ቅዱሳት መጻህፍት
አልማ ፵፰


ምዕራፍ ፵፰

አማሊቅያ ላማናውያንን በኔፋውያን ላይ አነሳሳ—ሞሮኒ የክርስቲያን ጉዳዮችን እንዲከላከሉ ህዝቡን አዘጋጀ—እርሱም በመብትና በነፃነት ተደሰተ እናም የእግዚአብሔር ኃያል ሰው ነው። በ፸፪ ም.ዓ. ገደማ።

እናም እንዲህ ሆነ አማሊቅያ ግዛቱን እንዳገኘ የላማናውያንን የልብ ስሜት በኔፊ ህዝብ ላይ እንዲነሳሱ ቀሰቀሰ፤ አዎን፣ ሰዎች ኔፋውያንን በመቃወም ከሰገነታቸው ላይ በመሆን ለላማናውያን እንዲናገሩ ሾማቸው።

እናም ወደ መሣፍንቱ የአስራ ዘጠነኛው የንግስ ዘመን መጨረሻ ላይ አማሊቅያ ልባቸው በኔፋውያን ላይ እንዲነሳሳ አደረገ፤ ዕቅዱን እስከዚህ ድረስ በመፈፀሙ፤ አዎን በላማናውያን ላይ ንጉስ ለመሆን እንደፈለገው በመደረጉ፣ በምድሪቱ ላይም ደግሞ፤ አዎን፣ እናም በኔፋውያንም ሆነ በላማናውያን ምድር ባሉት ሰዎች ሁሉ ላይ እንዲነግስ ፈለገ።

ስለዚህ የላማናውያንን ልብ በማጠጠሩ፣ እናም አዕምሮአቸው እንዲታወር በማድረጉ፣ እናም ለቁጣ እነርሱን በማነሳሳቱ፣ ብዙ ወታደሮች ኔፋውያንን ለመዋጋት በአንድ ላይ እራሳቸውን እስከሚሰበስቡ ድረስ ዕቅዱን ፈፀመ።

እርሱም ኔፋውያንን ለመግዛት፣ እናም እነርሱን ወደ ባርነት ለማምጣት የሰዎቹ ቁጥር ታላቅ በመሆኑ ታላቅ ውሳኔን አድርጎ ነበር።

እናም የኔፋውያንን ብርታትና፣ የመጠለያ ቦታዎቻቸውን፣ እናም ደካማ የሆነውን የከተማቸውን ክፍል የሚያውቁ በመሆናቸው ዞራማውያንን ዋና ሻምበል በማድረግ ሾሞ ነበር፤ ስለዚህ እነርሱን በሠራዊቱ ላይ ዋና ሻምበል በማድረግ ሾመ።

እናም እንዲህ ሆነ የጦር ሰፈራቸውን አነሱና፣ በምድረበዳው ውስጥ ወደ ዛራሔምላ ምድር ሄዱ።

እንግዲህ እንዲህ ሆነ አማሊቅያ ስልጣንን በማምታታት፣ እና በማጭበርበር እያገኘ ባለበት ጊዜ፣ ሞሮኒ፣ በሌላ በኩል የሰዎችን አዕምሮ ለጌታ ለአምላካቸው ታማኝ እንዲሆኑ ያዘጋጅ ነበር።

አዎን፣ የኔፋውያን ወታደሮችን አጠናከረ፣ እናም ትናንሽ ምሽጎችን፣ ወይንም የመጠለያ ስፍራዎችን እንዲሰሩ አደረገ፤ ወታደሮቹን ለመክበብ መሬቱ እንዲቆለል፣ እናም ደግሞ በድንጋይ ግድግዳም ዙሪያውን፣ ከተሞቻቸውንና የምድሪቱን ዳርቻ፣ አዎን፣ በምድሪቱ ዙሪያ ሁሉ ከበበ።

እናም በደንብ ባልተዘጋጀው ምሽጋቸው ብዙ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች አስቀምጦ ነበር፤ እናም በኔፋውያን የተያዙትን ምድር እንደዚህ አጠረና አጠናከረ።

እናም በጌታ ይኖሩ ዘንድ፣ እናም በጠላቶቻቸው የክርስቲያኖች ጉዳይ ተብሎ የተጠራውን ይጠብቁ ዘንድ፣ ነፃነታቸውን፣ ምድራቸውን፣ ሚስቶቻቸውን፣ ልጆቻቸውንና ሰላማቸውን ለመደገፍ ተዘጋጅቶ ነበር።

፲፩ እናም ሞሮኒ ጠንካራና፣ ኃያል ሰው ነበር፤ እርሱም ፍፁም የሆነ ዕውቀት ያለው ሰው ነበር፤ አዎን በደም መፋሰስ የማይደሰት ሰው ነበር፤ ነፍሱም በሀገሩመብትና ነጻነት፣ እናም በወንድሞቹ ከመታሰርና ከባርነት መብትና ነጻነት ትደሰታለች፤

፲፪ አዎን፣ እግዚአብሔር በህዝቡ ላይ ብዛት ያላቸው ልዩ መብቶችን፣ እናም በረከቶችን በማድረጉ ለአምላክ ምስጋናን በማቅረብ ልቡ የተሞላ፤ ለህዝቡ ደህንነት እናም ጥበቃ ሲል እጅግ የሰራ ሰው ነው።

፲፫ አዎን፣ እናም እርሱ በክርስቶስ ፅኑ እምነት ያለው ሰው ነበር፤ እናም የህዝቡን መብት፣ ሀገሩንና ኃይማኖቱን፣ ደሙ እስከሚፈስ ድረስ እንኳን ለመጠበቅ መሃላ ምሎ ነበር።

