ቅዱሳት መጻህፍት
አልማ ፳፰


ምዕራፍ ፳፰

ላማናውያን በአስገራሚው ውጊያ ተሸነፉ—በሺዎች የሚቆጠሩ ሞቱ—ኃጢአተኞች ማብቂያ ለሌለው መከራ ይሰጣሉ፤ ፃድቃኖች ማብቂያ የሌለውን ደስታ ያገኛሉ። ከ፸፯–፸፮ ም.ዓ. ገደማ።

እናም አሁን እንዲህ ሆነ የአሞን ህዝብ በኢየርሾን ምድር ከሰፈሩ፣ እናም ደግሞ ቤተክርስቲያንም ካቋቋሙባት በኋላ፣ የኔፋውያን ወታደሮች በኢየርሾን ምድር ዙሪያ፣ አዎን፣ በዛራሔምላ ምድር ዳርቻ ዙሪያ ተመደቡ፤ እነሆ የላማናውያን ወታደሮች ወንድሞቻቸውን በምድረበዳው ተከትለዋቸው ነበር።

እናም በዚያ አስገራሚ ውጊያ ነበር፤ አዎን፣ በሁሉም ህዝብ መካከል ሌሂ ኢየሩሳሌምን ለቆ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ አይነት እንኳን፤ አዎን፣ እናም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ላማናውያን ተገደሉ፣ ወደ ውጪም ተበተኑ።

አዎን፣ እናም ደግሞ በኔፋውያን መካከል አስገራሚ ግድያ ነበር፤ ይሁን እንጂ፣ ላማናውያን ተባረሩና ተበታተኑ፣ እናም የኔፊ ህዝብ በድጋሚ ወደ ሥፍራቸው ተመለሱ።

እናም አሁን ይህ ታላቅ ሀዘንና ልቅሶ በኔፋውያን ህዝብ ሁሉ መካከል የተሰማበት ጊዜ ነበር—

አዎን፣ ባልቴቶቹ ለባሎቻቸው፣ ደግሞም አባቶች ለወንድ ልጆቻቸውና፣ ሴት ልጅ ለወንድሟ፣ አዎን፣ ወንድምም ለአባቱ በማዘን ልቅሶአቸው ተሰምቷል፤ እናም የሀዘን ለቅሶ በሁሉም መካከል ተሰምቷል፣ ለተገደሉ ወገኖቻቸው ሁሉ ሀዘን ነበር።

እናም አሁን ይህ አሳዛኝ ቀን ነበር፤ አዎን፣ የማስተዋልም ጊዜና፣ እጅግ የሚጾምበትና የሚጸለይበት ጊዜ ነበር።

እናም በዚህ በኔፊ ህዝብ መካከል አሥራ አምስተኛው የመሳፍንት አገዛዝ አበቃ፤

እናም ይህ አሞንና ወንድሞቹ በኔፊ ምድር ውስጥ የነበራቸው ጉዞአቸው፣ በምድሪቱ ስቃያቸው፣ ሀዘናቸውና መከራቸው፣ እናም ለማስተዋል የማይቻል ደስታቸው፣ እንዲሁም በኢየርሾን ምድር ያሉ ወንድሞች አቀባበላቸውና ደህንነታቸው ታሪክ ነው። እናም አሁን የሰው ልጆች ሁሉ አዳኝ ጌታ ለዘለዓለም ነፍሳቸውን ይባርክ።

እናም ይህ በኔፋውያን መካከል የነበረው ፀብና ደግሞ በኔፋውያንና በላማናውያን መካከል የነበረው ጦርነት ታሪክ ነው፤ እናም አሥራ አምስተኛው የመሳፍንት አገዛዝ በዚሁ ተፈፀመ።

እናም ከመጀመሪያው ዓመት ጀምሮ እስከ አሥራ አምስተኛው ዓመት ድረስ በሺህ የሚቆጠሩ ነፍሳት ጠፍተዋል፤ አዎን፣ አሰቃቂ የደም መፍሰስም ነበር።

፲፩ እናም በሺህ የሚቆጠሩት ሰውነቶች በምድር ውስጥ ሲቀበሩ ብዙዎች ደግሞ በሺህ የሚቆጠሩት በምድር ገፅ ተቆልለው በስብሰዋል፤ አዎን፣ እናም ብዙ ሺህዎች ለአለቁት ወገኖቻቸው አዝነዋል፣ ምክንያቱም በጌታ ቃል ኪዳን መሰረት በዚያም መጨረሻ ለሌለው ስቃይ እንደተመደቡ የመፍራት ምክንያት ነበራቸውና።

፲፪ ሌሎች ብዙ ሺዎች ዘሮቻቸው በመጥፋታቸው ቢያዝኑም፣ ነገር ግን በተስፋ፣ እናም በጌታ ቃል ኪዳን መሰረት መጨረሻ በሌለው ደስታ በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ በኩል ለመኖር እንደሚነሱ በማወቃቸው ይደሰቱ፣ እናም ሐሴት ያደርጉ ነበር።

፲፫ እናም በኃጢያትና በመተላለፍምና የሰው ልጆችን የልብ ለማጥመድ ብልህ በሆነው እቅዱ በሚመጣው በዲያብሎስ ሀይል ምክንያት የሰዎችን ልዩነት ታላቅነቱን እንዴት እንደሆነ እንደዚህ ለመመልከት ይቻለናል።

፲፬ እናም በጌታ የወይን ስፍራ ሰዎች እንዲሰሩ ታላቁን የትጋት ጥሪ እንደዚህ እንመለከታለን፤ እናም የታላቁን ሀዘንና፣ ደግሞ የደስታን መንስኤ ምክንያትንም እንደዚህ እንመለከታለን—በሞቱና በሰዎች መጥፋት የተነሳ ሃዘን፣ እናም በክርስቶስ የህይወት ብርሃንም ምክንያት ደስታን እንመለከታለን።