጋችሁን አሁንም ትቀጥላላችሁን?

፶፬ አዎን፣ እናንተን ከሌሎች የተሻላችሁ አድርጋችሁ መገመትን ትቀጥላላችሁን? አዎን፣ በእግዚአብሔር ቅዱሱ ስርዓት የሚራመዱትንና እራሳቸውን ትሁት ያደረጉትን ወንድሞቻችሁን ማሳደድ ትቀጥላላችሁ? በዚህም ወደዚህች ቤተክርስቲያን መጥተዋል፣ በቅዱሱ መንፈስ ተቀድሰዋል፣ እናም ለንስሀ የሚያበቁአቸውን ስራዎቻቸውንም አምጥተዋል—

፶፭ አዎን በድሆች ላይና በተቸገሩ ላይ ትከሻችሁን ማዞር፣ እንዲሁም ያሉአችሁን ሳታካፍሉ ትቀጥላላችሁን?

፶፮ እናም በመጨረሻ፣ በክፋታችሁ የምትቀጥሉ ሁሉ፣ በፍጥነት ንስሀ ካልገቡ በስተቀር ተቆርጠው ወደ እሳቱ የሚጣሉት እነርሱ እንደሆኑ እነግራችኋለሁ።

፶፯ እናም አሁን የመልካሙን እረኛ ድምፅ ለመከተል የምትፈልጉ ሁሉ፣ ከክፉዎች ውጡና ተለዩ፣ እንዲሁም እርኩስ ነገሮቻቸውን አትንኩ እላችኋለሁ፤ እናም እነሆ፣ የኃጢአተኞች ስም ከህዝቤም ጋር አይቀላቀልም፣ የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይፈፀም ዘንድ ስማቸው ይሰረዛል፣ የክፉዎች ስም ከፃድቃኖች ጋርም አይቆጠርም።

፶፰ የፃድቃኖች ስም በህይወት መፅሐፍ ይፃፋል፤ እናም ለእነርሱ በቀኝ እጄ ያለውን ውርስ እሰጣቸዋለሁ። እናም አሁን ወንድሞቼ ከዚህ ተቃራኒ የሆነን ምን ትናገራላችሁ? እላችኋለሁ፣ ከዚህ ተቃራኒ የምትሉ ከሆነ፣ ይህ ምንም አይደለም፣ የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸማልና።

፶፱ በእናንተ መካከል የትኛው እረኛ ነው ብዙ በጎች እያሉት፣ ተኩላዎችስ ገብተው መንጋዎቹን እንዳይበሉበት የማይጠብቃቸው? እናም እነሆ፣ ተኩላው ሲገባበት እርሱ አያባርርምን? አዎን፣ እናም የሚቻለው ከሆነ እርሱንም ያጠፋዋል።

እናም አሁን መልካሙ እረኛ ይጠራችኋል እላችኋለሁ፤ እናም ቃሉን የምታዳምጡ ከሆነ ወደ በረቱ ያመጣችኋል፤ እናንተም የእርሱ በጎች ናችሁ፤ እንዳትጠፉ ደም የተጠማውን ተኩላ በመካከላችሁ እንዲገባ እንዳትፈቅዱም ያዛችኋል።

፷፩ እናም አሁን እኔ፣ አልማ፣ እኔ የተናገርኳችሁንም ቃላት እንድታደርጉ፣ እኔን ባዘዘኝ በእርሱ ቋንቋ አዛችኋለሁ።

፷፪ ከቤተክርስቲያኗ ለሆናችሁ በትዕዛዝ መልክ እናገራለሁ፤ እናም ከቤተክርስቲያኗ ላልሆኑት በግብዣ መልክ እንዲህ በማለት እናገራለሁ፥ የህይወት ዛፍ ፍሬን ደግሞ ትካፈሉ ዘንድ ኑ እናም ለንስሀ ተጠመቁ።