፲፬ እንግዲህ አስፈላጊ ከሆነ ኔፋውያን ደማቸው እስከሚፈስም ድረስ እንኳን ከጠላቶቻቸው እራሳቸውን እንዲከላከሉ ተምረዋል፤ አዎን፣ እናም ደግሞ ህይወታቸውን ከመጠበቅ በቀር በጭራሽ እንዳያጠቁ፣ አዎን፣ እናም በጠላቶቻቸው ላይ ካልሆነ በቀር ጎራዴያቸውን እንዳያነሱ፣ ተምረዋል።

፲፭ እናም ይህ እምነታቸው ነበር፣ ይህንንም በማድረግ እግዚአብሔር በምድሪቱ ላይ ያበለፅጋቸዋል፣ ወይንም በሌላ አነጋገር የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በመጠበቅ ታማኞች እስከሆኑ ድረስ በምድሪቱ ላይ ያበለፅጋቸዋል፤ አዎን፣ እንዲሸሹ፣ አለበለዚያም በሚመጣባቸው አደጋ መሰረት ለጦርነት እንዲዘጋጁ ያስጠነቅቃቸዋል፤

፲፮ እናም ደግሞ፣ እግዚአብሔርም ከጠላቶቻቸው ለመከላከል ወዴት እንደሚሄዱ እንዲያውቁ ያደርጋቸዋል፣ ይህንንም በማድረግ፣ ጌታ ያድናቸዋል፤ ይህም የሞሮኒ እምነት ነበር፣ እናም በደም መፋሰስ ሳይሆን በመልካም ስራ ሕዝቡን ለመጠበቅ፤ አዎን፣ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በመጠበቅ፣ አዎን፣ እናም ክፋትን በመቋቋም ልቡም በዚያ ተመካች።

፲፯ አዎን፣ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ ሰዎች ሁሉ እንደ ሞሮኒ ከሆኑና ከነበሩ፣ እናም የሚሆኑ ከሆነ፣ እነሆ፣ የሲኦል ኃይል እራሱ ለዘለዓለም ይናወጥ ነበር፤ አዎን፣ ዲያብሎስም በሰው ልጆች ልብ ላይ ስልጣን በጭራሽ ባልኖረውም ነበር።

፲፰ እነሆ እርሱም የሞዛያ ልጅ እንደነበረው እንደ አሞን ዓይነት ነበር፤ አዎን፣ እናም እንደሌሎቹ የሞዛያ ልጆች ነበር፤ አዎን፣ እናም ደግሞ የእግዚአብሔር ሰዎች እንደነበሩት እንደ አልማና ልጆቹ ነበር።

፲፱ እናም እነሆ፣ ሔለማንና ወንድሞቹ ለህዝቡ ከሞሮኒ ያነሰን አገልግሎት የሰጡ አልነበሩም፤ ምክንያቱም እነርሱ የእግዚአብሔርን ቃል ሰብከዋል፣ እናም ቃላቸውን የሰሙአቸውን ሰዎች በሙሉ ለንስሃ አጥምቀዋቸዋል።

እናም እነርሱ ሄዱና፣ ህዝቡ በቃላቸው የተነሳ በጌታ የተመረጡ እስከሚሆኑ ድረስ እራሳቸውን ዝቅ አደረጉ፣ እናም አዎን ለአራት ዓመታትም ያህል በራሳቸው መካከል ከጦርነትና ከፀብ ነፃ ሆኑ።

፳፩ ነገር ግን፣ እንደተናገርኩት፣ በአስራ ዘጠነኛው ዓመት መጨረሻ፣ አዎን፣ በመካከላቸው ሰላም ቢሆንም እንኳን፣ ሳይፈልጉ ከወንድሞቻቸው ከላማናውያን ጋር እንዲጣሉ ተገደዱ።

፳፪ አዎን፣ እናም በአጠቃላይ ፈቃደኞች ባይሆኑም እንኳን፣ ከላማናውያን ጋር ለብዙ ዓመታት ጦርነትን በጭራሽ አላቆሙም ነበር።

፳፫ እንግዲህ በደም መፋሰሱ ደስተኞች ባለመሆናቸው በላማናውያን ላይ ጦርነት በማስነሳታቸው አዝነው ነበር፤ አዎን፣ እናም ይህ ብቻም አልነበረም—ብዙ ወንድሞቻቸውንም ከዚህ ዓለም ወደ ዘለአለማዊው ዓለም ከአምላካቸው ጋር ለመገናኘት ሳይዘጋጁ እንዲላኩ መንስኤ በመሆናቸው አዝነው ነበር።

፳፬ ይሁን እንጂ፣ በአንድ ወቅት ወንድሞቻቸው በነበሩት፣ አዎን፣ እናም ከቤተክርስቲያናቸው በተገነጠሉትና፣ ትተዋቸው በሄዱት፣ እናም ከላማናውያን ጋር በመሆን ሊያጠፋቸው በሄዱት አረመኔ ሰዎች ጭካኔ ሚስቶቻቸውና፣ ልጆቻቸው እንዲጨፈጨፉና እንዲያጠፏቸው ዘንድ ህይወታቸውን ለመስጠት ለመፍቀድ አልቻሉም።

፳፭ አዎን፣ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የጠበቀ እስካለ ድረስ ወንድሞቻቸው በኔፋውያን ደም ደስታን እንዲያገኙ ለመመልከት አይቻላቸውም፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን እንደነበረው፣ ትዕዛዛቱን ከጠበቁ በምድሪቱ ላይ ይበለፅጋሉ።