ቅዱሳት መጻህፍት
አልማ ፳፬


ምዕራፍ ፳፬

ላማናውያን የእግዚአብሔር በሆኑት ሰዎች ላይ መጡ—አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች በክርስቶስ ተደሰቱ፣ እናም በመልአክት ተጎበኙ—እራሳቸውን ከመከላከል ይልቅ በሞት መሰቃየትን መረጡ—በርካታ ላማናውያን ተለወጡ። ከ፺–፸፯ ም.ዓ. ገደማ።

እናም እንዲህ ሆነ አማሌቂውያንና፣ አሙሎናውያንም፣ በአሙሎን ምድር፣ ደግሞ በሔላም ምድር የነበሩት ላማናውያንም፣ እናም በኢየሩሳሌም ምድርና፣ በአጠቃላይ በምድሪቱ ሁሉ የነበሩት፣ ያልተለወጡት፣ እናም የአንቲ-ኔፊ- ሌሂን ስም ያልወሰዱት፣ በአማሌቂውያንና በአሙሎናውያን በወንድሞቻቸው ላይ ለማስቆጣት ተነሳስተው ነበር።

እናም ጥላቻቸው በእነርሱ ላይ መሪር ነበር፤ እንዲህም ሆኖ በንጉሳቸውም ላይ እስከሚያምፁ ድረስ፣ እርሱ ንጉሳቸው እንዲሆን አልፈለጉም ነበር፤ ስለዚህ በአንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች ህዝብ ላይም የጦር መሳሪያዎቻቸውን አነሱ።

እንግዲህ ንጉሱ በልጁ ላይ መንግስቱን አፀደቀ፣ እናም ስሙን አንቲ-ኔፊ- ሌሂ በማለት ጠራው።

እናም ንጉሱ ላማናውያን በእግዚአብሔር ሰዎች ላይ ለጦርነት ዝግጅት በጀመሩበት ዓመት ሞተ።

እንግዲህ አሞንና ወንድሞቹ እንዲሁም ከእርሱ ጋር የመጡት ሁሉ ላማናውያን ወንድሞቻቸውን ለማጥፋት መዘጋጀታቸውን በተመለከቱ ጊዜ፣ ወደ ምድያም ምድር መጡ፣ እናም እዚያ አሞን ወንድሞቹን በሙሉ ተገናኘ፤ እናም እራሳቸውን ከላማናውያን ለመከላከል ምን ማድረግ እንዳለባቸው ከላሞኒና ደግሞ ከአንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች ጋር ለመወያየት ወደ እስማኤል ምድር መጡ።

እንግዲህ ወደ ጌታ ከተለወጡት ሰዎች መካከል በወንድሙ ላይ የጦር መሣሪያን የሚያነሳ አንድም ሰው አልነበረም፤ ለጦርነትም ቢሆን ምንም ዓይነት ዝግጅት ማንም አያደርግም፤ አዎን እናም ደግሞ ንጉሳቸው ለጦርነት እንዳይዘጋጁ አዟል።

እንግዲህ፣ ይህንን በተመለከተ ለህዝቡ የተናገራቸው ቃላት እነዚህ ናቸው፥ የተወደዱትንም ሕዝቦቼን፣ ታላቁ አምላካችን በቸርነቱ እነዚህን ኔፋውያን ወንድሞቻችን ለእኛ እንዲሰብኩ፣ እናም የአባቶቻችንን ክፉ ባህሎች እንዲያሳምኑን ስለላካቸው እግዚአብሔር አምላኬን አመሰግናለሁ።

እናም እነሆ፣ ከእነዚህ ከኔፋውያን ወንድሞችም ጋር ጓደኝነት እንድንጀምር፣ ልባችንን ለማራራት የመንፈሱን ክፍል ስለላከልን ታላቁ አምላኬን አመሰግናለሁ።

እናም እነሆ፣ ይህንን ጓደኝነት በመጀመር ኃጢአታችንንና ብዙ ግድያዎችን መፈፀማችንን ስላመንን ደግሞ አምላኬን አመሰግናለሁ።

እናም ለእነዚህን ነገሮች ንስሃ እንድንገባ ስለፈቀደልንና፣ ደግሞ ለፈፀምናቸው ኃጢአቶችና ግድያዎች ይቅር ስላለን፣ እናም ጥፋታችንን በልጁ አማካኝነት ከልባችን ስለወሰደው አምላኬን፣ አዎን ታላቅ የሆነውን አምላኬን አመሰግነዋለሁ።

፲፩ እናም አሁን እነሆ፣ ወንድሞቼ፣ (ከሰው ዘር ሁሉ በላይ የጠፋን እኛ በመሆናችን) ለኃጢአታችን ሁሉ እንዲሁም በርካታ ግድያዎችን ለፈፀምንበት ንስሃ ለመግባት፣ እናም እነዚህን እግዚአብሔር ከልባችን እንዲያስወግድልን ለማድረግ የምንችለውን ሁሉ ይህ ብቻ ስለነበረ፣ ምክንያቱም በእግዚአብሔር ፊት በበቂ ሁኔታ ንስሃ ገብተን እርሱም ጥፋታችንን ሊወስድ በሚችልበት ሁሉ ልናደርግ የምንችለው ሁሉ ይህ ነበርና፤

፲፪ እንግዲህ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ እግዚአብሔር እንከናችንን በመውሰዱ፣ እናም ጎራዴዎቻችን ስላበሩ፣ ከእንግዲህ ጎራዴዎቻችንን በወንድሞቻችን ደም አናጎድፋቸው።

፲፫ እነሆ፣ እንዲህ እላችኋለሁ፣ አይሆንም፣ በወንድሞቻችን ደም እንዳይጎድፉ ዘንድ ጎራዴዎቻችንን እናስቀምጣቸው፤ ምናልባትም ጎራዴዎቻችንን በድጋሚ ካጎደፍናቸው ለኃጢአታችን ክፍያ በሚሆነው በታላቁ አምላካችን ልጅ ደም ከእንግዲህ ሊነፁ አይችሉም ይሆናልና።

፲፬ እናም ታላቁ አምላክ በእኛ ላይ ምህረትንና፣ እንዳንጠፋ እነዚህን ነገሮች እናድናውቃቸው አድርጓል፤ አዎን፣ እናም ነፍሶቻችንን ልጆቻችንን ከመውደዱ ያህል ድረስ ስለሚወድ አስቀድሞ እነዚህን ነገሮች እንድናውቃቸው አድርጓል፤ ስለዚህ፣ የደህንነት ዕቅድ ለእኛ እንዲሁም ለወደፊቱ ትውልድ እንዲታወቅ በምህረቱ በመላዕክቱ ጎብኝቶናል።

፲፭ አቤቱ አምላካችን እንዴት መሀሪ ነው! እናም አሁን እነሆ፣ ጉድፋችንን ከራሳችን ለማስወገድ ይህን ያህል ብቻ ማድረግ በመቻላችን እናም ጎራዴዎቻችን እንዲያበሩ በመደረጋቸው፣ ቃሉን ለእኛ ከሰጠንና በዚህም ንጹህ ካደረገን በኋላ ጎራዴያችንን በወንድሞቻችን ደም እንዳልበከልን በመጨረሻው ቀን፣ ወይም በፊቱም እንዲፈረድብን በምንቆምበት ቀን ለአምላካችን ምስክር እንዲሆኑ፣ ጎራዴዎቻችን እያበሩ እንድንጠብቃቸው እንደብቃቸው።

፲፮ እናም አሁን፣ ወንድሞቼ፣ ወንድሞቻችን ሊያጠፉን ከፈለጉ፣ እነሆ፣ ጎራዴዎቻችንን እንደብቃቸዋለን፤ አዎን፣ በመጨረሻው ቀንም እንዳልተጠቀምንባቸው ምስክር ይሆኑ ዘንድ አንፀባራቂ እንዲሆኑ በመሬቱ ውስጥ እንደብቃቸዋለን፤ እናም ወንድሞቻችን የሚያጠፉን ከሆነ፣ እነሆ፣ ወደ አምላካችን እንሄዳለንም፣ እንድናለንም።

፲፯ እናም አሁን እንዲህ ሆነ ንጉሱ ይህንን አባባል በጨረሰና፣ ህዝቡም በአንድ ላይ በተሰበሰበ ጊዜ፣ ጎራዴያቸውን፣ እናም የሰው ደም ለማፍሰስ የሚያገለግሉትን መሳሪያዎች ሁሉ ወሰዱና፣ በመሬት ውስጥም ቀበሩአቸው

፲፰ እናም ይህንን ያደረጉት ከእንግዲህ መሳሪያዎቹን የሰው ልጆችን ደም ለማፍሰስ በድጋሚ እንደማይጠቀሙበት በእነርሱ አመለካከት ለእግዚአብሔርና ለሰዎች ምስክር እንዲሆን ነበር፤ እናም ይህን ያደረጉት የወንድሞቻቸውን ደም ከማፍሰስ ህይወታቸውን አሳልፈው እንደሚሰጡና፣ ከወንድም ከመውሰድ ይልቅ ለእርሱ መስጠት እንደሚሻል ነበር፤ እናም ስራ በመፍታት ጊዜያቸውን ከማሳለፍ በእጆቻቸው ብዙ እንደሚሰሩ ለማረጋገጥና ከእግዚአብሔርም ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት ነው።

፲፱ እናም እነዚህ ላማናውያን እንዲያምኑና እውነትን እንዲያውቁ በመጡ ጊዜ፣ የፀኑ እንደነበሩ፣ እናም ኃጢያትን ከመፈፀም ሞት እንደሚሻላቸው እንደዚህ ተመልክተናል፤ የሰላም መሳሪያዎቻቸውን እንደደበቁ፣ ወይም የጦርነት መሳሪያዎቻቸውንም ለሰላም ሲሉ እንደደበቁ ተምልክተናል።

እናም እንዲህ ሆነ ወንድሞቻቸው ላማናውያንም ለጦርነት ተዘጋጁና፣ ንጉሱን ለማጥፋትና፣ ሌላውንም በቦታው ለመተካት፣ እናም ደግሞ የአንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች ህዝቦችንም ከምድሪቱ ለማጥፋት ወደ ኔፊ ምድር መጡ።

፳፩ እናም ህዝቡ ላማናውያን በእነርሱ ላይ መምጣታቸውን በተመለከቱ ጊዜ ከእነርሱ ጋር ለማገናኘት ሄዱና፣ በፊታቸውም ወደ መሬት ዝቅ አሉላቸው፣ እናም የጌታን ስም መጥራት ጀመሩና፤ ላማናውያን በእነርሱ ላይ በመጡና በጎራዴው እነርሱን መግደል በጀመሩ ጊዜ በዚህ ሁኔታ ነበሩ።

፳፪ እናም የሚቋቋማቸውን ሳያገኙ አንድ ሺህ አምስት የሚሆኑትን ገደሉ፤ እናም እነርሱ ከአምላካቸው ጋር ለመኖር በመሄዳቸው የተባረኩ እንደሆኑ እናውቃለን።

፳፫ እናም ላማናውያን ወንድሞቻቸው ከጎራዴው እንዳልሸሹ እንዲሁም ወደ ቀኝም ሆነ ወደግራ ፈቀቅ አለማለታቸውን፣ ነገር ግን እንደወደቁና እንደጠፉ፣ እናም በጎራዴው እየጠፉ እያለ አምላካቸውን ማመስገናቸውን በተመለከቱ ጊዜ—

፳፬ እናም ላማናውያን ይህንን በተመለከቱ ጊዜ እነርሱን ከመግደል ተገቱ፤ እናም በጎራዴው ለወደቁት ወንድሞቻቸው በውስጣቸው ልባቸውም ያዘኑ ብዙዎች ነበሩ፣ ስላደረጓቸውም ነገሮች ንስሃ ገብተዋልና።

፳፭ እናም እንዲህ ሆነ የጦር መሳሪያዎቻቸውን ጣሉና፣ በድጋሚ አይወሰዱአቸውም፣ ምክንያቱም በፈፀሟቸው ግድያዎች ተፀፅተዋልና፤ እናም እነርሱን ለመግደል ክንዶቻቸውን በእነርሱ ላይ በሚያነሱት ምህረት በመተማመን እንደ ወንድሞቻቸው ተንበረከኩ።

፳፮ እናም እንዲህ ሆነ ከተገደሉት በበለጠ የእግዚአብሔር የሆኑት በዚያን ቀን ተጨመሩ፤ እናም እነዚያ የተገደሉትም ፃድቃን ነበሩ፣ ነገር ግን እነርሱ እንደዳኑ ስለዚህ ለጥርጣሬ ምንም ምክንያት አልነበረንም።

፳፯ እናም ከእነርሱ መካከል ኃጢአተኛ የሆነ የተገደለ አልነበረም፤ ነገር ግን ከሺዎች የሚበልጡ እውነትን ወደማወቅ መጥተዋል፤ ስለዚህ ጌታ ለህዝቡ ደህንነት በብዙ መንገድ እንደሚሰራ እንመለከታለን።

፳፰ አሁን ብዙዎቹን ወንድሞቻቸውን የገደሉት ብዙ ቁጥር ያላቸው ላማናውያን አማሌቂውያን እና አሙሎናውያን ነበሩ፣ ብዙዎቹም የኔሆር ስርዓትን የሚየሚከተሉ ነበሩ።

፳፱ እንግዲህ፣ የጌታን ሰዎች ከተቀላቀሉት መካከል፣ አማሌቂውያንም ሆነ አሙሎናውያን የተባሉ፣ በኔሆር ስርዓትም የሚጓዙ አልነበሩም፣ ነገር ግን እነርሱ የላማንና የልሙኤል ዝርያዎች ነበሩ።

እናም ህዝቡ በጌታ መንፈስ አንዴ ከታነፁ፣ እናም ፅድቅን በሚመለከቱ ነገሮች ታላቅ እውቀትን ካገኙ በኋላ፤ እናም ወደ ኃጢያትና መተላለፍ በመውደቃቸው ይበልጥ ጠጣሮች መሆናቸውንና፣ ሁኔታቸውም እነዚህን ነገሮች በጭራሽ የማያውቁ ከሚመስለው ይበልጥ የከፋ እንደሆነ በዚህ በግልጽ ለመለየት ይቻለናል።